የማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል ሰላምና ፀጥታ ቢሮ

  • Home
  • Ethiopia
  • Hossana
  • የማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል ሰላምና ፀጥታ ቢሮ

የማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል ሰላምና ፀጥታ ቢሮ ይህ የማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል መንግስት ሰላምና ፀጥታ ቢሮ ትክክለኛ የፌስቡክ ገፅ ነው ።

የ7ኛው ጠቅላላ ምርጫ ያለምንም የፀጥታ ችግር መጠናቀቁን የማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል ሰላም እና ፀጥታ ቢሮ ገለጸሆሳዕና 25/09/2018 (ሀድያ ቴሌቪዥን)የ7ኛው ጠቅላላ ምርጫ ያለምንም የፀጥ...
02/06/2026

የ7ኛው ጠቅላላ ምርጫ ያለምንም የፀጥታ ችግር መጠናቀቁን የማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል ሰላም እና ፀጥታ ቢሮ ገለጸ

ሆሳዕና 25/09/2018 (ሀድያ ቴሌቪዥን)

የ7ኛው ጠቅላላ ምርጫ ያለምንም የፀጥታ ችግር መጠናቀቁን የማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል ሰላም እና ፀጥታ ቢሮ ኃላፊ አቶ ተመስገን ካሳ ገለጹ።

ምርጫው መጠናቀቁን ተከትሎም ቢሮው መግለጫ ሰጥቷል።

ግንቦት 24 ቀን 2018 ዓ.ም ዜጎች በሀገረ-መንግስት ግንባታ ላይ ያላቸውን የላቀ ተሳትፎ ያሳዩበት ዕለት መሆኑን የጠቀሱት አቶ ተመስገን ካሳ፤ በማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል ከማለዳው 12:00 ሰዓት ጀምሮ የተካሄደው ድምፅ የመስጠት ሂደት ያለምንም የፀጥታ ችግር በሰላም መጠናቀቁን አስታውቀዋል።

ከምርጫው አስቀድሞ በክልሉ በሚገኙ ሁሉም አካባቢዎች የምርጫ ሂደቱ የተረጋጋ እና ሰላማዊ እንዲሆን የሚያስችሉ የቅድመ ዝግጅት ሥራዎች ሲከናወኑ መቆየታቸውን ኃላፊው በመግለጫቸው አንስተዋል።

በተመሳሳይ ሁኔታ ከምርጫ በኋላ (በድህረ-ምርጫ) ሊኖሩ ስለሚገባቸው የፀጥታ ሥራዎች ጭምር ዝግጅት ሲደረግ እንደነበር ገልጸዋል።

በምርጫው ወቅት ሊደረጉ ስለሚገቡ ጥንቃቄዎች ኅብረተሰቡን ከማስተማር ጀምሮ፣ በየአካባቢው ሰላምን ለማስከበር የተመደቡ የፀጥታ አካላት በአጠቃላይ ሂደቱ ላይ ምን ዓይነት ሚና ሊኖራቸው እንደሚገባ የሚያስገነዝብ ሥልጠና መሰጠቱንም አቶ ተመስገን ጠቁመዋል።

ግንቦት 24 ቀን በተደረገው የድምፅ አሰጣጥ ሂደት በክልሉ ሥር ባሉ የምርጫ ክልሎችና ጣቢያዎች የነበረው አጠቃላይ እንቅስቃሴ ሰላማዊና የኅብረተሰቡ ጉልህ ተሳትፎ የታየበት እንደነበር ተገልጿል።

በምሽቱ መርሃ ግብር የተከናወነው የድምፅ ቆጠራ ሂደትም ፍፁም ሰላማዊ እንደነበር የገለጹት ኃላፊው፤ በክልሉ በሚገኙ አንዳንድ የምርጫ ጣቢያዎች ግን እስከ ምሽቱ 4:00 ሰዓት ድረስ የድምፅ አሰጣጥ ሂደቱ ቀጥሎ እንደነበር አስረድተዋል።

በድምፅ አሰጣጥ ሂደት ወቅት የታየው የኅብረተሰቡ ከፍተኛ እገዛና ተሳትፎ፣ በቀጣይም የምርጫ ውጤት በሚገለጽበት ወቅት ተጠናክሮ ሊቀጥል ይገባል ብለዋል።

ኃላፊው በመጨረሻም፣ በቅድመ-ምርጫና በምርጫው ዕለት አጠቃላይ ሂደቱ በሰላማዊ መንገድ እንዲጠናቀቅ የበኩላቸውን አስተዋጽኦ ላበረከቱና ከተቋሙ ጋር ለተባበሩ አካላት በሙሉ ምስጋናቸውን አቅርበዋል።

ሀገሪቱ የጀመረችውን የልማት የዕድገት ስራዎችን ማስቀጠል እንዲቻል ምርጫ ወሳኝ በመሆኑ በክልሉ ያለውን ሰላም በማረጋገጥ ምርጫው በስኬት እንዲጠናቀቅ ሰላም ወዳድ የሆነው የክልሉ ህዝብና የጸጥ...
31/05/2026

ሀገሪቱ የጀመረችውን የልማት የዕድገት ስራዎችን ማስቀጠል እንዲቻል ምርጫ ወሳኝ በመሆኑ በክልሉ ያለውን ሰላም በማረጋገጥ ምርጫው በስኬት እንዲጠናቀቅ ሰላም ወዳድ የሆነው የክልሉ ህዝብና የጸጥታ ኃይሉ የተለመደውን ቅንጅታዊ ስራ አጠናክሮ እንዲያስቀጥል ተጠየቀ።

ሆሳዕና :- ግንቦት 23/2018 ዓ.ም የማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል መንግስት ፖሊስ ኮሚሽን 7ኛውን ጠቅላላ ምርጫ በማስመልከት በአጠቃላይ የፀጥታ ስራ ዙሪያ መግለጫ ሰጥቷል።

የማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል ኢትዮጵያ ክልል ፖሊስ ኮሚሽን ኮሚሽነር ም/ኮሚሽነር ሽመልስ ካሳ ለደቡብ ሬዲዮና ቴሌቪዥን ድርጅት በሰጡት መግለጫ ክልሉ በሰባት ዞኖችና በሶስት ልዩ ወረዳዎች የተደራጀ ሲሆን አዲስ ክልል እንደመሆኑ የምርጫ ሁነትን ሲያስተናገድ የመጀመሪያው መሆኑን ገልፀዋል።

በክልሉ ሰባተኛውን ጠቅላላ ምርጫ በማስመልከት በቅድመ ምርጫ ወቅት በርካታ የፀጥታ ስራዎች መሰራታቸውንም ገልጸዋል።

በየደረጃው የፀጥታ ግብረ ሃይል በማቋቋም እና ምርጫው ያለምንም የጸጥታ ስጋት በሰላማዊ ሁኔታ እንዲጠናቀቅ ስራዎች መሠራታቸውን ተናግረዋል።

በየአካባቢው ወንጀልን በመከላከልና አጥፊውን በማጋለጥ ሂደት ማህበረሰቡ ከፀጥታ አካላት ጎን መቆም እንዲችልና ምርጫው በሰላምና በስኬት እንዲካሄድ በሁሉም አካባቢዎች በጸጥታ ዙሪያ ሰፊ ውይይት መደረጉንም ም/ኮሚሽነሩ አብራርተዋል።

ከዚህ ጎን ለጎን አጥፊዎችን የመያዝና ከክልሉ ፍትህ ቢሮ ጋር በመሆን ወንጀልን በምርመራ የማጣራትና በህግ እንዲጠየቁ የማድረግ ስራ ሲሰራ መቆየቱንም በመግለጫቸው አክለዋል።

ይህ ሁሉ ስራ ሲሰራ መላው የፀጥታ ኃይል በጋራ እና በቅንጀት በመስራታቸው እንዲሁም አጠቃላይ የፀጥታ ስራዎችን የክልሉ ርዕሰ መስተዳደር በጋራ በመገምገም አቅጣጫ እየሰጡ በመሄዳቸው በቅድመ ምርጫ ወቅት በተሰሩ የጸጥታ ስራዎች በክልሉ የተሻለ ሰላም መኖሩንም አስረድተዋል።

በክልሉ ሰባተኛው ጠቅላላ ምርጫ የሚካሄድባቸው 35 ምርጫ ክልሎችና 2ሺ 9መቶ98 ምርጫ ጣቢያዎች መኖራቸውን የገለጹት ምክትል ኮሚሽነሩ በሁሉም ቦታዎች የጸጥታ ኃይል ተሰማርቶ ስራላይ መሆኑንም ገልጸዋል።

ከስምሪት በፊት በቂ የምርጫ ስነምግባር ስልጠና በመስጠት የጸጥታ ኃይሉ ነጻና ገለልተኛ ሆኖ እንዲሰራ መደረጉንም ም/ ኮሚሽነር ሽመልስ ካሳ ገልጸዋል።

ለስኬቱ የፌዴራል ፖሊስና የሃገር መከላከያ ሰራዊት ተገቢውን ድጋፍ እያደረጉ መቆየታቸውን ገልጸው ለዚህም ምስጋና አቅርበዋል።

ሀገር የጀመረችውን የልማት የዕድገትና የቴክኖሎጂ ስራዎች ህልውናዋ ተጠብቆ ማስቀጠል እንዲቻል ምርጫ ወሳኝ በመሆኑ በክልሉ ያለውን ሰላም በማስቀጠል ምርጫው በስኬት እንዲጠናቀቅ ሰላም ወዳድ የሆነው የክልሉ ህዝብና የጸጥታ ኃይሉ የተለመደውን ቅንጅታዊ ስራ አጠናክሮ እንዲያስቀጥልም ጥሪ አቅርበዋል።

እንዲሁም ተወዳዳሪ ፓርቲዎች ታዛቢዎች ምርጫ አስፈጻሚዎች እና በምርጫው ስራ ላይ የተሰማሩ ሁሉም አካላት የምርጫ ስነምግባር ደንብ በመከተል የምርጫ ስራውን በመስራት ለስኬት መስራት እንዳለባቸው አሳስበዋል።

ችግሮች ሲከሰቱም ወዲያው ለፀጥታ ኃይል ማሳወቅ እንደሚገባ ም/ኮሚሽነሩ አስገንዝበዋል።

7ኛው ጠቅላላ ምርጫ በስኬት እንዲጠናቀቅ የፀጥታና ደኅንነት የጋራ ግብረ ኃይል ተግባሩን አጠናክሮ ይቀጥላል - ፊልድ ማርሻል ብርሃኑ ጁላአዲስ አበባ፣ ግንቦት 22፣ 2018 (ኤፍ ኤም ሲ) የ...
30/05/2026

7ኛው ጠቅላላ ምርጫ በስኬት እንዲጠናቀቅ የፀጥታና ደኅንነት የጋራ ግብረ ኃይል ተግባሩን አጠናክሮ ይቀጥላል - ፊልድ ማርሻል ብርሃኑ ጁላ

አዲስ አበባ፣ ግንቦት 22፣ 2018 (ኤፍ ኤም ሲ) የኢፌዴሪ ጦር ኃይሎች ጠቅላይ ኤታማዦር ሹም ፊልድ ማርሻል ብርሃኑ ጁላ 7ኛው ጠቅላላ ምርጫ በስኬት እንዲጠናቀቅ የፀጥታና ደኅንነት የጋራ ግብረ ኃይል እያደረገ ያለውን ተግባር አጠናክሮ ይቀጥላል አሉ።

የኢትዮጵያ ፌደራል ፖሊስ 7ኛው ጠቅላላ ምርጫ በስኬት እንዲጠናቀቅ በሰው ኃይል፣ በትጥቅና በቴክኖሎጂ ያደረገውን ቅድመ ዝግጅት አስመልክቶ ለፀጥታና ደኅንነት የጋራ ግብረ ኃይል ማብራሪያ ሰጥቷል።

በዚሁ ወቅት ፊልድ ማርሻል ብርሃኑ ጁላ የፀጥታና ደኅንነት የጋራ ግብረ ኃይሉ ለምርጫው ያደረገው ዝግጅት እጅግ ጠንካራ መሆኑን ተናግረዋል።

ምርጫውን ለማደናቀፍ የሚንቀሳቀሱ ኃይሎች የተለያዩ ሙከራዎችን እያደረጉ ቢሆንም መከላከያ ሠራዊት ከሌሎች የፀጥታና ደኅንነት ኃይሎች እነዚህን የጥፋት ዕቅዶች ማክሸፉን አረጋግጠዋል።

አክለውም የኢትዮጵያ ፌዴራል ፖሊስ የዜጎችን ደህንነት ለመጠበቅና በተለይም 7ኛው ጠቅላላ ምርጫ ሰላማዊ ሆኖ እንዲጠናቀቅ ከፍተኛ ድርሻ እንዳለው አመልክተዋል።

የኢትዮጵያ ፌደራል ፖሊስ ጠቅላይ አዛዥ ኮሚሽነር ጀነራል ደመላሽ ገብረሚካኤል በበኩላቸው÷ የጋራ ግብረ ኃይሉ ከምርጫ ቦርድ ጋር መረጃዎችን በመለዋወጥና ከሕዝቡ ጋር በመተባበር እየሰራ ነው ብለዋል።

በዚህም በቅድመ ምርጫ የመራጮች ምዝገባ ሂደት፣ የምርጫ አስፈጻሚዎች እና የምርጫ ቁሳቁስ ስርጭት ደህንነት በተሳካ ሁኔታ መከናወኑን አንስተዋል።

FBC

የምርጫውን ሂደት ሠላማዊ ለማድረግ የተጀመረው ጥረት ተጠናክሮ መቀጠል ይኖርበታል _ ርዕሰ መስተዳድር እንዳሻው ጣሰው (ዶ/ር ) ሆሳዕና ፣ ግንቦት 17 ፣ 2018፦የማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል ...
25/05/2026

የምርጫውን ሂደት ሠላማዊ ለማድረግ የተጀመረው ጥረት ተጠናክሮ መቀጠል ይኖርበታል _ ርዕሰ መስተዳድር እንዳሻው ጣሰው (ዶ/ር )
ሆሳዕና ፣ ግንቦት 17 ፣ 2018፦የማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል ርዕሰ መስተዳድር እንዳሻው ጣሰው (ዶ/ር ) በተገኙበት ሰባተኛውን ጠቅላላ ሀገራዊ የምርጫ ሂደት ሠላማዊ በማድረግ ላይ ያተኮረ ውይይት ዛሬ በሆሳዕና ከተማ ተካሂዷል ።
በመድረኩ ፣የምርጫውን ሂደት ሠላማዊ ከማድረግ አኳያ የእሰከ አሁኑን አዝማሚያ የሚያመላክት አጭር ሪፖርት ቀርቦ ዉይይት ተካሂዷል፤ ቀጣይ ትኩረቶችም ተመላክተዋል።

ርዕሰ መስተዳድር እንዳሻው ጣሰው (ዶ/ር ) በመድረኩ እንደገለፁት ፣የቅድመ _ምርጫ፣ የምርጫና የድህረ_ ምረጫውን ሂደት ሠላማዊ ለማድረግ የተጀመረው ጥረት ተጠናክሮ ይቀጥላል።
የምርጫ ሂደት ሠላማዊና ደህንነቱ የተጠበቀ ሆኖ እንዲቀጥል ፣ ከምርጫ ጣቢያ ጀምሮ በተደራጀና በተናበበ መንገድ በትኩረት ሊሠራ እንደሚገባ ርዕሰ መስተዳድሩ አሳስበዋል ።
በውይይት መድረኩ፣ የየአካባቢውን ወቅታዊ የሠላምና ፀጥታ አዝማሚያዎች የዳሰሰ ዉይይት ከመደረጉ ባሻገር፣ በቀጣይ አቅጣጫዎች ላይ መግባባት በመፍጠር ተጠናቅቋል ።

በዉይይት መድረኩ፣ብርጌደር ጄኔራል ተመስገን መሎሬ:- በመከላከያ ሚኒስቴር የሰው ሀብት ዋና መምሪያ መረጃና ማስረጃ መምሪያ ሀላፊና የክልሉ ጸጥታ ግብረ ሀይል ሰብሳቢ ፣ አቶ ተመስገን ካሳ የክልሉ ሠላምና ፀጥታ ቢሮ ሀላፊ፣ የከልል፣የዞኖች እና የልዩ ወረዳዎች ሠላምና ፀጥታ መዋቅር አመራሮች ፣የክልሉ ፖሊስ ኮሚሽን አመራሮች፣ የዞኖችና ልዩ ወረዳዎች ፖሊስ አዛዦች ፣ የክልል፣ የዞኖች እና የልዩ ወረዳዎች የሚልሻ ጽህፈት ቤቶች አመራሮች ተገኝተዋል።

የማዕከላዊ ክልል ሰላምና ፀጥታ ቢሮ 7ኛው ሀገራዊ ምርጫ በክልሉ ፍጹም ሰላማዊ፣ ፍትሃዊ እና ዴሞክራሲያዊ በሆነ መንገድ እንዲካሄድ ከተለያዩ ባለድርሻ አካላት ጋር ሰፊና ገንቢ ውይይት አካሂዷ...
21/05/2026

የማዕከላዊ ክልል ሰላምና ፀጥታ ቢሮ 7ኛው ሀገራዊ ምርጫ በክልሉ ፍጹም ሰላማዊ፣ ፍትሃዊ እና ዴሞክራሲያዊ በሆነ መንገድ እንዲካሄድ ከተለያዩ ባለድርሻ አካላት ጋር ሰፊና ገንቢ ውይይት አካሂዷል።

በውይይቱ ላይ የፀጥታ አካላት፣ የህዝብ ተወካዮች፣ የሃይማኖት አባቶች፣ ወጣቶች፣ ሴቶች እና ሌሎች ተቋማት በመሳተፍ የምርጫውን ሰላማዊነት ለማረጋገጥ የሁሉም አካላት የጋራ ሀላፊነት መሆኑ ተጠናክሮ ተገልጿል።

በመድረኩም የክልሉ ፀጥታ ቢሮ ኃላፊ አቶ ተመስገን ካሳ ባስተላለፉት መልዕክት፤ “ሰላም የልማት መሰረት ነው፤ ምርጫው የህዝብ ድምፅ የሚከበርበት ዴሞክራሲያዊ ሂደት በመሆኑ ሁሉም አካላት በጥንቃቄ፣ በአንድነት እና በኃላፊነት ሊሳተፉ ይገባል” ብለዋል።

አቶ ተመስገን አክለውም በክልሉ የሚኖረውን ሰላምና መረጋጋት ለማስቀጠል የፀጥታ አካላት ከህዝቡ ጋር በቅንጅት እየሰሩ መሆናቸውን ገልጸው፣ ህዝቡም ከሀሰተኛ መረጃዎች በመራቅ ለሀገራዊ አንድነትና ሰላም አጋርነቱን እንዲያጠናክር ጥሪ አቅርበዋል።

“ሰላማዊ ምርጫ የጠንካራ ዴሞክራሲ መሰረት ነው!”
“አንድነታችን ለሀገራችን ዋስትና ነው!”

ሰባተኛው ሀገራዊ ምርጫ ያለ ምንም የጸጥታ ስጋት ሰላማዊ ሆኖ እንዲጠናቀቅ በቅንጅት እየተሰራ መሆኑን የክልሉ ሰላምና ጸጥታ ቢሮ አስታወቀ ።(ሆሳዕና፣ ግንቦት 12/ 2018)፣ሰባተኛው ሀገራዊ...
20/05/2026

ሰባተኛው ሀገራዊ ምርጫ ያለ ምንም የጸጥታ ስጋት ሰላማዊ ሆኖ እንዲጠናቀቅ በቅንጅት እየተሰራ መሆኑን የክልሉ ሰላምና ጸጥታ ቢሮ አስታወቀ ።

(ሆሳዕና፣ ግንቦት 12/ 2018)፣

ሰባተኛው ሀገራዊ ምርጫ ያለ ምንም የጸጥታ ስጋት ሰላማዊ ሆኖ እንዲጠናቀቅ በቅንጅት እየተሰራ መሆኑን የማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል ሰላምና ጸጥታ ቢሮ አስታውቋል ።

ቢሮው በመጪው ግንቦት 24/2018 በሚካሄደው ሰባተኛው ሀገራዊ ጠቅላላ ምርጫ የጸጥታ መዋቅሮች ዝግጅት ዙሪያ በሆሳዕና ከተማ ውይይት አካሂዷል።

የቢሮው ሃላፊ አቶ ተመስገን ካሳ በዚሁ ወቅት እንዳሉት መራጩ ህዝብ ያለ ስጋት ሰላማዊ በሆነ መንገድ ምርጫውን ማካሄድ እንዲችል መዋቅሩ ምቹ ሁኔታ መፍጠር ይጠበቅበታል።

ለዚህ ደግሞ የጸጥታ መዋቅሩ ገለልተኛ ሆኖ ሰላምን ማስፈን እንደሚጠበቅበት ገልጸዋል ።

በቀሩት ቀናት ቀሪ የቅድመ ምርጫ ሂደቶች፣ የድምፅ መስጫ እለት እና የድህረ ምርጫ ሂደቶች ሰላማዊ በሆነ መልኩ እንዲጠናቀቁ ሰፊ ቅንጅታዊ ዝግጅቶች እየተደረጉ ይገኛሉ ብለዋል።

በተለይም ደግሞ በድምፅ መስጫ እለት ህገ ወጥ ድርጊቶች እንዳይፈጸሙና ዜጎች ዴሞክራሲያዊ መብቶቻቸውን ያለ ስጋት እንዲተገብሩ ማድረግ ያስፈልጋል ብለዋል።

20/05/2026
የክልሉ ሰላምና ጸጥታ ቢሮ ወቅታዊ የክልሉ የጸጥታ ሁኔታን እየገመገመ ነው። የማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል ሰላምና ጸጥታ ቢሮ ወቅታዊ የክልሉ የጸጥታ ሁኔታን እየገመገመ ነው። ቢሮው ከዞንና ልዩ ...
20/05/2026

የክልሉ ሰላምና ጸጥታ ቢሮ ወቅታዊ የክልሉ የጸጥታ ሁኔታን እየገመገመ ነው።

የማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል ሰላምና ጸጥታ ቢሮ ወቅታዊ የክልሉ የጸጥታ ሁኔታን እየገመገመ ነው።

ቢሮው ከዞንና ልዩ ወረዳ መዋቅሮች ጋር ወቅታዊ የክልሉን የጸጥታ ሁኔታ በሆሳዕና ከተማ እየገመገመ ይገኛል።

በመድረኩ ወቅታዊ የጸጥታ ሁኔታዎችና የመዋቅሩ የዘጠኝ ወራት እቅድ አፈጻጸም እንደሚገመገም ተጠቁሟል።

ሠላምን በማፅናት የዜጎችን ደህንነት ለማረጋገጥ ግጭትን አስቀድሞ መከላከል የሚያስችል ጠንካራ ተቋም መገንባት እንደሚገባ ተመላከተ(ሆሳዕና፣ ግንቦት 10/2018) ፣ የማዕካላዊ ኢትዮጵያ ክልል...
18/05/2026

ሠላምን በማፅናት የዜጎችን ደህንነት ለማረጋገጥ ግጭትን አስቀድሞ መከላከል የሚያስችል ጠንካራ ተቋም መገንባት እንደሚገባ ተመላከተ

(ሆሳዕና፣ ግንቦት 10/2018) ፣ የማዕካላዊ ኢትዮጵያ ክልል ሰላምና ፀጥታ ቢሮ የእቅድ አፈፃፀምና ወቅታዊ የፀጥታ ሁኔታን ከተጠሪ ተቋማት ጋር በሆሳዕና ከተማ ገምግሟል።

የቢሮ ሀላፊ ተወካይና የፀጥታ መረጃ ዘርፍ ሀላፊ አቶ መስቀሉ መንጃ እንደተናገሩት ቢሮው ሠላምን በማፅናት የዜጎችን ደህንነት ለማረጋገጥ ግጭትን አስቀድሞ መከላከል የሚያስችል ጠንካራ ተቋም ለመገንባት በቅንጅት እየተሰራ ነው ብለዋል።

እንደሀገርና ክልል የተለያዩ በርካታ ፍላጎቶች የሚስተዋልበት ወቅት በመሆኑ የፀጥታ መዋቅሩን አደረጃጀት በማጠናከር ሠላምን ዋነኛ አማራጭ በማድረግ በልዩ ትኩረት እየተሰራ መሆኑን ተናግረዋል።

የተቋሙም ሆነ የተጠሪ ተቋማት ተልዕኮ ዘላቂ ሠላም ማረጋገጥ እና የህዝቦችን ደህንነት ማረጋገጥ መሆኑን የተናገሩት አቶ መስቀሉ የሚፈጠሩ አለመግባባቶች የመከላከልና ሲከሰቱ የመቆጣጠር ስራ ተጠናክሮ እየተሰራ ነው ብለዋል።

የፀጥታ ስራው ህዝባዊ መሠረት እንዲያገኝ በማድረግ በሠላም እሴት ግንባታና በግጭት አፈታት ከሀገር ሽማግሌዎች፣ከወጣቶች ፣ከሴቶች እና ከተለያዩ አደረጃጀት ጋር በቅንጅት በተሰራው ስራም ተጨባጭ ውጤት መጥቷል ብለዋል።

ግጭት ሳይፈጠር አስቀድሞ ለመከላከል የመረጃ ስርዓትን በማጠናከርና ለግጭት ተጋላጭ የሆኑ አካባቢዎች በመለየት እየተሰራ መሆኑን አመላክተው ይህን የሚሸረሽሩ በፀረ ሠላም ሀይሎችና በጽንፈኛ የማህበራዊ ሚዲያ የሚለቀቁ መረጃዎች ምንጭ እንዲሁም ተዓማኒነት በመለየት መመከት ከማህበረሰቡ ይጠበቃል ብለዋል።

ሠላምን በአንድ አካል ብቻ ማረጋገጥ ስለማይቻል ከህብረተሰቡ ፣ከየአካባቢው የፀጥታ አካላትና ከአጎራባች ክልሎች ጋር ጠንካራ ግንኙነት በመፍጠር ሰፊ ስራዎች መሰራታቸውን ተናግረዋል።

የማዕካላዊ ኢትዮጵያ ክልል ሰላምና ፀጥታ ቢሮ ሀላፊ አማካሪ አቶ ሸረፋ ሌገሶ በበኩላቸው ሠላም የሁሉም ድምር ውጤት በመሆኑ ቅንጅታዊ አሰራር በማጠናከር መስራት ተገቢ መሆኑን አንስተዋል።

በህዝቦች መካከል ያለውን የአብሮነት እሴቶችን በማጠናከር የክልሉን ሰላም በዘላቂነት ማጽናት እንደሚገባ ተናግረው ከማህበረሰቡ ጋር በሠላም ጉዳይ መድረኮች በመፍጠር ግንዛቤ የመስጠት ስራው ተጠናክሮ የሚሰራ ነው ብለዋል።

ሰባተኛው ጠቅላላ ሀገራዊ ምርጫው ሠላማዊ ዲሞክራሲያዊ ሆኖ ሂደቱ ያለምንም የፀጥታ ስጋት እንዲከናወን ልዩ ትኩረት ተሰጥቶ እየተሰራ መሆኑንም ተናግረዋል።

በግምገማው መድረክ የክልሉ ፖሊስ ኮሚሽን ኮሚሽነር ሽመልስ ካሳን ጨምሮ የሠላምና ፀጥታ ቢሮ፣የፖሊስ፣የሚሊሻ እና የወሳኝ ኩነቶች ምዝገባ ኤጀንሲ ከፍተኛ የስራ ሀላፊዎችና ባለሞያዎች እንዲሁም ባለድርሻ አካላት ተሳትፈዋል።

የማዕካላዊ ኢትዮጵያ ክልል ሰላምና ፀጥታ ቢሮ የዕቅድ አፈፃፀምና ወቅታዊ የፀጥታ ሁኔታን ከተጠሪ ተቋማት ጋር እየገመገመ ነው።ሆሳዕና፣ ግንቦት 10/2018የማዕካላዊ ኢትዮጵያ ክልል ሰላምና ፀ...
18/05/2026

የማዕካላዊ ኢትዮጵያ ክልል ሰላምና ፀጥታ ቢሮ የዕቅድ አፈፃፀምና ወቅታዊ የፀጥታ ሁኔታን ከተጠሪ ተቋማት ጋር እየገመገመ ነው።

ሆሳዕና፣ ግንቦት 10/2018

የማዕካላዊ ኢትዮጵያ ክልል ሰላምና ፀጥታ ቢሮ የ2018 በጀት አመት የዘጠኝ ወር ዕቅድ አፈፃፀምና ወቅታዊ የፀጥታ ሁኔታን ከተጠሪ ተቋማት ጋር በሆሳዕና ከተማ እየገመገመ ይገኛል።

በመድረኩ የቢሮዉ ዋና ዋና ዘርፎች እና የተጠሪ ተቋማት የፖሊስ ፣ የሚሊሻ እና የወሳኝኝ ኩነት የዘጠኝ ወር ዕቅድ አፈፃፀም በዝርዝር ቀርቦ ውይይት በማድረግ የጋራ አቋም የሚያዝበትና የቀጣይ አቅጣጫ የሚቀመጥበት እንደሚሆን ይጠበቃል።

Address

Hossana

Alerts

Be the first to know and let us send you an email when የማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል ሰላምና ፀጥታ ቢሮ posts news and promotions. Your email address will not be used for any other purpose, and you can unsubscribe at any time.

Share