Debay pp youth league office

Debay pp youth league office ዛሬም ነገም ብልፅግና ለሁሉም

በምስራቅ ጎጃም ዞን የደባይ ጥላት ግን ወረዳ አስተዳደር  በመልሶ ማደራጀቱ የተዋቀረ የካቢኒ አባላት ሹመት1/ አቶ ጎጃም ሰዋለ--------ም/አስተዳዳሪ2/ አቶ ፀሐይ በለጠ--------ብልፅ...
19/01/2022

በምስራቅ ጎጃም ዞን የደባይ ጥላት ግን ወረዳ አስተዳደር በመልሶ ማደራጀቱ የተዋቀረ የካቢኒ አባላት ሹመት
1/ አቶ ጎጃም ሰዋለ--------ም/አስተዳዳሪ
2/ አቶ ፀሐይ በለጠ--------ብልፅግና ፅ/ቤት ሃላፊ
3/ ወ/ሮ የሻለም አበበ-------- ብልፅግና አደረጃጀት ዘርፍ ሃላፊ
4/ አቶ ጤነው አለ ---------የሲ/ሰ/ፅ/ቤት ሃላፊ
5/ ወ/ሮ ታውራኝ ባየ-----------ዋና አፈ ጉባኤ
6/ ወ/ሮ ካሱየ አላምኔ---------ም/አፈ ጉባኤ
6/ አቶ ልቅነው ጌታቸው--------ብልፅግና ፓ/ምክትል ሃላፊ
7/ አቶ ደምስ ብርቁ---------ብልፅግና አደረጃጀት ምክትል ሃላፊ
8/ አቶ ግዛቸው ጥላሁን-------ኦ/ቁ/ኮሚሽን ሃላፊ
9/ አቶ ሰዋለ መኮነን---------አስተዳደር ፅ/ቤት ሃላፊ
10/ አቶ ጌታሰው ገድፍ--------አ/መ/ም/ዋ/ተ/ፅ/ቤት ሃላፊ
11/ አቶ ተፈራ በዜ-----------የመስኖ እና ቆላማ /አካ/ፅ/ቤት ሃላፊ
12/ አቶ በላቸው አቦዝን--------ሰላምና ደህንነት ፅ/ቤት ሃላፊ
13/ አቶ ትልቅሰው አጥናፋ-------ወጣቶችና ስፓርት ፅ/ቤት ሃላፊ
14/ አቶ ግዛቸው ሰጋሆዴ---------ጤና ፅ/ቤት ሃላፊ
15/ አቶ አበበ ንጉሴ----------ጤና ፅ/ቤት ምክትል ሃላፊ
16/ አቶ ሽመልስ አሳቡ----------ስራና ስልጠና ፅ/ቤት ሃላፊ
17/ ወ/ሮ ያየሽ ሙሉ----------የስራና ስልጠና ፅ/ቤት ም/ሃላፊ
18/ አቶ ደመቀ ብርሃኑ -----------የትምህርት ፅ/ቤት ሃላፊ
19/ አቶ ይፍረድ ጌቴ---------ትም/ት ፅ/ቤት ምክትል ሃላፊ
20/ አቶ ተኮላ ብዙአየሁ--------የመንገድ ትራንስፓርት ፅ/ቤት ሃላፊ
22/ አቶ ይታየው ካሳ----------ገቢዎች ፅ/ቤት ሃላፊ
23/ አቶ ሙሉጌታ መኩ--------ገ/ኢ/ል/ፅ/ቤት ሃላፊ
24/ አቶ ጌትነት ዋገው ------------የገ/ኢ/ል/ፅ/ቤት ም/ ሃላፊ
24/ አቶ ባያብል ሃይማኖት ------------የኢንቨስትመንት ፅ/ቤት ሃላፊ
25/ ወ/ሮ ጥሩወርቅ አባተ-------የሴ/ህ/ማ/ጉ/ፅ/ቤት ሃላፊ
26/ ወ/ሮ የሽወርቅ ተስፋየ ----------የመ/ኮ/ጉ/ፅ/ቤት ሃላፊ
27/ ወ/ሮ ማንጠግቦሽ አሰፋ ----------የባ/ቱ/ፅ/ቤት ሃላፊ
28/ አቶ ታሪኩ ምንዋገው -------የወ/ሊግ ፅ/ቤት ሃላፊ
29/ ወ/ሮ ስንቱ ታየ---------የወ/ሊግ ም /ሃላፊ
30/ ወ/ሮ መልካም ባንታምላክ-----ሴ/ሊግ ሃላፊ
31/ ወ/ሮ ሙሉ ብርሃን -------ሴ/ሊግ ም/ሃላፊ
32/ አቶ ባንቴ ህብስቱ ---------የቁይ መሪ መዘጋጃ ስራ አስኪያጅ
33/ አቶ ሙሉሰው ገበየሁ ------የቁይ መሪ መዘጋጃ ምክትል ስራ አስኪያጅ
34/ አቶ ቢያዝን ቸኮል--------የከ/ል/ቤ/ኮ ፅቤት ሃላፊ
35/ አቶ መናሰው መኮነን-------ግብርና ፅ/ቤት ሃላፊ
36/ አቶ ዳምጤ አድማስ ------የህ/ስ/ማ/ፅ/ቤት ሃላፊ
37/ አቶ መኩሬው ትዕዛዙ --------የእን/አሳ/ሃ/ል ፅ/ቤት ሃላፊ
38/ አቶ ብርሃኑ ፈንቴ--------የውሃ ሀብት ፅ/ቤት ሃላፊ
39/ አቶ ያሬ ዳኘ ---------የገ/መ/አስ/አጠ/ፅ/ቤት ሃላፊ
40/ ወ/ሮ ሙሉአለም ግዛቸው -------የግብርና ምክትል ሃላፊ
41/ አቶ ሳላስብ ደባስ -------ሰ/ደ/ፅ/ቤት ም/ሃላፊ
42/ አቶ ተመስጌን ያለው ------ንግ/ገበ/ል/ፅ/ቤት ሃላፊ

በመሆን የተሾሙ ሲሆን የሴቶች ኮታ 26% አሳትፏል።
50% በአዲስ የተዋቀረ ነው። ለተሿሚዎች መልካም የስራ ዘመን ይሁን።
ማገልገል ክቡር ነው! አገልጋዬች እንሁን::

ጥምቀት ሲመጣ ኢትዮጵያ ታሸበርቃለችእንኳን ለብርሀነ ጥምቀቱ በሰላም በጤና አደረሳችሁ    የጥምቀት  በዓል የሰላም የጤና የፍቅር የመተሳሰብ ማህበራዊ ሀብቶቻችንን  የምናንፀባርቅበት እዲሆን ...
18/01/2022

ጥምቀት ሲመጣ ኢትዮጵያ ታሸበርቃለች
እንኳን ለብርሀነ ጥምቀቱ በሰላም በጤና አደረሳችሁ
የጥምቀት በዓል የሰላም የጤና የፍቅር የመተሳሰብ ማህበራዊ ሀብቶቻችንን የምናንፀባርቅበት እዲሆን የደባይ ጥላት ግን ወረዳ ብልፅግና ፓርቲ ወጣቶች ሊግ ጽ/ቤት ሀላፊ አቶ ትልቅሰው አጥናፉ መልክታቸውን አስተላልፈዋል ወጣቱ ሀይልም የድርሻውን ሀላፊነት እንዲወጣም መልክት አስተላልፈዋል።
"መልካም የጥምቀት በዓል"

መንግሥት ፋኖን ትጠጥቅ ሊያስፈታ ነው የሚለው አሉባልታ መሰረተቢስና የአማራን ሕዝብ ለመከፋፈል የታለመ የጠላት ሴራ መሆኑን የአማራ ክልል መንግሥት አስታወቀ። መንግሥት ፋኖን ትጠጥቅ ሊያስፈታ...
15/01/2022

መንግሥት ፋኖን ትጠጥቅ ሊያስፈታ ነው የሚለው አሉባልታ መሰረተቢስና የአማራን ሕዝብ ለመከፋፈል የታለመ የጠላት ሴራ መሆኑን የአማራ ክልል መንግሥት አስታወቀ።

መንግሥት ፋኖን ትጠጥቅ ሊያስፈታ ነው የሚለው አሉባልታ መሰረተቢስና የአማራን ሕዝብ ለመከፋፈል የታለመ የጠላት ሴራ መሆኑን የአማራ ክልል መንግሥት አስታውቋል።

የክልሉ መንግሥት ከፋኖ አደረጃጀት አባላት ጋር ተወያይቷል።

ፋኖ ከሌሎች የፀጥታ አካላት ጋር በመቀናጀት ሀገርና ሕዝብን እየታደገ ያለ መከታ ኃይል ነው። ስለሆነም የፌደራልም ኾነ የክልል መንግሥት ፋኖን ትጥቅ የማስፈታት ሐሳብ የለውም፤ ሊኖረውም አይችልም ተብሏል በመድረኩ።

በቀጣይ የክልሉ መንግሥት የመሳሪያ አስተዳደር ሥርዓቱን ሊያሻሽል እንደሚችልም ተገልጿል።

ፋኖ በስምም ሆነ በግብሩ የአማራ ሕዝብ ክብር መገለጫ በመሆኑ በፋኖ ስም የሚነግዱ አካላትን ፋኖና መንግሥት በጋራ ይታገላሉ ተብሏል። ፋኖን ማደራጀትና ማጠናከር የክልሉ መንግሥት አቅጣጫና ተግባር ኾኖ ሳለ ትጥቅ ማስፈታት የሚለው አሉባልታ አማራን የመከፋፈል እርስ በርስ የማጋጨት የማዳከም ሴራ አካል መሆኑም ተገልጿል።

አሚኮ

#ኢትዮጵያን እናልማ፣እንገንባ፣እንዘጋጅ!

ጎንደር በፍቅርና በደስታ ለምትቀበላቸው ውድ እንግዶቿ ያላትንና ቤቷ ያፈራውን ሁሉ ለመስጠት አትነፍግም!******************የጥምቀትን በዓል በታሪካዊቷ ጎንደር ከተማ ለመታደም ወደ ሀ...
13/01/2022

ጎንደር በፍቅርና በደስታ ለምትቀበላቸው ውድ እንግዶቿ ያላትንና ቤቷ ያፈራውን ሁሉ ለመስጠት አትነፍግም!
******************
የጥምቀትን በዓል በታሪካዊቷ ጎንደር ከተማ ለመታደም ወደ ሀገራችሁ ለገባችሁ ኢትዮጵያውያንና የኢትዮጵያ ወዳጆች በሙሉ የእናተን መምጣት በክብር፣ በናፍቆት፣ በፍቅርና በደስታ የምትጠባበቀው የእናት ዓለም ጎንደር ቤት ጓዳም አይነተ ብዙና በበርካታ ታሪካዊና ተፈጥሯዊ ጸጋዎች የተሞላ ነው። የአጼዎቹ መናገሻ የሆነችው እማማ ጎንደርም በጸጋዋ ልክ በደስታ ለምትቀበላቸው ውድ እንግዶቿ ያላትንና ቤቷ ያፈራውን ለመስጠትና ለመለገስ አትሰስትም። አትነፍግም። በክብር፣ በእልልታ በደስታ ለመቀበልም አትለግምም። ወደኋላም አትልም። እነሆ ዝግጅቷን አጠናቃ፤ እንግዶቿን ለመቀበል በመጠባበቅ ላይ ትገኛለች።
የጥምቀት በዓልን በውቢቷ ጎንደር ለመታደም ወደ ክልላችን የገባችሁና በመግባት ላይ ለምትገኙ ትውለደ ኢትዮጵያውያንና የኢትዮጵያ ወዳጆች በሙሉ ጎንደር እልፍኝና አዳራሹ ሰፊ፣ ጥንታዊና ታሪካዊ ቦታዎቹ አስተማሪ፣ እምቅ የተፈጥሮ ሀብቶቹ ማራኪ፣ ባህል፣ ወግና ጥበቡ አስደናቂ ነው። በቀደምት ጠቢባን አባቶቹ ብርቱ ክንድ ታንጾ ለትውልድ የተሻገረውና በዓለም ቅርስ መዝገብ በዩኔስኮ የተመዘገበው ጥንታዊውና ታሪካዊው የአጼዎቹ አብያተ መንግሥታት ኪነ ህንጻ ባለቤት ነው።
በዘመኑ ጠቢባን የታነጸው ጥንታዊው የአፄ ፋሲለደስ ቤተ መንግሥትም የቀደምት ታሪካችን ገናናነት ለዓለም የሚያስተጋባ ህያው ምስክር ነው። የአፄ ፋሲል ቤተ መንግስት የተገነባው በአፄ ፋሲለደስ ዘመነ መንግስት በ1632 ዓ.ም. ሲሆን ኪነ ህንጻዎቹ በ70 ሺህ ካሬ ሜትር ቦታ ላይ የታነጹ ናቸው፡፡ ኪነ ህንጻው አስራ ሁለት መግቢያና መውጫ በሮችን ያካተተ ነው፡፡
የኪነ- ህንጻው በሮችም የመጀመሪያው የንጉሶች ወይንም የሹማምንቶች መግቢያና መውጫ "ወንበር በር"፣ የቤተመንግስቱ ዋና በር ወይም የነገሥታቱ ቤተሰብ መግቢያና መውጫ "ፊት በር (ጃንተከል በር)"፣ ባለሙያዎችና ልዩ ልዩ አገልግሎት የሚሰጡበትና የቤተክርስቲያን ንዋያተ ቅዱሳን የተቀመጠበት እንዲሁም ያሬዳዊ ዝማሬዎችን የሚያቀርቡ መግቢያና መውጫ "ግምጃ ቤት በር"፡፡
በእቴጌ ምንትዋብ እናት ስም የተሰየመው "እንኳየ በር"፣ የራስ ማዕርግ ያገኙ የሚገቡበትና የሚወጡበት "ራስ በር"፣ ለቤተ መንግስቱ ለግንባታ የሚውሉ (የሚያሰፈልጉ) እቃዎች የሚገቡበት "ቀጭን አሸዋ በር"፣ በእድሜ የገፉ እናቶችና አባቶች መግቢያና መውጫ "ደናግላን /ርግብ በር"፣ የንጉሱ አጃቢዎች ከነ ፈረሶቻቸው ከፈረስ ሳይወርዱ የሚገቡበትና የሚወጡበት "ፈረስ /ባልደራስ በር"፣ እቴጌ ምንትዋብ በነገሰችበት ጊዜ ሴቶችን የምታሰለጥንበት ቦታ ነው፡፡ ዶሮ እንዴት እንደሚሰራ፣ ፈትል እንዴት እንደሚፈተል፣ ባህላዊ መጠጦች እንዴት እንደሚዘጋጁ፣ ጠጁ እንዴት እንደሚጣልና ጠላውም እንዴት እንደሚጠመቅ የሚማሩ ሰልጣኞቹ መውጫና መግቢያ "ኳሊ በር"፡፡
ቤተ- መንግስቱ ውስጥ የሚኖሩ ነገስታቱና ቤተሰቦቻቸው የሚያውቁት ነገር ግን በማኅበረሰቡ ዘንድ የማይታወቅ ሚስጥራዊ የአደጋ ጊዜ መውጫ "አደናግር በር"፣ የንጉሱ ታዛዥ ወይንም ተላላኪዎች ለታችኞቹ ክፍሎች መልዕክት ለማስተላለፍ የሚገቡበት እና የሚወጡበት "ተስካሩ በር" እንዲሁም የሙዚቃ ተጫዋቾቹ መሳሪያዎቻቸውን እያጫወቱና እየተጫወቱ የሚገቡበትና የሚወጡበት "እምቢልታ በር" ናቸው፡፡
በተጨማሪም በኪነ ህንጻው ውስጥ የስድስት ነገስታት ቤተ-መንግስት ይገኛል፡፡ እነዚህም አፄ ዮሀንስ፣ አድያም ሰገድ ኢያሱ፣ አፄ በካፋ፣ ቋረኛ ኢያሱ፣ አፄ ፋሲለደስ እና እቴጌ ምንትዋብ ናቸው፡፡ የአፄ ፋሲል ቤተ መንግስት

 # ዘመቻ በላይ ዘለቀ!!                                                                                 ህዳር16/03/2014ዓ.ምየደባይ ጥላ...
26/11/2021

# ዘመቻ በላይ ዘለቀ!! ህዳር16/03/2014ዓ.ም
የደባይ ጥላት ግን ወረዳ ወጣቶች እና የመንግስት ሰራተኞች ወጣቶች አሸባሪውን የህዋሀት አሸባሪ ቡድን ወይም ጁንታ ለአንዴ እና ለመጨረሻ ለመደምሰስ ወደ ማሠልጠኛ ጣቢያዎች እና ወደ ጦር ግንባር እየዘመቱ ነው ቀጣይ ለመዝመት እየተዘጋጁ ያሉ ወጣቶችም የምሳ ግብዣ አድርገው በድል ተመለሱልን የኛ ጀግኖች ብለው ሽኝት አድርገዋል ‼‼‼

ዘመቻ   በላይ ዘለቀበምስራቅ ጎጃም ዞን የደባይ ጥላት ግን ወረዳ አስተዳደር ምክር ቤት እና የደብረ ማርቆስ ዪኒቨርስቲ ሙህራን ትብብር በወቅታዊ አገራዊ ጉዳይ ዙሪያ ላይ  ከተለያዩ ከመንግስ...
14/11/2021

ዘመቻ በላይ ዘለቀ
በምስራቅ ጎጃም ዞን የደባይ ጥላት ግን ወረዳ አስተዳደር ምክር ቤት እና የደብረ ማርቆስ ዪኒቨርስቲ ሙህራን ትብብር በወቅታዊ አገራዊ ጉዳይ ዙሪያ ላይ ከተለያዩ ከመንግስ ሰራተኛ ፣ ከሀይማኖት አባቶች፣ ከወጣቶች ፣ ከሴቶች ጋር የተዘጋጀ የባለ ድርሻ አካላት ዘመቻ በላይ ዘለቀ በቀን05/03/2014ዓ.ም የምክክር መድረክ ተካሂዷል።
የሀገራችን ጠላት የሆነውን የህዋት አሸባሪ ቡድን ለመደምሰስ አስፈላጊውን ዘመቻ ሁሉ በመሰለፍ እናአሸባሪ የትግራይ ወራሪ ኃይል ከምድር ገጽ እስኪጠፋ ድረስ ለመታገል ዝግጁ መሆናቸውና የጀመርነውን የሎጀስቲክ ድጋፍ አጠናክረን በመቀጠልና በየግንባሩ በመዝመት ሀገርን ከብተና የምንታደግበት ጊዜው አሁን ነው ሲሉ ተሳታፊዎች የተናገሩ ሲሆን በመጨረሻም የአማራ ማንነት ለማጥፋትና ኢትዮጲያን ለማፍረስ የተነሳውን አሸባሪው ወራሪ የህወሃት ቡድን አኩይ አላመውን ለማሳካት አውጭ ጠላቶች ጋር ወግኖ በሃገራችን ሉዋላዊነት ላይ ከባድ ፈተና ደቀኗል። ስለዚህ ይህንአሸባሪ ቡድን የጀመረውን የሽበርተኝነት ወረራና ዘረፋ ለማስቆምና ወራሪ ኃይሉን ከስር መሰረቱ ደምስሶ የሀገርን ሉዋላዊነትን የህዝብን ሰላምን ለማስጠበቅ ከመንግስ ጎን እንደሚቆ ሙዝግጁ መሆናቸውን ተናግረዋል።

አሸባሪነት ይቀበራል
#አማራነት ይለመልማል
🇪🇹ኢትዮጲያነትም ትቀጥላለች !!!

የምስራቅ ጎጃም ዞን ደባይ ጥላት ግን ወረዳ የሎጀስቲክስ ድጋፍ ወደ ግንባር ዛሬም በቀን 03/03/2014 ዓ.ም በተጠናከረ መንገድ  እንደቀጠለ ነው  የደባይ ማህበረሰብ እጅግ ምስጉን ለወገን...
12/11/2021

የምስራቅ ጎጃም ዞን ደባይ ጥላት ግን ወረዳ የሎጀስቲክስ ድጋፍ ወደ ግንባር ዛሬም በቀን 03/03/2014 ዓ.ም በተጠናከረ መንገድ እንደቀጠለ ነው የደባይ ማህበረሰብ እጅግ ምስጉን ለወገን ደራሽ ጁንታን ደምሳሽ መሆኑን እያሳየ ስለሆነ እናመሰግናለን ነገም ተጠናክረን እንቀጥላለንም ብለዋል።
"ድል ለኢትዮጵያ "

01/11/2021

ከአማራ ክልል መስተዳድር ምክር ቤት የተላለፈ አስቸኳይ ጥሪ
የትህነግ አሸባሪና ወራሪ ኃይል በአማራ ክልል ሕዝቦች ላይ
መጠነ ሰፊ ጥቃት
እየፈፀመ ህዝቡን እየገደለና እያዋረደ፤ ንብረቱን እየዘረፈ፣
እያወደመ እና
ኢትዮጵያን ለማፍረስ የመጨረሻ የሞት ሽረት ትግል እያደረገ
ነው፡፡ ይህንን
በተጨባጭ እየገጠመን ያለውን የሕልውና አደጋ ለመቀልበስ
በመደበኛው
የሕግ ማስከበር ሥርዓት ብቻ ማሸነፍ የማይቻል ሆኖ በመገኘቱ፤
የአማራ ክልል መስተዳድር ምክር ቤት ጥቅምት 21 ቀን 2014
ዓ.ም ባካሄደው
6ኛ ዙር፣ 1ኛ ዓመት የሥራ ዘመን 4ኛ አስቸኳይ ስብሰባ
የሚከተሉትን የአስቸካይ
ጥሪ ውሳኔዎች አስተላልፏል፡፡
1. ከሚሰጡት አገልግሎት አስፈላጊነት አኳያ እየተመዘነ የሚወሰን
መሆኑ
እንደተጠበቀ ሆኖ፣ ማንኛውም የመንግስት ተቋም መደበኛ
አገልግሎቱን አቋርጦ
በጀቱን ጨምሮ ሁሉንም ነገር የገጠመንን የህልውና ዘመቻ
ለመቀልበስ
በሚያስችሉ ጉዳዮች ላይ እንዲረባረብ ተወስኗል፣
2. ሁሉም የመንግስት ተሸከርካሪ ወደ አንድ ማዕከል በማሰባሰብ
ለሕልውናው
ዘመቻ አገልግሎት እንዲውል እንዲደረግ፣
3. የግል ተሸከርካሪ ባለቤቶች ለሕልውና ዘመቻው ስኬት ሲባል
በተፈለገ ጊዜ
ሁሉ ተሸከርካሪዎቻቸውን በመስጠት ኃላፊነታቸውን እንዲወጡ
ተወስኗል፣
4. በየደረጃው የሚገኝ አመራር የሕልውና ዘመቻውን ተቀብሎ
የሚሰለፈውን
ሕዝብ አደራጅቶ ከፊት ሆኖ እየመራ ወደ ግንባር እንዲዘምት
ይህን በማያደርጉ
አመራሮች ላይ ህጋዊና አስተዳደራዊ እርምጃ እንዲወሰድ
ተወስኗል፣
5. ሁሉም የመንግስትና የግል የጦር መሳሪያ የታጠቀ በሙሉ
ለሕልውና
ዘመቻው አገልግሎት እንዲውል ተወስኗል፡፡ ይህ እንደተጠበቀ
ሆኖ ማንኛውም
የግል መሳሪያ የታጠቀ የክልሉ ነዋሪ በማንኛውም ምክንያት
በሕልውና ዘመቻው
ላይ የማይሳተፍ ከሆነ የታጠቀውን የግል መሳሪያ በአደራ
ለመንግስት
እንዲያስረክብ ወይም እድሜው ለትግል ለደረሰ እና አካላዊ
ጤንነት ላለው
ለቤተሰብ አባሉ ወይም ለሌላ ሰው በማስተላለፍ ለህልውና
ዘመቻው
አገልግሎት እንዲውል እንዲያደርግ፣
6. በደጀንነት የሚገኘው ሕዝባችን ለሕልውና ዘመቻው
የሚያስፈልገውን
የሎጂስቲክስ አገልግሎት በማቅረብ የሕልውና ዘመቻውን
ውጤታማ
እንዲያደርግ፣ በየደረጃው የሚገኘው አመራርም አቅርቦቱ
የተሳለጠ እንዲሆን
አስፈላጊውን እንዲፈጽም ተወስኗል፣
7. የሕልውና ዘመቻውን ተቀብሎ በግንባር ለመፋለም
ከሚሰማሩት ውጭ ያለው
ማንኛውም የክልሉ ነዋሪ በየአካባቢው ተደራጅቶ የአካባውን
ጸጥታ እንዲጠብቅ፣
ጸጉረ ለውጦችንና ሰርጎ ገቦችን እንዲከታልና ለሕግ አስከባሪ
አካላት አሳልፎ
እንዲሰጥና ለሕልውና ዘመቻው የበኩሉን ኃላፊነት ሁሉ
እንዲወጣ፣
8. የህልውናውን ዘመቻ ውጤታማ ለማድረግ በሚደረገው
እንቅስቃሴ ላይ
ለትግሉ በተለያየ መንገድ እንቅፋት በሚሆን ማንኛውም ሰው
ወይም ቡድን ላይ
በየደረጃው እየተወሰነ የጸጥታ አካሉ አስፈላጊውን እርምጃ
እንዲወስድ
ተወስኗል፣
9. የተለያዩ አገልግሎቶችን እንዲሰጡ ከተፈቀደላቸው ተቋማት
ውጭ በሁሉም
ከተሞች ከምሽቱ 2፡00 በኋላ እንቅስቃሴ ማድረግ አይቻልም፣
እነዚህን ዘጠኝ አስገዳጅ ውሳኔዎች ዝርዝር አፈጻጸም በተመለከተ
በክልል ደረጃ
በተቋቋመው የዘመቻ መምሪያ በሚቀመጥ አሰራር የሚወሰን
ይሆናል፡፡
ጥቅምት 21 ቀን 2014 ዓ.ም
ባህር ዳር

አሁን ላይ ገፊ እና ተገፊ አያስፈልግም ሁሉም ወደ ግንባር መዝመት አለበት ወንድነታችንን ማሳየት አለብን በሀገር ጉደይ ማስመሰል ይቁም የደባይ ወጣት ሁልህም ሴትም ሆነ ወንድ ቆርጠህ ተነስ እ...
30/10/2021

አሁን ላይ ገፊ እና ተገፊ አያስፈልግም ሁሉም ወደ ግንባር መዝመት አለበት ወንድነታችንን ማሳየት አለብን በሀገር ጉደይ ማስመሰል ይቁም የደባይ ወጣት ሁልህም ሴትም ሆነ ወንድ ቆርጠህ ተነስ እንነሳ ከፍርሃት ድባብ ወጥተን በውስጥም በውጭም የሚኖርን ጠላት እንደምስስ ኢትዮጵያዊነት ወኔ እንላበስ እኛ የእነ በላይ ዘለቀ ዘሮች መሆናችንን ማሳየት አለብን ።

30/10/2021

አሸባሪውን የትግራይ ወራሪ ኀይል ለመደምሰስ እድሜ እና አካላዊ ብቃቱ የፈቀደለት የአማራ ክልል ሀገር ወዳድ ዜጋ ኹሉ ከዛሬ ጀምሮ እስከ ጥቅምት 23/2014 ዓ.ም ድረስ ትጥቅ፣ ማንኛውንም መሣሪያ እና ስንቅ በመያዝ ወደ ወረዳ ማዕከል ክተቱን ተቀብሎ እንዲገባ የአማራ ክልል መንግሥት ታላቅ የኅልውና ዘመቻ አቀረበ።

የአማራ ብሔራዊ ክልላዊ መንግሥት በወቅታዊ ጉዳይ መግለጫ ሰጥቷል።

የመግለጫው ሙሉ መልዕክት ቀጥሎ ቀርቧል:-

እጅግ የተከበርከው የአማራ ክልል ሕዝብ ሆይ! በአሸባሪው የትግራይ ወራሪ ኃይል ሀገርን ማፍረስ ዋነኛ ቀዳሚ ዓላማ አድርጎ ይህንኑ ፍላጎቱን ለማስጠበቅ በአይነቱ የተለየ፣ በተሳሳተ ትርክትና የጥላቻ ፕሮፖጋንዳ የተጠለፈ ሕዝባዊ አሰላለፍ በመፍጠር መጠነ ሰፊ ወረራ መፈፀሙና እየፈፀመ መሆኑ ይታወቃል።
እድሜያቸው ከ12 እስከ 65 ዓመት የሚደርሱ ወንድና ሴቶች፣ አካል ጉዳተኞችና ነፍሰ ጡሮች፣ ካህናትና ሸኮች ሳይቀር እያስገደደ በማሰማራት ወደ አማራና አጎራባች የአፋር ክልሎች አዝምቷል።

በዚህ ወረራ ወደር የሌለው ጭካኔ በመላበስ አማራን እስከወዲያኛው አንገት ለማስደፋት በየደረሰበት አካባቢ ሴቶችን በመድፈር፣ ንጹሐንን በመረሸን፣ መሰረተ ልማቶችን በማውደም፣ የመንግሥትና የግለሰብ ሀብቶችን በመዝረፍ፣ የቤት እንሰሳትን በጥይት በመግደል ሕዝብን እያሸበረ ከቀየው እንዲሰደድ በማድረግ ላይ ይገኛል።

የትግራይ ወራሪ ኃይል ሀገርን የማፍረስና አማራን እንደ ሕዝብ የማጥፋት ዘመቻው ከመደበኛ ወታደራዊ አደረጃጀት በተጨማሪ በሕዝባዊ ማዕበል መቀልበስና መደምሰስ እንዳለበት ግድ የሚል ሁኔታ ስለተፈጠረ ሀገራዊ የመንግሥት ጥሪ መተላለፉ ይታወቃል።

ይህ ሀገራዊ የመንግሥት ጥሪ እንደተጠበቀ ኾኖ በአማራ ክልል ደረጃ ፈጣንና የተደራጀ ሁሉ አቀፍ ሕዝባዊ ዘመቻ ማካሄድ ጊዜ የማይሰጠው እጅግ አጣዳፊ ጉዳይ ሆኗል። ስለሆነም እድሜውና አካላዊ ብቃቱ የፈቀደለት የክልላችን ሀገር ወዳድ ዜጋ ኹሉ ከዛሬ ጀምሮ እስከ ጥቅምት 23/2014 ዓ.ም ድረስ ማንኛውንም መሳርያና ስንቅ በመያዝ ወደ ወረዳ ማዕከላት የክተት ጥሪውን ተቀብሎ እንዲገባ የክልሉ መንግሥት ታላቅ የሕልውና ዘመቻ ጥሪ አቅርቦልሃል።

ሁሉ አቀፍ የሕልውና ዘመቻውን የተደራጀ አመራር፣ በሕዝባዊ ማዕበል ተመስርቶ በእልህና በወኔ ለማከናወን የሚያስችል ዝርዝር ማስፈፀሚያ መመርያ በየአካባቢው ይደርስሃል።

የዚህ ክተት ዘመቻ ዋነኛ ኃይላችን ለመስዋእትነት የተዘጋጀ ሕዝባችን መሆኑን የክልላችን መንግሥት ያምናል። በመሆኑም አሸባሪውን የትግራይ ወራሪ ኃይል የከፋ ምኞች ማምከን ብሎም የገባበት ገብቶ ለመደምሰስ የቀረበውን የጀግንነት ጥሪ በመቀበል ኢትዮጵያን ለማዳን እንዲሁም የአማራ ክልልን ሕዝብ ከውርደት ለመታደግ እንድንዘምት የክልሉ መንግሥት ጥሪውን በድጋሜ ያስተላልፋል።

ህልውናችንን በትግላችን እናረጋግጣለን! እናሸንፋለን!

የአማራ ብሔራዊ ክልላዊ መንግሥት
ጥቅምት 20/2014 ዓ.ም
ባሕርዳር፣ ኢትዮጵያ

"ክንዳችንን እናበርታ። ትከሻችንን እናስፋ። ልባችንንም እናጽና። ከውጭና ከውስጥ የተሠነዘረብንን ጥቃት ድል አድርገን መሻገር ብርቃችን እንዳልሆነ እናስመስክር። በምንምና በማንም ካሰብነው መን...
30/10/2021

"ክንዳችንን እናበርታ። ትከሻችንን እናስፋ። ልባችንንም እናጽና። ከውጭና ከውስጥ የተሠነዘረብንን ጥቃት ድል አድርገን መሻገር ብርቃችን እንዳልሆነ እናስመስክር።

በምንምና በማንም ካሰብነው መንገድ እንቀርም። ያቀድነውን ከማሳካት የሚያግደን ምድራዊ ኃይል የለም። አንድ ሆነን የምንይዘው ጋሻ ኃያላኑን ሁሉ ሲመክት የኖረ ነው። ዛሬም ያንን ጋሻ በአንድነት እናንሣ። ሁላችንም፣ በየቦታችን፣ 24 ሰዓት፣ ለኢትዮጵያ እንቁም።"

ጠቅላይ ሚኒስትር ዶክተር አብይ አህመድ

"ክንዳችንን እናበርታ። ትከሻችንን እናስፋ። ልባችንንም እናጽና። ከውጭና ከውስጥ የተሠነዘረብንን ጥቃት ድል አድርገን መሻገር ብርቃችን እንዳልሆነ እናስመስክር። በምንምና በማንም ካሰብነው መን...
30/10/2021

"ክንዳችንን እናበርታ። ትከሻችንን እናስፋ። ልባችንንም እናጽና። ከውጭና ከውስጥ የተሠነዘረብንን ጥቃት ድል አድርገን መሻገር ብርቃችን እንዳልሆነ እናስመስክር።

በምንምና በማንም ካሰብነው መንገድ እንቀርም። ያቀድነውን ከማሳካት የሚያግደን ምድራዊ ኃይል የለም። አንድ ሆነን የምንይዘው ጋሻ ኃያላኑን ሁሉ ሲመክት የኖረ ነው። ዛሬም ያንን ጋሻ በአንድነት እናንሣ። ሁላችንም፣ በየቦታችን፣ 24 ሰዓት፣ ለኢትዮጵያ እንቁም።"

ጠቅላይ ሚኒስትር ዶክተር አብይ አህመድ

Address

Debay Tilat Gen Wereda
K'uy
0920262403

Website

Alerts

Be the first to know and let us send you an email when Debay pp youth league office posts news and promotions. Your email address will not be used for any other purpose, and you can unsubscribe at any time.

Share