21/11/2025
የነህሚያ ጥናት
ክፍል ሁለት አጠቃላይ መግቢያ
ነህሚያ ምን አይነት ሰው ነበር?
✍️ የነህሚያ ግለ ህይወት ውይም ከመፅሃፉ በመነሳት ስለላከለው ማንነት መመልከት እና መማር አስፈላጊ ነው።
1= የፀሎት ሰው ነበር ፡፡ ነህ 1፥4-5, 2:4
✍️ ሁሉንም ስራ በፀሎት ይጀምር ነበር፣ ይጸልይ፣ ይጾም፣ ያለቀሰም ነበር
✍️ ይህ ማንነቱ ለሚሰማው ነገር ሁሉ ከምንም ቀድሞ ፀሎትን ያስቀድም ነበር ::
✍️ መፀለይ የህይወቱ ዋና ጉዳይ እንደሆነ እንመለከታለን በንጉስ ለቀረበት ነፃ ጥያቄ ፀሎት ማስቀደሙ አስተማሪ የህይወቱ ክፍል ነው። ለአያሌ ቀናትም (4ወር) ቅፅበታዊም ይሁን ፀሎት ምርጫው ያደረገ ሰው መሆኑ አሁን በዚህ ዘመን ላለን አገልጋዮችም ይሁን ምዕመናን ትልቅ ትምህርት ነው::
✍️ ፀሎትን በተግባሩ የገለጠ
2=በእግዚአብሄር የሚታመን ሰው ነው ፡፡ ነህ 2፥20
✍️ በተቃዋሚዎችም ሆነ ውስጥ በሚፈጠሩ ችግሮች እግዚአብሄርን የሚያምን እና የሚያስቀድም ሰው ነበር::
3= በንጉስ ፊት የታመነ የቅርብ ሰው
👉 በስራው በንጉስ እጅግ የሚያምነው ሰው ነበር።
4= እግዚአብሄርን የሚፈራ ትዕዛዚቱንም የሚያደርግ ሰው ነበር፡፡ ነህ 5 ፥ 15 ፤ ነህ 7፥2
5= ተቃዋሚዎችን ለመግጠም የማይፈራ ቢሆንም ሌሎችን ለመርዳት ታታሪ ሰው ነበር፡፡
ነህ 5 ፥ 11፤ ነህ 5፥18
6= ለእግዚአብሄር ሃሳብ የሚወገን ሰው ነበር፡፡ ነህ 13 ፥ 1
7= የሚገባውን ነገር የሚተው ሰው ነበር ፡፡ ነህ 5 ፥ 14
8= በጥንቃቄ የሚመላለስ ሰው ነበር
👉 ለተገለጠለት ነገር በጥንቃቄ የሚያደርግ በተጠና፣ ራዕዩን ያለጊዜውን እና ቦታ የማያወራ፣
9= ትክክለኛ አስተዳዳሪና መሪ ነበር
✍️ የሚያነቃቃ በእውነት ላይ በመቆም ህዝቡ የችግሩን ሁኔታ እንዲያዩ የሚያነሳሳ ሲደክሙ ደግሞ የሚያበረታታ
✍️ በሚገባ የሚያደራጅ ስራ በማከፋፈል የሚያሰራ፣ የጠላትን ሁኔታ በሚገባ ያገናዘበ ዝግጅት የሚያደርግ
10= ስራን በማከፋፈል በህብረት የሚሰራ ነህ 3 ፥ 6-32
✍️ ኑ እንስራ የሚሰራ እኔ ብቻ የማይል አጠገብ አጠገብ በማድረግ በህብረት የሚያንቀሳቅስ
ልክ እንደ ጳውሎስ 2ኛተሰ 3 ፥ 8-9
👉 ጠንካራ ስብዕና ያለውና ህዝብን ለስራ የማነሳሳት የመቀስቀስ የሚችል ሰው ነበር
✍️እነዚህ እና ከመፅሃፉ በእያንዳዱ ምዕራፍ ውስጥ እናገኛለን
✍️ ለዛሬዋን ቤተ ክርስቲያን ለፈረሰባት ቅጥር ብዙ አውቅልሻለሁ የሚላት ሁሉ ከዚህ በራቅ የህይወት ምልልስ ቅጥሯን ከመስራት ይልቅ የሚያፈርሳት የበዛበት ዘመን ላይ እግዚአብሄር በዚህ እውነት እየባረክ ጠቃሚ አብሮ ሰራተኞች መጠቀሚያ እቃ ይድርገን።
በእየሱስ ስም አሜን