28/03/2026
ዲጂታል 2030 ለሀዋሳ ብልጽግና በሚል መሪቃል ለሀዋሳ ከተማ አስተዳደር ውስኝ ኩነቶች ምዝገባ ጽ/ቤት ሰራተኞች ስልጠና ተሰጠ።
ስልጠናው ኢትዮጽያ በ2030 ለማሳካት ያነገበችውን ግብ እውን ያደርጋል ተብሎ በታሰበው በኢትዮ 5 ሚሊየን ኮደርስ ላይ ትኩረቱን ያደረገ ነው።
ስልጠናው እንደ ሀገር የተያዘውን ዲጂታል ኢትዮጽያ 2030 ግብን ለማሳካት ዘርፈ ብዙ ተግባራት እየተከናወኑ ያሉ ሲሆን ከእነዚህም የ5 ሚሊየን ኮደርስን እንደ ሀገር ማፍራት አንዱ ሲሆን ሀገራችን እየተከተለች ካለቺው የቴክኖሎጂ እንቅስቃሴ በየደረጃው ያሉ ፐብሊክ ሰርቫንት ሆነ አመራሩ የዚህ ኮርስ ተካፋይ በመሆን ጊዜውን የወጀ አመራረ ና ባለሙያ ሆኖ ለመገኘት ጉልህ ሚና ይጫወታል።
ዲጂታል ሀዋሳው እውን ከማድረግ አንጻር በየመምሪያው እና በየጽ/ቤቱ የሚገኙ ፐብሊክ ሰርቫንት ይህንን ኢንሼቲቭ በትጋት መውስድ እንደሚጠበቅ የተገለፀ ሲሆን ዛሬ በቀን 18/07/2018 እየተሰጠ ያለውም ስልጠና የዚሁ ኢንሼቲቭ አካል መሆኑን ተብራርቷል።
የስልጠና መርሀግብሩን የመሩት አቶ ሰለሞን ኤርሚያስ በበኩላቸው በከተማችን የዲጂታላይዜሽን ተጠቃሚነት እና ተደራሽነት በማስፋት ዘርፈ ብዙ ተግባራት ተነድፈው እየተሰራ መሆኑን አብራርተዋል ተወዳዳሪ እና ተለዋወጭ ከሆነውን የቴክኖሎጂ አለም ጋር አብሮ ለመራመድ የሚያስሉ እድሎች በመንግስት ደረጃ መመቻቸታቸውን በመገንዘብ እንደ ዛሬው አይነት የአምስት ሚሊዮን ኢትዮ ኮደርስ ያሉ እድሎችን በመጠቀም እራስን ብቁ እና አለም አቀፍ ተወዳዳሪ ማድረግ እንደሚገባ ገልፀዋል።
በስልጠና ላይ የኢትዮ ኮደርስ ኦንላይን ስልጠና መውሰድ በሚያስችሉ ሂደት ላይ ጥልቅ ማብራሪያ ተሰጥቷል።
መጋብት 18/2018 ዓ.ም
ሀዋሳ