የአማራ ክልል ጠቅላይ ፍርድ ቤት/ Supreme Court of Amhara Region

  • Home
  • Ethiopia
  • Kebele 13
  • የአማራ ክልል ጠቅላይ ፍርድ ቤት/ Supreme Court of Amhara Region
Call Website

የአማራ ክልል ጠቅላይ ፍርድ ቤት/ Supreme Court of Amhara Region ራዕያችን በአገር አቀፍ ደረጃ ተምሳሌት የሆነ ፍርድ ቤት መገንባት ነው ! / Our vision is excelling to become a model judiciary in Ethiopia !

የፈተና ውጤት ስለመግለጽ፤በአማራ ክልል ጠቅላይ ፍርድ ቤት የአይ.ሲ.ቲ ዳይሬክቶሬት ዳይሬክተር ቦታ ለመቀጠር ነሐሴ 18 ቀን 2018 ዓ.ም የጽሑፍ ፈተና የወሰዳችሁ ተወዳዳሪዎች፣ ውጤታችሁ ከ...
24/09/2026

የፈተና ውጤት ስለመግለጽ፤

በአማራ ክልል ጠቅላይ ፍርድ ቤት የአይ.ሲ.ቲ ዳይሬክቶሬት ዳይሬክተር ቦታ ለመቀጠር ነሐሴ 18 ቀን 2018 ዓ.ም የጽሑፍ ፈተና የወሰዳችሁ ተወዳዳሪዎች፣ ውጤታችሁ ከዚህ በታች በየመለያ ኮድ የተገለጸ ሲሆን፣ ለቀጣይ ዙር ፈተና ያለፋችሁ ተወዳዳሪዎች በ18/01/2019 ዓ. ም ከጥዋቱ 2፡30 ጠቅላይ ፍርድ ቤት (ባሕር ዳር) በአካል በመገኘት የቃለ-መጠይቅ ፈተና እንድትወሰዱ እናሳውቃለን፡፡

የፈተና ቀን ስለማሳወቅ፤የአማራ ከልል ጠቅላይ ፍርድ ቤት በ05/3/2018 ዓ.ም ለተለያዩ የአይሲቲ ክፍል ውድድሮች የፈተና ውጤት ማሳወቁ ይታወሳል፡፡ ስለሆነም፣ ቀደም ሲል የተሰጡትን ፈተናዎ...
18/09/2026

የፈተና ቀን ስለማሳወቅ፤

የአማራ ከልል ጠቅላይ ፍርድ ቤት በ05/3/2018 ዓ.ም ለተለያዩ የአይሲቲ ክፍል ውድድሮች የፈተና ውጤት ማሳወቁ ይታወሳል፡፡

ስለሆነም፣ ቀደም ሲል የተሰጡትን ፈተናዎች በማለፍ ለቀጣዩ የተግባር እና ቃለ መጠይቅ ፈተና ያለፋችሁ አመልካቾች ከዚህ በታች በተገለጸው ቀን፣ሰዓት እና ቦታ ማንነታችሁን የሚያረጋግጥ መታወቂያ በመያዝ ፈተናውን እንድትወስዱ እናሳውቃለን፡፡

የፈተና ውጤት ስለመግለጽ፤የአማራ ክልል ጠቅላይ ፍርድ ቤት በተለያዩ የአይ.ሰ..ቲ. የሥራ መደቦች ላይ በጠቅላይ ፍርድ ቤቱና በየከፍተኛ ፍርድ ቤቶች ሊያገለግሉ የሚችሉ ብቁ አመልካቾችን በሹመ...
10/09/2026

የፈተና ውጤት ስለመግለጽ፤

የአማራ ክልል ጠቅላይ ፍርድ ቤት በተለያዩ የአይ.ሰ..ቲ. የሥራ መደቦች ላይ በጠቅላይ ፍርድ ቤቱና በየከፍተኛ ፍርድ ቤቶች ሊያገለግሉ የሚችሉ ብቁ አመልካቾችን በሹመት ለመቅጠር አመልካቾችን በልዩ ልዩ የማጣሪያ መስፈርቶች በመለዬት ሂደት ላይ ይገኛል፡፡
በዚህም መሠረት የቅድመ ማጣሪያ መሥፈርቶችን ላለፉ ተወዳዳሪዎች ነሐሴ 18 እና 20 ቀን 2018 ዓ.ም የጽሑፍ እና የተግባር ፈተና መሰጠቱ ይታወሳል፡፡
ስለሆነም የተወዳዳሪዎችን ብዛት፣ በፈተና የተመዘገበውን ነጥብ እና ለሥራ መደቡ የሚፈለገውን የሰው ኃይል ብዛት ታሳቢ በማድረግ የመቁረጫ ነጥብ የሚከተለው እንዲሆን ተወስኗል፡፡
በዚህም መሰረት ወደ ቀጣይ ማጣሪያ የተመረጡ እና ያልተመረጡ በየፈተና ኮዱ ከዚህ በታች የተገለጸ በመሆኑ፣ ተወዳዳሪዎች በኮዳቸው አማካኝነት ውጤታቸውን እንዲያዩ እናሳውቃለን።

እንኳን ለ 2019 አዲስ ዓመት አደረሳችሁ!የአማራ ክልል ጠቅላይ ፍርድ ቤት ፕሬዝደንት ክቡር አቶ አለምአንተ  አግደው፣ በየደረጃው ለሚገኙ የክልሉ ፍርድ ቤቶች ዳኞች እና ሰራተኞች፣ ተገልጋዮ...
10/09/2026

እንኳን ለ 2019 አዲስ ዓመት አደረሳችሁ!

የአማራ ክልል ጠቅላይ ፍርድ ቤት ፕሬዝደንት ክቡር አቶ አለምአንተ አግደው፣ በየደረጃው ለሚገኙ የክልሉ ፍርድ ቤቶች ዳኞች እና ሰራተኞች፣ ተገልጋዮች፣ ለመላው የክልሉ ሕዝብ እና ኢትዮጵያውያን በሙሉ እንኳን ለ2019 አዲስ ዓመት አደረሳችሁ ብለዋል።

የትምህርት እድል ምልመላ ማስታወቂያ፤የአማራ ክልል ጠቅላይ ፍርድ ቤት በ2019 በጀት ዓመት በየደረጃው ከሚገኙ ፍርድ ቤቶች በሕግ የመጀመሪያ ዲግሪ ካላቸው ዳኞች እና የጉባኤ ተሿሚዎች መካከል...
08/09/2026

የትምህርት እድል ምልመላ ማስታወቂያ፤

የአማራ ክልል ጠቅላይ ፍርድ ቤት በ2019 በጀት ዓመት በየደረጃው ከሚገኙ ፍርድ ቤቶች በሕግ የመጀመሪያ ዲግሪ ካላቸው ዳኞች እና የጉባኤ ተሿሚዎች መካከል አወዳድሮ በሕግ በሁለተኛ ዲግሪ ኘሮግራም ለማስተማር ይፈልጋል፡፡

ስለሆነም የሚከተሉትን መመዘኛዎች የምታሟሉ ተወዳዳሪዎች እንድትወዳደሩ ተጋብዛችኋል፡፡

የአማራ ክልል ጠቅላይ ፍርድ ቤት እና አክሽን ፎር ዴቨሎፕመንት ኤንድ ኢንቫይሮንመንታል ፕሮቴክሽን ኦርጋናይዜሽን (አስዴፖ) በጋራ ለመስራት የመግባቢያ ስምምነት ተፈራረሙአዲስ አበባ፣ጳጉሜ 2/...
08/09/2026

የአማራ ክልል ጠቅላይ ፍርድ ቤት እና አክሽን ፎር ዴቨሎፕመንት ኤንድ ኢንቫይሮንመንታል ፕሮቴክሽን ኦርጋናይዜሽን (አስዴፖ) በጋራ ለመስራት የመግባቢያ ስምምነት ተፈራረሙ

አዲስ አበባ፣ጳጉሜ 2/2018 (የአማራ ክልል ጠቅላይ ፍርድ ቤት)

የአማራ ክልል ጠቅላይ ፍርድ ቤት እና አስዴፖ በትብብር በመስራት የዳኝነት እንዲሁም የፍትህ ሥርዓቱን ውጤታማነት ማደበር የሚያስችል ስምምነት፣ የአማራ ክልል ጠቅላይ ፍርድ ቤት ፕሬዝዳንት ዓለምአንተ አግደው እና የአስዴፖ ዋና ዳይሬክተር አቶ ምህረትአብ በላይ ተፈራርመዋል፡፡

በስምምነት ሰነዱ ተቋማቱ በፍርድ ቤቱ የሚደረጉ የሠው ሃብት አቅም ግንባታ ስራዎች፣ ተጋላጭ የሆኑ የማህበረሰብ አካላት ጥበቃ በተለይ የህፃናት መብት ጥበቃ፣ የፆታዊ ጥቃት ተጋላጭ የሆኑ የማህበረሰብ ክፍል ጥበቃ፣ ዘላቂ ሰላም ግንባታ እና የአካባቢ ጥበቃ ላይ በጋራ ለመስራት ስምምነት አድርገዋል፡፡

ክቡር ፕሬዝዳንቱ በክልሉ ፍርድ ቤቶች የተሰሩ ስራዎች እና ቀጣይ የትኩረት አቅጣጫዎች ያብራሩ ሲሆን፣ የአስዴፖ ዋና ዳይሬክተር ፍርድ ቤቱ በአጭር ግዜ ያከናወናቸውን ተግባራትን በማድነቅ ተቋማቸው በተሰማራባቸው ዘርፍ ላይ ፍርድ ቤቱን ለማገዝ ያላቸውን ቁርጠኝነት ገልፀዋል፡፡

የአማራ ክልል ምክር ቤት ዋና አፈ- ጉባኤ፣ የተከበሩ ወይዘሮ ፋንቱ ተስፋዬ የአማራ ክልል ጠቅላይ ፍርድ ቤት ያስገነባው የፍትሕ ሙዚየም ነሐሴ 28/2018 ዓ.ም ተመርቆ በተከፈተበት ወቅት ሙ...
07/09/2026

የአማራ ክልል ምክር ቤት ዋና አፈ- ጉባኤ፣ የተከበሩ ወይዘሮ ፋንቱ ተስፋዬ የአማራ ክልል ጠቅላይ ፍርድ ቤት ያስገነባው የፍትሕ ሙዚየም ነሐሴ 28/2018 ዓ.ም ተመርቆ በተከፈተበት ወቅት ሙዚየሙን ከጎበኙ በኋላ ከሰጡት አስተያየት የተወሰደ፤

"ሙዚየሙ የፍትሕ ሥርዓታችን የተጓዘበትን ጉዞ በግልጽ የሚያሳይ፣ ለቀጣይ የፍትሕ ሥርዓት ማሻሻያ ምርምር ለማድረግ ጉልበት የሚሆን መረጃ የተሰባሰበበት፣ ትላንትን ከዛሬ፣ ዛሬን ከነገ የሚያስተሳስር እና የዘመኑ ሪፎርም የታየበት ነው"

የአማራ ክልል ርዕሰ መስተዳደር ክቡር አቶ አረጋ ከበደ፣ ነሐሴ 28/2018 ዓ.ም የአማራ ክልል ጠቅላይ ፍርድ ቤት ያስገነባውን ዘመናዊ የፍትሕ ሙዚየም መርቀው በከፈቱበት ወቅት ከተናገሩት የ...
07/09/2026

የአማራ ክልል ርዕሰ መስተዳደር ክቡር አቶ አረጋ ከበደ፣ ነሐሴ 28/2018 ዓ.ም የአማራ ክልል ጠቅላይ ፍርድ ቤት ያስገነባውን ዘመናዊ የፍትሕ ሙዚየም መርቀው በከፈቱበት ወቅት ከተናገሩት የተወሰደ፤

" የዳኝነትና የፍትሕ ታሪካችንን በአንድ ማዕከል የሚያሳየው ይህ ሙዚየም፣ ለትውልድ ማስተማሪያ፣ ለጥናትና ምርምር አጋዥ እንዲሁም የሕብረተሰባችን የማንነት መገለጫ ነው"

የአማራ ክልል ጠቅላይ ፍርድ ቤት ፕሬዝደንት ክቡር አቶ አለምአንተ አግደው የጠቅላይ ፍርድ ቤቱ ፍትሕ ሙዚየም በይፋ ተመርቆ ለጉብኝት ክፍት በሆነበት ወቅት ከተናገሩት የተወሰደ 👇"የአማራ ክል...
05/09/2026

የአማራ ክልል ጠቅላይ ፍርድ ቤት ፕሬዝደንት ክቡር አቶ አለምአንተ አግደው የጠቅላይ ፍርድ ቤቱ ፍትሕ ሙዚየም በይፋ ተመርቆ ለጉብኝት ክፍት በሆነበት ወቅት ከተናገሩት የተወሰደ 👇

"የአማራ ክልል የፍትሕ ሙዚየም ተቀዳሚ አላማዎች ታሪክን ጠብቆ ለማቆየት፣ለጥናትና ምርምር እንዲሁም ለቀጣይ የፍትሕ ሥርዓት ማሻሻያዎች መነሻ ሆኖ ማገልገል ነው"

Address

Bahir Dar
Kebele 13
P.BOX901

Alerts

Be the first to know and let us send you an email when የአማራ ክልል ጠቅላይ ፍርድ ቤት/ Supreme Court of Amhara Region posts news and promotions. Your email address will not be used for any other purpose, and you can unsubscribe at any time.

Shortcuts

Share