24/07/2026
የሌራ ከተማ ማዘጋጃ ቤት ከ ምዕ/አዘ/በ/ወ/ከ/ል/ኮ ፅ/ቤት ጋራ በመሆን የ2018 በጀት አመት የ12 ወር የህዝብ ክንፍ ስብሰባ አደረገ።
ቀን 17/11/2018 ዓ.ም
ሌራ
👉 በስብሰባውም የሌራ ከተማ ማዘጋጃ ቤት ስራስኪያጅ አቶ ሙባሪክ አክመል፣የምዕ/አዘ/በ/ወ/ከ/ል/ኮ/ፅ/ቤት ሀላፊ አቶ ተማም አወል፣የምዕ/አዘ/በ/ወ/ከ/ል/ኮ/ፅ/ቤት የስነ-ምግባርና ፀረ ሙስና ክትትል አስተባባሪ አቶ አ/ረህማን ሪድዋን፣የምዕ/አዘ/በ/ወ/ኢንተርፕራይዝ እንዱስትሪና ስራ እድል ፈጠራ ፅ/ቤት ሀላፊ አቶ ሙከሚል ባለኬር፣የሌራ ከተማ ቀበሌ ስራስኪያጅ አቶ ፈድሉ ሁልጫፎ፣የምዕ/አዘ/በ/ወ/ማህበራዊ ዋስትና ፅ/ቤት ሀላፊ ወ/ሮ ለይላ አብድልሰመድ፣ ከቀበሌ ደጋፊ አመራር አቶ ሰኢድ አዴቦ፣የሌራ ከተማ ቀበሌ የ13ቱም መንደር ተጠሪዎች፣የሀይማኖት አባቶች፣የከተማው የሀገር ሽማግሌዎች፣የፐብሊክ ሰርቪስ ተወካዮች ፣ የሴክተሩ ባለሞያዎች እንዲሁም ሌሎች ጥሪ የተደረገላቸው እንግዶች በተገኙበት ስብሰባው ተካሄዷል።
👉የስብሰባውንም መክፈቻ አቶ ሙባሪክ አክመል ያደረጉ ሲሆን የሌራ ከተማ ማዘጋጃ ቤት የህብረተሰብ ልማት ተሳትፎ ስራ ሂደት አስተባባሪ ወይዘሪት ሰናይት ወ/ሰንበት ስለስብሰባው አንድምታ አጭር ገለጻ በማድረግ የእለቱ ውይይት የተጀመረ ሲሆን:-
የከተማው ማዘጋጃ ቤት ስራስኪያጅ አጠቃላይ በ12ቱ ወር የተከናወኑ ተግባራትን ለተሰብሳቢዎች ዝርዝር ሪፖርት አቅርበዋል በሪፖርቱም ካቀረቧቸው ዋና ዋና ተግባራት መካከል
👉 ከመሬት ልማትና ማኔጅመንት በተለይ ከመረጃ አያያዝ ጋር በተያያዘ የዘመነ እና የካይዘን ፍልስፍና ን የተከተለ አሰራር ማዘጋጃ ቤቱ ተግባራዊ ያደረገ በመሆኑ የተገልጋዮችን እንግልት ሊቀንስ የቻለ ስራ መስራት እንደተቻለ፣
👉ልቅ እንሰሳትንና ከዛ ጋር የተያያዙ የከተሞችን ፅዳትና ውበት ስራዎች ከፍተኛ መሻሻል ያለበት ሁኔታ ላይ እንደሚገኝ እንደውም በዚህ አመት ብቻ ከልቅ እንሰሳት ቅጣት ከ 350,000 ብር በላይ ገቢን መሰብሰብ እንደተቻለ በሪፖርቱ ገልፀዋል።
👉 በህብረተሰብ ንቁ ተሳትፎ እስከ 15000000 ብር የተሰበሰበ ሲሆን በዚህም ገቢ የኮሊደር ልማት ፕሮጀክት ስራ ፣በከተማዋ በተለያዩ መንደሮች የተሰሩ የመንገድ ከፈታና ጠረጋ ስራዎች፣የውሃ መስመር ዝርጋታ እና የማብራት ማስፋፊያ ስራዎች በሰፊው መሰራታቸውንም አውስተዋል።ለዚህም ተግባር የከተማው ህብረተሰብ ሳይታክት ለከተማው ልማትና መሰረተ ልማት ስራዎች ላደረገው የላቀ ተሳትፎ ምስጋናቸውን አቅርበዋል።👇
👉 ሌላው ደሞ ሰሞኑን በፕላን መንገድ ላይ አፈር፣አሻዋ፣ድንጋይ፣እንጨት የመሳሰሉትን በማስደፋት ለህብረተሰቡ እና ለተሽከርካሪዎች አስቸጋሪ ሆነው የሚገኙ ግለሰቦችን በመመሪያው መሰረት ቅጣት እያከፈሉ የማስነሳት ስራን መስራት የተጀመረ ሲሆን በዚህ ሁለት ቀን ብቻ 37000 ገቢ መሰብሰብ እንደተቻለ በሪፖርቱ ግልፀዋል።
ከዚህ ባሻገርም ሌሎች የተከናወኑ ተግባራትን በስፋት የዳሰሱ ሲሆን በመቀጠልም የመድረኩ ተሳታፊዎች እድል በመውሰድ ወሳኝ የሆኑ ነጥቦችን በጥያቄና አስተያያት መልክ በማንሳት በመድረኩ በሰፊው ሀሳብ ተንሸራሽሮባቸዋል።
👉በመጨረሻም ከመድረኩ ለተነሱ ጥያቄዎች አቶ ሙባሪክ አክመል ምላሽ የሰጡ ሲሆን ለተሰነዘሩ አስተያየቶችም ዝርዝር ማብራሪያ በመስጠት እና አስተያየቶችን በመጨመር የእለቱን መድረክ አጠናቀዋል።