Jiga town prosperity party youth league

Jiga town prosperity party youth league Contact information, map and directions, contact form, opening hours, services, ratings, photos, videos and announcements from Jiga town prosperity party youth league, Political organisation, Jiga.

በምዕራብ ጎጃም ዞን የጅጋ ከተማ አስተዳደር ብልፅግና ፓርቲ ቅርንጫፍ ጽ/ቤት " በላቀ የወጣቶች  ተሳትፎ ኢትዮጽያን ወደ ተምሳሌት ሀገር" በሚል መሪ ቃል በ7ኛው ጠቅላላ ምርጫ ዙሪያ  የአደ...
22/05/2026

በምዕራብ ጎጃም ዞን የጅጋ ከተማ አስተዳደር ብልፅግና ፓርቲ ቅርንጫፍ ጽ/ቤት " በላቀ የወጣቶች ተሳትፎ ኢትዮጽያን ወደ ተምሳሌት ሀገር" በሚል መሪ ቃል በ7ኛው ጠቅላላ ምርጫ ዙሪያ የአደባባይ ላይ የምረጡኝ ቅስቀሳ፣ የምርጫ ምልክት እና የእጩዎች የትውውቅ ሰላማዊ ሰልፍ ተካሄደ ።
በሰላማዊ ሰልፉ ተገኝተው መልዕክት ያስተላለፉት የጅጋ ከተማ አስተዳደር ም/ከንቲባ አቶ ምስጋናው ድንቁ "ብልፅግና ለወጣቶች ተጠቃሚነት በልዩ ትኩረት ይሰራል" ብለዋል።
በፕሮግራሙ የምዕ/ጎጃም ዞን ጤና መምሪያ ም/ኃላፊ አቶ መዝገቡ ውቤ እንዲሁም የጅጋ ከተማ አስተዳደር አመራሮች ተገኝተዋል።

በምዕራብ ጎጃም ዞን በጅጋ ከተማ አስተዳደር የ7ኛው ሀገራዊ እና ክልላዊ ምርጫ የምረጡኝ ቅስቀሳና የእጩና የምርጫ ምልክት ትውውቅ  እና የቡና ጠጡ ፕሮግራም በቀበሌዎች  ተካሄደ።   በጅጋ ከ...
20/05/2026

በምዕራብ ጎጃም ዞን በጅጋ ከተማ አስተዳደር የ7ኛው ሀገራዊ እና ክልላዊ ምርጫ የምረጡኝ ቅስቀሳና የእጩና የምርጫ ምልክት ትውውቅ እና የቡና ጠጡ ፕሮግራም በቀበሌዎች ተካሄደ።
በጅጋ ከተማ አስተዳደር በ01 ቀበሌ የተዘጋጀ የቡና ጠጡ ፕሮግራም የተካሄደ ሲሆን በፕረግራሙ የጥያቄና መልስ ውድድር እና በከተማ አስተዳደሩ የተሰሩ የተለያዩ ፕሮጀክቶች ተጎብኝተዋል።
በፕሮግራሙ የምዕራብ ጎጃም ዞን ጤና መምሪያ ም/ኃላፊ አቶ መዝገቡ ውቤ እንዲሁም የጅጋ ከተማ አስተዳደር አመራሮችና ጥሪ የተደረገላቸው የከተማው ነዋሪዎች ተገኝቸዋል።

በምዕራብ ጎጃም ዞን በጅጋ ከተማ አስተዳደር የ7ኛው ሀገራዊ እና ክልላዊ ምርጫ የምረጡኝ ቅስቀሳና የእጩና የምርጫ ምልክት ትውውቅ ተካሄደ።   በጅጋ ከተማ የተሰሩ የፕሮጀክት ስራዎችን ማህበረ...
19/05/2026

በምዕራብ ጎጃም ዞን በጅጋ ከተማ አስተዳደር የ7ኛው ሀገራዊ እና ክልላዊ ምርጫ የምረጡኝ ቅስቀሳና የእጩና የምርጫ ምልክት ትውውቅ ተካሄደ።
በጅጋ ከተማ የተሰሩ የፕሮጀክት ስራዎችን ማህበረሰቡ እንዲጎበኛቸው በማድረግና ከህዝቡ የሚጠበቀውን ተሳትፎ አጠናክሮ እንዲቀጥል እና በምርጫው ንቁ ተሳታፊ እንዲሆን የእጩዎችና የምርጫ ምልክት ትውውቅ ተካሄዷል።
በመድረኩም የከተማ አስተዳደሩ ከንቲባ አቶ ምስጋናው ድንቁ እና የከተማ አስተዳደራችን ብልፅግና ፓርቲ ቅ/ጽ/ቤት ኃላፊ አቶ ናትናኤል በላይ እንዲሁም ጥሪ የተደረገላቸው የሀገር ሽማግሌዎች እና የሀይማኖት አባቶች ተገኝተዋል።

"በላቀ የኢኮኖሚና የፖለቲካ ተሳትፎ ኢትዮጽያን ወደ ተምሳሌት ሀገር"በምዕራብ ጎጃም ዞን የጅጋ ከተማ አስተዳደር ብልፅግና ፓርቲ ቅርንጫፍ ጽ/ቤት " በላቀ የኢኮኖሚና የፖለቲካ ተሳትፎ ኢትዮጽ...
17/05/2026

"በላቀ የኢኮኖሚና የፖለቲካ ተሳትፎ ኢትዮጽያን ወደ ተምሳሌት ሀገር"

በምዕራብ ጎጃም ዞን የጅጋ ከተማ አስተዳደር ብልፅግና ፓርቲ ቅርንጫፍ ጽ/ቤት " በላቀ የኢኮኖሚና የፖለቲካ ተሳትፎ ኢትዮጽያን ወደ ተምሳሌት ሀገር" በሚል መሪ ቃል በ7ኛው ጠቅላላ ምርጫ ዙሪያ ከከተማ አስተዳደሩ ከተለያዩ የህብረተሰብ ክፍሎች ከተውጣጡ የከተማ ነዋሪዎች ጋር የምረጡኝ ቅስቀሳና የምርጫ ምልክት እና የእጩዎች የትውውቅ መድረክ እየተካሄደ ነው።

በመረሀ ግብሩ የዞንና የወረዳ የስራ ኃላፊዎች እንዲሁም የየሀገር ሽማግሌዎችና የሀይማኖት አባቶች ተገኝተዋል።

ብልፅግና ፓርቲን ይምረጡ!
ምልክታችን የስንዴ ነዶ ነዉ!

"በላቀ የኢኮኖሚና የፖለቲካ ተሳትፎ ኢትዮጽያን ወደ ተምሳሌት ሀገር"በምዕራብ ጎጃም ዞን የጅጋ ከተማ አስተዳደር ብልፅግና ፓርቲ ቅርንጫፍ ጽ/ቤት " በላቀ የኢኮኖሚና የፖለቲካ ተሳትፎ ኢትዮጽ...
15/05/2026

"በላቀ የኢኮኖሚና የፖለቲካ ተሳትፎ ኢትዮጽያን ወደ ተምሳሌት ሀገር"

በምዕራብ ጎጃም ዞን የጅጋ ከተማ አስተዳደር ብልፅግና ፓርቲ ቅርንጫፍ ጽ/ቤት " በላቀ የኢኮኖሚና የፖለቲካ ተሳትፎ ኢትዮጽያን ወደ ተምሳሌት ሀገር" በሚል መሪ ቃል በ7ኛው ጠቅላላ ምርጫ ዙሪያ ከሀይማኖት አባቶች እና የሀገር ሽማግሎች በተገኙበት የምረጡኝ ቅስቀሳና የምርጫ ምልክት እና የእጩዎች የትውውቅ መድረክ እየተካሄደ ነው።

በመረሀ ግብሩ የዞንና የወረዳ የስራ ኃላፊዎች እንዲሁም የየሀገር ሽማግሌዎችና የሀይማኖት አባቶች ተገኝተዋል።

ብልፅግና ፓርቲን ይምረጡ!
ምልክታችን የስንዴ ነዶ ነዉ!

Jiga town Prosperity

ባለፉት 5 አመታት ክፉ ደጉን የተመለከተችው ጅጋ ከተማ የሚበጃትን በአስተውሎት ትመረጣለች።የጅጋ ህዝብ ጦረነትን ሳይሆን ሰላምን፤ ጥላቻን ሳይሆን ፍቅርን የሚሰብክላትን ወኪል ትፈልጋለች።ክብር...
14/05/2026

ባለፉት 5 አመታት ክፉ ደጉን የተመለከተችው ጅጋ ከተማ የሚበጃትን በአስተውሎት ትመረጣለች።

የጅጋ ህዝብ ጦረነትን ሳይሆን ሰላምን፤ ጥላቻን ሳይሆን ፍቅርን የሚሰብክላትን ወኪል ትፈልጋለች።

ክብርት ወ/ሮ የዝና ታደለ ለተወካዮች ም/ቤት፣ ክብርት ሰርክአዲስ አታሌ ደግሞ ለክልል ምክርቤት እጩ ሆነው ቀርበዋል።

ሁለቱም እንስቶች ጠንካራ የፖለቲካ አቅምና የአካዳሚካል አቅም ባለቤቶች ናቸው።

ብልጽግና የሴቶችን የአመራር ሰጭነት አቅም እያጎለበተና እየተጠቀመ ያለ አሳታፊ ፓርቲ ነው።

ሁለቱ እጩዎች የጅጋ ከተማን ህዝብ በመወከል በ7ኛው ሀገራዊ ጠቅላላ ምርጫ ላይ ይሳተፋሉ።

ባለፉት 5 አመታት ክፉ ደጉውን ያየህው የጅጋ ህዝብ ሆይ የብልጽግና ፍሬዎችህን እንድትመረጥ ጥሪ ተደርጎልሀል።


በምዕ ጎጃም ዞን በጅጋ ከተማ አስተዳደር ብልፅግና ፓርቲ ቅርንጫፍ ጽ/ቤት "በላቀ የነጋዴዎች ተሳትፎ  ኢትዮጵያን ወደ ተምሳሌት ሀገር" በሚል መሪ ቃል ሀሳብ በ7ኛው ጠቅላላ ምርጫ የነጋዴ ማ...
14/05/2026

በምዕ ጎጃም ዞን በጅጋ ከተማ አስተዳደር ብልፅግና ፓርቲ ቅርንጫፍ ጽ/ቤት "በላቀ የነጋዴዎች ተሳትፎ ኢትዮጵያን ወደ ተምሳሌት ሀገር" በሚል መሪ ቃል ሀሳብ በ7ኛው ጠቅላላ ምርጫ የነጋዴ ማህበረሰብና አባላት ደጋፊዎች የምርጫ ምልክትና የእጩዎች ትውውቅ መድረክ እየተካሄደ ነው።
በመድረኩ የምዕራብ ጎጃም ዞን ጤና መምሪያ ምክትል ሀላፊ አቶ መዝገቡ ውቤ እና የጅጋ ከተማ አስተዳደር አመራሮች ተገኝተዋል።

"ወጣቶች 7ኛው ሀገራዊ ጠቅላላ ምርጫ  በሂደቱ ሰላማዊ፣ ዴሞክራሲያዊ እና ታዓማኒነት ያለው እንዲሆን በመስራት ለትውልድ እየሰራ የሚገኘውን  ብልጽግና ፓርቲን ምርጫቸው ሊያደርጉ ይገባል"ወጣት...
13/05/2026

"ወጣቶች 7ኛው ሀገራዊ ጠቅላላ ምርጫ በሂደቱ ሰላማዊ፣ ዴሞክራሲያዊ እና ታዓማኒነት ያለው እንዲሆን በመስራት ለትውልድ እየሰራ የሚገኘውን ብልጽግና ፓርቲን ምርጫቸው ሊያደርጉ ይገባል"

ወጣት በላቸው ፈጠነ
በምዕራብ ጎጃም ዞን ብልጽግና ፓርቲ የወጣቶች ክንፍ ኃላፊ

በምዕራብ ጎጃም ዞን በሚገኙ ወረዳዎችና ከተማ አስተዳደሮች "በላቀ የወጣቶች ተሳትፎ ፤ኢትዮጰያን ወደ ተምሳሌት ሀገር !"በሚል መሪ ሀሳብ 7ኛው ሀገራዊ እና ክልላዊ ጠቅላላ ምርጫ የወጣቶች ክንፍ አባላትና ደጋፊዎች በተገኙበት የውይይት መድረክ ተካሂዷል።

የምዕራብ ጎጃም ዞን ብልጽግና ፓርቲ የወጣቶች ክንፍ ኃላፊ ወጣት በላቸው ፈጠነ እንደገለጹት ወጣቶች 7ኛው ሀገራዊ ጠቅላላ ምርጫ በሂደቱ ሰላማዊና ዴሞክራሲያዊ እና ታዓማኒነት ያለው እንዲሆን በመስራት ለትውልድ እየሰራ ለሚገኝውን ፓርቲ ምርጫቸው ሊያደርጉ እንደሚገባ ጥሪ አቅርቧል።

ወጣቶች በቀጣዩ ግንቦት 24 በሚካሄደው 7ኛው ሀገራዊ እና ክልላዊ ጠቀስ ላላ ምርጫ ነፃ፣ ፍትሃዊና ዴሞክራሲያዊ ሆኖ በስኬት እንዲጠናቀቅ ሚናቸውን እንዲወጡ እየተሰራ ነው ብሏል።

ኢትዮጵያ በፖለቲካው፣በማህበራዊ፣በኢኮኖሚውና በዲፕሎማሲ መስኮች ያላትን ህልሞች እንዲሳኩ ወጣቶች በምርጫው በንቃት ሊሳተፉ እንደሚገባ ተመላክቷል።

ብልጽግና ፓርቲ ለትውልድ እየሰራ ያለ አሻጋሪ ሀገራዊ
ግዙፍ ፓርቲ መሆኑም ተገልጿል።ብልጽግና ፓርቲ በኢኮኖሚው ዘርፍ ከእዳ ወደ ምንዳ ሽግግር በማለድረግ የበለጸገች አፍሪካዊት ኢትዮጵያን ለመገንባት እየመጣ ያለውን ውጤት ለማቀጠል እየተጋ ያለ ፓርቲ መሆኑ ተገልጿል።

በምዕ ጎጃም ዞን በጅጋ ከተማ አስተዳደር ብልፅግና ፓርቲ ቅርንጫፍ ጽ/ቤት "በላቀ የሴቶች ተሳትፎ  ኢትዮጵያን ወደ ተምሳሌት ሀገር" በሚል መሪ ቃል ሀሳብ በ7ኛው ጠቅላላ ምርጫ የሴቶች ክንፍ...
13/05/2026

በምዕ ጎጃም ዞን በጅጋ ከተማ አስተዳደር ብልፅግና ፓርቲ ቅርንጫፍ ጽ/ቤት "በላቀ የሴቶች ተሳትፎ ኢትዮጵያን ወደ ተምሳሌት ሀገር" በሚል መሪ ቃል ሀሳብ በ7ኛው ጠቅላላ ምርጫ የሴቶች ክንፍ አባላትና ደጋፊዎች የምርጫ ምልክትና የእጩዎች ትውውቅ መድረክ እየተካሄደ ነው።
በመድረኩ የጅጋ ከተማ ሴት እና ሴት የመንግስት ሰራተኛ አባላት ተገኝተዋል።

በምዕ ጎጃም ዞን በጅጋ ከተማ አስተዳደር ብልፅግና ፓርቲ ቅርንጫፍ ጽ/ቤት "በላቀ የወጣቶች ተሳትፎ  ኢትዮጵያን ወደ ተምሳሌት ሀገር" በሚል መሪ ቃል ሀሳብ በ7ኛው ጠቅላላ ምርጫ የወጣቶች ክ...
12/05/2026

በምዕ ጎጃም ዞን በጅጋ ከተማ አስተዳደር ብልፅግና ፓርቲ ቅርንጫፍ ጽ/ቤት "በላቀ የወጣቶች ተሳትፎ ኢትዮጵያን ወደ ተምሳሌት ሀገር" በሚል መሪ ቃል ሀሳብ በ7ኛው ጠቅላላ ምርጫ የወጣቶች ክንፍ አባላትና ደጋፊዎች የምርጫ ምልክትና የእጩዎች ትውውቅ መድረክ እየተካሄደ ነው።
በመድረኩ የምዕ/ጎጃም ዞን ጤና መምሪያ ምክትል ኃላፊ አቶ መዝገቡ ውቤ እና የከተማ አስተዳደራችን አመራሮች ተገኝተዋል።

Address

Jiga

Website

Alerts

Be the first to know and let us send you an email when Jiga town prosperity party youth league posts news and promotions. Your email address will not be used for any other purpose, and you can unsubscribe at any time.

Share