27/09/2019
ተፋሰሶቻችን ሕወይታችን የሆነው የመጠጥ ውሃ ምንጮቻችን ናቸው። ከ200,000 በላይ ለሆነው ለወልቂጤ እና እንዲብር ከተማ ሕዝብ የመጠጥ ውሃ ምንጭ የሆነው የጎተም ተፋሰስን መንከባከብ የሕልውና ጉዳይ ነው። በጉራጌ ልማት ማህበር በኩል አስተባባሪነት በተፋሰሱ ላይ ከዞኑ ውጭ የሚኖሩ የጉራጌ ተወላጆችን የመስቀል በዓላትን ምክንያት በማድረግ የሚደረጉ የችግኝ ተከላና እንክብካቤ ወደ ሌሎች የክልላችን ዞኖች ሊሰፋ የሚገባ ተሞክሮ ነው። በዘንድሮውም 2012 በዞኑ የመስቀል በዓልን ምክንያት በማድረግ የተተከሉ ችግኞች እንክብካቤ ሥራው ተጠናክሮ ይቀጥላል ተብሎ ይጠበቃል።
ተፋሰሶቻችንን መንከባከብ ሕብረተሰባችን ዘላቂ ሕይወት እንዲመራ ማስቻል ነው!!!