Hadiya Zone Lemo Woreda Government Communication Affairs

Hadiya Zone Lemo Woreda Government Communication Affairs Central Ethiopia Regional Government Hadiya Zone Lemo Woreda Government Communication Affairs office Hossana ,Ethiopia

ጳጉሜ 3:-የጽናት ቀን! በሀዲያ ዞን ''ጽኑ መሠረት ብርቱ ሀገር '' በሚል መሪ ቃል የጽናት ቀን በድምቀት እየተከበረ ነው። ሆሳዕና፣ጳጉሜ03/2018 ዓ.ም(ሌሞ ወረዳ ኮሚዩኒኬሽን) ዛሬ ጳ...
08/09/2026

ጳጉሜ 3:-የጽናት ቀን!

በሀዲያ ዞን ''ጽኑ መሠረት ብርቱ ሀገር '' በሚል መሪ ቃል የጽናት ቀን በድምቀት እየተከበረ ነው።

ሆሳዕና፣ጳጉሜ03/2018 ዓ.ም(ሌሞ ወረዳ ኮሚዩኒኬሽን)

ዛሬ ጳጉሜ 3 ነው::ቀኑ የጽናት ቀን ነው ። ቀኑም በዞኑ ''ጽኑ መሠረት ብርቱ ሀገር!''በሚል መሪ ቃል በፖሊስ ትርዕትና በሌሎችም ዝግጅቶች በሆሳዕና ከተማ በድምቀት እየተከበረ ነው።

የዕለቱ መርሃ ግብር የሀገራችን ኢትዮጵያ ሰንደቅ ዓላማን በማውለብለብ እና በሰንደቀላማ ሥር ሀገራችንን በአንድነትና ሠላም በጽኑ ዓለት ላይ ለማቆም ቃለ ማሃለ በመፈፀም ተጀምሯል ።

በመቀጠልም ዕለቱን በማስመልከት ለሚካሄደው የውይይት መድረክ የመነሻ ሰነድ የሀዲያ ዞን ሠላምና ፀጥታ መምሪያ ኃላፊ በአቶ ደመቀ በዶሬ እየቀረበ ይገኛል።

በሥነ ሥርዓቱም የሀዲያ ዞን ምክር ቤት ዋና አፈ_ጉባዔ ክብርት ወይዘሮ እቴነሽ ሙሉጌታ፣የሀዲያ ዞን ዋና የመንግስት ተጠሪና የብልጽግና ፓርቲ ጽህፈት ቤት ኃላፊ አቶ ታምራት ግዛው፣የሀዲያ ዞን ከፍተኛ ፍርድ ቤት ፕሬዝዳንት ዳኛ ጥላሁን ዴታሞን ጨምሮ የክልል የሆሳዕና ማዕከል አመራሮች፣የሀዲያ ዞን ከፍተኛ የመንግስት የሥራ ኃላፊዎች፣የሆሳዕና ከተማ አመራሮች፣የሀዲያ ዞን የፍትህ፣የሠላምና ፀጥታ አመራሮች፣የባህል ሽማግሌዎች፣የሀይማኖት አባቶች ፣ከሁሉም መምሪያ የተወጣጡ የማኔጅመንት አባላት፣የፖሊስ አባላት እንዲሁም ጥሪ የተደረገላቸው እንግዶች ተሳታፊ ናቸው።

ሀዲያ ዞን ኮሚዩኒኬሽን

በሀዲያ ዞን የሌሞ ወረዳ ፕላን ልማት ጽ/ቤት የአስፈጻሚ መስሪያ ቤቶች  የ2018 በጀት ዓመት ክንውን አፈፃፀም ሪፖርት እና የ2019 በጀት ዓመት ዕቅድ ግምገማ መድረክ አካሄዷል ። ሆሣዕና፣...
07/09/2026

በሀዲያ ዞን የሌሞ ወረዳ ፕላን ልማት ጽ/ቤት የአስፈጻሚ መስሪያ ቤቶች የ2018 በጀት ዓመት ክንውን አፈፃፀም ሪፖርት እና የ2019 በጀት ዓመት ዕቅድ ግምገማ መድረክ አካሄዷል ።

ሆሣዕና፣ጳጉሜ 2/2018(ሌሞ ወረዳ ኮሚዩኒኬሽን)

የሌሞ ወረዳ ፕላንና ልማት ጽ/ቤት ኃላፊ አቶ ሙሉቀን ሻፊ የሌሞ ወረዳ አስተዳደር የአስፈፃሚ መስሪያ ቤቶችን የ2018 በጀት ዓመት ዕቅድ ክንውን ሪፖርት እና የ2019 በጀት ዓመት መነሻ ዕቅድ አቅርበው በሁሉም አስፈጻሚ ተቋማት ኃላፊዎች ተገምግሟል።

የ2018 በጀት ዓመት አፈጻጸም ማጠቃለያ ሪፖርት ቀጣይ የ2019 ዕቅድን ለማሻሻልና ይበልጥ በተቀናጀ አሰራር እንዲሰራ አቅጣጫ በማስቀመጥ የተገመገመ ሲሆን የ2019 በጀት ዓመት ዕቅድ ለጥጦ ከማቀድ አንፃር ሁሉም ተቋማት በየዘርፉ በተቀናጀ እና በተናበበ አሰራር ተዘርግቶ እንዲሰራም ተጠቁሟል።

የሌሞ ወረዳ ዋና አስተዳዳሪ አቶ ታደለ ደምሴ በግምገማው በሰጡት አስተያየት የተሰሩ ተግባራትን በጥልቀት መገምገም ለቀጣይ የወረዳውን አፈጻጸም የተሻለ ውጤት ለማስመዝገብ የሚረዳ መሆኑን በመግለፅ የተነሱ ጉድለቶችን በየተቋሙ በመዉሰድ በቀጣይ 2019 በጀት ዓመት የዕቅድ አካል ሆኖ ወደ ተግባር መቀየር እንደሚያስፈልግ ገልጸዋል።

ግምገማውም በወረዳው አስፈጻሚ ተቋማት ላይ ለተነሱ ጥያቄዎች በኃላፊዎቹ ምላሽና ማብራሪያ ተሰጥቶበት ተጠናቋል።

ዘጋቢ:-ዕፁብ አዳነ

የከተማ መረጃዎችን በማዘመን ቀልጣፋ አገልግሎት ለመስጠት የቢሮዎችን ግንባታ ማመቻቸት ቅድሚያ የሚሰጠው ተግባር መሆኑ ተገለጸ ሆሳዕና፣ጳጉሜ 2/2018 ዓ.ም(ሌሞ ኮሚዩኒኬሽን) የጳጉሜ 2 የኢ...
07/09/2026

የከተማ መረጃዎችን በማዘመን ቀልጣፋ አገልግሎት ለመስጠት የቢሮዎችን ግንባታ ማመቻቸት ቅድሚያ የሚሰጠው ተግባር መሆኑ ተገለጸ

ሆሳዕና፣ጳጉሜ 2/2018 ዓ.ም(ሌሞ ኮሚዩኒኬሽን)

የጳጉሜ 2 የኢትዮጵያ “የመንሰራፋት ቀን”ን ምክንያት በማድረግ፣ የሌሞ ወረዳ "ዘላቂ ልማት ለሀገራዊ ማንሰራራት" በሚል መሪ ቃል በበሌሣ ከተማ ታዳጊ ማዘጋጃ ቤት በመንግሥትና በሕዝብ ተሳትፎ የተከናወኑ የልማት ሥራዎችን የጉብኝት መርሃ ግብር አካሂዷል።

በዚህም በከተማዋ የተከናወነው "አንድ ከተማ፣ አንድ ፕሮጀክት" ሥራ የጉብኝቱ አካል ሆኗል።

የሌሞ ወረዳ ዋና አስተዳዳሪ አቶ ታደለ ደምሴ በጉብኝቱ ወቅት እንዳሉት፤ የከተማ መረጃዎችን በማዘመን ለሕብረተሰቡ ቀልጣፋ አገልግሎት ለመስጠት የሥራ ቢሮዎችን ማመቻቸት ቅድሚያ የሚሰጠው ተግባር ነው።

"አንድ ከተማ፣ አንድ ፕሮጀክት" የተሰኘውን ሀገራዊ ኢኒሼቲቭ በበሌሣ ከተማ በተግባር ማየት መቻሉን የገለጹት አቶ ታደለ፤ ከእጅ ንክኪ ነፃ የሆነ ዲጂታል የአገልግሎት አሰጣጥ በቅርቡ በሁሉም ከተሞች እንደሚጀመር ተናግረዋል።

የሌሞ ወረዳ ከተማ ልማትና ኮንስትራክሽን ጽሕፈት ቤት ኃላፊ አቶ ደሣለኝ በየነ በበኩላቸው፤ "የማንሰራራት ቀን" በከተሞች በብዙ ጥረትና ዋጋ የተከናወኑ የልማት ሥራዎች ለሕዝብ እይታ እንዲበቁ ዕድል የፈጠረ መሆኑን ገልጸዋል።

በከተሞች የሚሰጡ አገልግሎቶች ቀልጣፋ እና ከእጅ ንክኪ ነጻ እንዲሆኑ በመንግሥት በኩል ትኩረት ተሰጥቶ እየተሠራ እንደሚገኝ ጠቁመው፤ በወረዳው በመንግሥት እንዲሁም በሕብረተሰብ ተሳትፎ በርካታ ተግባራት መከናወናቸውን አብራርተዋል።

የበሌሣ ከተማ ታዳጊ ማዘጋጃ ቤት በበጀት ዓመቱ ያከናወናቸው ተግባራት ውጤታማ መሆናቸውን የጠቀሱት አቶ ደሣለኝ፤ በተለይም የሊዝ ጨረታዎችን በማውጣትና ሕብረተሰቡን በማሳተፍ ለከተማዋ ልማት የሚውል አጥጋቢ ገቢ መሰብሰብ መቻሉን ገልጸዋል።

የበሌሣ ከተማ ታዳጊ ማዘጋጃ ቤት ሥራ አስኪያጅ አቶ ኢያሱ ምትኩ፤ በከተማዋ በመንግሥትና በግል ባለሀብቶች ሕብረተሰቡን ተጠቃሚ የሚያደርጉ የተለያዩ የልማት ሥራዎች እየተከናወኑ እንደሚገኙ ገልጸዋል።

"አንድ ከተማ፣ አንድ ፕሮጀክት" በሚለው ሀገራዊ መመሪያ መሠረት የማዘጋጃ ቤቱን አዳዲስ የቢሮ አገልግሎት መስጫ ክፍሎች መገንባታቸውን ጠቁመው፤ የተገነቡት ቢሮዎች በቀጣይ የከተማዋን መረጃዎች ዘመናዊ ለማድረግ ለሚደረገው እንቅስቃሴ ከፍተኛ አስተዋጽኦ እንደሚኖራቸው አስረድተዋል።

በሀዲያ ዞን ሌሞ ወረዳ ጳጉሜን-2 "የማንሰራራት ቀን" ምክንያት በማድረግ በበሌሳ ከተማ የተገነቡ የከተማ ግብርና እና ሌሎቾ ልማቶችን በመጎብኘት ተከበረ። ሆሳዕና፣ጳጉሜ2/2018 ዓ.ም(ሌሞ ...
07/09/2026

በሀዲያ ዞን ሌሞ ወረዳ ጳጉሜን-2 "የማንሰራራት ቀን" ምክንያት በማድረግ በበሌሳ ከተማ የተገነቡ የከተማ ግብርና እና ሌሎቾ ልማቶችን በመጎብኘት ተከበረ።

ሆሳዕና፣ጳጉሜ2/2018 ዓ.ም(ሌሞ ኮሚዩኒኬሽን)

"ዘላቂ ልማት ለሀገራዊ ማንሰራራት" በሚል መሪ ቃል የማንሰራራት ቀንን በማስመልከት በበሌሳ ከተማ የተገነባውን ኢትዮ-ካናዳ ግርማ አሰፋ አግሮ ፋርም ዘመናዊ የከብት እርባታና የወተት አቅረቦት ድርጅት የሚመረተውን የከተማ ጥምር የግብርና ስራዎች፣የወተት አቅርቦት እንዲሁም የከብቶች መኖ አዘገጃጀትን በመጎብኘት ተከብሮ ውሏል።

የሌሞ ወረዳ ዋና አስተዳዳሪ አቶ ታደለ ደምሴ ባስተላለፉት መልዕክት የኢትዮጵያ የማንሰራራት ጉዞ ዕውን ለማድረግ የሁላችን ትጋት ያስፈልጋል ብለዋል።

ጳጉሜ 2 «የማንሰራራት ቀን» ተብሎ የሚከበረው የኢትዮጵያን አዲስ ዓመት አቀባበል መነሻ በማድረግ እና የተስፋ፣ የእድገት እንዲሁም የለውጥን አስፈላጊነት ለማሳሰብ መሆኑንም ገልፀዋል።

ዋና አስተዳዳሪው ባዩት ነገር ደስተኛ መሆናቸውን ገልፀው ድርጅቱም በስሩ ለበርካታ ስራ ፈላጊዎች ስራ በመፍጠር ረገድ የሰራው ስራ የሚያስመሰግን መሆኑንም አንስተዋል።

የኢትዮ-ካናዳ ግርማ አሰፋ አግሮ ፋርም ዘመናዊ የከብት እርባታና የወተት አቅረቦት ድርጅት ስራ አስኪያጅ አቶ ውድነህ ዲንቦሬ ጳጉሜ 2 የማንሰራራት ቀንን ምክንያት በማድረግ የወረዳውና የቀበሌያት አመራሮች ስለጎበኟቸው ምስጋና አቅርበው ድርጅቱ ከበሌሳ አካባቢ በተጨማሪ ለሆሳዕና ከተማ በስፋት ወተት እንደሚያቀርብና በቀጣይም በሌሎች የኢንቨስትመንት ዘርፎች ለመሰማራት እያሰቡ በመሆኑ ወረዳው በአስፈላጊው ሁሉ እንዲደግፋቸው ጠይቀዋል።

በቀጣይም እንደዚህ አይነት ስራዎች ተጠናክረው መቀጠል እንዳለባቸው አስተያየታቸውን የሰጡት ጎብኝዎቹ በበሌሳ ከተማ እየተሰሩ ያሉ ስራዎች የነዋሪዎችን የወተት ፍላጎት የሚያሟሉ በመሆናቸው ተጠናክረው ሊቀጥሉ ይገባል ሲሉ አሳስበዋል።

በጉብኝት ፕሮግራሙ የሌሞ ወረዳና የቀበሌ አመራሮች እንዲሁም የበሌሣ ከተማ ነዋሪዎች ተገኝተዋል።

ዘጋቢ:-ዕፁብ አዳነ

"የማንሰራራት ቀን" በሀዲያ ዞን ሌሞ ወረዳ ጳጉሜን 2 አከባበር በፎቶ
07/09/2026

"የማንሰራራት ቀን" በሀዲያ ዞን ሌሞ ወረዳ ጳጉሜን 2 አከባበር በፎቶ

የሃይማኖት ተቋማት ከሃይማኖታዊ ተልዕኳቸው ጎን ለጎን በማህበራዊ ኃላፊነቶች ላይ ያላቸው ተሳትፎ ተጠናክሮ መቀጠል እንዳለበት ተጠቆመ ሆሳዕና፣ጳጉሜ1/2018 ዓ.ም(ሌሞ ኮሚዩኒኬሽን) የቤተ ክ...
06/09/2026

የሃይማኖት ተቋማት ከሃይማኖታዊ ተልዕኳቸው ጎን ለጎን በማህበራዊ ኃላፊነቶች ላይ ያላቸው ተሳትፎ ተጠናክሮ መቀጠል እንዳለበት ተጠቆመ

ሆሳዕና፣ጳጉሜ1/2018 ዓ.ም(ሌሞ ኮሚዩኒኬሽን)

የቤተ ክርስቲያኒቱ መሥራችና ባለራዕይ ወንጌላዊ ማቲዎስ ጡምሶ፤ በጎ ማድረግና ለሌለው ማካፈል ለቤተ ክርስቲያን ከተሰጡ ተልዕኮዎች አንዱ እንደሆነ ተናግረዋል።

አክለውም የሃይማኖት ተቋማት ከሃይማኖታዊ ተልዕኳቸው ጎን ለጎን በማህበራዊ ኃላፊነቶች ላይ ያላቸው ተሳትፎ ተጠናክሮ መቀጠል እንዳለበት ገልጸው፣ ለዚህ መልካም ተግባር የበኩላቸውን ድርሻ ላበረከቱ አካላት በሙሉ ምስጋና አቅርበዋል።

በድጋፍ መርሃ ግብሩ ላይ የተገኙት የሌሞ ወረዳ ሠራተኛና ማህበራዊ ጉዳይ ጽሕፈት ቤት ኃላፊ ወይዘሮ ብርሃነሽ አባቢያ፤ በወረዳው በክረምት በጎ ፈቃድ አገልግሎት በሀገር አቀፍ ደረጃ «በጎነት ለኢትዮጵያ ከፍታ» በሚል መሪ ቃል በርካታ ሰው ተኮር ተግባራት እየተከናወኑ እንደሚገኙና ከወረዳውም ከተለያዩ ቀበሌያት ለመጡ አቅመ ደካሞች ድጋፍ እንደተደረገላቸው ገልጸዋል።

በዚህም የሃይማኖት ተቋማት፣ የመንግሥትና መንግሥታዊ ያልሆኑ ተቋማት እንዲሁም ባለሀብቶች የሚያደርጉት አስተዋጽዖ ከፍተኛ መሆኑን ገልጸዋል።

በዕለቱ የአማኑኤል ቦቢቾ ቃለ ሕይወት ቤተ ክርስቲያን ለ200 አቅመ ደካሞች ያበረከተችው አስተዋጽዖ የሚበረታታ መሆኑን በመግለጽ፣ ይህም ተጠናክሮ መቀጠል እንዳለበት አሳስበዋል።

በዕለቱ ድጋፍ የተደረገላቸው አካላትም በተደረገላቸው ድጋፍ መደሰታቸውን ገልጸው ምስጋናቸውን አቅርበዋል።

ሀዲያ ቲቪ

በሀዲያ ዞን ሌሞ ወረዳ "እምርታ ለዘላቂ ከፍታ" በሚል መሪ ሀሳብ ጳጉሜን 1 የእምርታ ቀን በተለያዩ ተግባራት ተከብሯል። ሆሣዕና፣ጳጉሜ 1/2018(ሌሞ ወረዳ ኮሚዩኒኬሽን) ጳጉሜን 1 የሌሞ ...
06/09/2026

በሀዲያ ዞን ሌሞ ወረዳ "እምርታ ለዘላቂ ከፍታ" በሚል መሪ ሀሳብ ጳጉሜን 1 የእምርታ ቀን በተለያዩ ተግባራት ተከብሯል።

ሆሣዕና፣ጳጉሜ 1/2018(ሌሞ ወረዳ ኮሚዩኒኬሽን)

ጳጉሜን 1 የሌሞ ወረዳ እና የወረዳው ቀበሌያት አመራሮች በጋራ ቀኑን አክብረዋል።

የሌሞ ወረዳ ዋና አስተዳዳሪ አቶ ታደለ ደምሴ ለጳጉሜን 1 የእምርታ ቀን የእንኳን አደረሳችሁ መልዕክት በማስተላለፍ የጳጉሜ ቀናት ከለውጡ ወዲህ በልዩ ልዩ ተግባራት ትርጉም ተሰጥቷቸው እየተከናወኑ እንደሚገኙ ገልጸው ይህም መዳረሻ ወደ ሆነው ሁለንተናዊ የብልጽግና ለሚደረገው ጉዞ አጋዥ መሆኑን ጠቁመዋል።

አቶ ታደለ አያይዘውም ወረዳው በግብርናው ዘርፍ በርካታ እምርታዎችን እያስመዘገበ እንደሚገኝ በመግለጽ ከዚህ ቀደም ሌሞ ወረዳ በስንዴ ምርት የሚታወቅ ቢሆንም አሁን ጤፍና ሌሎች ሰብሎችንም በማምረት ከተረጂነት ወደ ምርታማነት ለሚደረገው ጉዞ ከፍተኛ አስተዋጽኦ እያበረከተ እንደሚገኝና በዓመት ከአንድ ግዜ በላይ በማምረት የአርሶ አደሩ ኢኮኖሚም እያደገ እንደሚገኝ ገልጸዋል።

የሌሞ ወረዳ ግብርና ጽ/ቤት ኃላፊ አቶ ሰልፋሞ ወ/ዮሐንስ በበኩላቸው በግብርናው ዘርፍ ምርትና ምርታማነትን ለማሳደግ በተለያዩ ዘርፎች ምርጥ ዘር አቅርቦት ላይ ትኩረት ተሰጥቶ እየተሠራ እንደሚገኝና በግብርናው ዘርፍ በዝሪያ ማሻሻልና በኩታ ገጠም እርሻ የተመዘገበው እምርታ የሚጠቀስ እንደሆነም ገልጸዋል።

በሌሞ ወረዳ የጳጉሜን 1 የእምርታ ቀንን ምክንያት በማድረግ በተደረገው የመስክ ምልከታ የሌሞ ወረዳ ስራ አስፈጻሚዎች፣ የወረዳውና የሁሉም ቀበሌያት አመራሮች እና ሌሎች አካላት በመስክ በመገኘት በአምብቾ ጎዴ ቀበሌ በኩታ ገጠም የተመረተ የጤፍ ማሳ እንዲሁም በቃልሻ ቀበሌ የሌማት ትሩፋት የሆነውን የወተት ከብት እርባታ፣የከብት መኖ ምርት እንዲሁም የጓሮ ቡና ምርትን ጎብኝተዋል።

ዘጋቢ:-ዕፁብ አዳነ

"እምርታ ለዘላቂ ከፍታ" በሀዲያ ዞን ሌሞ ወረዳ የጷጉሜ 1 ቀን አከባበር በፎቶ
06/09/2026

"እምርታ ለዘላቂ ከፍታ" በሀዲያ ዞን ሌሞ ወረዳ የጷጉሜ 1 ቀን አከባበር በፎቶ

በሀዲያ ዞን የሌሞ ወረዳ ገቢዎች ጽ/ቤት ከባለድርሻ አካላት ጋር በመቀናጀት ገቢን አሟጦ በመሰብሰብ የህብረተሰቡን የልማት ጥያቄ ምላሽ ለመስጠት በትኩረት እየሰራ መሆኑን ገለጸ። ሆሣዕና፣ነሐሴ...
03/09/2026

በሀዲያ ዞን የሌሞ ወረዳ ገቢዎች ጽ/ቤት ከባለድርሻ አካላት ጋር በመቀናጀት ገቢን አሟጦ በመሰብሰብ የህብረተሰቡን የልማት ጥያቄ ምላሽ ለመስጠት በትኩረት እየሰራ መሆኑን ገለጸ።

ሆሣዕና፣ነሐሴ 28/2018(ሌሞ ወረዳ ኮሚዩኒኬሽን)

በ2018 በጀት ዓመት በገቢ አሰባሰብ ረገድ ለታየው ውጤታማ አፈጻጸም የምስጋናና የዕውቅና መድረክ ተካሂዷል።

በውይይት መድረኩ የተገኙት የሌሞ ወረዳ ዋና አስተዳዳሪ አቶ ታደለ ደምሴ እንደተናገሩት በተለያዩ መንገዶች የሚሰበሰበውን ገቢ አሟጦ በመሰብሰብ የመሠረተ ልማትና ሌሎች ጥያቄዎችን በተሟላ ሁኔታ ለመመለስ በቅንጅት ሲሰራ እንደነበር ገልጸዋል።

በትራንስፖርቱ ዘርፍ ህግን የሚተላለፉ ባለንብረቶችን በማስተማር ተጠቃሚው ማህበረሰብ ተገቢውን አገልግሎት እንዲያገኝ አስቻይ ሁኔታ ከመፈጠሩም ባሻገር ህግን በተላለፉ አሽከርካሪዎች ላይ አስተማሪ ቅጣት በመጣል ህብረተሰቡ ላይ የሚፈጠረውን ጫና መቀነስ መቻሉን አንስተዋል።

በ2019 በጀት ዓመት በገቢ አሰባሰብ ረገድ ጠንካራ ቅንጅታዊ አሰራር በመዘርጋት በደንብ ማስከበርና በማዕድን ቀረጥ ገቢ ውጤታማ ለመሆን በትኩረት እንደሚሰራም አቶ ታደለ ተናግረዋል።

የሌሞ ወረዳ ገቢዎች ቅርንጫፍ ጽ/ቤት ኃላፊ አቶ ሽፈራው አለቃ በበኩላቸው ገቢ ለወረዳው ልማት ወሳኝ በመሆኑ በ2018 በጀት ዓመት በወረዳው ካሉ ባለድርሻ መስሪያ ቤቶች ጋር በቅንጅት በተሰራው ስራ ውጤታማነት ምስጋና እና ዕውቅና የሰጡ ሲሆን በቀጣይ 2019 በጀት ዓመትም በጋራ በመስራት የተሻለ ውጤት ይመዘገባል የሚል እምነት እንዳላቸው ገልጸዋል።

የሌሞ ወረዳ ፋይናንስና ኢኮኖሚ ልማት ጽ/ቤት ኃላፊ አቶ አድማሱ ወልደ ማርያም በውይይቱ እንደተናገሩት በ2018 በጀት ዓመት የተደረገው ገቢን አሟጦ የመሰብሰብ ተግባር ለባለድርሻ አካላቱ ምስጋና አቅርበው በወረዳው ለሚነሱ የተለያዩ ጥያቄዎች በፋይናንስ ተቋም ምላሽ መስጠት እንዲቻል በ2019 በጀት ዓመትም በተሻለ መልኩ በቅንጅት ገቢ መሰብሰብ አለበት በማለት የወረዳው ፋይናንስም ለባለድርሻ አካላቱ በሚያስፈልገው ሁሉ ድጋፍ እንደሚያደርግ ገልጸዋል።

ከውይይቱ ተሳታፊዎችም የተለያዩ ጥያቄዎችና አስተያየቶች ተሰጥተው በዋና አሰተዳዳሪና በፋይናንስ ኃላፊ ምላሽና ማብራሪያ በመስጠት ውይይቱ ተጠናቋል።

ዘጋቢ፣ዕፁብ አዳነ

ህግና ደንብን በአግባቡ ባልተገበሩ የባለሁለት እግር ሞተር አሽከርካሪዎች ላይ እርምጃ መውሰዱን በሀዲያ ዞን የሌሞ ወረዳ ፖሊስ አስታወቀ። ሆሣዕና፣ነሐሴ 22/2018(ሌሞ ወረዳ ኮሚዩኒኬሽን) ...
28/08/2026

ህግና ደንብን በአግባቡ ባልተገበሩ የባለሁለት እግር ሞተር አሽከርካሪዎች ላይ እርምጃ መውሰዱን በሀዲያ ዞን የሌሞ ወረዳ ፖሊስ አስታወቀ።

ሆሣዕና፣ነሐሴ 22/2018(ሌሞ ወረዳ ኮሚዩኒኬሽን)

በሀዲያ ዞን የሌሞ ወረዳ አስተዳደር ፖሊስ፣መንገድ ትራንስፖርት እና የፀጥታ ሀይሎች ባደረጉት የተቀናጀ ስራ ለአደጋ ተጋላጭ የሆኑ በቁጥር በርካታ የባለሁለት እግር ሞተር ተሽከርካሪዎች መያዛቸው ተገልጿል።

የሌሞ ወረዳ ፖሊስ ጽ/ቤት አዛዥ የሆኑት ምክትል ኢ/ር አሸናፊ መኔቦ እንደገለፁት ከተፈቀደው ሰው በላይ በመጫን፣የሰሌዳ ቁጥር ባለመኖር፣የባለቤትነት ማረጋገጫ፣የራስ መከላከያ ቆብ፣መንጃ ፍቃድ የሌላቸው 103 ሞተሮች በቁጥጥር ስር መዋላቸውን ገልፀዋል።

የሌሞ ወረዳ ፖሊስ ጽ/ቤት ትራፊክ ፍሰት ቁጥጥርና ቴክኒክ ምርመራ ዘርፍ ኃላፊ ኮማንደር ሽፈራው ቲሮሮ በዕለቱ ለባለሁለት እግር ሞተር አሽከርካሪዎች በሰጡት የግንዛቤ ማስጨበጫ ሞተር ሳይክሎች የአደጋ መንስኤ ከመሆናቸውም በላይ የወንጀል ድርጊት መፈፀሚያ ስለሚሆኑ ጥብቅ ክትትል እንደሚደረግና አሽከርካሪዎች እራሳቸውን እና ሌሎችንም ከአደጋ የመጠበቅ ሀላፊነታቸውን እንዲወጡ አሳስበዋል።

ኮማንደር ሽፈራው አክለውም የባለሁለት እግር ሞተር አሽከርካሪዎች የትራፊክ ህጎችና ደንቦችን እንዲያከብሩ እንዲሁም ከአንድ ሰው በላይ እንዳይጭኑና እና ሌሎች ከአደጋ መታደግ የሚያስችሉና አስፈላጊውን ሁሉ እንዲያሟሉ ሙያዊ ምክር ለግሰዋል።

የሀድያ ዞን ፖሊስ መምሪያ የወንጀል መከላከል ዘርፍ ኃላፊ ኮማንደር ሳይሉ ኃይሉ እንደተናገሩት መንጃ ፍቃድ ይዘው ህጋዊ ሆነው በማያሽከረክሩ፣ የጭንቅላት ቆብ(ሔልሜት) በአግባቡ ባልተጠቀሙ የባለሁለት እግር የሞተር አሽከርካሪዎች ላይ በቀጣይም እርምጃ እንደሚወሰድና ህግና ደንብን ጥሰው ከተገኙ በህግ እንደሚጠየቁ ለሞተረኞቹ አስረድተዋል።

የሌሞ ወረዳ መንገድና ትራንስፓርት ጽ/ቤት ምክትልና የትራንስፖርት ዘርፍ ኃላፊ አቶ ወንድሙ ወ/ሰንበት የባለሁለት እግር ሞተር ተሽከርካሪ ባለንብረቶች ለራሳቸው ደህንነት ሲሉ ከሚፈጠረው የትራፊክ አደጋ ለመከለከል የጭንቅላት ቆብ እንዲጠቀሙ ለባለሞተሮች መልዕክት አስተላልፈዋል።

የሌሞ ወረዳ ሰላምና ጸጥታ ጽ/ቤት ኃላፊ አቶ ተሻለ የሱፍ እንደተናገሩት ከህብረተሰቡ ከሚደርሱ ጥቆማዎች ውስጥ ታርጋ የሌላቸው እና ለመለየት የሚያስቸግሩ እንዲሁም በከፍተኛ ፍጥነት የሚያሽከረክሩ ሞተረኞች የስጋት ምንጭ በመሆናቸው በተቀናጀ መልኩ እርምጃው መወሰዱን ገልፀው በቀጣይም ከሀዲያ ዞንና ከሆሣዕና ከተማ ግብረ ኃይል ጋር ቅንጅታዊ አሰራርን በማጠናከር የወንጀል ድርጅት ለመቀነስ እየተሰራ እንደሚገኝ ገልፀዋል።

የሞተር አሽከርካሪዎችም በሰጡት አስተያየት የሚደረገው ቁጥጥር የራሳቸውንና የተሳፋሪውን ደህንነት ለመጠበቅ እንዲሁም የአካባቢውን ሰላም ለማስጠበቅ በመሆኑ በቀጣይ ስህተታቸውን በማረም ከፖሊስ ጎን እንደሚሆኑና ምንም አይነት አጠራጣሪ ነገሮችን ለፀጥታ አካላት በመጠቆም የበኩላቸውን እንደሚወጡ ቃል ገብተዋል።

ዘጋቢ:-ዕፁብ አዳነ

Address

Hossana

Website

Alerts

Be the first to know and let us send you an email when Hadiya Zone Lemo Woreda Government Communication Affairs posts news and promotions. Your email address will not be used for any other purpose, and you can unsubscribe at any time.

Shortcuts

Share