Awi Administration Justice Department/አዊ ብሔ/አስ/ፍትህ መምሪያ

  • Home
  • Ethiopia
  • Injibara
  • Awi Administration Justice Department/አዊ ብሔ/አስ/ፍትህ መምሪያ

Awi Administration Justice Department/አዊ ብሔ/አስ/ፍትህ መምሪያ ለህግ፣ ፍትሕና ርትዕ እንሰራለን!! Strives for upholding rule of law, justice and equity!

 #ህገ-ወጥ ናፍጣ ሲያጓጉዝ የተገኘ ተከሳሽ በጽኑ እስራት ተቀጣ።ተከሳሽ የኢፌድሪ የወ/ህ አንቀጽ 32/1/ሀ እና የንግድ መዝገብ አዋጅ ቁጥር 980/2006 አንቀጽ 21(1) እና 49(2) በ...
05/06/2026

#ህገ-ወጥ ናፍጣ ሲያጓጉዝ የተገኘ ተከሳሽ በጽኑ እስራት ተቀጣ።
ተከሳሽ የኢፌድሪ የወ/ህ አንቀጽ 32/1/ሀ እና የንግድ መዝገብ አዋጅ ቁጥር 980/2006 አንቀጽ 21(1) እና 49(2) በመተላለፍ
ተከሳሽ ጌታሁን መኮነን የተባለው ሜያዚያ 15 ቀን 2018 ዓ/ም ከጥዋቱ 12፡00 ሰዓት ሲሆን ቻግኒ መውጫ ኬላ ተብሎ ከሚጠራው ስፍራ በሰሌዳ ቁጥር 36248 አ.አ ኤፍኤስአር መኪና ብዛቱ 13 ጃሪካን በመጫን ደብቆ ሲያጓጉዝ በጸጥታ ሀይሎች ክትትል ተይዞ ምርመራ ተጠርቶ ለአዊ ብሄ/አስ/ፍትህ መምሪያ ተልኮ ክስ በተፈጠነ ስነ ስራዓት ክስ ቀርቦበት የዐ/ህግ ምስክሮች ቀርበው በበቂ ሁኔታ የተመሰከረው ስለሆነ እንዲከላከል እድል ተሰጥቶ የመ/ምስክር አቅርቦ ማሰማትና ማስተባባል ያልቻለ ስለሆነ የአዊ ብሔ/አስ/ከፍ/ፍ/ቤት በቀን 28/09/2018 ዓ/ም በዋለው ችሎት 5 ዓመት ጽኑ እስራት እና ብር 10000 የተቀጣ ሲሆን በኢግዚቪትነት የተያዘው 13 ጃሪካን ለመንግስት ገቢ ተድርጓል።


#ናፍጣ
#ቤንዚን

#⚖️ #ፍትህ
🚔 #የህግአስፈጻሚ
❗️ #ወንጀል
🔴 #ከባድወንጀል
🏛 #ፍርድቤት
🌍
📰
🇪🇹
⚖️
🚨

• ⚖️ ፍትህ እንዲኖር አስተያየታችሁን አጋሩ!
• 📣 ህግ ከሁሉ በላይ መሆኑን እናሳይ፤ ሼር ያድርጉ!
• 🔁 ይህን ጉዳይ ሌሎችም እንዲያውቁ አጋሩ!
• 💬 እርስዎ ምን ያስባሉ? ኮመንት ይጻፉ!
• 👍 ፍትህ እንዲበረታ ልጥፉን ላይክ እና ሼር ያድርጉ!

01/06/2026

28/05/2026

“The Concept of Law and Morality”

1. ሕግና ሞራልነት ማህበረሰብ እንዴት እንደሚያገናኝ

ሕግና ሞራልነት አንድ ነገር ናቸው ቢሆንም የተለያዩ ናቸው።

ሕግ የመንግስት የተደጋጋሚ መለኪያ ሲሆን በአንዳንድ ጊዜ ሞራል ያልሆነ ነገርን እንዲቆጣጠር ይችላል።

ሞራልነት ደግሞ ከሃይማኖት፣ ባህል፣ ግል የሚያገኝ የተለያዩ እሴቶችና አስተሳሰቦች ናቸው፣ እና መንግስት አይገደብም።

2. ሞራልነት (Morality)

ሞራልነት ማህበረሰብ ወይም ግል የእኩልነትና የስህተት እሴቶችን የሚያነጋግር ነው።
የሞራልነት አገናኝ መንገድ የግል ስሜት (conscience) እና የማህበረሰብ ግፊት (social pressure) ነው።
ሞራልነት እንደ ግል ሃሳብ ለተለያዩ ሰዎች፣ ባህላዊ ትምህርቶችና ጊዜ ይለያያል።

3. ሕግ (Law)

ሕግ የመንግስት የተፈጠረ እና የተገናኘ የግዴታ ህጎች ናቸው።
ሕግ የማህበረሰብ ተግባርን ለማስተካከል እና ስርዓትን ለማስቀመጥ እንዲሁም የማህበረሰብ ሞራል እሴቶችን እንዲያስተካክል ይደርሳል።

ሕግ በሕጋዊ ቅጥያ የተገናኘ ተግባሮችን እንዲቆጣጠር ይጠቀማል፤ ይህም የፍርድ ቅጥያ፣ ቅጣት ወይም የቤተ-መንግስት ተግባር ሊኖረው ይችላል።

4. ሕግና ሞራልነት የሚልዩት

የተለያዩ ገጽታዎች

ሕግ (Law) መንግስት፣ ህጎች፣በመንግስት ይተገበራል፣የግዴታ እና ቅጣት፣የማህበረሰብ ሁሉ ና ህጋዊ ቅጣት ይኖራል።

ሞራልነት (Morality)ባህል፣ ሃይማኖት፣ ግል ስሜት፣በግል ስሜት እና ማህበረሰብ ግፊት፣እኩልነት እና እሴቶች በግል ስሜት፣የግልና የማህበረሰብ ተለያዩ አካባቢ፣ማህበረሰብ ድጋፍ ወይም ግፊት

5. ሕግና ሞራልነት በመገጣጠም

አንዳንድ ጊዜ ሕግ ትክክል ሆኖም ሞራል የማይሆን ነገር ሊኖረው ይችላል፣ እንዲሁም ሞራል ትክክል ሆኖም ሕጋዊ የማይሆን ነገር ሊኖረው ይችላል።

ሕግ የማህበረሰብ ማንኛውንም ዝርዝር በመቆጣጠር የማህበረሰብ ስርዓትን ይጠብቃል።
ብዙ ሕጎች በሞራል እሴቶች የተመሰረቱ ሲሆን ማህበረሰብ ስሜትን ለማሻሻል ያገለግላሉ።

ማጠቃለያ:

ሕግ የመንግስት ተግባራዊ መለኪያ እንደሆነ ተግባርን እንዲያገናኝ ይጠቀማል።
ሞራልነት ደግሞ በግል ስሜትና ማህበረሰብ ግፊት ተቆጣጣሪ ነው።

ሕግና ሞራልነት በማህበረሰብ ልማትና ትስስር ላይ ተግባር ይኖራል።
learner

23/05/2026

#በከባድ #ውንብድና ወንጀል የተከሰሰው ተከሣሽ #በ14 ዓመት ፅኑ እስራት ተቀጣ ።
============================
ግንቦት 15 ቀን 2018 ዓ/ም(አዊ ብሔ/አስ/ፍትህ መምሪያ)
ተከሣሽ ባንቲገኝ አበራ የተባለው ግለሰብ ናሀሴ 10 ቀን 2017 ዓ/ም በግምት ከጥዋቱ 1:00 ሰዓት ላይ ፈግታ ለኮማ ወረዳ አመሻ ሽንኩሪ ቀበሌ ዑደን ተብሎ ከሚጠራው ጎጥ የግል ተበዳዮችን ዳሳሸ በየን ፣ንብረት ፈንታሁን እና ገነት አስረስን ወደ አዲስ ቅዳም ከተማ መሄድ ለይ እያሉ ተገቢ ያልሆነ ብልፅግና ለራሱ ለማግኘት በጬቤ እወጋቸዋለሁ ብሎ በማስፈራራት በዛቻ አስገድዶቸው ከአንደኛ ተበዳይ ከቦርሳዋ ይዛው የነበረችውን ሶስት ሺህ ብር ፣ከሁለተኛ ተበዳይ አንድ ሺህ ብርና ትንሽ ስልክ ግምቷ ሁለት ሺህ ብር እና ከሶስተኛ ተበዳይ አስገድዶ በሀይል አንገቷ ላይ አድርጋው የነበረችውን ሁለት ጠገራ ብር ጠቅላላ ግምቱ ስድስት ሺህ ብር የወሰዳበቸው በመሆኑ በአዊ ብሔ/አስ/ፍትህ መምሪያ መደበኛ ወንጀል በተደራራቢ ሶስት ክሶች ቀርቦበት ዐ/ህግ የሠው ማስረጃዎችን አቅርቦ ተገቢውን የህግ ክርክር በማድረግ ከጥርጣሬ በፀዳ መልኩ የተመሠከረበት ስለሆነ እንዲከለከል ዕድል ተሠጥቶት ባቀረበቸው የመከላከያ ማስረጃዎች ወንጀሉን አለመፈፀሙን ማስተባበል ያልቻለ ስለሆነ የአዊ ብሔ/አስ/ከፍ/ፍ/ቤት በቀን 14/09/2018 ዓ/ም በዋለው የወንጀል ችሎት ተከሣሽ በተከሠሠበት ሶስቱም ክሶች ጥፋተኛ ነው በማለት የ14 ዓመት እስራት ተወስኗል ።



゚viralシ




Awi Administration Justice Department/አዊ ብሔ/አስ/ፍትህ መምሪያ

 #የጓንጓ     #ቀጠሮ
23/05/2026

#የጓንጓ #ቀጠሮ

19/05/2026

የምርጫ አይነቶች ምን ምን እንደሆኑ ያዉቃሉ?
🌿🌿🌿🌿🌿🌿

አጠቃላይ በፖለቲካዊ ሥርዓቶች፣ በሕገ-መንግሥትና በዲሞክራሲያዊ ሂደቶች ውስጥ የምርጫ ዓይነቶች እንደየአስፈላጊነታቸውና እንደየወቅቱ ሁኔታ በተለያዩ መንገዶች ይከፈላሉ። ዋና ዋናዎቹም

1. መደበኛ (ጠቅላላ) ምርጫ (General Election)
ይህ በአንድ ሀገር ውስጥ በሕግ የተወሰነዉ የሥልጣን ዘመን (የምርጫ ዘመን) ሲያበቃ አዲስ መንግሥት ለመመሥረት በየ 5 ወይም በየ 6 ዓመቱ የሚደረግ ሀገር አቀፍ ምርጫ ነው።

2. የአካባቢ ምርጫ (Local Election)
የአካባቢን ልማትና አስተዳደር በቅርበት ለመምራት የክልል፣ የዞን፣ የወረዳ ወይም የቀበሌ ምክር ቤት አባላትን ለመምረጥ የሚካሄድ ምርጫ ነው። ይህም ሕዝቡ በራሱ አቅራቢያ ያሉ መሪዎችን በቀጥታ የሚመርጥበት ነዉ።

3. ማሟያ ምርጫ (By-election)
አንድ የተመረጠ የሕዝብ ተወካይ በሞት፣ በፈቃደኝነት ሥራ በመልቀቅ፣ ከሥልጣን በመሻር ወይም በሌላ ምክንያት ቦታው ክፍት በሚሆንበት ጊዜ፣ ያንን የጎደለ ቦታ ለመተካት በዚያ የተወሰነ የምርጫ ክልል ብቻ የሚደረግ ልዩ ምርጫ ነው።

4. ድጋሚ ምርጫ (Re-election / Run-off)
ይህ ምርጫ የሚካሄደው በመጀመሪያው ምርጫ ላይ ማጭበርበር ወይም ከባድ የሕግ ጥሰት ተከስቶ ውጤቱ በኮሚሽን ወይም በፍርድ ቤት ሲሰረዝ እንደገና የሚካሄድ ምርጫ።

5. ሕዝበ-ውሳኔ (Referendum)
ይህ ለሰዎች ወይም ለፓርቲዎች ድምፅ የሚሰጥበት ምርጫ ሳይሆን፣ በአንድ ትልቅ ሀገራዊ ወሳኝ ጉዳይ ላይ ሕዝቡ በቀጥታ "አዎ" ወይም "አይደለም" ("እቀበላለሁ" ወይም "አልቀበልም") በማለት ውሳኔ የሚሰጥበት የዲሞክራሲ ሂደት ነው።
ምሳሌ፡ ሕገ-መንግሥት ለማጽደቅ፣ አዲስ ክልል ለመመሥረት ወይም ከአንድ ሀገር ለመገንጠል የሚደረጉ ውሳኔዎች ናቸዉ።

17/05/2026
 #በከባድ የሰው  #ግድያ ሙከራ ወንጀል የተከሰሰው ተከሣሽ  #በ10 ዓመት ፅኑ እስራት  ተቀጣ ።    ግንቦት 7/2018(አዊ ብሔ/አስ/ፍትህ መምሪያ)ተከሣሽ ዲ/ን   #ዘላለም ምህረቱ የተ...
15/05/2026

#በከባድ የሰው #ግድያ ሙከራ ወንጀል የተከሰሰው ተከሣሽ #በ10 ዓመት ፅኑ እስራት ተቀጣ ።
ግንቦት 7/2018(አዊ ብሔ/አስ/ፍትህ መምሪያ)
ተከሣሽ ዲ/ን #ዘላለም ምህረቱ የተባለው ግለሰብ ጥቅምት 16 ቀን 2018 ዓ/ም በግምት ከምሽቱ 1:00 ሰዓት ሲሆን ወንዲጊ ውንቢሪ ቀበሌ መስቀልታ ጎጥ ተብሎ ከሚጠራው ስፍራ በያዘው ጩቤ የእንጀራ እናት የሆነቸውን ወ/ሮ ህዝባዩሽ ተገኘን የምትባለውን ግለሰብ በጭካኔ በተሞላበት ሁኔታ የግራ አይኗን በመውጋት የግራ አይኗ እንዲጠፋ ያደረገት በመሆኑ የአዊ ብሔ/አስ/ፍትህ መምሪያ መደበኛ ወንጀል የወ/ህ/ቁ 32/1/ሀ/፣27 እና 539/1/ሀ/ በመጥቀስ ክስ አቅርቦ ዐ/ህግ ተገቢውን የህግ ክርክር በማድረግ ከጥርጣሬ በፀዳ መልኩ የተመሠከረበት ስለሆነ እንዲከለከል ዕድል ተሠጥቶት ባቀረበው የመከላከያ ማስረጃዎች ወንጀሉን አለመፈፀሙን ማስተባበል ያልቻለ ስለሆነ የአዊ ብሔ/አስ/ከፍ/ፍ/ቤት በቀን 07/09/2018 ዓ/ም በዋለው የወንጀል ችሎት ተከሣሽ በተከሠሠበት ክስ ጥፋተኛ ነው በማለት የ10 ዓመት እስራት እንዲቀጣ ወስኗል።
#ዜና
#ቅጣት

Address

Injibara
Injibara

Website

Alerts

Be the first to know and let us send you an email when Awi Administration Justice Department/አዊ ብሔ/አስ/ፍትህ መምሪያ posts news and promotions. Your email address will not be used for any other purpose, and you can unsubscribe at any time.

Share