Habtamu Erkibo Abate

Habtamu Erkibo Abate Contact information, map and directions, contact form, opening hours, services, ratings, photos, videos and announcements from Habtamu Erkibo Abate, Public & Government Service, Hossana.

02/01/2024

የኢትዮጵያ ስብራት ጥገና ቀን!

የኢትዮጵያ ሰብአዊ መብቶች ኮሚሽን በማዕከላዊ ኢትዮጵያ እና ደቡብ ኢትዮጵያን ጨምሮ በተለይም አዲሱ የክልል አደረጃጀት ተከትሎ የተለያዩ አስተዳደሮች እና መዋቅሮች መልሶ መቋቋም ወይም ተያያዥ...
23/12/2023

የኢትዮጵያ ሰብአዊ መብቶች ኮሚሽን በማዕከላዊ ኢትዮጵያ እና ደቡብ ኢትዮጵያን ጨምሮ በተለይም አዲሱ የክልል አደረጃጀት ተከትሎ የተለያዩ አስተዳደሮች እና መዋቅሮች መልሶ መቋቋም ወይም ተያያዥ ውሳኔዎች ሂደት ጋር የሚነሱ የደመወዝ መዘግየት እና ያለመከፈል የተመለከቱ አቤቱታዎችን፣ እንዲሁም ጥቆማዎችን መነሻ በማድረግ የሰብአዊ መብቶች ክትትል ሲያደርግ ቆይቷል።

ይህ በተመለከት ከላይ የተያያዘውን መግለጫ ልኮልናል።

ገራድ ሃንሳሪ ሁንድ አድል  ፕሮፌሰር በየነ ጴጥሮስ
23/11/2023

ገራድ ሃንሳሪ ሁንድ አድል ፕሮፌሰር በየነ ጴጥሮስ

የኢትዮጵያ የባህር በር የጋራ ተጠቃሚነት ጥያቄ አማራጭ ሳይሆን የህልውና ጉዳይ ነው - ፕ/ር በየነ ጴጥሮስ

አዲስ አበባ፣ ሕዳር 8፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) የኢትዮጵያ የባህር በር የጋራ ተጠቃሚነት ጥያቄ አማራጭ ሳይሆን የህልውና ጉዳይ ነው ሲሉ አንጋፋው ፖለቲከኛ ፕሮፌሰር በየነ ጴጥሮስ ገለጹ።

በአሁኑ ወቅት የኢትዮጵያ ፖሊሲ ጥናት ኢንስቲትዩት ዋና ዳይሬክተር በመሆን እያገለገሉ የሚገኙት ፕሮፌሰር በየነ ጴጥሮስ የኢትዮጵያን የባህር በር ጥያቄ አስመልክቶ ከፋና ብሮድካስቲንግ ጋር ቆይታ አድርገዋል።

የኤርትራ ነጻነት ከመታወጁ በፊት በተካሄደው የቻርተር ጉባኤ ላይ መሳተፋቸውን ያስታወሱት ፕ/ር በየነ፤ በወቅቱ የኢትዮጵያ የባህር በር ባለቤትነት ጉዳይ ጥያቄ ሲነሳበት እንደነበር ጠቅሰዋል።

ኤርትራ በሪፈረንደም ነጻ ስለመውጣት ወስናለች ተብሎ በቻርተር ጉባኤ አቅጣጫ ሲቀመጥ የባህር በሩስ እንዴት ነው ስምምነት ላይ የሚደረሰው የሚል ጥያቄ በወቅቱ ተነስቶ ነበር ብለዋል።

ለተነሳው ጥያቄ ከኤርትራ ፖለቲካ መሪዎች ጋር ስምምነት ላይ ደርሰናል የሚል ምላሽ ተሰጥቶበት እንደነበር አስታውሰዋል።

በወቅቱ ታዲያ በሁለቱ ሀገራት ህዝቦች መካከል የባህር በር የጋራ ተጠቃሚነትን ከማረጋገጥ አኳያ ስጋቶችና የሚነሱ ጥያቄዎች ነበሩ ብለዋል ፕሮፌሰር በየነ።

ለዘመናት የኢትዮጵያ መሆኑ የሚታወቀው የባህር በር ከኢትዮጵያ እጅ ወጣ ማለት የህዝባችንን ጉሮሮ የሚያንቅ ነው፤ ስለዚህ ይህንን ነገር መፍቀድ ማለት በታሪክ ያስጠይቀናል እስከማለት ተደርሷል ሲሉ ገልጸዋል።

በፖለቲካ መሪዎቹ ዘንድ ወደቦቹን በጋራ እንጠቀማለን የሚል ቃል ከመገባቱ ባለፈ በጽሁፍ የተገባ ውል ስለመኖሩም ተጠይቆ እንደነበር አንስተዋል።

ያ ሁሉ ሆኖ በጊዜ ሂደት የሁለት ወደብ ባለቤት የነበረችው ኢትዮጵያ ከወደብ ተጠቃሚነት ተነፍጋ ቆይታለች።

በመሆኑም የባህር በር ጥያቄው መነሳቱ ተገቢነት ያለው ነው ያሉት ፕ/ር በየነ፤ የጋራ ተጠቃሚነት ጥያቄው አማራጭ ሳይሆን የህልውና ጉዳይ ነው በማለት አስገንዝበዋል።

ኢትዮጵያ የባህር በር ጥያቄውን መቼም ቢሆን መጠየቅ አለባት፤ መደራደር እፈልጋለሁ ማለት አለባት ሲሉም ገልጸዋል።

ጥያቄው ውጤት እንዲያመጣ መንግስት ከሚያደርገው ጥረት ባሻገር ምሁራንን ጨምሮ የሚመለከታቸውን ለውይይት መጋበዝ እንደሚያስፈልግ አስረድተዋል።

የጉዳዮችን ምክንያታዊነት በግልጽ በማስቀመጥ የጎረቤት ሀገራትን ምሁራንና ህዝብን ያሳተፈ ስራ በመስራት ማሳመን እንደሚገባ ጠቁመዋል።

በሳሙኤል ወርቅአየሁ

ቤተሰብ ተጨንቋል አባካቹ ሼር በማድረግ ተባበሩ።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።ወጣት ፈዲላ ወራቄ ሎብጊቾ የተባለች ግለሰብ ከ2012 ጀምሮ ለስራ ጉዳይ ከማረቆ ልዩ ወረዳ...
23/11/2023

ቤተሰብ ተጨንቋል አባካቹ ሼር በማድረግ ተባበሩ
።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።
ወጣት ፈዲላ ወራቄ ሎብጊቾ የተባለች ግለሰብ
ከ2012 ጀምሮ ለስራ ጉዳይ ከማረቆ ልዩ ወረዳ
ከኡዳሳ ቀበሌ ወደ አ/አበባ ብላ እንደወጣች አልተመለሰችም።

ወጣት ፈዲላ መልኳ ጠይም ዕድሜዋ 22 እንደሆነ የተናገሩት ቤተሰቦቿ እስከ ቅርብ ጊዜ ስልክ እየደወለች እንደነበረ እና ከዚህ ቀደም ከነበረችበት ቤት ወጥታ የት እንዳለች አናውቅም ድምጿንም ከሰማን ከሶስት ወር በላይ ሆኗል በማለት በጣም ጭንቅ ውስጥ እንደሆኑ በመናገር እባካቹን ልጃችንን አፋልጉን እያሉ ይማፀናሉ።

#ሼር በማድረግ መረጃውን ተደራሽ እናድርግ

አቶ ወራቄ ሎብጊች የወጣት ፈዲላ ወላጅ አባት

Address

Hossana
36447096275333

Alerts

Be the first to know and let us send you an email when Habtamu Erkibo Abate posts news and promotions. Your email address will not be used for any other purpose, and you can unsubscribe at any time.

Contact The Organization

Send a message to Habtamu Erkibo Abate:

Share