የኮሬ ዞን ፖሊስ መምሪያ - Koore Zone Police Department

  • Home
  • Ethiopia
  • Kele
  • የኮሬ ዞን ፖሊስ መምሪያ - Koore Zone Police Department

የኮሬ ዞን ፖሊስ መምሪያ - Koore Zone Police  Department ያለህዝብ ተሳትፎ ሠላምን በዘላቂነት ማረጋገጥ አይቻልም

ዜና ችሎትበኮሬ ዞን ኬሌ ከተማ አስተዳደር የመጀመሪያ ደረጃ ፍርድ ቤት ዛሬ በዋለው ችሎት እጅ ከፍንጅ ተይዘው በከባድ ስርቆት ወንጀል ተከሰው በቀረቡ 5 ተከሳሾች ላይ ውሳኔ መስጠቱን አስታወ...
30/05/2026

ዜና ችሎት

በኮሬ ዞን ኬሌ ከተማ አስተዳደር የመጀመሪያ ደረጃ ፍርድ ቤት ዛሬ በዋለው ችሎት እጅ ከፍንጅ ተይዘው በከባድ ስርቆት ወንጀል ተከሰው በቀረቡ 5 ተከሳሾች ላይ ውሳኔ መስጠቱን አስታወቀ።

ኬሌ ፦ግንቦት 22/2018ዓ.ም

በከሌ ከተማ አስተዳደር 01 ከተማ ቀበሌ ቀጠና 3 ልዩ ስም ኤፍትስ/ፋጫ ተብሎ በሚጠራበት አከባቢ ተከሳሾች:-

1ኛ ምህረቱ መከሩ
2ኛ ማርቆስ ዮሐንስ
3ኛ ጌቱ አበበ
4ኛ ደስታ ደረሰ
5ኛ ቀቸለ ቦይለ የተባሉት በጋራ በመተባበር ጨለማን ተገን በማድረግ በቀን 21/9/2018 ዓ/ም ዕለተ ዓርብ ከለሊቱ 8:00 ሰዓት ገደማ ግል ተበዳይ ከሆነዉ ከአቶ ደሳለኝ ዱባሌ መኖርያ ቤት ዉስጥ ዘልቆ በመግባት ከከብቶቹ መሐል ትልቁን ኮርማ ዳላቻ በሬ ዋጋዉ 95 ሺህ ብር የሚያወጣውን ከታሰረበት ገመዱን በመፍታት ከባድ የስርቆት ወንጀል ፈፅመዉ ሲያመልጡ እጅ ከፍንጅ ተይዘው በቁጥጥር ስር ውለዋል በማለት ዓቃቤ ህግ በወንጀል ህግ አንቀጽ 32/1/ሀ/ እና 669 ንዑስ 3/ለ/መሠረት ክስ መስርቶባቸዉ አቅርቧል።

በዚህም መሠረት 1ኛ ተከሳሽ የሆነዉ እጅ ከፍንጅ ከበሬዉ ጋር እንደ ተያዘና ሌሎች ተከሳሾች ሮጠዉ ካመለጡበት ተይዘዉ እንደቀረቡ ዓቃቤ ህግ በክሱ አስረድቷል።

3ኛ ተከሳሽ አጠገብ ከምዕራብ ጉጅ ዞን ሰርቀዉ ካመጣቸዉ ከብቶች ስሸጡ ከቀሩት 2 ሴት ጥጃዎችን ኤግዚብት በማቅረብ በወንጀለኛ መቅጫ ሥነ ሥርዓት በ35 መሠረት የእምነት ክህደት ቃላቸዉን በመቀበል ክስ መስርቶ ለፍርድ ቤት አቅርቧል።

ተከሳሾችም ፍርድ ቤት ቀርበዉ የክስ ቻርጅ እያንዳንቸዉን ደርሶ አንብበዉ ከተረዱ በኃላ ፍርድ ቤት የክሱን ተቃዉሞ ጠይቆ ክሱን አንቃወምም በማለት ሃሳባቸዉን ሰጥተዋል።

ፍርድ ቤቱም በግላቸው ወይም በጠበቃ እንደምከራከሩና ጠይቆ በራሳቸዉ እንደሚከራከሩ አስረድተዉ 1ኛ, 2ኛና 3ኛ ተከሳሾች ወንጀሉን ፈጽመናል ስሉ 4ኛና 5ኛ ተከሳሾች አልፈፀምንም በማለት ክደዉ ተከራክረዋሉ።

ዓቃቤ ህግ አጠቃላይ በተፈፀመዉ ወንጀል ላይ የሚያስረዱ ምስክሮች አሉኝ በማለት 5 የሰዎችን ማስረጃ በማቅረብ በእያንዳንዳቸው አስመስክሮ ተከሻሾችም የመስቀለኛ ጥያቄዎችን ዐቃቤ ህግ ምስክሮችን ጠይቀዋል።

በዚህም መሠረት ፍርድም ቤቱ እያንዳቸውን ያስተምራል ሌሎችንም ያስተምራል ያላቸዉን
1ኛ ተከሳሽ 7 ዓመት ከ5 ወር
2ኛተከሳሽ 7 ዓመት ከ5 ወር
3ኛ ተከሳሽ 7 ዓመት ከ5 ወር
4ኛ ተከሳሽ 8 ዓመት
5ኛ ተከሳሽ 7 ዓመት ከ5 ወር በአጠቃላይ ተከሳሾችን በፅኑ እስራት ተቀተዋሉ።

በመጨረሻም ፖሊስና የፍትህ ተቋም በጋራ በሰጡት አስተያየት በዝህ መልክ በአካባቢያችን የሚከሰቱ ወንጀሎችን ለመከላከል ከፖሊስ ጎን በመቆም የተለመደዉን ድጋፍ እንድያደርግ ሀሳባቸዉን ሰጥተዋሉ።

በኮሬ ዞን የኬሌ ከተማ አሰተዳደር ፖሊስ ጽ/ቤት አዛዥ ረዳት ኢንስፔክተር አስረስ ሙልጌታ የአዉሮፓ ሻምፒዮንስ ሊግ ፍፃሜ ጫወታን በተመለከተ የጥንቃቄ መልዕክት አስተላልፈዋል።   ግንቦት 22...
30/05/2026

በኮሬ ዞን የኬሌ ከተማ አሰተዳደር ፖሊስ ጽ/ቤት አዛዥ ረዳት ኢንስፔክተር አስረስ ሙልጌታ የአዉሮፓ ሻምፒዮንስ ሊግ ፍፃሜ ጫወታን በተመለከተ የጥንቃቄ መልዕክት አስተላልፈዋል።

ግንቦት 22/2018 ዓ/ም

በኮሬ ዞን የኬሌ ከተማ አሰተዳደር ፖሊስ ጽ/ቤት አዛዥ ረዳት ኢንስፔክተር አስረስ ሙልጌታ የአዉሮፓ ሻምፒዮንስ ሊግ ፍፃሜ ጫወታን በተመለከተ የጥንቃቄ መልዕክት አስተላልፈዋል።

በመልዕክታቸውም የአዉሮፓ ሻምፒዮንስ ሊግ ፍፃሜ ጫወታ በሁለቱም ትላልቅ ክለቦች የሚደረግ እንደመሆኑ ደጋፊዎች የአሸናፊነት ደስታቸውን በሚገልጹበት ወቅት የስፖርታዊ ስነ ምግባር ጨዋነት በተላበሰ መልክ መሆን እንዳለበት አሳስበዋል ።

እያንዳንዱ ደጋፊ ደስታውን ሲገልጽ የስፖርታዊ ጨዋነትን መርህ በተከተለ በልክ መሆን እንዳለበት ያሳሰበው ፖሊስ ምንም ዓይነት የማህበረሰባችንን ሠላምና ደህንነት ማወክ አላስፈላጊ ድርጊቶችን መፈፀምና እርስ በርስ ትንኮሳዎች ፈጽሞ ተቀባይነት የሌላቸው መሆኑን አስገንዝበዋል።

በዚህም መሠረት ማንኛውም ባለ ሁለት እግር ሞተር ሳይክል ከፍጥነት ወሰን በላይ ማሽከርከር፣አላግባብ የሆኑ ድምፆችን ገጥሞ ማስጮህ እንድሁም ለደስታ መግለጫ ተብሎ በማንኛውም ተሽከርካሪ ሰልፍ መፍጠር ወይም መንገድ መዝጋትም በጥብቅ የተከለከለ መሆኑ ተገልጿል።

ይህን ጥሰው በሚገኙ አካላት ላይ ፖሊስ ህጋዊ እርምጃ በመውሰድ ህግ የማስከበር ስራ የምሰራ መሆኑን እያሳሰበ፣ማህበረሰባችን ወንጀልን በጋራ ከመከላከል ረገድ የተለመደውን ትብብር እንዲያደርግ ጥሪውን አቅርቧል።

የኮሬ ዞን ህዝብ ግንኙነትና ገፅታ ግንባታ ዲቪዥን

በኮሬ ዞን  የኬሌ ከተማ አሰተዳደር በዛሬው ዕለት በዋለው ችሎት የምርጫ ማስታወቂያ ምልክትን በመቅደድ የተከሰሰዉን ወጣት ተድላ ቶሼ የ2 ወራት ቀላል እስራት መቅጣቱን አስታወቀ።  ግንቦት 2...
29/05/2026

በኮሬ ዞን የኬሌ ከተማ አሰተዳደር በዛሬው ዕለት በዋለው ችሎት የምርጫ ማስታወቂያ ምልክትን በመቅደድ የተከሰሰዉን ወጣት ተድላ ቶሼ የ2 ወራት ቀላል እስራት መቅጣቱን አስታወቀ።

ግንቦት 21/2018 ዓ/ም

የኬሌ ከተማ አሰተዳደር ፖሊስ ጽ/ቤት ተከሳሽ ወንጀሉን በተፈጸመበት ቀን ወዲያውኑ ቦታው ላይ በቁጥጥር ስር ካዋለው በኋላ የምርመራ መዝገብ ከፍቶ ምርመራውን አጠናቅቆ ለከሌ ከተማ አስተዳደር ፍትህ ጽ/ቤት መዝገቡን አድርሷል።

አቃቤ-ህግ ተከሳሹን የኢትዮጵያ ምርጫ፤ የፖለቲካ ፓርቲዎች ምዝገባና የምርጫ ሥነ ምግባር አዋጅ ቁጥር 1162/2012 አንቀጽ 158 ላይ የተመለከተውን የህግ ድንጋጌ በመተላለፍ በቀን 29/08/2018 ዓ/ም በዕለተ ሐሙስ ከቀኑ 10:00 ሰዓት በከተማ አስተዳደር ቀበሌ 02 ቀጠና 1 በወ/ሮ ደመቀች ጴጾ ጠጅ ቤት ዉስጥ የብልጽግና ፖለቲካ ፓርቲ ደጋፊ የሆነ ግለሰብ የስንዴ ነዶ ያለበትን የብልጽግና ፓርቲ የምርጫ ምልክት ያለበትን ቲ-ሸርት ለምን ትለብሳለህ በማለት ፀብ በማንሳት የብልጽግና ልብሱን በመቅደድ የኢትዮጵያ ምርጫ ፖለተካ ፓርቲዎች የምዝገባና የምርጫ ሥነ ምግባር ተላልፏል በማለት ክስ ቀርቦበታል።

ለተከሳሽ የክስ ቻርጅ ደርሶ ችሎት ቀርቦ ድርጊቱን አልፈፀምኩም ብሎ ክዶ የተከራከረ ብሆንም ምስክሮች ቀርበው ተከሳሽ በፖለቲካ ክርክር ምክንያት ብቻ ወንጀሉን ሰለመፈጸሙ መስክረው የቀረቡ መከላከያዎች የቀረበውን ክስ ማስተባበል ያልቻሉ በመሆናቸው ፍርድ ቤቱ ተከሳሹ ተከሶ በቀረበበት የህግ ድንጋጌ ሥር ጥፋተኛ ካለው በኋላ የግራ ቀኙን የቅጣት ማቅለያ እና ማክበጃ ምክንያቶችን ተቀብሎ መርምሮ ተከሳሽን ያስተምራል ሌሎችንም ከተመሳሳይ ተግባር እንዲቆጠቡ ያደርጋል ያለውን በ2 ወር ቀላል እስራት መቅጣቱን አስታውቋል።

በኮሬ ዞን ጎርካ ወረዳ የኬሌ ምድብ ችሎት በዛሬው ዕለት በዋለው ችሎት የምርጫ ማስታወቂያ ምልክትን በመቅደድ የተከሰሰ ግለሰብ በ5 ወራት ቀላል እስራት መቅጣቱን አስታወቀ።  ግንቦት 21/20...
29/05/2026

በኮሬ ዞን ጎርካ ወረዳ የኬሌ ምድብ ችሎት በዛሬው ዕለት በዋለው ችሎት የምርጫ ማስታወቂያ ምልክትን በመቅደድ የተከሰሰ ግለሰብ በ5 ወራት ቀላል እስራት መቅጣቱን አስታወቀ።

ግንቦት 21/2018 ዓ/ም

የጎርካ ወረዳ ፖሊስ ጽ/ቤት ተከሳሽ ወንጀሉ በተፈጸመበት ቀን ወዲያውኑ ቦታው ላይ በቁጥጥር ስር ካዋለው በኋላ የምርመራ መዝገብ ከፍቶ ምርመራውን አጠናቅቆ ለጎርካ ወረዳ ፍትህ ጽ/ቤት መዝገቡን አድርሷል።

አቃቤ-ህግ ተከሳሹን የኢትዮጵያ ምርጫ፤ የፖለቲካ ፓርቲዎች ምዝገባና የምርጫ ሥነ ምግባር አዋጅ ቁጥር 1162/2012 አንቀጽ 158 ላይ የተመለከተውን የህግ ድንጋጌ በመተላለፍ በቀን 11/09/2018 ዓ/ም በእለተ ማክሰኞ ከቀኑ 11:00 ሰዓት በኬረዳ ቀበሌ በኬረዳ ከተማ ውስጥ በአቶ ኤርሚያስ ጠጅ ቤት አስመላሽ አሻግሬ የተባለው የብልጽግና ፖለቲካ ፓርቲ ደጋፊ የሆነ ግለሰብ የስንዴ ነዶ ያለበትን የብልጽግና ፓርቲ የምርጫ ማስታወቂያ ምልክት ያለበትን ቲ-ሸርት ለብሶ ጤጅ ቤት ውስጥ ተቀምጦ እየጠጣ ባለበት ወቅት የኢትዮጵያ ለዜጎች ማህበሪዊ ፓርቲ(ኢዜማ) የሚዛን ምልክት ያለበትን የምርጫ ቅስቀሳ ማስታወቂያ ቲ-ሸርት ለብሶ በመምጣት እንዴት የብልጽግና ፓርቲ ትደግፋለህ? በማለት ተነስቶ በመያዝ የለበሰውን የስንዴ ነዶ ያለበትን የብልጽግና ፓርቲ የምርጫ ምልክት ያለበትን ቲ-ሸርት ቀድዷል በማለት ክስ ቀርቦበታል።

ለተከሳሽ የክስ ቻርጅ ደርሶ ችሎት ቀርቦ ድርጊቱን አልፈፀምኩም ብሎ ክዶ የተከራከረ በመሆኑ ምስክሮች ቀርበው ተከሳሽ በፖለቲካ ክርክር ምክንያት ብቻ ወንጀሉን ሰለመፈጸሙ መስክረው የቀረቡ መከላከያዎች የቀረበውን ክስ ማስተባበል ያልቻሉ በመሆናቸው ፍርድ ቤቱ ተከሳቹ ተከሶ በቀረበበት የህግ ድንጋጌ ሥር ጥፋተኛ ካለው በኋላ የግራ ቀኙን የቅጣት ማቅለያ እና ማክበጃ ምክንያቶችን ተቀብሎ መርምሮ ተከሳሽን ያስተምራል ሌሎችንም ከተመሳሳይ ተግባር እንዲቆጠቡ ያደርጋል ያለውን ነፃነትን በሚያሳጣ 5 ወር ቀላል እስራት መቅጣቱን አስታውቋል።

ከኮሬ ዞን ፖሊስ መምሪያ የሰባተኛው ሀገራዊና ክልላዊ ምርጫን በተመለከተ የተላለፈ መልዕክትዘንድሮ የሚካሄደው የሰባተኛው ሀገራዊና ክልላዊ ምርጫ ሥራ ተጀምሮ አሁን ወደ ማጠቃለያው ማለትም የድ...
27/05/2026

ከኮሬ ዞን ፖሊስ መምሪያ የሰባተኛው ሀገራዊና ክልላዊ ምርጫን በተመለከተ የተላለፈ መልዕክት

ዘንድሮ የሚካሄደው የሰባተኛው ሀገራዊና ክልላዊ ምርጫ ሥራ ተጀምሮ አሁን ወደ ማጠቃለያው ማለትም የድምፅ አሰጣጥ ሂደት ለማከናወን ጥቅት ቀናቶች ይቀራሉ።

ስለሆነም ከግንቦት 20/2018 ዓ.ም ጀምሮ የድምፅ አሰጣጥ ሂደት እስከሚካሄድበት ድረስ ማነኛውም የፖለቲካ ፓርቲዎች ከብሔራዊ ምርጫ ቦርድ የተላለፉ መልዕክቶችን ማክበር አለባቸው።

የፖለቲካ ፓርቲዎች እና አባሎቻቸዉ በፍጹም ማድረግ የሌለባቸው ነገሮች

✍️ፖለቲካ ተኮር የህዝብ ስብሰባዎችና ሰልፎች
✍️የቤት ለቤትና የአደባባይ ላይ ቅስቀሳዎች
✍️የቅስቀሳ ሕትመቶች እና ቁሳቁሶችን መለጠፍ
✍️የቅስቀሳ አልባሳትን መልበስ
✍️የቀጥታም ሆነ የተቀረጹ የዕጩ ወይም የፓርቲ ፕሮግራሞች ሥርጭት
✍️የማህበራዊ ትስስር ገጾችን በመጠቀም ቅስቀሳ ማድረግ
✍️በምርጫ ቦርድ መመሪያዎች ላይ ያልተደነገጉ ምርጫ ተኮር ተግባራትን መፈጸም በፍጹም የተከለከለ መሆኑን እናሳውቃለን።

የኮሬ ዞን ፖሊስ መምሪያ አዛዥ ኮማንደር ስዳሞ ማዳሞ ለመላው ሙስሊም እምነት ተከታዮች እንኳን ለ1447ኛው ኢድ አል አድሃ/አረፋ በዓል በሠላም አደረሳችሁ አደረሰን በማለት መልካም ምኞታቸውን...
26/05/2026

የኮሬ ዞን ፖሊስ መምሪያ አዛዥ ኮማንደር ስዳሞ ማዳሞ ለመላው ሙስሊም እምነት ተከታዮች እንኳን ለ1447ኛው ኢድ አል አድሃ/አረፋ በዓል በሠላም አደረሳችሁ አደረሰን በማለት መልካም ምኞታቸውን አስተላልፈዋሉ፡፡

ኮማንደር ስዳሞ ማዳሞ14447ኛ ጊዜ የኢድ አል አደሃ አረፋ በዓል በሀገር አቀፍ እንዲሁም በደቡብ ኢትዮጵያ ክልል ባሉ ዞኖች እንድሁም በኮሬ ዞን ባሉ በሁለቱም ወረዳዎች እና በከተማ አስተዳደር በድምቀ በአደባባይ የሚከበር በመሆኑ ህዝበ ሙስሊሙ በዓሉን ሲያከብር የእምነቱን አስተምሮ በመከተልና በመተግበር ሊሆን እንደሚገባ በመልዕክታቸው ገለፀዋሉ፡፡

አክለዉም በዓሉ በከተማዉ አደባባዩ እና በወረዳዎች በጋራ በሰላት እና በስግደት የእምነቱ ተከታዮች በብዛት በሚወጡበት ሚከበር በመሆኑ የእምነቱ ተከታዮች ለሰላት ስግደት በሚንቀሳቀሱበት ወቅት ራሳቸውንና ቤተሰቦቻቸውን የህዝብ መሰብሰብን እንደ መልካም አጋጣሚ በማድረግ ከሚፈፀሙ ወንጀል ድርጊቶች እና የሰዉን ህይወት እየቀጠፈ ካለዉ እንድሁም የሀገርቱን ኢኮኖሚ እየጎዳ ካለዉ ከትራፊክ አደጋ ራሳቸዉንና ቤተሰቦቻቸውን በመጠበቅ በዓሉን ማክበር እንዳለባቸዉ ገልፀዉ ፍፁም ሰላማዊ ሆኖ እንዲጠናቀቅ የዞኑ ፖሊስ በየደረጃው ከሚገኙ መዋቅሮች ጋር በትኩረት በዓሉን በማስመልከት እየሰራ እንደሚገኝ ገልፀዋል፡፡

የኮሬ ዞን ፖሊስ መምሪያ ማህበረሰብ አቀፍ ወንንጀል መከላከል ዲቪዥን ኃላፍ ምክትል ኢንስፔክተር አራርሶ ነጋሽ ማህበረሰባችን በሀይማኖት መቻቻል እርስ በራሳቸው ተከባብረዉ የሚኖሩ በመሆናቸዉ በጋራ የሙስሊም እምነት ተከታዮች ኃይማኖታዊ በዓል በአደባባይ ስከበር ከፀጥታ አካል ጋር በመሆን ማንኛውንም የወንጀሉን ድርጊት ከጅምሩ ለማስቀረትና ተፈፅሞም ስገኝ ጥቆማዎችን በመስጠትና በመተባበር መሆን እንዳለበት ስገንዝበዉ።

በመጨረሻም ለእስልምና እምነት ተከታዮች በድጋሚ እንኳን ለ1447ኛው የዒድ አል አደሃ አረፋ በዓል በሰላም አደረሳችሁ ሲሉም የዞኑ አመራሮች መልካም ምኞታቸውን ገልጸዋሉ።

ዘገባዉ የኮሬ ዞን ፖሊስ መምሪያ ህዝብ ግንኙነት ዲቪዥን ነዉ

የኮሬ ዞን ፖሊስ መምሪያ እና ኬሌ ከተማ አስተዳደር ፖሊስ ጽ/ቤት  አመራር እንድሁም አባላቶች በጋራ በመሆን የቡድን ማስ ስፖርት መርሃግብር አከናውነዋል።ኬሌ፦ ግንቦት 12/2018 ዓ.ም በማ...
20/05/2026

የኮሬ ዞን ፖሊስ መምሪያ እና ኬሌ ከተማ አስተዳደር ፖሊስ ጽ/ቤት አመራር እንድሁም አባላቶች በጋራ በመሆን የቡድን ማስ ስፖርት መርሃግብር አከናውነዋል።

ኬሌ፦ ግንቦት 12/2018 ዓ.ም

በማስ ስፖር ላይ የተገኙ ኮማንደር አበበ ጣሰዉ የዞኑ አመራር በሰጡት አስተያየት የአካል ብቃት እንቅስቃሴ ለጤንነት አስፈላጊና የተሻለ ወታደራዊ ቁመናን ለማስተካከል አስፈላጊ በመሆኑ ክልል ባስቀመጠዉ ፕሮግራም መሠረት ከአመራር እስከ አባላት በመሳተፍ የማስ ቡድን ስፖርቱ እየተሰራ እንዳለ አስረድተዋል።

ኢንስፔክተር አራርሶ ነጋሽ በበኩላቸዉ የቡድን ስፖርት አባላት በስነ ልቦና እና በአካል ብቃት የነቃና ፖሊስ ተቋም ለመገንባት የአካል እንቅስቃሴ ወሳኝ ነዉ በማለት አልፎም በአባላቱ መካከል መቀራረብ የምንፈጥርበት አንዱ መንገድ እንደሆነ ገልጸዋል።

የኮሬ ዞን ፖሊስ መምሪያ የታክቲክ ምርመራ ዲቪዥን ኃላፍ የሥራ ርክክብ  የትዉዉቅ እና በተግባር አፈፃፀም ዙርያ የጋራ ዉይይት ማድረጉን አስታወቀግንቦት 10/2018 ዓ/ምየኮሬ ዞን ፖሊስ መም...
18/05/2026

የኮሬ ዞን ፖሊስ መምሪያ የታክቲክ ምርመራ ዲቪዥን ኃላፍ የሥራ ርክክብ የትዉዉቅ እና በተግባር አፈፃፀም ዙርያ የጋራ ዉይይት ማድረጉን አስታወቀ

ግንቦት 10/2018 ዓ/ም

የኮሬ ዞን ፖሊስ መምሪያ የታክቲክ ምርመራ ዲቪዥን ኃላፍ የሥራ ርክክብ የትዉዉቅ እና በተግባር አፈፃፀም ዙርያ የጋራ ዉይይት ማድረጉን አስታወቀ

የዞኑ ታክቲክ ምርመራ ኃላፍ ዋና ኢንስፔክተር ተክሌ ጫትሜ እንኳን ደህና መጣችሁ መልዕክት አስተላልፈዉ ዲቪዥኑን ስመራ ከነበረዉ ከኢንስፔክተር ድልነሳዉ ካሣ የሥራ ርክክብ አድርገዉ ከሌሎች ምርመራ ዲቪዥን ኃላፍዎች እና ከባለ ሙያዎች ጋር ትዉዉቅ በማድረግ ተግባር አፈፃፀም ዙርያ ዉይይት ማድረጋቸዉን ገልፀዋሉ።

አክለዉም የተግባር አፈፃፀማችንን በወቅቱና ቀን በቀን እየገመገምን የተሻለ ለማድረግ የእያንዳንዳችን ድርሻ ስለሆነ ሁሉም የምርመራ ሥራዎችን በትኩረት እና በቁርጠኝነት መስራት እንዳለበት አሳስበዋል።

በዉይይቱ ላይ የተገኙ የምርመራ ባለሙያዎችም ወደ ሥራ ሂደቱ እንኳን ደህና መጡ በማለት ቀጣይ መስራት ያለብንን ሥራዎችን በጋራ በቅርበት በመናበብ የተሻለ ተግባር አፈፃፀም ለማስመዝገብ ተረባርበን በመስራት የማህበረሰብን እርካታ ለማሳደግ የበኩላችንን ሙያዊ ድርሻችንን እንወጣለን በማለት ሀሳባቸውን አስቀምጠዋሉ።

በማጠቃለያዉ የታክቲክ ምርመራ ዲቪዥን ኃላፍ ተክሌ ጫትሜ የሥራ ስምርቶችን በመስጠት ወደ ተግባሮቻችሁ በመሰማራት ያልተሰሩ ቀሪ ስራዎች ካሉ በመፈተሽ በትጋት እንድትሰሩ በማለት ዉይይቱን አጠቃለዋሉ።

የዘገበው ኮሬ ዞን ህዝብ ግንኙነት ነዉ

ከኮሬ ዞን ፖሊስ መምሪያ የኬሌ ከነማ እግርኳስ ቡድን አቀባበልን በተመለከተ የተላለፈ መልዕክት ዛሬ በቀን 9/9/2018 ዓ.ም በደቡብ ኢትዮጵያ ክልል ክለቦች ሻሚፒዮን የሆነው የኬሌ ከነማ እ...
17/05/2026

ከኮሬ ዞን ፖሊስ መምሪያ የኬሌ ከነማ እግርኳስ ቡድን አቀባበልን በተመለከተ የተላለፈ መልዕክት

ዛሬ በቀን 9/9/2018 ዓ.ም በደቡብ ኢትዮጵያ ክልል ክለቦች ሻሚፒዮን የሆነው የኬሌ ከነማ እግርኳስ ወደ ኬሌ ከተማ ይገባሉ። ይህንን ምክንያት በማድረግ በዞኑ ባሉ መዋቅሮች ደማቅ አቀባበል ይደረጋል።

ይህንን የአቀባበል ፕሮግራም በሰላማዊ መንገድ ያለ ምንም ችግር እንዲጠናቀቅ አሽከርካሪዎች በጥንቃቄ እንዲያሽከረክሩና ደስታን ለመግለጽ ከርችት ጀሞሮ ያሉ ማንኛውም ተተኳሽ ነገሮችን ባለመተኮስ አቀባበሉ በሰላማዊ መንገድ እንዲጠናቀቅ ሁሉም የህብረተሰብ ክፍል ጥንቃቄ እንዲያደርግ ጥሪ እናስተላልፋለን።

የኮሬ ዞን ፖሊስ መምሪያ ኃላፊ ም/ኮማንደር ስዳሞ ማደሞ ለኬሌ ከነማ እግር ኳስ ቡድን የእንኳን ደስ አላችሁ መልዕክት አስተላልፈዋል።በደቡብ ኢትዮጵያ ክልል አዘጋጅነት በጂንካ ከተማ ሲካሄድ ...
15/05/2026

የኮሬ ዞን ፖሊስ መምሪያ ኃላፊ ም/ኮማንደር ስዳሞ ማደሞ ለኬሌ ከነማ እግር ኳስ ቡድን የእንኳን ደስ አላችሁ መልዕክት አስተላልፈዋል።

በደቡብ ኢትዮጵያ ክልል አዘጋጅነት በጂንካ ከተማ ሲካሄድ የቆየዉ የደቡብ ኢትዮጵያ ክልል ሻሚፒዮን ላይ ኮሬ ዞንን በመወከል ለፍፃሜ የቀረበዉ የኬሌ ከነማ እግርኳስ ክለብ የአርባምንጭ ዙሪያ እግርኳስ ቡድንን በመለያ ምት በማሸነፍ የዋንጫ ባለቤት ሆኗል።

ደስታዉን ምክንያት በማድረግ አሽከርካሪዎች በተለይም ሞተረኞች ደስታቸዉን ስገልጹ በጥንቃቄ እንዲያሽከረክሩ ም/ኮማንደር ስዳሞ ጥሪ አስተላልፈዋል።

 #ሹመት1. ረዳት ኢንስፔክተር አስረስ ሙሉጌታ-የኬሌ ከተማ አስተዳደር ፖሊስ አዛዥ 2. ዋና ኢንስፔክተር ተክሌ ጫትመ-የኮሬ ዞን ፖሊስ መምሪያ ታክትክ ወንጀል ምርመራ ዲቭዥን ኃላፊ በመሆን ...
10/05/2026

#ሹመት

1. ረዳት ኢንስፔክተር አስረስ ሙሉጌታ-የኬሌ ከተማ አስተዳደር ፖሊስ አዛዥ

2. ዋና ኢንስፔክተር ተክሌ ጫትመ-የኮሬ ዞን ፖሊስ መምሪያ ታክትክ ወንጀል ምርመራ ዲቭዥን ኃላፊ በመሆን ተሹመዋል።

መልካም የሥራ ዘመን!

Address

Amaro Kele
Kele

Alerts

Be the first to know and let us send you an email when የኮሬ ዞን ፖሊስ መምሪያ - Koore Zone Police Department posts news and promotions. Your email address will not be used for any other purpose, and you can unsubscribe at any time.

Share