Awi Culture, Tourism & Sport Department

Awi Culture, Tourism & Sport Department Awi Zone Youth and Sport

በእንጅባራ ዩኒቨርሲቲ በአገው ጥናት ኢንስቲትዩት አዘጋጅነት“እንጃቢሪ ዳማይ እና እንጅባራዬ” የሚሉ ሁለት ሙዚቃዊ ኳሪዎች ለመድረክ በቁ።የአገው ጥናት ኢንስቲትዩት ከተቋቋማለት አላማ አንፃርበ...
04/06/2026

በእንጅባራ ዩኒቨርሲቲ በአገው ጥናት ኢንስቲትዩት አዘጋጅነት“እንጃቢሪ ዳማይ እና እንጅባራዬ” የሚሉ ሁለት ሙዚቃዊ ኳሪዎች ለመድረክ በቁ።

የአገው ጥናት ኢንስቲትዩት ከተቋቋማለት አላማ አንፃር
በአገው ህዝብ ቋንቋ ፣ ባህል፣ ሀገር በቀል እውቀት ላይ ትኩረት አድርጎ እየሰራ ይገኛል።

በኢንስቲትዩቱ ዳይሬክተር ብርሃኑ አሳየ(ረ/ፕሮፌሰር) አዘጋጅነት ሁለት ሙዚቃዊ ኳሪዎች (በአገዎኛና በአማረኛ) ቋንቋዎች የተሰናዱ ናቸው።

ለቅምሻ ያክል
እንጃቢሪ ዳማይ ከተሰኘው ሙዚቃዊ ኳሪ ...

ዳማይ (4) እንጃቢሪ ዳማይ፣
ዙማቲው ሜፃፍሊ እንዳራይ አሴብቴ፣
ግዴቴኪ ኩልቴ፣ ጛሬ ግቢትስቴ፣
ሴታኪ ዱንጊቴ፣ አልማዝታ ዋርቕቴ፣
አኖጂኪ ሲፍና እንትኪ ፍንዳ ፌቴ ፡፡........ይቀጥላል

Communication

" ስፖርታዊ ውድድር ለሰላማዊ ምርጫ"‎በፋግታ ለኮማ ወረዳ የ7ኛው አገራዊ ምርጫ የብልጽግና ፓርቲ የማጠቃለያ የምርጫ ቅሰቀሳና የምልክት ማስተዋወቅ መርሀ ግብርን በማስመልከት በልዩ ልዩ ስፖር...
25/05/2026

" ስፖርታዊ ውድድር ለሰላማዊ ምርጫ"
‎በፋግታ ለኮማ ወረዳ የ7ኛው አገራዊ ምርጫ የብልጽግና ፓርቲ የማጠቃለያ የምርጫ ቅሰቀሳና የምልክት ማስተዋወቅ መርሀ ግብርን በማስመልከት በልዩ ልዩ ስፖርታዊ ኩነት ታጅቦ የወዳጅነት የእግር ኳስ ጨዋታ ተካሄደ።

''‎ስፖርታዊ ውድድር ለሰላማዊ ምርጫ" በሚል መሪ ቃል የፋግታ ለኮማ ወረዳ አመራሮች ከአዲስ ቅዳም ከተማ አስተዳደር አመራሮች ጋር የወዳጅነት የእግር ኳስ ጨዋታቸውን አካሂደዋል።

በውድድሩ የፋግታ ለኮማ ወረዳ አመራሮች ፍፁም ከጨዋታ ብልጫ ጋር 4ለ0 በማሸነፍ ከዕለቱ የክብር እንግዳ ከሆኑት ከአብክመ ም/ቤት የመንግስት ዋና ተጠሪ ከአቶ አየን ብርሀን እጅ የዋንጫ ሽልማትን ወስደዋል።

በጨዋታው የፋግታ ለኮማ ወረዳ ም/ዋና አስተዳዳሪ አቶ ታገል እጅጉ ኮኮብ ግብ አግቢ በመሆን የጨረሱ ሲሆን አቶ አለሙ ደነቀው ከከተማ አስተዳደር ኮከብ ተጨዋች በመሆን አጠናቀዋል።

‎በስፖርታዊ ውድድሩ ላይ የአብክመ ም/ቤት የመንግስት ዋና ተጠሪ አቶ አየን ብርሀን፣ የአዊ ብሔ/አስ/ብልጽግና ፓርቲ ቅ/ጽ/ቤት የፖለቲካና አቅም ግንባታ ዘርፍ ኃላፊ አቶ ዘለቀ ከፋለ፣ የአዊ ብሔ/አስ/ም/ቤት ዋና አፈ- ጉባኤ ክብርት ሙሉዓዳም እጅጉ፣ የአዊ ብሔ/አስ/ህብረት ስራ ማህበራት መምሪያ ኃላፊ አቶ አብርሐም ዳኘው፣ የወረዳ አመራሮች፣ የብልጽግና ፓርቲ አባላትና ደጋፊዎች ታድመዋል።

‎ አዲስ ቅዳም:- ግንቦት 17/2018ዓ.ም

"‎ኢትዮጵያን_ወደ_ተምሳሌት_ሀገር"''ስፖርታዊ ውድድር ለሰላማዊ ምርጫ" ‎‎በሚል መሪቃል በአዊ ብሔረሰብ አሰተዳደር በጓጉሳ ሽኩዳድ ወረዳ የ7ኛው አገራዊ ምርጫ የብልጽግና ፓርቲ የምርጫ ቅሰ...
23/05/2026

"‎ኢትዮጵያን_ወደ_ተምሳሌት_ሀገር"

''ስፖርታዊ ውድድር ለሰላማዊ ምርጫ" ‎‎በሚል መሪቃል በአዊ ብሔረሰብ አሰተዳደር በጓጉሳ ሽኩዳድ ወረዳ የ7ኛው አገራዊ ምርጫ የብልጽግና ፓርቲ የምርጫ ቅሰቀሳን በማስመልከት በወረዳ አመራሩ መካከል የመረብ ኳስ ጨዋታ ማካሄድ ተችሏል።

በስፖርታዊ ውድድሩ ላይ የወረዳ አመራሩ፣ የብልጽግና ፓርቲ አባላትና ደጋፊዎች ታድመዋል።

‎" "!!

ጓጉሳ ሸኩዳድ ኮሙኒኬሽን
‎ግንቦት 15/2018 ዓ.ም

‎​"ኢትዮጽያን ወደ ተምሳሌት ሀገር"!! በአዊ ብሔረሰብ አስተዳደር በጓንጓ ወረዳ ኢትዮጵያ ወደ ተምሳሌት ሀገር በሚል መሪ መልዕክት የብልጽግና ፓርቲ አባላት እና ደጋፊዎች የአደባባይ የአካል...
23/05/2026

‎​"ኢትዮጽያን ወደ ተምሳሌት ሀገር"!!

በአዊ ብሔረሰብ አስተዳደር በጓንጓ ወረዳ ኢትዮጵያ ወደ ተምሳሌት ሀገር በሚል መሪ መልዕክት የብልጽግና ፓርቲ አባላት እና ደጋፊዎች የአደባባይ የአካል ብቃት እንቅስቃሴ በማቅረብ የምረጡኝ ቅስቀሳ አካሂደዋል።

በእንጅባራ ከተማ ታሪክ፣ በአገው ቋንቋ፣ ባህልና ሀገር-በቀል እውቀት ላይ ያተኮረ ሀገር-አቀፍ የምርምር ኮንፈረንስ እየተካሄደ ነው።በእንጅባራ ከተማ ታሪክ፣ በአገው ቋንቋ፣ ባህል እና ሀገር-...
23/05/2026

በእንጅባራ ከተማ ታሪክ፣ በአገው ቋንቋ፣ ባህልና ሀገር-በቀል እውቀት ላይ ያተኮረ ሀገር-አቀፍ የምርምር ኮንፈረንስ እየተካሄደ ነው።

በእንጅባራ ከተማ ታሪክ፣ በአገው ቋንቋ፣ ባህል እና ሀገር-በቀል እውቀቶች ዙሪያ የሚያተኩር ታላቅ ሀገር-አቀፍ የምርምር ኮንፈረንስ ዛሬ ግንቦት 15 ቀን 2018 ዓ.ም መካሄድ ጀምሯል።

​ይህን ከፍተኛ የምርምር መድረክ ያዘጋጃው በእንጅባራ ዩኒቨርሲቲ የአገው ጥናት ኢንስቲትዩት ነው።

‎ለ7ኛው ሀገራዊ እና ክልላዊ  ምርጫ ስኬታማነት  የወጣቶች ንቁ ተሳትፎ ወሳኝ ነው-ቃለአብ ከሃሊ በእንጅባራ ከተማ 7ኛውን ሀገራዊና ክልላዊ ምርጫ አስመልክቶ  "ኢትዮጵያን_ወደ_ተምሳሌት_ሀገ...
23/05/2026

‎ለ7ኛው ሀገራዊ እና ክልላዊ ምርጫ ስኬታማነት የወጣቶች ንቁ ተሳትፎ ወሳኝ ነው-ቃለአብ ከሃሊ

በእንጅባራ ከተማ 7ኛውን ሀገራዊና ክልላዊ ምርጫ አስመልክቶ "ኢትዮጵያን_ወደ_ተምሳሌት_ሀገር በሚል መሪ ቃል ስፖርታዊ የአካል ብቃት እንቅስቃሴ ተካሄደ።

በምርሃ ግብሩ የአዊ ብሄ/አስ ባህል፣ቱሪዝምና ስፖርት መምሪያ ሀላፊ ቃለአብ ከሃሊ ፥ በአካልና በስነልቦና የዳበረ ወጣት ለማፍራት ስፖርታዊ የአካል ብቃት እንቅስቃሴ ትኩረት እየተሰራ ይገኛል።

ለምርጫው ስኬታማነት ወጣቶች ሚና ከፍተኛ ነው ያሉት ሀላፊው ሰላማዊ ፣ዴሞክራሰላማዊእና ፍትሃዊ ሆኖ እንዲጠናቀቅ ንቁ ተሳትፎ ማድረግ እንዳለባቸው አሳስበዋል ።

Communication

የአዊ ብሔ/አስ/ ባህል፣ ቱሪዝምና ስፖርት መምሪያ የ2018 በጀት ዓመት 3ኛ ሩብ ዓመት እቅድ አፈፃፀም ከ ባ/ቱ/ስ/ጽ/ቤቶችና ከአጋር እና ባለድርሻ አካላት ጋር ግምገማ አካሄደ።
22/05/2026

የአዊ ብሔ/አስ/ ባህል፣ ቱሪዝምና ስፖርት መምሪያ የ2018 በጀት ዓመት 3ኛ ሩብ ዓመት እቅድ አፈፃፀም ከ ባ/ቱ/ስ/ጽ/ቤቶችና ከአጋር እና ባለድርሻ አካላት ጋር ግምገማ አካሄደ።

⚽️ የእንጅባራ ከተማ ወጣቶች በስፖርታዊ ውድድር ደምቀው ውለዋል! 🏆እንጅባራ | ግንቦት 12/2018 ዓ.ምየእንጅባራ ከተማ አስተዳደር ወጣቶችና ስፖርት ጽሕፈት ቤት ወጣቶችን በስፖርቱ ዘርፍ ...
20/05/2026

⚽️ የእንጅባራ ከተማ ወጣቶች በስፖርታዊ ውድድር ደምቀው ውለዋል! 🏆
እንጅባራ | ግንቦት 12/2018 ዓ.ም
የእንጅባራ ከተማ አስተዳደር ወጣቶችና ስፖርት ጽሕፈት ቤት ወጣቶችን በስፖርቱ ዘርፍ ለማሳተፍና በከተማዋ ያለውን ስፖርታዊ መነቃቃት ይበልጥ ለማጠናከር ያለመ የውስጥ ለውስጥ የእግር ኳስ እና የቮሊቦል ውድድር በታላቅ ድምቀት አካሂዷል።
ይህ ውድድር የወጣቶችን የእርስ በርስ ግንኙነት ከማጠናከሩ ባለፈ፣ ተሰጥኦ ያላቸውን ስፖርተኞች ለመለየትና ለከተማዋ ስፖርት እድገት የራሱን ድርሻ ለማበርከት ታስቦ የተዘጋጀ ሲሆን፣ በዕለቱ የታየው ከፍተኛ ፍላጎትና የተመልካቾች ድጋፍ ለውድድሩ ልዩ ድምቀትን ሰጥቶታል።
🥇 የፍፃሜ ጨዋታዎች ውጤት
የዘንድሮው ውድድር በከፍተኛ ፉክክር ተጠናቆ የሚከተሉት ክለቦች የድሉ ባለቤት መሆን ችለዋል፦
• በእግር ኳስ፦ በአበበ ሆቴል እና በግሻጉም ሆቴል መካከል በተደረገው እጅግ አጓጊ ጨዋታ አበበ ሆቴል ተጋጣሚውን በማሸነፍ የዋንጫው ባለቤት ሆኗል።
• በቮሊቦል፦ በስፖርት ማደያ እና ቻሌ ግሻጉም መካከል በተደረገው በቻሌ ግሻጉም ፍልሚያ አሸናፊ መሆን ችሏል።
🎯 የውድድሩ ዋና ዓላማዎች፦
• ጤናማና ንቁ ማህበረሰብን ለመገንባት፣
• ወጣቶችን ከአልባሌ ቦታዎችና ተግባራት ለመታደግ፣
• በከተማዋ ውስጥ ስፖርታዊ ጨዋነትን ለማስፈን።
የከተማው ወጣቶችና ስፖርት ጽሕፈት ቤት ስፖርቱ በሁሉም ዘርፍ እንዲያድግና መሰል መድረኮች ተጠናክረው እንዲቀጥሉ በትኩረት እየሰራ እንደሚገኝ ገልጿል።
ለአሸናፊዎች በሙሉ እንኳን ደስ ያላችሁ!

Communication

በአዊ ብሔ/አስ በፈንድቃ ከተማ አስተዳደር ላለፋት 14 ቀን ሲካሄድ የነበረው የበጋ የውስጥ ለውስጥ የቮሊቦል ውድድር ተጠናቀቀ።**********በፈንድቃ ከተማ አስተዳደር ላለፋት 14 ቀን ሲካ...
17/05/2026

በአዊ ብሔ/አስ በፈንድቃ ከተማ አስተዳደር ላለፋት 14 ቀን ሲካሄድ የነበረው የበጋ የውስጥ ለውስጥ የቮሊቦል ውድድር ተጠናቀቀ።
**********

በፈንድቃ ከተማ አስተዳደር ላለፋት 14 ቀን ሲካሄድ የነበረው የበጋ የውስጥ ለውስጥ የቮሊቦል ውድድር በምህራን ቮሊቦል ቡድን ዋንጫ አሸናፊነት ተጠናቀቀ።

በማጠቃለያ ፕሮግራሙ ላይ የተገኙት የፈንድቃ ከተማ አስተዳደር ባህል፣ቱሪዝምና ስፖርት ጽ/ቤት ኃላፊ አቶ ሃይማኖት ማሞ፥ በውድድሩ ላይ የታዩ አንድነቶች፣ መከባበርና መቻቻሎች የወጣቱ የዘወትር ተግባር መሆን እንዳለበት ገልጸዋል።

ውድድሩ ተተኪ ስፖርተኞችን ለማፍራት ያለመ መሆኑን እና ውድድሩ ወጣቶች ከአልባሌ ቦታ ከሚውሉ በስፖርት ማዘውተሪያ እዲውሉ ያበረታታ መሆኑን ገልጸው ሁሉም ወጣቶች በውድድር ጊዜ ብቻ ሳይሆን ሁሌም በሰፖርት ማዘውተሪያ ቦታ እንዲያሳልፋ መልዕክት አስተላልፈዋል።

መርሃግብሩ ለተከታታይ 14 ቀን የቆየ ሲሆን ሰባት ተሳታፊ ቡድኖች እንደነበሩም ገልጸዋል ኃላፊው።

በውድድሩ መጨረሻ ቀን የመምህራን ቮሊቦል ቡድን እና ከልዩዎቹ ቮሊቦል ቡድን የተገናኙ ሲሆን መምህራን ቮልቦል 3ለ1 አሸናፊና የዋንጫ ባለቤት ሆኖ ውድድሩ ተጠናቋል።
@ፈንድቃ ኮሚኒኬሽን

የሐዘን መግለጫ*********የአዊ ብሔ/አስ/ባህል፣ቱሩዝምና ስፖርት መምሪያ ሠራተኞች እና የስፖርት ም/ቤት አባላት ብሔረሰብ አስተድዳደሩን በተለያዩ ጊዜያት በመወከል፣በአዊ እምፕልቕ እና እን...
16/05/2026

የሐዘን መግለጫ
*********
የአዊ ብሔ/አስ/ባህል፣ቱሩዝምና ስፖርት መምሪያ ሠራተኞች እና የስፖርት ም/ቤት አባላት ብሔረሰብ አስተድዳደሩን በተለያዩ ጊዜያት በመወከል፣በአዊ እምፕልቕ እና እንጅባራ ከተማ እግር ኳስ ክለብ ተጫዋችነት እና አሰልጣኝነት ከፍተኛ ተሳትፎ በነበረው ወንድማችን ግሩም ገሠሠ ድንገተኛ ህልፈተ ህይወት የተሰማንን ጥልቅ ሐዘን እየገለፅን፣ ለቤተሰቦቹ፣ ለወዳጅ ዘመዶቹ እንዲሁም ለስፖርት ቤተሰቡ መፅናናትን እንመኛለን፡፡

የአዊ ብሔ/አስ/ባህል፣ቱሪዝምና ስፖርት መምሪያ

Address

Chagni Mewcha
Injibara

Telephone

+251582270024

Alerts

Be the first to know and let us send you an email when Awi Culture, Tourism & Sport Department posts news and promotions. Your email address will not be used for any other purpose, and you can unsubscribe at any time.

Share