Argoba Special worda educational office /አርጎባ ልዩ ወረዳ ትምህርት ፅ/ቤት

  • Home
  • Ethiopia
  • Harbu
  • Argoba Special worda educational office /አርጎባ ልዩ ወረዳ ትምህርት ፅ/ቤት

Argoba Special worda educational office /አርጎባ ልዩ ወረዳ ትምህርት ፅ/ቤት የትምህርት ጥራትን ማስጠበቅ ትዉልድን ወደ ተሻለ ቦታ በማሻገር ተወዳዳሪ እና ብቁ ዜጋ መፍጠር ነዉ አላማችን !!!

  ዉድ ወንድምና እህቶች‼እንኳን ለ1447 ዓ.ሒ. የዒድ አል-አድሃ (አረፋ) በዓል በሰላም አደረሳችሁ፣ በዓሉ የሰላም እና የደስታ እንዲሆንላችሁ እመኛለሁ።
26/05/2026

ዉድ ወንድምና እህቶች‼
እንኳን ለ1447 ዓ.ሒ. የዒድ አል-አድሃ (አረፋ) በዓል በሰላም አደረሳችሁ፣ በዓሉ የሰላም እና የደስታ እንዲሆንላችሁ እመኛለሁ።

በአርጎባ ብሄረሰብ ልዩ ወረዳ የ6ኛ እና 8ኛ ክፍል ክልል አቀፍ ሞዴል ፈተና መጀመሩ ተገለፀ​መዲና -ግንቦት 17/2018 ዓ/ም (አርጎባ ኮሙኒኬሽን)​በአርጎባ ብሄረሰብ ልዩ ወረዳ የ2018 ...
25/05/2026

በአርጎባ ብሄረሰብ ልዩ ወረዳ የ6ኛ እና 8ኛ ክፍል ክልል አቀፍ ሞዴል ፈተና መጀመሩ ተገለፀ

​መዲና -ግንቦት 17/2018 ዓ/ም (አርጎባ ኮሙኒኬሽን)

​በአርጎባ ብሄረሰብ ልዩ ወረዳ የ2018 ዓ/ም የ6ኛ እና የ8ኛ ክፍል ክልል አቀፍ ሞዴል ፈተና ከዛሬ ጀምሮ መሰጠት መጀመሩን የወረዳው ትምህርት ጽ/ቤት አስታወቀ።

ከዛሬ ግንቦት 17 እስከ ነገ ግንቦት 18 ቀን 2018 ዓ/ም ለሁለት ተከታታይ ቀናት በሚቆየው በዚህ የሞዴል ፈተና ላይ በአጠቃላይ 1,269 ተማሪዎች በመፈተን ላይ ይገኛሉ።

​በወረዳው ስር በሚገኙ 30 ት/ቤቶች 827 የ6ኛ ክፍል ተማሪዎች እንዲሁም በ21 ት/ቤቶች 442 የ8ኛ ክፍል ተማሪዎች ፈተናውን እየወሰዱ ነው።

​የወረዳው ት/ቤት ኃላፊ አቶ አብዱ አሊ እንደገለጹት ይህ የሞዴል ፈተና ተማሪዎች በቀጣይ ለሚወስዱት ክልል አቀፍና አገራዊ ፈተናዎች ራሳቸውን ቀድመው የሚገመግሙበትና ክፍተታቸውን ለይተው የሚዘጋጁበት ጭምር ነው። ፈተናው ተማሪዎች በቀሪው የዝግጅት ጊዜያቸው ይበልጥ ትኩረት ሰጥተው በደንብ እንዲዘጋጁ ለማድረግ ትልቅ እገዛ እንዳለውም ኃላፊው አክለው ገልጸዋል።

ፈተናው በሁሉም የትምህርት ተቋማት ፍጹም ከኩረጃ በፀዳ፣ እውነተኛ የተማሪዎችን አቅም በሚያሳይ እና በሰላማዊ ሁኔታ እየተሰጠ እንደሚገኝ የጽ/ቤቱ ኃላፊ አስታውቀዋል።

መዲና 2ኛ ደረጃ ት/ቤት የተማሪዎች የአካል ብቃት እንቅስቃሴ
21/05/2026

መዲና 2ኛ ደረጃ ት/ቤት የተማሪዎች የአካል ብቃት እንቅስቃሴ

በአርጎባ ብሄረሰብ ልዩ ወረዳ የተጠናቀቁ  የልማት ስራዎች የጉብኝትና ምርቃት ፕሮግራም ተካሄደ በደቡብ ወሎ ዞን በአርጎባ ብሄረሰብ ልዩ ወረዳ ዘንድሮው የበጀት አመት የህዝብን ተጠቃሚነት የሚ...
20/05/2026

በአርጎባ ብሄረሰብ ልዩ ወረዳ የተጠናቀቁ የልማት ስራዎች የጉብኝትና ምርቃት ፕሮግራም ተካሄደ

በደቡብ ወሎ ዞን በአርጎባ ብሄረሰብ ልዩ ወረዳ ዘንድሮው የበጀት አመት የህዝብን ተጠቃሚነት የሚያረጋግጡ የልማት ስራዎች ተጠናቀው በዛሬው ዕለት ከተለያዩ የህብረተሰብ ክፍሎች የተውጣጡ የመዲና ከተማ ነዋሪዎችና የወረዳው ጠቅላላ አመራሮች በተገኙበት ተመርቀው ተጎብኝተዋል።

ለምረቃ ከበቁት የልማት ስራዎች መካከል፦
1.የባህል ሙዚየም
2.የማህበረሰብ ሬዲዮ ጣቢያ
3.የመዲና ከተማ አፀደ ህፃናት
4.የመዲና ከተማ ኮሪደር ልማት በዛሬው ዕለት በይፋ ተመርቀዋል።

በወረዳው እየተከናወኑ የሚገኙ የልማት ስራዎች በተሻለ ፍጥነትና ጥራት በማጠናቀቅ ለአገልግሎት ማብቃት ተችሏል ።

18/05/2026
የ2018 ዓ.ም ክረምት የመምህራንና የት/ቤት አመራሮች የአቅም ግንባታ ስልጠና የመመልመያ መስፈርቶች
14/05/2026

የ2018 ዓ.ም ክረምት የመምህራንና የት/ቤት አመራሮች የአቅም ግንባታ ስልጠና የመመልመያ መስፈርቶች

የአርጎባ ልዩ ወረዳ ትምህርት ፅ/ቤት የመዲና ጉድኝት ማዕከል በጉድኝቱ ሱፐርቫይዘር አማካኝነት በየቀኑ ከምሽቱ  12:30 እስከ 2:30 ድረስ የጎልማሶች ትም/ት እየተሰጠ ይገኛል። በመዲና ከ...
11/05/2026

የአርጎባ ልዩ ወረዳ ትምህርት ፅ/ቤት የመዲና ጉድኝት ማዕከል በጉድኝቱ ሱፐርቫይዘር አማካኝነት በየቀኑ ከምሽቱ 12:30 እስከ 2:30 ድረስ የጎልማሶች ትም/ት እየተሰጠ ይገኛል።

በመዲና ከተማ ቅድመ አንደኛ ትምህርት ቤት የጎልማሶች ትምህርት በምሽት መርሃ ግብር እየተሰጠ ነው

​በአርጎባ ብሄረሰብ ወረዳ መዲና ከተማ 01 ቀበሌ የሚገኙ ጎልማሶች፣ የቀን የሥራ ውሏቸውን ሳይረብሹ በምሽት መርሃ ግብር መሠረታዊ የንባብና የጽሕፈት ትምህርት እየተከታተሉ ይገኛሉ።

​ይህ የጎልማሶች ትምህርት መርሃ ግብር፣ ተማሪዎቹ በሥራ ምክንያት ሊያመልጣቸው የሚችለውን የዕውቀት ዕድል በምሽት እንዲያገኙ በማመቻቸቱ ትልቅ ሚና እየተጫወተ ነው።

ትምህርቱን እየተከታተሉ የሚገኙ ጎልማሶችም፣ መርሃ ግብሩ መሠረታዊ የማንበብና የመጻፍ ክህሎት እንዲያዳብሩ የሚያስችል መሆኑን ገልጸዋል።

የሲቪል ሰርቪስ ሰራተኞች ማረጋገጫ (Verification) መመሪያ📌​​​​​​​​​​​​ይህ ሰነድ የማረጋገጫ ሂደቱ ስልታዊ እና ቀልጣፋ በሆነ መንገድ እንዲከናወን የሚረዱ ሶስት ዋና ዋና ክፍሎ...
10/05/2026

የሲቪል ሰርቪስ ሰራተኞች ማረጋገጫ (Verification) መመሪያ
📌​​​​​​​​​​​​ይህ ሰነድ የማረጋገጫ ሂደቱ ስልታዊ እና ቀልጣፋ በሆነ መንገድ እንዲከናወን የሚረዱ ሶስት ዋና ዋና ክፍሎችን ይዟል።
​📋 ክፍል 1፡ የግድ መሟላት ያለባቸው ሰነዶች (11 ዓይነቶች)
​ለእያንዳንዱ ሰራተኛ ሊሟሉ የሚገባቸው መሰረታዊ የሰው ኃይል መረጃዎች፦
📌​​​​​​​​​​​​ብሄራዊ መታወቂያ፡ ከተመዘገበበት ስልክ ቁጥር ጋር።
📌​​​​​​​​​​​​የቢሮ መታወቂያ፡ ወቅታዊ የሆነ።
📌​​​​​​​​​​​​የቅጥር ደብዳቤ፡ የመጀመሪያ ቅጥር ሰነድ።
📌​​​​​​​​​​​​የዝውውር ሰነድ፡ ከሌላ መሥሪያ ቤት የመጡ ከሆነ።
📌​​​​​​​​​​​​የደረጃ እድገት፡ የተሰጡ የደረጃ እድገት ደብዳቤዎች።
📌​​​​​​​​​​​​የአገልግሎት ማራዘሚያ፡ ጡረታ ወጥተው ለሚሰሩ ብቻ።
📌​​​​​​​​​​​​የትምህርት ማስረጃዎች፡ ሁሉም የትምህርት ደረጃዎች።
📌​​​​​​​​​​​​የጡረታ ፎርም፡ የተሞላ የጡረታ መረጃ።
📌​​​​​​​​​​​​የስራ ልምድ፡ የቀድሞ የስራ ልምድ ማስረጃዎች።
📌​​​​​​​​​​​​የሹመት ደብዳቤ፡ ተሿሚ ለሆኑ አመራሮች።
📌​​​​​​​​​​​​የድልድል/ምደባ ደብዳቤ፡ አዲስ ድልድል ተደርጎ ከሆነ።
​💍 ክፍል 2፡ ተጨማሪ የማህበራዊ ሁኔታ ሰነዶች
📌​​​​​​​​​​​​የጋብቻ ሰርተፍኬት
📌​​​​​​​​​​​​የልጆች የልደት ሰርተፍኬት (ልጆች ካሉ)
​⚙️ ክፍል 3፡ የአሰራር ቅደም ተከተልና መመሪያዎች
✍​ሂደቱ ያለምንም መስተጓጎል እንዲሄድ ተቋማት የሚከተሉትን ተግባራት ማከናወን ይኖርባቸዋል፦
📌​​​​​​​​​​​​መርሃ-ግብር ማዘጋጀት፡ በቀን ለአንድ መረጃ ሰብሳቢ 7 ሰራተኞችን በማደራጀት ቀኑን አስቀድሞ ማሳወቅ።
📌​​​​​​​​​​​​የአካል መገኘት፡ በወሊድ፣ በህመም ወይም በአመት እረፍት ላይ ያሉ ሰራተኞች በአካል ቀርበው መመዝገብ አለባቸው።
📌​​​​​​​​​​​​የሰው ኃይል መመደብ፡ ስራውን የሚከታተል፣ ጥንቃቄ ያለውና የIT እውቀት ያለው ኃላፊ መመደብ።
📌​​​​ መረጃዎችን - በጊዜ፣ በጥራትና በማደራጀት የዲጅታል ሲቪል ሰርቪስ ግንባታን ለማሳካት የድርሻቸውን እንወጣ። መልዕክታችን ነው።

ምንጭ:👉የአብክመ ሲቪል ሰርቪስና የሰው ኃብት ልማት ቢሮ

Address

South Wollo Harbu City
Harbu

Telephone

+251913832392

Website

Alerts

Be the first to know and let us send you an email when Argoba Special worda educational office /አርጎባ ልዩ ወረዳ ትምህርት ፅ/ቤት posts news and promotions. Your email address will not be used for any other purpose, and you can unsubscribe at any time.

Contact The Organization

Send a message to Argoba Special worda educational office /አርጎባ ልዩ ወረዳ ትምህርት ፅ/ቤት:

Share