11/01/2026
''የወተት ምርትና ምርታማነትን ለማረጋገጥ የእንስሳት ዝርያን ማሻሻል ቅድምያ የሚሰጥ ጉዳይ ነው''
ከድር መሀመድ
የከሚሴ ከተማ እንስሳት ዓሳ ሀብት ልማት ጽ/ቤት ሀላፊ
በሀገር ደረጃ ከታቀዱት የተለያዩ ኢንሼቲቮች መካካል አንዱ የሌማት ትሩፋት ነው በመሆኑ የሌማት ትሩፋት ተግባራቶች ውስጥ የወተት መንደር ትልቁን ድርሻ ይይዛል በመሆኑም የወተት ምርትና ምርታማነትን ለማረጋገጥ የእንስሳት ዝርያን ማሻሻል ቅድምያ የሚሰጥ ጉዳይ ሲሆን በዚህ ዘረፍ ውጤት ማስመዝገብ ከቻልን እንደ በሀገር የተያዙ እቅዶችን ማሳካት እንደሚቻል አመላክተዋል።
በዛሬው እለት በከሚሴ ከተማ 02 ቀበሌ የዝርያ ማሻሻል ንቅናቄ መድረክ በይፍ መጀመሩን አብስረው እንስሳቶች ዝርያቸው ከተሻሻሉ፣ ጤናቸው ከተጠበቀ እና የአመጋገብ ሁኔታቸውን ከሻሻልን ከእንስሳቱ ዘርፍ የሚጠበቀውን ምርት ሁሉ በሚገባ መግኛት እንደሚቻል ገልጸዋል ።