05/12/2025
የማርበርግ ቫይረስ ምላሽን ለማሳደግ የሚረዳ የሙኩራ ክትባት ለተጋላጭ የማህበረሰብ ክፍሎች ሊሰጥ ነው
፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨
#የማርበርግ ቫይረስ ምላሽ ለመስጠት የሚደረገውን ጥረት የሚደግፍ 5,000 የማርበርግ ቫይረስ የሙከራ ክትባት ከአሜሪካ መንግስት በድጋፍ የተገኘ ሲሆን፤ ክትባቱን ለኢትዮጵያ የመድኃኒት አቅርቦት አገልግሎት የአሜሪካ በኢትዮጵያ አምባሳደር አርቪን ማሲንጋ አስረክበዋል።
ክትባቱ በአርማወር ሃንሰን የምርምር ተቋም በሚመራ ፈጣን የደረጃ 2 ክሊኒካዊ ሙከራ ተደርጎለት ጥቅም ላይ እንደሚውል የገለጹት ክትባቱን የተረከቡት የጤና ሚኒስትር ዶ/ር መቅደስ ዳባ ሲሆኑ፣ የምርመራ ተቋሙ ከኢትዮጵያ የምግብ እና የመድኃኒት ባለስልጣን ጋር በመተባበር ቁጥጥር እንደሚያደርግም አክለዋል። ክትባቱን ከህዳር 29 ቀን ጀምሮ መስጠት የሚጀመር ሲሆን የጤና ባለሙያዎችን እና ከፍተኛ ተጋላጭ ለሆኑ ቡድኖች ቅድሚያ ይሰጣል ብለዋል።
ዩናይትድ ስቴትስ በባርዳ እና በሳቢን የክትባት ተቋም በኩል ክትባቱን ተደራሽ ማድረጉን የገለጹት አምባሳደር ማሲንጋ፤ የማርበርግ ወረርሽኝ ከጀመረበት ጊዜ ጀምሮ ዩናይትድ ስቴትስ ለኢትዮጵያ ጠንካራ አጋር መሆኗን ማረጋገጧን ተናግረዋል።
ጤና ሚኒስቴር ወርሽኙን ለመግታት ከሚመለከታችዉ ባለድርሻ አካላት ጋር በመሆን የሚላሽ አሰጣጡን አጠናክረዉ የቀጠሉ ሲሆን የቅኝትና ቁጥጥር ስራዉን ማጠናከር፣ የጤና ባለሙያዉንና ጤና ሰራተኞች ጨምሮ ተጋላጭ የሆኑትን በመጠበቅ ላይ ትኩረት በማድረግ የመከላከል ስራው ተጠናክሮ እንደሚቀጥል ዶ/ር መቅደስ ተናግረዋል።
ምንጭ ፣ጤና ሚንስቴር