Central Ethiopia Region - Prosperity Party - ብልፅግና

  • Home
  • Central Ethiopia Region - Prosperity Party - ብልፅግና

Central Ethiopia Region - Prosperity Party - ብልፅግና This is the official Central ER Prosperity Party page where you can get all the latest info.
(10)

Detail contact information
phone number :+251939060376
E-mail:[email protected]

01/06/2026

የኢትዮጵያ ሕዝብ አስደናቂም ተአምረኛም ሕዝብ ነው። ከፈጣሪ በቀር ሕዝባችንን አሟልቶ ሊያውቅና ሊገመግም የሚችል ማን ነው? የዳበረ ባህል፣ ሀገር ወዳድና የወል መሻቱን መጠበቅ የሚችል ሕዝብ መሆኑን በዘንድሮው ምርጫ ዳግም ለዓለም አሳይቷል። በዛሬው ታሪካዊ ዕለት፡-

• የሌሊቱ ብርድና ጨለማ ያላስፈራቸው፣
• የቀትሩ ፀሐይና ድንገተኛ ዝናብ ያልበገራቸው
• ሠርግ፣ ኀዘን፣ ወሊድና ሌሎች ማኅበራዊ ሁነቶች ያላገዳቸው፣
• ረጃጅም ሰልፎች ያላታከታቸው፣
• የአካል ጉዳት ድምጽ ለመስጠት ያልገደባቸው፣
• ሕመም እና እርጅና የሀገር ተስፋን ከማየት ያላገዳቸው፣
• የነገ ሀገር ተረካቢ ጨቅላ ልጃቸውን ማዘል ያላደከማቸው፣
• ከምንም በላይ የጠላት ጩኸትና ማስፈራሪያ ያላስቆማቸው ዜጎች፤

በብዙ ውጣ ውረዶች መካከል (against all odds) ያሳያችሁት ጽናት ለዴሞክራሲና ለሀገር ሕልውና የተከፈለ ነውና ከልብ የመነጨ ምስጋና ይገባቸዋል፡፡

ይሄንን ሕዝብ ማገልገል መታደል ነውና ተመራጮች ያከበራችሁን አክብራችሁ ለዴሞክራሲ ሥርዓት ዋጋ የከፈለውን ይሄንን ሕዝብ በንጽሕና ለማገልገል ያብቃችሁ።

Uummanni Itoophiyaa dinqisiisaafi ajaa'ibsiisaadha! Uumaa malee uummata keenya guutummaan beekuufi gamaaggamuu kan danda'u eenyu? Aadaa gabbataa, uummata biyya jaallatuufi fedhiisaa waloo eeguu danda'u ta'uusaa filannoo baranaatiin irradeebiidhaan addunyaatti agarsiiseera. Guyyaa seena-qabeessa har'aatiin:
- Qorriifi dukkanni halkani kan isaani hin sodaachifne,
- Aduun saafaafi bokkaan tasaa kan isaan jilbeenfachiifne,
- Cidhi, gaddi, da'umsiifi taateewwan hawaasummaa kanbiroon kan isaan dhorkine,
- Hiriironni dhedheeroon kan isaan hin nuffisiifne,
- Qaama miidhamtummaan sagalee kennuuf kan isaan hin daangessine,
- Dhukkubniifi dullumni abdii biyyaa arguuf kan isaan hin dhowwine,
- Daa'imasaanii kichuu bor biyya dhaalu baatanii filuun kan isaan hin dadhabsiifne
- Hundumaa caalaa lammiilee iyyiifi sodaachiifni diinaa isaan hin dhaabsifne,
Ciminni bu'aa bayii hedduu keessatti agarsiiftan gatii diimokraasiifi jiraachuu biyyatiif kanfalame waan ta'eef galata guddaatu malaafi.

Uummata kana tajaajiluun carroomuu waan ta'eef filatamtoonni warra isin kabajan kabajjanii uummata sirna diimookraasiif gatii baase kana qulqullummadhaan tajaajiluuf isin haa gahu.

The people of Ethiopia are an extraordinary and remarkable people. Other than the Creator, who can truly know and assess our people in their entirety? Through this year’s election, Ethiopians have once again shown the world that they are a people with a rich culture, deep patriotism, and the ability to safeguard the common good.

On this historic day:

* Citizens who were not intimidated by the cold and darkness of the night,
* Who were not deterred by the midday sun or sudden rain,
* Whom weddings, funerals, childbirth, and other social obligations did not prevent from participating,
* Who were not wearied by long lines,
* Whose physical disabilities did not stop them from casting their vote,
* Those whose illness and old age did not prevent from witnessing the hope of their country,
* Who were not exhausted by carrying their infant children; the future inheritors of the nation,
* And above all, whom the shouting and threats of enemies could not intimidate or stop;

The perseverance you demonstrated amid many challenges and hardships, against all odds, was a contribution made for democracy and for the very survival of the nation. For this, you deserve heartfelt gratitude.

It is a privilege to serve such a people. Therefore, may those who have been elected honor the trust placed in them and serve this people, with integrity and sincerity! A people who have paid a great price for the democratic system. May you be worthy of that responsibility.

በሆሳዕና ከተማ የመራጮች የምሽት ድምጽ አሰጣጥ ሂደት (በምስል)፦
01/06/2026

በሆሳዕና ከተማ የመራጮች የምሽት ድምጽ አሰጣጥ ሂደት (በምስል)፦

01/06/2026

እዉነትም ኢትዮጵያ 🇪🇹 እየመረጠች ነው!

ከአካል ጉዳተኛ እስከ ሀገር መሪ ሁሉንም እኩል ያሳተፈዉ ምርጫ

7ኛው ጠቅላላ ምርጫ አገራችን ዲሞክራሲያዊ ሥርዓትን ለማፅናትና ሕዝባዊ ሉዓላዊነትን ለማረጋገጥ የምታደርገውን ጉዞ በግልጽ ያሳየ ታሪካዊ ምዕራፍ ነው!

ምሽቱን የቀጠለው የድምፅ አሰጣጥ ሂደት ፦
01/06/2026

ምሽቱን የቀጠለው የድምፅ አሰጣጥ ሂደት ፦

የድምፅ መስጠት ሂደት እስከ ምሽት 6:00 ድረስ ተራዝሟል፡- የኢትዮጵያ ብሔራዊ ምርጫ ቦርድኢትዮጵያ እየመረጠች ነው!
01/06/2026

የድምፅ መስጠት ሂደት እስከ ምሽት 6:00 ድረስ ተራዝሟል፡- የኢትዮጵያ ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ

ኢትዮጵያ እየመረጠች ነው!

የኢትዮጵያ ሰብዓዊ መብቶች ኮሚሽን (ኢሰመኮ) በ7ኛው ጠቅላላ ምርጫ አጠቃላይ ሂደት ላይ የሰብዓዊ መብት ጥሰት እንደሌለ ገለጸ፡፡የኢትዮጵያ ሰብዓዊ መብቶች ኮሚሽን (ኢሰመኮ) በ7ኛው ጠቅላላ ...
01/06/2026

የኢትዮጵያ ሰብዓዊ መብቶች ኮሚሽን (ኢሰመኮ) በ7ኛው ጠቅላላ ምርጫ አጠቃላይ ሂደት ላይ የሰብዓዊ መብት ጥሰት እንደሌለ ገለጸ፡፡

የኢትዮጵያ ሰብዓዊ መብቶች ኮሚሽን (ኢሰመኮ) በ7ኛው ጠቅላላ ምርጫ አጠቃላይ ሂደት ላይ ባደረገው ሰፊ ምልከታ፣ እስካሁን ባለው ሂደት ምንም ዓይነት ያልተገባ የሰብዓዊ መብት አያያዝ እንዳልተመለከተ አስታወቀ።

የኮሚሽኑ ዋና ኮሚሽነር ብርሃኑ አዴሎ የተመራ የከፍተኛ የሥራ ኃላፊዎች ቡድን በአርባ ምንጭ እና በጅማ ከተሞች የሚገኙ የምርጫ ጣቢያዎችን በአካል ተገኝቶ በመዘዋወር የድምፅ አሰጣጥ ሂደቱን በቅርበት ታዝቧል።

ዋና ኮሚሽነሩ በምልከታቸው ወቅት እንዳረጋገጡት፤ የምርጫ ጣቢያዎች ለአካል ጉዳተኞች ጭምር ምቹ ተደርገው የተዘጋጁ ከመሆናቸውም በላይ፣ አጠቃላይ ሂደቱ ሙሉ በሙሉ የምርጫ መስፈርቶችን ያሟላ መሆኑን መታዘብ እንደቻሉ አረጋግጠዋል። ሂደቱ ፍጹም ሰላማዊና ምንም ዓይነት መስተጓጉል ያልታየበት መሆኑንም ገልጸዋል።

ኢሰመኮ በአሁኑ ወቅት በአገር አቀፍ ደረጃ በ175 የምርጫ ክልሎችና ከ2 ሺህ 700 በላይ በሚሆኑ የምርጫ ጣቢያዎች ላይ ታዛቢዎቹን በስፋት በማሰማራት የክትትል ሥራ እያከናወነ ይገኛል። ከዚህም በተጨማሪ፣ በምርጫ ሂደቱ ላይ ሊነሱ የሚችሉ ቅሬታዎችን በወቅቱ ለማስተናገድ የተዘረጋውን የቅሬታ መከታተያ ሥርዓት በመጠቀም ሂደቱን በንቃት እየተከታተለ መሆኑ ተብራርቷል።

ኮሚሽኑ በምርጫው ወቅት ያለውን የሰብዓዊ መብት ሁኔታ ከመታዘብ ባለፈ፣ በድህረ-ምርጫ የሚኖረውንም ሂደት በአግባቡ በመምራትና በመከታተል ሥራውን አጠናክሮ እንደሚቀጥል አረጋግጧል።

01/06/2026

በማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል በድምጽ አሰጣጥ ሂደቱ የመራጮች አስተያየት ፣

የኢትዮጵያ 7ኛው ጠቅላላ ምርጫ በሰላም እና በተዓማኒነት እየተካሄደ ነው፡- ኡሁሩ ኬንያታ የአፍሪካ ኅብረት የምርጫ ታዛቢ ቡድን መሪ እና የቀድሞው የኬንያ ፕሬዝዳንት ኡሁሩ ኬንያታ በኢትዮጵያ...
01/06/2026

የኢትዮጵያ 7ኛው ጠቅላላ ምርጫ በሰላም እና በተዓማኒነት እየተካሄደ ነው፡- ኡሁሩ ኬንያታ

የአፍሪካ ኅብረት የምርጫ ታዛቢ ቡድን መሪ እና የቀድሞው የኬንያ ፕሬዝዳንት ኡሁሩ ኬንያታ በኢትዮጵያ እየተካሄደ ስላለው 7ኛው ጠቅላላ ምርጫ መግለጫ ሰጥተዋል።

ኡሁሩ ኬንያታ እንደገለጹት፣ የአፍሪካ ኅብረት ታዛቢዎች ከጠዋት ጀምሮ በመላው ኢትዮጵያ የሚገኙ የምርጫ ጣቢያዎችን በመከታተል ላይ ሲሆኑ፣ አብዛኞቹ ጣቢያዎች በተያዘላቸው ሰዓት መከፈታቸውን እና የምርጫ ሂደቱም በተያዘለት ቅደም ተከተል እየተከናወነ መሆኑን አረጋግጠናል ብለዋል።

ታዛቢዎቹ ባደረጉት ምልከታ፣ የኢትዮጵያ ዜጎች የመምረጥ መብታቸውን በነፃነት እና በሙሉ ፈቃዳቸው እየተጠቀሙበት እንደሚገኙ መመልከታቸውን ገልጸው፣ ዜጎች ዴሞክራሲያዊ መብታቸውን በተግባር እያሳዩ ነው ሲሉ አድናቆታቸውን ገልጸዋል።

“በታዘብነው መሠረት ዜጎች ያለምንም ጫና የሚፈልጉትን ፓርቲ እየመረጡ ነው” ያሉት ኡሁሩ ኬንያታ፣ ምርጫው ፍጹም ሰላማዊ እና በተዓማኒነት የተሞላ ሂደት መሆኑን ገልጸዋል።

አክለውም በሁሉም የኢትዮጵያ ክፍሎች የተመደቡ የአፍሪካ ኅብረት ታዛቢዎች የምርጫውን ሂደት በቀጣይነት እየተከታተሉ ሲሆን፣ በቀጣይ ቀናትም ዝርዝር ግምገማቸውን እንደሚያቀርቡ ጠቁመዋል።

በአጠቃላይ የአፍሪካ ኅብረት ታዛቢ ቡድን እስካሁን ባለው ምልከታ፣ ምርጫው በሰላማዊ እና በምቹ ሁኔታ በመቀጠል ላይ እንደሚገኝ፣ የጸጥታ ሁኔታውም የተረጋጋ መሆኑን ገልጿል።

በሰርጋቸው እለት ድምጽ የሰጡ ሙሽሮችሙሽሮቹ በሆሳዕና ከተማ በሌሞ 01 የምርጫ ክልል በሄጦ ቀበሌ መስኪድ ሰፈር ምርጫ ጣቢያ 07 በመገኘት ድምጻቸውን ሰጥተዋል።
01/06/2026

በሰርጋቸው እለት ድምጽ የሰጡ ሙሽሮች

ሙሽሮቹ በሆሳዕና ከተማ በሌሞ 01 የምርጫ ክልል በሄጦ ቀበሌ መስኪድ ሰፈር ምርጫ ጣቢያ 07 በመገኘት ድምጻቸውን ሰጥተዋል።

01/06/2026

በማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል በሰባተኛው ሀገራዊ ምርጫ የድምጽ አሰጣጥ ዙሪያ የመራጮች አስተያየት ፣

Address

HOSSANA, ETHIOPIA

Alerts

Be the first to know and let us send you an email when Central Ethiopia Region - Prosperity Party - ብልፅግና posts news and promotions. Your email address will not be used for any other purpose, and you can unsubscribe at any time.

Contact The Organization

Send a message to Central Ethiopia Region - Prosperity Party - ብልፅግና:

  • Want your organization to be the top-listed Government Service?

Share