Kombolcha city peace& security department

Kombolcha city peace& security  department የህዝቡን ሰላምና ደህንነት ማስጠበቅ

19/04/2026
ለሰላም ዘብ የሚቆመው የሚሊሻ አባል 30ኛ ዓመት የምስረታ በዓል በቢራሮ ክፍለ ከተማ ተከበረ።​ኮምቦልቻ ኮሙኒኬሽን፤ ሚያዚያ 11/2018 ዓ.ም በኮምቦልቻ ከተማ አስተዳደር የቢራሮ ክፍለ ከተ...
19/04/2026

ለሰላም ዘብ የሚቆመው የሚሊሻ አባል 30ኛ ዓመት የምስረታ በዓል በቢራሮ ክፍለ ከተማ ተከበረ።

​ኮምቦልቻ ኮሙኒኬሽን፤ ሚያዚያ 11/2018 ዓ.ም
በኮምቦልቻ ከተማ አስተዳደር የቢራሮ ክፍለ ከተማ የሚሊሻ አባላት “ለሰላም ዘብ እንቆማለን!” በሚል መሪ ቃል 30ኛ ዓመት የምስረታ በዓላቸውን በድምቀት አክብረዋል።

​በክብረ በዓሉ ላይ የተገኙት የኮምቦልቻ ከተማ አስተዳደር ሰላምና ፀጥታ መምሪያ ምክትል ኃላፊ አቶ ወንድሙ ነጋ ባስተላለፉት መልዕክት፤ ሚሊሻው ላለፉት ሦስት አስርተ ዓመታት የአካባቢውን እና ሰላምና ፀጥታ በማስከበር ረገድ የማይተካ ሚና ሲጫወት መቆየቱን ገልጸዋል።

ሚሊሻው ከመደበኛ የሰላም ጥበቃ ስራው ባለፈ በልማት ስራዎች ላይም ግንባር ቀደም ተሳታፊ በመሆን ህዝባዊ ወገንተኝነቱን በተግባር እያሳየ ይገኛል ብለዋል።

​የኮምቦልቻ ከተማ ሚሊሻ ቅ/ጽህፈት ቤት ኃላፊ ኮሎኔል ጌታውይ ዘገየ በበኩላቸው፤ የሚሊሻ አባላት እያከናወኑት ያለው የጀግንነት ስራ የሚደነቅ መሆኑን ጠቅሰው፣ በቀጣይም የከተማዋን አስተማማኝ # ሰላም ለማረጋገጥ ዝግጁነታቸውን አረጋግጠዋል።

ኮሎኔሉ አክለውም “ይህ 30ኛ ዓመት የምስረታ በዓል ያለፉ ስኬቶችን ከመዘከር ባለፈ፣ ለወደፊት ግዳጆች ይበልጥ የምንዘጋጅበትና አንድነታችንን የምናጠናክርበት ነው” ሲሉ ገልጸዋል።

​በበዓሉ ላይ የተሳተፉ የሚሊሻ አባላት በሰጡት አስተያየት፤ ህዝባቸውንና አካባቢያቸውን ከማንኛውም የጸጥታ ስጋት ለመጠበቅ የገቡትን ቃል በማደስ፣ በቁርጠኝነት መስራታቸውን እንደሚቀጥሉ ገልጸዋል።

አባላቱ በተለይም ከህብረተሰቡ ጋር ያላቸውን ግንኙነት በማጠናከር የወንጀል ድርጊቶችን አስቀድሞ በመከላከል ረገድ በንቃት እንደሚሳተፉ ተናግረዋል።

በመርሀ ግብሩ ላይ በአገልግሎት ጊዜያቸውን ያጠናቀቁ ለሚሊሻ አባላትና በተለያዩ ግዳጆች የተለየ ጀብዱ ለፈፀሙ የሰላም አስከባሪ አባላት እና አጋር አካላት እውቅናና ሽልማት ተሰጥቷል።
በእውቅና ፕሮግራሙ የመምሪያ እና የክፍለ ከተማ አመራሮችና ባለሙያዎች ተሳትፈውበታል።

በኮምቦልቻ ከተማ ፖሊስ መምሪያ የሀሰን ሀገር ክፍለ ከተማ ፖሊስ ጽ /ቤት ከተለያዩ የህብረተሰብ ክፍሎች ጋር ውያይት አኳሄደ።   ሰላምና ፀጥታ መምሪያ ኮሙኒኬሽን 24/7 / 2018 ዓ.ም  ...
02/04/2026

በኮምቦልቻ ከተማ ፖሊስ መምሪያ የሀሰን ሀገር ክፍለ ከተማ ፖሊስ ጽ /ቤት ከተለያዩ የህብረተሰብ ክፍሎች ጋር ውያይት አኳሄደ።
ሰላምና ፀጥታ መምሪያ ኮሙኒኬሽን 24/7 / 2018 ዓ.ም
በክፍለ ከተማው ጽ/ቤት ሃለፊ ም/ኢ /ር ከድር አህመድ የውይያቱን አስፈላጊነት ፣ በክፍለ ከተማችን ውስጥ ካሉ የተለያዩ አደረጃጀቶች ጋር ውይይት ማካሄድ በማስፈለጉ የተዘጋጀ ነው ። በመሆኑም ""እኔም ለሰላሙ አስዋፅዖ አለኝ ""በሚል መሪ ቃል ይካሄዳል ካሉ በሗላ የክፍለ ከተማውን ዋና ስራ አስፈፃሚ የመክፈቻ ንግግር አድርገዋል፡ ፡
ዋና ስራ አስፈፃሚ አቶ ማንደፋሮ ሁሴን ዋነኛው የፀጥታ ባለ ቤቶች የሆናችሁ የሀይማኖት አባቶች፣ የወጣት፣ የሴቶች ተወካዮች ፣ የንግዱ ማህበረሰብ፣ የቀጠና እና የብሎክ አመራሮች ፣ የክፍለ ከተማና የዞን አመራሮች እንኳን ደህና ሙጣችሁ ብለዋል ። አክለውም የከተማችንን ሰላምና ፀጥታ ባለቤቶች በመሆናችሁ የተሸለ ውይይት እንደምታ ደርጉ በመተማ ማን ነው ብለዋል።
ለውይይት መነሻ የሚሆን ፅሁፍ ያቀረቡት የኮምቦልቻ ከተማ ፖሊስ ዋና መምሪያ ምክትል መምሪያ ሃላፊ ኮማንደር ይመር አባተ የከተማችን አሁናዊ የፀጥታ ሁኔታ አብራርተው አቅርበዋል ።
በቀረበው የውይይት መነሻ ፅሁፍ ላይ ተሳታፊዎች ሃሳብ፣ አስተያየት እና ጥያቄ አቅርበዋል ።
በቀርቡት ጥያቄና አስተያየቶች ላይ ምላሽና ማብራሪያ የሰጡት የሰላምና ፀጥታ መምሪያ ምክትል ሃላፊ አቶ ወንድሙ ነጋ በከተማችን ዋነኛው የፀጥታ ባለቤት በሆናችሁ ልት ኮሩ ይገባል ብለዋል ፣ሃለፈው አክለውም የእናንተን ጠንካራ አደረጃጀት በአግባቡ መጠቀም ብተቻ ምንም አይነት ፀጉር ልውጥ ይሁን ስርጎ ገብ ለፀጥታችን እንቅፋት ሊሆነን አይችልም ብለዋል ።
@@እኔም ለሰላሙ አስዋፅዖ አለኝ @@

“ለሀገር ሰላም  እና ልማት እንቅፋት የሚሆኑ ኃይሎችን እንቃወማለን” የኮምቦልቻ ከተማ አስተዳደር  የኃይማኖት አባቶች።ኮምቦልቻ ኮሙዩኒኬሽን ጥር 27/2018 ዓ.ም "በመደመር መንግስት እይታ...
06/03/2026

“ለሀገር ሰላም እና ልማት እንቅፋት የሚሆኑ ኃይሎችን እንቃወማለን” የኮምቦልቻ ከተማ አስተዳደር የኃይማኖት አባቶች።

ኮምቦልቻ ኮሙዩኒኬሽን ጥር 27/2018 ዓ.ም "በመደመር መንግስት እይታ የሀይማኖት ተቋማት መሪዎች ሚና" በሚል መሪ መልዕክት የኮምቦልቻ ከተማ አስተዳደር የሀይማኖት አባቶች እና የሀገር ሽማግሌዎች መድረክ ተካሄደ።

መድረኩን በንግግር የከፈቱት የኮምቦልቻ ከተማ አስተዳደር ምክትል ከንቲባ አቶ ወንዶሰን ልሳነወርቅ እንደገለፁት የኢትዮጵያ ብልፅግና እንዲረጋገጥ እና ብሄራዊ ጥቅሟ እንዲከበር ውስጣዊ ሰላምን ማጠናከር አስፈላጊ ነው ብለዋል።

ሰላም የሁሉም ነገር መሠረት በመሆኑ ፣ ሰላምን በማስፈን ረገድ እና ሁሉም የህብረተሰብ ክፍል ለሰላም ዘብ እንዲቆም የሃማኖት አባቶች የድርችሁን ልትወጡ ይገባል ብለዋል።

በአማራ ክልል የተከሰቱ ግጭቶች ከፍተኛ ሰብዓዊና ቁሳዊ ጉዳት እንዲሁም ማኅበራዊና ኢኮኖሚያዊ ቀውስ ማስከተላቸውን የሀይማኖት አባቶች ገልፀዋል።

ለሀገር ሰላምና ልማት እንቅፋት የሚሆኑ ኃይሎችን እንደሚቃወሙ የገለፁት የሀይማኖት አባቶች ሀገር የምትበለፅገው እና ዜጎች የሚያትርፉት ከሰላም ብቻ መሆኑን አስረድተዋል።

የሀይማኖት አባቶቹ ግጭትን በማቀጣጠል እና በማራዘም ሕዝቡን ለመከፋፈል የሚሞክሩ ታሪካዊ የኢትዮጵያ ጠላቶች ከሴራቸው እንዲታቀቡ ጠይቀዋል።

ዜጎችን ከሰላም ፣ ከውይይት እና ከምክክር ውጭ ያሉ የትግል አማራጮችን ይዞ የሚታገል የውጭም ሆነ የውስጥ አካልን ዕቅዱን በማክሸፍ በሀገራችን ሰላም እንዲሰፍን እያንዳንዱ ዜጋ የድርሻውን እንዲወጣ አሳስበዋል።

የኮምቦልቻ ከተማ አስተዳደር ከንቲባ አቶ ሙሀመድአሚን የሱፍ እንደገለፁት የሀገራችንም ሆነ የክልላችን ሰላም እና ልማት ዘላቂ እና አስተማማኝ ለማድረግ የሃይማኖት አባቶች እና የሀገር ሽማግሌዎች ሚና ከፍተኛ መሆኑን ገልፀዋል።

መንግሥት በክልሉ የተከሰተውን ግጭት በሰላማዊ መንገድ ለመፍታት ባደረገው ጥረት በርካታ በጫካ የሚንቀሳቀሱ ወገኖች ወደ ሰላማዊ ሂይወታቸው እንዲመለሱ ማድረግ ተችሏል ብለዋል።

አሁንም በጫካ ያሉ እና ትግሉን በጠመንጃ ለመፍታት የሚጥሩ ታጣቂዎች በጦርነት የሚፈታ ጥያቄ አመለኖሩን እንዲረዱ እና ማንኛውም ጥያቄ ያለው አካል በሰላማዊ መንገድ ብቻ እንዲታገል የሀይማኖት አባቶችና የሀገር ሽማግሌዎች የድርሻቸውን እንዲወጡ ጠይቀዋል ።

የኮምቦልቻ ከተማ አስተዳደር ብልፅግና ፓርቲ ቅርጫፍ ፅ/ቤት ኃላፊ አቶ ሙሉጌታ አቢ በበኩላቸው የመደመር መንግስት የሃይማኖት አባቶች እና የሀገር ሽማግሌዎች ዘላቂ ሰላምን እና ልማትን በማረጋገጥ ረገድ ሚናቸው የጎላ መሆኑን በፅኑ ያምናል ብለዋል።

ሀይማኖት አባቶች አማኙ ማህበረሰብ በሀገር ሰላም ፣ ልማት እና ዘላቂ ጥቅም ላይ በአንድነት እንዲቆም ከመስበክ ባሻገር ለሀገራችን ሰላምና ልማት ፀሎት ማድረግ እንደሚገባቸው አሳስበዋል።

የኮምቦልቻ ከተማ አስተዳደር ብልፅግና ፓርቲ ቅርጫፍ ፅ/ቤት የፖለቲካ ዘርፍ ኃላፊ አቶ ጀማል መሀመድ ለውይይቱን የመነሻ ጹሑፍ አቅርበው ሰፊ ውይይት ተካሂዷል።
መረጃው የኮምቦልቻ ከተማ መንግስት ኮሙኒኬሽን ነው።

በኮምቦልቻ ከተማ አስተዳደር በሀገራዊና ክልላዊ ወቅታዊ ጉዳዮች እንዲሁም በልማት ስራዎች ላይ ያተኮረ የጠቅላላ አመራር የውይይት መድረክ ተካሄደ።ኮምቦልቻ  ኮሙኒኬሽን የካቲት 25/2018 ዓ....
04/03/2026

በኮምቦልቻ ከተማ አስተዳደር በሀገራዊና ክልላዊ ወቅታዊ ጉዳዮች እንዲሁም በልማት ስራዎች ላይ ያተኮረ የጠቅላላ አመራር የውይይት መድረክ ተካሄደ።

ኮምቦልቻ ኮሙኒኬሽን የካቲት 25/2018 ዓ.ም በውይይቱ “ለሰላም ዘብ እንቆማለን፤ የልማት አርበኛ እንሆናለን” በሚል መሪ መልዕክት ተካሂዶ አመራሩ በወቅታዊ ጉዳዮች ላይ ያለውን አቋም እና ተግባራዊ ተልዕኮ በግልፅ ተረድቶ መስራት እንደሚገባው ተገልጿል።

የኮምቦልቻ ከተማ ብልፅግና ፓርቲ ቅርንጫፍ ጽ/ቤት የፖለቲካ ዘርፍ ምክትል ኃላፊ አቶ አስቻለው ብርሃኑ የውይይት ሰነዱን ያቀረቡ ሲሆን ሀገራዊና ክልላዊ የሰላም፣ የልማት፣ የፖለቲካና የመልካም አስተዳደር ጉዳዮችን በስፋት አብራርተዋል።

መድረኩን የመሩት የኮምቦልቻ ከተማ አስተዳደር ከንቲባ አቶ መሀመድአሚን የሱፍ እንደገለፁት፣ በየደረጃው ያለው የፖለቲካ አመራር ወቅቱ የሚጠይቀውን ቁመና በመላበስ የዓለም የጂኦ-ፖለቲካ አውድን እና ቀጠናዊ የሀይል አሰላለፎችን በጥልቀት ተረድቶ የሰላም፣ የልማትና የፖለቲካ ተልዕኮዎችን በተገቢው መፈፀም አለበት ብለዋል።

ከንቲባው አክለውም ሀገራችን የጀመረችው ሁለንተናዊ የለውጥና የብልፅግና ጉዞ በማንኛውም አይነት እኩይ እንቅስቃሴ እንደማይደናቀፍ ገልፀው፣ አመራሩ በአንድነት ቆሞ የሰላምና የልማት ጉዞውን ማስቀጠል እንዳለበት አሳስበዋል።

በመድረኩ ላይ የከተማው ከፍተኛ አመራሮችን ጨምሮ በየደረጃው ያሉ የመምሪያ፣ የክፍለ ከተማ እና የቀበሌ አመራሮች ተሳትፈው በቀረቡ ሀሳቦች ላይ አስተያየታቸውን ሰጥተዋል።

ኮምቦልቻ ለሰላም ዘብ ቆማለች፤ ለልማት በተግባር ትተጋለች!
መረጃው የመንግስት ኮሙዩኒኬሽን ነወ።

"የብሔራዊ የበጎ ፈቃድ የማህበረሰብ አገልግሎት ዋና ዓላማው  ዘላቂ ሰላሟ የተረጋገጠባት እና የበለፀገች ሀገር መገንባት ነው"የኮምቦልቻ ከተማ አስተዳደር ሰላም ፀጥታ መምሪያ ምክትል ኃላፊ አ...
26/12/2025

"የብሔራዊ የበጎ ፈቃድ የማህበረሰብ አገልግሎት ዋና ዓላማው ዘላቂ ሰላሟ የተረጋገጠባት እና የበለፀገች ሀገር መገንባት ነው"

የኮምቦልቻ ከተማ አስተዳደር ሰላም ፀጥታ መምሪያ ምክትል ኃላፊ አቶ ወንድሙ ነጋ።

ኮምቦልቻ ሰላምና ፀጥታ ኮሙኒኬሽን ታህሳስ 17/2018 ዓ.ም
የኮምቦልቻ ከተማ አስተዳደር ሰላም እና ፀጥታ መምሪያ የበጎ ፈቃድ ማህበረሰብ አገልግሎት ፕሮግራም የ6ወር የስራ አፈፃፀም ግምገማ እና የቀጣይ የ6 ወር የእቅድ ትውውቅ ፣ የምስጋና እና የእውቅና መርሀ ግብር አካሂዷል።

መርሃ ግብሩ ላይ ንግግር ያደረጉት የኮምቦልቻ ከተማ አስተዳደር ሰላም ፀጥታ መምሪያ ምክትል ኃላፊ አቶ ወንድሙ ነጋ የብሔራዊ የበጎ ፈቃድ የማህበረሰብ አገልግሎት ዋና ዓላማው ዘላቂ ሰላሟ የተረጋገጠባት እና የበለፀገች ሀገር መገንባት ነው ብለዋል።

የብሔራዊ የበጎ ፈቃድ የማህበረሰብ አገልግሎት ፕሮግራም ከየትኛውም የፖለቲካ ጣልቃ ገብነት ነፃ ሆኖ ሰብዓዊነት ላይ ብቻ ትኩረት አድርጎ በመስራት ወጣቶች በሀገራቸው ጉዳይ ላይ ተቆርቋሪ እና ንቁ ተሳታፊ እንዲሆኑ ማድረግ ነው ብለዋል።

መምሪያው የበጎ ፈቃድ ማህበረሰብ አገልግሎት ፕሮግራም የተሳተፉ የ13ኛ ዙር እውቅናና በ14ኛ ዙር የቀጣይ የስራ ስምሪት ዙሪያ የብሔራዊ የበጎ ፈቃድ የማህበረሰብ አገልግሎት ተሳታፊዎች በተገኙበት ውይይት ተካሂዷል።

በሰላምና ፀጥታ መምሪያ የሰላምና መከባበር ማስፈን ባለሙያ እና የኮምቦልቻ ከተማ የብሄራዊ የበጎ ፈቃድ ወጣቶች አስተባባሪ አቶ ሰለሞን ዮሐንስ እንደተናገሩት የብሔራዊ የበጎ ፈቃድ የማህበረሰብ አገልግሎት ፕሮግራም ወጣቶች ያላቸውን ዕምቅ ዕውቀት እና ችሎታ አውጥተው ማህበረሰቡን በቅንነት የሚያገለግሉበት በገንዘብ የማይተመን ሰብዓዊ አገልግሎት ነው ብለዋል።

በሰላምና ፀጥታ መምሪያ የበጎ ፈቃድ ወጣቶች ረዳት አመቻች መቅደስ ከበደ የብሔራዊ የበጎ ፈቃድ የማህበረሰብ አገልግሎት ፕሮግራም ዓላማ የወጣቶችን ሁለንተናዊ ስብዕና በማሳደግ ለመጭው ትውልድ በጎ አሻራ ጥሎ ማለፍ መሆኑን አብራርተዋል።

የፕሮግራሙ ተሳታፊዎች በበኩላቸው የብሔራዊ የበጎ ፈቃድ የማህበረሰብ አገልግሎት ላይ በመሳተፋቸው የህሊና ደስታ ከማግኘታቸው በተጨማሪ ማህበረሰብን ለማገልገል ልምድ እንደቀሰሙበት አስረድተዋል።

"የሰላም አሰከባሪ ኃይላችን በጠንካራ ስነ ልቦና የተገነባ በመሆኑ የከተማዋን ዘላቂ ሰላም እያረጋገጠ ነው"የኮምቦልቻ ከተማ አስተዳደር ብልፅግና ፓርቲ ቅርጫፍ ጽ/ቤት ኃላፊ አቶ ሙሉጌታ አቢ።...
19/12/2025

"የሰላም አሰከባሪ ኃይላችን በጠንካራ ስነ ልቦና የተገነባ በመሆኑ የከተማዋን ዘላቂ ሰላም እያረጋገጠ ነው"

የኮምቦልቻ ከተማ አስተዳደር ብልፅግና ፓርቲ ቅርጫፍ ጽ/ቤት ኃላፊ አቶ ሙሉጌታ አቢ።

ኮምቦልቻ ኮሙኒኬሽን ታህሳስ 7/2018 ዓ.ም የኮምቦልቻ ከተማ አሰተዳደር
ሚሊሻ ጽ/ቤት የክፍለ ጦር የሰላም አስከባሪ አባላት ወታደራዊ የአቅም ግንባታ ስልጠና እየሰጠ ነው።

በመክፈቻ መርሃ ግብሩ ላይ ተገኝተው ንግግር ያደረጉት የኮምቦልቻ ከተማ አስተዳደር ብልፅግና ፓርቲ ቅርጫፍ ጽ/ቤት ኃላፊ አቶ ሙሉጌታ አቢ የሰላም አሰከባሪ ኃይላችን በጠንካራ ስነ ልቦና የተገነባ በመሆኑ የከተማዋን ዘላቂ ሰላም እያረጋገጠ ነው ብለዋል።

የተቋሙን ተልዕኮ የተረዳ እና ወታደራዊ ቁመናን የተላበሰ የሰላም አስከባሪ ሰራዊት ለመፍጠር የአቅም ግንባታ ስልጠናው አስፈላጊ ነው ብለዋል።

ስልጠናው ወታደራዊ ዲሲፕሊን ተቋማዊ ሃላፊነት በብቃት መወጣት ግዳጅን በላቀ ብቃትና በጀግንነት ለመፈፀም የሚያስችል በመሆኑ በትኩረት እንዲከታተሉም አሳስበዋል።

የኮምቦልቻ ከተማ አስተዳደር ሰላምና ፀጥታ መምሪያ ኃላፊ ኮማንደር ሰይድ ዓሊ በበኩላቸው የሰላም አስከባሪ ኃይላችን ለህዝብ የሚያገለግል እና ህግን ለማስከበር የሚሰራ በመሆኑ ወታደራዊ አቅሙን ለማጎልበት ስልጠናው አስፈላጊ ነው ብለዋል።

የሀገራችንን ዘላቂ ሰላም እና አስተማማኝ ልማት በማረጋገጥ ለመጭው ትውልድ የተሻለች ኢትዮጵያን ለማስረከብ የሰላም አስከባሪ ኃይችን ከሌሎች የፀጥታ ኃይሎች ጋር በትብብር ይሰራል ብለዋል።

የኮምቦልቻ ከተማ ሚሊሻ ጽ/ቤት ኃላፊ ኮሎኔል ጌታዎይ ዘገየ በበኩላቸው የሰላም አስከባሪ ኃይላችን የከተማዋን ዘላቂ ሰላም ከማረጋገጥ ባለፈ ሀገራችንን ከውጭ ጠላት ከውስጥ ባንዳ ለመጠበቅ ከምንግዜውም በላይ የስነ ልቦና ወታደራዊ አቅሙ አድጓል ብለዋል።

11/12/2025
የኃይማኖት ተቋማት ፍቅርን፣ ሰላምንና አብሮነትን በማስተማር ተቀዳሚ ተግባራቸው ሊሆን ይገባል"የኢትዮጵያ የሃይማኖት ተቋማት ጉባኤ ምክትል ጸሐፊ ሀጅ መስኡድ አደምኮምቦልቻ ሰላምና ፀጥታ ኮሙኒ...
03/12/2025

የኃይማኖት ተቋማት ፍቅርን፣ ሰላምንና አብሮነትን በማስተማር ተቀዳሚ ተግባራቸው ሊሆን ይገባል"

የኢትዮጵያ የሃይማኖት ተቋማት ጉባኤ ምክትል ጸሐፊ ሀጅ መስኡድ አደም

ኮምቦልቻ ሰላምና ፀጥታ ኮሙኒኬሽን
ህዳር 24/2018 ዓ.ም በኮምቦልቻ ከተማ አስተዳደር "የሃይማኖት ተቋማት ጉባኤ ሃይማኖታዊ እሴቶቻችን የአብሮነታችን እና የጥንካሬዎቻችን መሠረቶች ናቸው" በሚል መሪ ሃሳብ የሠላም ኮፍረንስ ተካሂዷል ።

በመድረኩ መክፈቻ ላይ የኢትዮጵያ የሃይማኖት ተቋማት ጉባኤ ምክትል ጽሐፊ ሀጅ መስኡድ አደም እንደገለፁት የኃይማኖት ተቋማት ፍቅርን፣ ሰላምንና አብሮነትን በማስተማር ተቀዳሚ ተግባራቸው ሊሆን ይገባል ብለዋል።

የሁሉም ሀይኖች አስተምህሮ ፍቅር፣ ፍትሀዊነት ፣እኩልነት ፣ መከባበር እና መቻቻልን የሚገልጽ በመሆኑ አስተምህሮውን መተግበር ይገባል ብለዋል።

የሃይማኖት ተቋማቶች አማኞቻቸው በሰነ ምግባር እና በሞራል ልዕልና ታንፀው ለሰላም መስፈን የድርሻውን እንዲውጡ የዘውትር ተግባራቸው ሊሆን እንደሚገባም አሳስበዋል።

ወሎ በርካታ ማንነቶች የተጋመዱበት በፍቅር ፣ በአንድነት ፣በመተሳሰብ እና በመከባበር የሚኖሩበት አካባቢ በመሆኑ ይህ እሴት ጉልቶ እንዲወጣ የኃይማኖት ተቋማት ያላሰለሰ ጥረት ማድረግ እንደሚገባቸውም አስገንዝበዋል።

የኮምቦልቻ ከተማ የሃይማኖት ተቋማት ጉባኤ ሰብሳቢ ሊቀ ትጉሀን መምህር ሰለሞን አሰፋ በበኩላቸው የሃይማኖት ተቋማት ዋነኛ ተግባራቸው የሆነውን ፍቅርን ፣ ሰላምን እና መተሳሰብን ከማስተማር በተጨማሪ ሰላምን የማጽናት ጉዳይ ላይ በትኩረት መስራት እንዳለባቸው ገልጸዋል ።

ቤተ -እምነቶች ስለ ሰላም በማስተማር እና በመፀለይ ለትውልድ ግንባታ ትልቅ አቅም መሆናቸውንም ተናግረዋል።

ሰላም የሁሉም ነገር መሠረት በመሆኑ ፍቅርን ፣ አብሮነት እና መከባበርን አንድነት እና አብሮነትን በማስተማር ከምንጊዜውም በላይ ሀገር ሰላም እንድትሆን መፀለይ እና መስራት እንደሚገባ አብራርተዋል።

የኮምቦልቻ ከተማ አስተዳደር ከንቲባ ጽ/ቤት ኃላፊ አቶ ሙሉጌታ ደርሴ እንደተናገሩት የኃይማኖት አባቶች አስተምህሮ ለሀገር ልማትና ዘላቂ ሰላም ግንባታ የራሱን ድርሻ እየተወጣ መሆኑን ገልጸዋል።

በከተማችን ለሰፈነው ዘላቂ ሰላም መረጋገጥ የሃይማኖት አባቶች አስተምሮ ሚና ትልቅ ድርሻ እንዳለው ገልፀው በከተማ አስተዳደሩ ዘላቂ ሰላም እንዲረጋገጥ እና የልማት ስራዎች በተያዘላቸው ጊዜ ተፈጽመው የተጀመረው የብልፅግና ጉዞ እውን እንዲሆን አበክሮ ይሰራል ብለዋል።

በመድረኩ ላይ የመጽሐፍ ቁዱስ እና የቅዱስ ቁርዓን አስተምሮ ስለ "ሰላም ምን ይላሉ የሚል ጹሑፍ በሁሉም ሃይማኖት አባቶች ቀርቦ ውይይት ተካሂዶበታል።

የኮምቦልቻ ከተማ አስተዳደር ፖሊስ መምሪያ የ 2017 ዓ.ም የማጠቃለያ ፕሮግራ ምና እውቅና ሰጠ ።  ኮምቦልቻ ከተማ ሰላምና ፀጥታ ኮሙኒኬሽን 4 / 03 / 2018 ዓ.ም የኮምቦልቻ ከተማ አ...
13/11/2025

የኮምቦልቻ ከተማ አስተዳደር ፖሊስ መምሪያ የ 2017 ዓ.ም የማጠቃለያ ፕሮግራ ምና እውቅና ሰጠ ።
ኮምቦልቻ ከተማ ሰላምና ፀጥታ ኮሙኒኬሽን 4 / 03 / 2018 ዓ.ም
የኮምቦልቻ ከተማ አስተዳደር ፖሊስ መምሪያ በ 2017 ዓ.ም የተሻለ አፈፃፀም ላላቸው የፖሊስ አባላቱ የማዕረግ እና የትምህርት ዕድል ሰጠ።
በፕሮግራሙ ላይ የመክፈቻ ንግግር ያደረጉት የኮምቦልቻ ከተማ አስተዳደር ፖሊስ መምሪያ ሃላፊ ኮማንደር ጌታቸው ሙህዬ የተሻለ አሰተሳሰብና እውቀት ላይ የደረሰ ፖሊስ በከተማ አስተዳደሩ ለመፍጠር የማንከፈለው መስዕዋትነት የለም ብለዋል።
የዕለቱ የክብር እንግዳ የኮምቦልቻ ከተማ አስተዳደር ብልፅግና ፓርቲ ቅ / ጽ /ቤት ሃለፊ አቶ ሙሉጌታ አቢ የከተማ አስተዳደሩ ፖሊስ አመራርና አባላት የከተማዋን ሰላም ለማረጋገጥ በርካታ የሚበሉ ችግሮችን አልፈው አሁን የረሱበትን ደረጃ ማየት ልብን የሚሞላ ኩራት የሚሰጥ ነው ብለዋል ።
የተለያዩ የፖሊስ መኮነነኖች እና የፖሊስ አባላት የማዕረግና የትምህርት ዕድል ተሰጥቷቸዋል፡
በፕሮግራሙ ላይ የኮምቦልቻ ከተማ ምክትል ኮንቲባ አቶ ወንድወስን ልሳነ ወርቅ ፣ ኮሎኔል ቶላ በቀለ የ 801 ኛ ኮር ምክትል አዛዥ ሌሎች የወታደራዊ መስመር አመራሮች፣ የኦረሞ ብሄረሰብ አስተዳደር ዞን ፖሊስ መምሪያ ሃላፊ የከተማው ከፍተኛ አመራሮች ፣ የክፍለ ከተማ አመራሮች የህብረተሰብ ክፍሎች በተገኙበት በድምቀት ተከብሯል ።

የፀጥ ሃይሉ“የውጭ ባዳዎችንና የውስጥ ባንዳዎችን ቅዠት በተገቢው ተገንዝበው እኩይ ሴራቸውን ማምከን እንደሚገባቸው  ተገለፀ።ኮምቦልቻ  ሰላምና ፀጥታ ኮሙኒኬሽን ጥቅምት 24/2018 ዓ.ም   ...
03/11/2025

የፀጥ ሃይሉ“የውጭ ባዳዎችንና የውስጥ ባንዳዎችን ቅዠት በተገቢው ተገንዝበው እኩይ ሴራቸውን ማምከን እንደሚገባቸው ተገለፀ።

ኮምቦልቻ ሰላምና ፀጥታ ኮሙኒኬሽን ጥቅምት 24/2018 ዓ.ም
በኮምቦልቻ ከተማ አስተዳደደር የፀጥታ አካላት "የዉጭ ባዳዎችንና የዉስጥ ባንዳዎችን ቅዠት በማምከን አንፀባራቂ ድሎች እናስመዘግባለን !" በሚል መሪ ሃሳብ ውይይት ተካሂዷል።

በውይይቱ ላይ ተገኝተው የመክፈቻ ንግግር ያደረጉት የሰላምና ፀጥታ መምሪያ ሃላፊ ኮማንደር ሰይር አሊ በኢትዮጵያ ባለፉት አመታት በማኅበራዊ፣ በኢኮኖሚያዊ እና በፖለቲካዊ ውጤቶች የተመዘገቡ ሲሆን ለዚህ ደግሞ የከተማችን የፀጥታ ሃይል ከአካል መጉዳል እስከ ህይወት መስዕዋትነት ድርስ የከፈለበት መሆኑን አንስተዋል : :

የውይይት መነሻ ፅሁፍ የቀረቡት የፖሊስ መምሪያ ሃለፊ ኮማንደር ጌታቸው ሙህዬ የፀጥታ አካሉ የውጭ ባዳ እና የውስጥ ባንዳ በጥልቀትና በዝርዝር አቅርበዋል።

በውይይቱም የፖሊስ ፣ የሰላም አስከበሪ እና የማረሚያ ፖሊስ አባላት ተሳታፋ ሲሆኑ የተለያዩ ሃሳብና አስተያየት አንስተዋል።
በተነሱት ሃሳብና አስተያየቶች ኮ/ል ጌታዊ ዘገየ የሚሊሻ የቤት ሃለፊ ፣ ኮ/ር ጌታቸው ውህዬ የፖሊስ መምሪያ ሃለፊ እና ኮ/ር ሲይድ አሊ የሰላምና ፀጥታ መምሪያ ሃለፊ ኢትዮጵያ ያላችበትን ቀጠናዊ ሁኔታ ያገናዘበ ምላሽና ማብራሪያ ሰጥተው በታል።

Address

Kembolcha

Telephone

+251335514415

Website

Alerts

Be the first to know and let us send you an email when Kombolcha city peace& security department posts news and promotions. Your email address will not be used for any other purpose, and you can unsubscribe at any time.

Share