የሀዲያ ዞን ብልጽግና ፓርቲ ኮሚዩኒኬሽን

የሀዲያ ዞን ብልጽግና ፓርቲ ኮሚዩኒኬሽን Contact information, map and directions, contact form, opening hours, services, ratings, photos, videos and announcements from የሀዲያ ዞን ብልጽግና ፓርቲ ኮሚዩኒኬሽን, Political organisation, Central Ethiopia Region, Hadiya Zone, Hossana.

23/05/2026
23/05/2026
"የሕዝብ አንድነትና ኅብረት ኢትዮጵያን ወደ ተምሳሌት ሀገር ለማሸጋገር ከፍተኛ ሚና አለው"- ዶ/ር ኤርጎጌ ተስፋዬሆሳዕና፤ ግንቦት 15/2018 በማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል በሀዲያ ዞን ምዕራብ...
23/05/2026

"የሕዝብ አንድነትና ኅብረት ኢትዮጵያን ወደ ተምሳሌት ሀገር ለማሸጋገር ከፍተኛ ሚና አለው"- ዶ/ር ኤርጎጌ ተስፋዬ

ሆሳዕና፤ ግንቦት 15/2018 በማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል በሀዲያ ዞን ምዕራብ ሶሮ ወረዳ 7ኛውን ሀገራዊ ምርጫ በማስመልከት የተዘጋጀው የምረጡን ቅስቀሳና የሕዝባዊ ድጋፍ ሰልፍ ወረዳዊ ማጠቃለያ በጃቾ ከተማ በታላቅ ድምቀት ተካሄዷል ።

በመድረኩ ላይ ተገኝተው መልዕክት ያስተላለፉት የኢፌዴሪ የሴቶችና ማኅበራዊ ጉዳይ ሚኒስትር ዶ/ር ኤርጎጌ ተስፋዬ፤ የሕዝብ አንድነት፣ እርስ በርስ መተጋገዝና ኅብረት ኢትዮጵያን ሁለንተናዊ ዕድገት ያስመዘገበች ተምሳሌት ሀገር የማድረግ ሂደት ቀጣይነት እንዲኖረው ለማስቻል ከፍተኛ ሚና እንዳለው ገልጸዋል።

ሚኒስትሯ አክለውም፤ ብልጽግና የገባውን ቃል በተግባር የሚፈጽም፣ የጀመራቸውን ታላላቅ የልማት ፕሮጀክቶች በጥራትና በፍጥነት አጠናቆ የሚያስረክብ ጠንካራ ፓርቲ መሆኑን አንስተው፣ ሕዝቡ በምርጫው ዕለት በነቂስ ወጥቶ ለብልጽግና ፓርቲ ድምፁን እንዲሰጥ ጥሪ አቅርበዋል።

የሀዲያ ዞን ዋና አስተዳዳሪ አቶ ማቴዎስ አኒዮ በበኩላቸው፤ የብልጽግና ፓርቲ የጀመራቸውን ሁለንተናዊ የልማትና የሰላም ሥራዎች ይበልጥ ለማጠናከር የሚያስችሉ አማራጭ ፖሊሲዎችን ነድፎ እየሠራ መሆኑን አስረድተዋል። በመሆኑም ሕዝቡ የመደመር መንግሥት ዓላማ ከግቡ እንዲደርስ ያለምንም ልዩነት በምርጫ ሂደቱ ላይ የድምፅ ተሳትፎውን እንዲያጠናክር ጠይቀዋል።

የምዕራብ ሶሮ ወረዳ ዋና አስተዳዳሪ አቶ ታሪኩ ታምራት በበኩላቸው፤ ይህ ታላቅ የድጋፍ ሰልፍ የሕዝቡን የልማት ፍላጎትና የፓርቲውን ጠንካራ ሕዝባዊ መሠረት በግልጽ ያሳየ መሆኑን ተናግረዋል።

ዋና አስተዳዳሪው ሕዝቡ በምርጫው ዕለት ድምፁን በሰላማዊና በዴሞክራሲያዊ መንገድ ለብልጽግና ፓርቲ በመስጠት፣ የአካባቢውን ሰላምና ዘላቂ ልማት እንዲያረጋግጥ አሳስበዋል።

በወረዳዊ ማጠቃለያ መርሃ-ግብር ላይ የማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል የቴክኒክና ሙያ ሥልጠና ቢሮ ምክትል ኃላፊ አቶ ይስሐቅ ማሶሬን ጨምሮ የዞን ከፍተኛ አመራሮች፣ የወረዳው ዋና የመንግሥት ተጠሪ አቶ አበጀ ተሰማ፣ የፌዴራልና የክልል ተወካዮች ምክር ቤት ዕጩዎች፣ የሀገር ሽማግሌዎች፣ የሃይማኖት አባቶች፣ ወጣቶች፣ ሴቶች እንዲሁም መላው የብልጽግና ፓርቲ ደጋፊዎች ተገኝተዋል።

"የብልጽግና መንግስት ባለፉት ስምንት የለውጥ ዓመታት በዞኑም ሆነ በሀገሪቱ ተጨባጭና ተስፋ ሰጪ ለውጦችን አስመዝግቧል" - አቶ ማቴዎስ አኒዮሆሳዕና፣ ግንቦት 15/2018  የብልጽግና መንግስ...
23/05/2026

"የብልጽግና መንግስት ባለፉት ስምንት የለውጥ ዓመታት በዞኑም ሆነ በሀገሪቱ ተጨባጭና ተስፋ ሰጪ ለውጦችን አስመዝግቧል" - አቶ ማቴዎስ አኒዮ

ሆሳዕና፣ ግንቦት 15/2018 የብልጽግና መንግስት ባለፉት ስምንት የለውጥ ዓመታት በዞኑም ሆነ በሀገሪቱ ተጨባጭና ተስፋ ሰጪ ለውጦችን አስመዝግቧል። የሀዲያ ዞን ዋና አስተዳዳሪ አቶ ማቴዎስ አኒዮ

ይህንን የገለጹት የሀገራዊ ለውጡን 8ኛ ዓመት እና 7ኛውን ጠቅላላ ምርጫ አስመልክቶ በዱና ወረዳ በተካሄደው የብልጽግና ፓርቲ የምርጫ ቅስቀሳና የድጋፍ ሰልፍ ላይ ነው።

በድጋፍ ሰልፉ ላይ የተገኙት ዋና አስተዳዳሪው፤ ዘጠኝ ቀናት ለቀረው ለ7ኛው ጠቅላላ ሀገራዊ ምርጫ የእንኳን አደረሳችሁ መልዕክት ያስተላለፉ ሲሆን፣ ብልጽግና ለተማሪው፣ ለነጋዴው፣ ለአርሶ አደሩና ለሁሉም የህብረተሰብ ክፍል ወሳኝ መሆኑን ጠቅሰው፤ ብልጽግና የሀብት ብቻ ሳይሆን የደስታም ምንጭ ነው ሲሉ ተናግረዋል።

"የብልጽግና መንግስት የመደመር እሳቤን የሰነቀ አቃፊ እንጂ ከፋፋይ አይደለም" ያሉት አቶ ማቴዎስ፤ ይህንን አንድነት ይበልጥ በማጠናከር የነገዋን ብሩህ ኢትዮጵያ ለመገንባት፣ ህዝቡ የቀረበለትን ዕድል በመጠቀም ብልጽግናን መምረጥ እንዳለበት አሳስበዋል።

የህዝብን የልማትና የመልካም አስተዳደር ጥያቄዎች በአግባቡ መመለስ የሚችለው የብልጽግና መንግስት መሆኑን የገለጹት ዋና አስተዳዳሪው፤ በቀጣይም በዞኑ የተጀመሩ የልማትና የለውጥ አጀንዳዎችን እውን ለማድረግ ህዝቡ ከፓርቲው ጎን በመሆን ድጋፉን አጠናክሮ እንዲቀጥል ጥሪ አቅርበዋል።

ባለፉት ዓመታት በዞኑ ከተከናወኑ ታላላቅ ተግባራት መካከል የህዝብን ሰላምና ደህንነት ማስጠበቅ ቀዳሚው መሆኑን የጠቀሱት አቶ ማቴዎስ አኒዮ፤ የዞኑን አስተማማኝ ሰላም ዘላቂ ለማድረግ ህዝቡ የብልጽግና ፓርቲን እንዲመርጥ ጠይቀዋል።

በተለያዩ ባህላዊና ፓለቲካዊ ክዋኔዎች ታጅቦ የዋለው የድጋፍ ሰልፍ መርሃ-ግብር፤ በኢትዮጵያ ብሔራዊ መዝሙር ፍጻሜውን አግኝቷል።

በህዝባዊ የድጋፍ ሰልፉ የሀዲያ ዞን ዋና አስተዳዳሪ አቶ ማቴዎስ አኒዮ፣ የሀዲያ ዞን ብልጽግና ፓርቲ ቅ/ጽ/ቤት ኃላፊ አቶ ታምራት ግዛውን ጨምሮ የኢፌዴሪ የህዝብ ተወካዮችና የክልል ምከር ቤት ዕጩ ተመራጮች፣ የዞን ከፍተኛ የስራ ኃላፊዎች፣ የክልልና የዞን ደጋፊ አመራሮች፣ የዱና ወረዳ የብልጽግና ፓርቲ አባላትና ደጋፊዎች ተሳትፈዋል።

ሀገራዊ ለውጡ እውን የሆነበትን 8ኛ ዓመትና ሰባተኛውን ሀገራዊ ጠቅላላ ምርጫ በማስመልከት በጃቾ ከተማ የብልጽግና ፓርቲ ደማቅ የምርጫ ቅስቀሳ የድጋፍ ሰልፍ እየተካሄደ ነው፤ ሆሳዕና፣ግንቦት ...
23/05/2026

ሀገራዊ ለውጡ እውን የሆነበትን 8ኛ ዓመትና ሰባተኛውን ሀገራዊ ጠቅላላ ምርጫ በማስመልከት በጃቾ ከተማ የብልጽግና ፓርቲ ደማቅ የምርጫ ቅስቀሳ የድጋፍ ሰልፍ እየተካሄደ ነው፤

ሆሳዕና፣ግንቦት 15/2018 "ኢትዮጵያን ወደ ተምሳሌት ሀገር!" - በሚል መሪ ሀሳብ በማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል ሀዲያ ዞን በምዕራብ ሶሮ ወረዳ ሀገራዊ ለውጡ እውን የሆነበትን 8ኛ ዓመት እና ሰባተኛውን ሀገራዊ ጠቅላላ ምርጫ በማስመልከት በጃቾ ከተማ የብልጽግና ፓርቲ ደማቅ የምርጫ ቅስቀሳ የድጋፍ ሰልፍ እየተካሄደ ነው።

በህዝባዊ የድጋፍ ሰልፉ የሀዲያ ዞን ዋና አስተዳዳሪ አቶ ማቴዎስ አኒዮ፣ የሀዲያ ዞን ብልጽግና ፓርቲ ቅ/ጽ/ቤት የፖለቲካና አቅም ግንባታ ዘርፍ ኃላፊ አቶ መሳይ ተስፋዮን ጨምሮ የኢፌዴሪ የህዝብ ተወካዮችና የክልል ምከር ቤት ዕጩ ተመራጮች፣ የዞን ከፍተኛ የስራ ኃላፊዎች፣ የክልልና የዞን ደጋፊ አመራሮች፣ የምዕራብ ሶሮ ወረዳ የብልጽግና ፓርቲ አባላትና ደጋፊዎች ተገኝተዋል።

ሀገራዊ ለውጡ እውን የሆነበትን 8ኛ ዓመትና ሰባተኛውን ሀገራዊ ጠቅላላ ምርጫ በማስመልከት በአንሾ ከተማ የብልጽግና ፓርቲ ደማቅ የምርጫ ቅስቀሳ የድጋፍ ሰልፍ እየተካሄደ ነው፤ ሆሳዕና፣ግንቦት...
23/05/2026

ሀገራዊ ለውጡ እውን የሆነበትን 8ኛ ዓመትና ሰባተኛውን ሀገራዊ ጠቅላላ ምርጫ በማስመልከት በአንሾ ከተማ የብልጽግና ፓርቲ ደማቅ የምርጫ ቅስቀሳ የድጋፍ ሰልፍ እየተካሄደ ነው፤

ሆሳዕና፣ግንቦት 15/2018 "ኢትዮጵያን ወደ ተምሳሌት ሀገር!" - በሚል መሪ ሀሳብ በማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል ሀዲያ ዞን በዱና ወረዳ ሀገራዊ ለውጡ እውን የሆነበትን 8ኛ ዓመት እና ሰባተኛውን ሀገራዊ ጠቅላላ ምርጫ በማስመልከት በአንሾ ከተማ የብልጽግና ፓርቲ ደማቅ የምርጫ ቅስቀሳ የድጋፍ ሰልፍ እየተካሄደ ነው።

በህዝባዊ የድጋፍ ሰልፉ የሀዲያ ዞን ዋና አስተዳዳሪ አቶ ማቴዎስ አኒዮ፣ የሀዲያ ዞን ብልጽግና ፓርቲ ቅ/ጽ/ቤት ኃላፊ አቶ ታምራት ግዛውን ጨምሮ የኢፌዴሪ የህዝብ ተወካዮችና የክልል ምከር ቤት ዕጩ ተመራጮች፣ የዞን ከፍተኛ የስራ ኃላፊዎች፣ የክልልና የዞን ደጋፊ አመራሮች፣ የዱና ወረዳ የብልጽግና ፓርቲ አባላትና ደጋፊዎች ተገኝተዋል።

23/05/2026

ኢትዮጵያን ወደ ተምሳሌት ሀገር!! በ Dolle'hee Dolle'hee.... ሙሉ ሀዲይሳ መዝሙር።

 እርስዎስ ግንቦት 24 ቀን 2018 ዓ.ም በድምፅዎ መሪዎን ለመምረጥ ተዘጋጅተዋል?
23/05/2026



እርስዎስ ግንቦት 24 ቀን 2018 ዓ.ም በድምፅዎ መሪዎን ለመምረጥ ተዘጋጅተዋል?

"ብልጽግና ፓርቲ በፈተናዎች ውስጥ ሆኖ ሰፋፊ ፕሮጀክቶችን ያጠናቀቀና አዳዲስ ግዙፍ ፕሮጀከቶችም ያስጀመረ ፓርቲ ነው"አቶ ታምራት ግዛው የሀዲያ ዞን ብልጽግና ፓርቲ ቅ/ጽ/ቤት ኃላፊ
22/05/2026

"ብልጽግና ፓርቲ በፈተናዎች ውስጥ ሆኖ ሰፋፊ ፕሮጀክቶችን ያጠናቀቀና አዳዲስ ግዙፍ ፕሮጀከቶችም ያስጀመረ ፓርቲ ነው"

አቶ ታምራት ግዛው
የሀዲያ ዞን ብልጽግና ፓርቲ ቅ/ጽ/ቤት ኃላፊ

Address

Central Ethiopia Region, Hadiya Zone
Hossana

Telephone

938488197

Website

Alerts

Be the first to know and let us send you an email when የሀዲያ ዞን ብልጽግና ፓርቲ ኮሚዩኒኬሽን posts news and promotions. Your email address will not be used for any other purpose, and you can unsubscribe at any time.

Share