ሀራ ከተማ አስተዳደር ንግድና ገበያ ልማት ጽ/ቤት

ሀራ ከተማ  አስተዳደር ንግድና ገበያ ልማት ጽ/ቤት የሀራ ከተማ አስተዳደር ንግድና ገበያ ልማት ፅህፈት ቤት ኦፊሻል የፌስቡክ ገፅ ነው።

02/04/2026

ከንግድና ቀጠናዊ ትስስር ሚኒስቴር የተሠጠ ጋዜጣዊ መግለጫ።

መግለጫዉ በዓለም አቀፍ ወቅታዊ ሁኔታዎች ምክንያት የተከሰተው የነዳጅ አቅርቦትና የዋጋ ማስተካከያን ይመለከታል፡፡

በመካከለኛው ምስራቅ የተከሰተውን ጦርነት ተከትሎ ከየካቲት 21 ቀን 2018 ዓ.ም ጀምሮ የዓለም የነዳጅ ዋጋ በከፍተኛ ሁኔታ ጨምሯል፡፡ ሁኔታው ከቀን ወደ ቀን ይሻሻላል ተብሎ ቢጠበቅም ነገሮች በመካረራቸው ምክንያት በነዳጅ አቅርቦት ላይ እጥረት ከመፈጠሩም በላይ የአንዳንድ የነዳጅ ምርቶች ዋጋ በከፍተኛ መጠን ሊጨምር ችሏል፡፡

ኢትዮጵያ ከውጭ አስገብታ የምትጠቀማቸው የነዳጅ አይነቶች ነጭ ናፍጣ፣ ቤንዚን፣ የአውሮፕላን ነዳጅ፣ ኬሮሲን፣ ከባድ ጥቁር ናፍጣ እና ቀላል ጥቁር ናፍጣ ሲሆኑ የግዥ ሂደቱም በመንግስትና መንግስት ስምምነት እንዲሁም በዓለም አቀፍ ግልጽ ጨረታ የሚከናወን ነው፡፡

ከመንግስት ጋር በተደረገው ስምምነት መሰረት ስልሳ በመቶ ነጭ ናፍጣ እና መቶ በመቶ የአውሮፕላን ነዳጅ ከኩዌት መንግስት የሚገዛ ሲሆን ቀሪው አርባ በመቶ ነጭ ናፍጣ እንዲሁም መቶ በመቶ ቤንዚንና ጥቁር ናፍጣዎች በጨረታ የሚቀርቡ ናቸው፡፡

ከኩዌት ጋር ያለው ኮንትራት ከጃንዋሪ አንድ ቀን ሁለት ሺህ ሃያ ስድስት እስከ ዲሴምበር ሰላሳ አንድ ቀን ሁለት ሺህ ሃያ ስድስት የሚዘልቅ ሲሆን ከመጫኛ ወደብ እስከ ጅቡቲ ድረስ ያለው የሎጂስቲክስ ዋጋ ወይም ፕሪሚየም ለሁለቱም ምርቶች በበርሜል 9.25 ዶላር ሆኖ በየዓመቱ በሚደረግ ድርድር የሚወሰን ነው፡፡

በአሁኑ ወቅት በጨረታ አሸናፊ የሆነው ቪቶል የተባለው ኩባንያ ለነጭ ናፍጣ 13.99 ዶላር እንዲሁም ለቤንዚን 10.99 ዶላር ፕሪሚየም በማስከፈል በ360 ቀናት ዱቤ እያቀረበ ይገኛል፡፡

ይህም ማለት የነዳጅ ዋጋ የሚሰላው የወሩ የዓለም አማካይ ዋጋ ላይ ፕሪሚየሙ ተደምሮ ነው፡፡ ለምሳሌ በየካቲት ወር የኩዌት ነጭ ናፍጣ ወርሃዊ አማካይ 86.03 ዶላር ሲሆን ከፕሪሚየሙ ጋር ተደምሮ 95.28 ዶላር ሆኗል፡፡

ሆኖም በጦርነቱ ምክንያት የኩዌት አቅርቦት በመዘጋቱ ለአጣዳፊ ግዥ በወጣው ጨረታ የተገኘው ፕሪሚየም ለአውሮፕላን ነዳጅ 86.33 ዶላር እንዲሁም ለነጭ ናፍጣ 92.88 ዶላር በበርሜል በመሆኑ ዋጋው እጅግ እንዲንር አድርጎታል፡፡

የዓለም አንድ አምስተኛ ድፍድፍ ነዳጅ የሚተላለፍበት የሆርሙዝ የባህር ሰርጥ በመዘጋቱ እንደ ሳዑዲ አረቢያ፣ ኩዌት፣ የተባበሩት አረብ ኤምሬትስ እና ኢራቅ ያሉ ሀገራት በቀን የሚያቀርቡት 140 ሚሊዮን በርሜል ነዳጅ ተቋርጧል፡፡

በዚህም ምክንያት ወደ ሀገራችን ይገባ የነበረ 120 ሺህ ሜትሪክ ቶን ነጭ ናፍጣ እና 60 ሺህ ሜትሪክ ቶን የአውሮፕላን ነዳጅ የጫኑ ሶስት መርከቦች በአረብ ባህረ ሰላጤ ላይ ቆመው ይገኛሉ፡፡

መንግስት መደበኛ አቅርቦቱ እንዳይቋረጥ ከተባራሪ ገበያ ወይም spot market በከፍተኛ ዋጋ በመግዛት ለማቅረብ ጥረት እያደረገ ይገኛል፡፡ ሆኖም በመንግስት ላይ ያለው የድጎማ ጫና ከ272 ቢሊዮን ብር በላይ ደርሷል፡፡

ባለፈው ሳምንት በወጣው ታሪፍ ነጭ ናፍጣ በ139.84 ብር ሲሸጥ መንግስት 95 ብር ይደጉም ነበር፤ ቤንዚንም በ132.18 ብር ሲሸጥ 42 ብር ድጎማ ይደረግለት ነበር፡፡ አሁን ባለው ሁኔታ ድጎማውን በነበረበት መቀጠል አስቸጋሪ በመሆኑ አዲስ የዋጋ ማስተካከያ ተደርጓል፡፡

በዚህም መሰረት አዲሱ የሊትር የችርቻሮ መሸጫ ዋጋ ቤንዚን 142.21 ብር፣ ኬሮሲን 151.39 ብር፣ ነጭ ናፍጣ 163.09 ብር፣ ቀላል ጥቁር ናፍጣ 163.98፣ ከባድ ጥቁር ናፍጣ 160.68 ብር እንዲሁም የአውሮፕላን ነዳጅ 150.48 ብር ሆኗል፡፡ የቀጥታ ተጠቃሚዎች የነጭ ናፍጣ መሸጫ ዋጋ ደግሞ 210 ሆኖ ተደንግጓል፡፡

መንግስት አሁንም ቢሆን በአንድ ሊትር ነጭ ናፍጣ ላይ 71 ብር እንዲሁም በቤንዚን ላይ 32 ብር ድጎማ እያደረገ ይገኛል፡፡ ይህ ድጎማ ባይኖር ኖሮ የናፍጣ ዋጋ 234.17 ብር እንዲሁም የቤንዚን ዋጋ 174.40 ብር ይደርስ ነበር፡፡

አሁንም ቢሆን የሀገራችን የነዳጅ ዋጋ ከጎረቤት ሀገራት ጋር ሲነፃፀር አነስተኛ ነው፡፡ ለምሳሌ በዶላር ሲሰላ በሀገራችን የናፍጣ ዋጋ 1.032 ዶላር ሲሆን በኬንያ 1.374፣ በጅቡቲ 1.741፣ በታንዛኒያ ደግሞ 1.09 ዶላር ነው፡፡

በአጠቃላይ የቤንዚን የአቅርቦት ችግር የሌለ ሲሆን ነጭ ናፍጣን ጨምሮ ሌሎች የነዳጅ አይነቶች የአቅርቦት እጥረት እና ዋጋ ጭማሪ ቀውስ እስኪስተካከል መንግስት ስርጭቱን የሚከታተልና የሚመራ ቡድን አደራጅቷል፡፡

ቡድኑ በሚያዘጋጀው የአቅርቦትና የስርጭት ቅደም ተከተል የሚቀርበውን ነዳጅ በቁጠባ እና በተቀመጠው የግብይት ስርአት ብቻ እንዲፈፀም ድጋፍና ርብርብ ማድረግም እንደሚገባ መንግስት ያሳስባል፡፡

በቅደም ተከተሉ መሰረትም ነዳጅ የሚያጓጉዙ ቦቴዎች፣ የወጪና ገቢ ምርት ተሽከርካሪዎች፣ የመሰረታዊ ፍጆታና የኤክስፖርት ምርት አምራች ኢንዱስትሪዎች፣ ቁልፍ የመንግስትና የግል የልማት ፕሮጀክቶች፣ መካናይዝድ እርሻዎች፣ የፀጥታና ደህንነት ተቋማት፣ የህዝብ ማመላለሻ ተሽከርካሪዎች፥የጤና አገልግሎቶች፣ የቴሌኮም ታወር ስራዎች፣ የምርጫ ስራዎች፣ የውሃና መብራት አጣዳፊ ስራዎች፣ የሚዲያና ሰብአዊ አገልግሎቶች እንዲሁም ከፍተኛ የተማሪ ቁጥር ያሉባቸው ዩኒቨርሲቲዎች የቅድሚያ አገልግሎት የሚያገኙ ናቸዉ፡፡

ህብረተሰቡ ይህንን አስቸጋሪ ወቅት ለመሻገር በሚደረገው ጥረት ተገቢውን ድጋፍና ትብብር እንዲያደርግ መንግስት ጥሪውን ያቀርባል፡፡

የንግድና ቀጠናዊ ትስስር ሚኒስቴር
መጋቢት 24 ቀን 2018 ዓ.ም
አዲስ አበባ

በሀራ ከተማ በህገወጥ መንገድ ሲዘዋወር የነበረ 83 ጀሪካን ነጭ ጋዝ በቁጥጥር ስር ዋለ፤ በሀራ ከተማ አስተዳደር በህገወጥ መንገድ ሲዘዋወር የነበረ 83 ጀሪካን ነጭ ጋዝ በፖሊስ ቁጥጥር ስር...
01/04/2026

በሀራ ከተማ በህገወጥ መንገድ ሲዘዋወር የነበረ 83 ጀሪካን ነጭ ጋዝ በቁጥጥር ስር ዋለ፤

በሀራ ከተማ አስተዳደር በህገወጥ መንገድ ሲዘዋወር የነበረ 83 ጀሪካን ነጭ ጋዝ በፖሊስ ቁጥጥር ስር መዋሉ ተገለጸ። ድርጊቱ የተፈጸመው የነዳጅ ምርትን ያለአግባብ በማከማቸትና በህገወጥ መስመር ለማዛወር ሲሞከር መሆኑ ታውቋል።

የከተማው ፖሊስ እንደገለጹት ይህ ህገወጥ ተግባር ሊጋለጥ የቻለው የጸጥታ አካላት ባደረጉት ጥብቅ ክትትልና ፍተሻ ነው። የተያዘው ነጭ ጋዝ በህብረተሰቡ የዕለት ተዕለት ኑሮ ላይ ጫና ለመፍጠር የታለመ የንግድ ማጭበርበር አካል እንደሆነም ተጠቁሟል።

የከተማ አስተዳደሩ የንግድና ገበያ ልማት ጽህፈት ቤት ከፖሊስና ከሌሎች ከሚመለከታቸው የጸጥታ አካላት ጋር በመቀናጀት፣ በነዳጅና መሰል ምርቶች ላይ የሚስተዋለውን ህገወጥ ዝውውር ለመግታት በትኩረት እየሰሩ ነው።

ሀራ ከተማ አስተዳደር ንግድና ገበያ ልማት ጽ/ቤት

31/03/2026

መንግሥት በመካከለኛው ምስራቅ ጦርነትና ዓለም አቀፍ ቀውስ ምክንያት በነዳጅ አቅርቦት ላይ ያጋጠመውን ችግር ለመቋቋም የሚያስችሉ ውሳኔዎችን ይፋ አደረገ

አዲስ አበባ፤ መጋቢት 22/2018 ፦ መንግሥት በመካከለኛው ምስራቅ ጦርነትና ዓለም አቀፍ ቀውስ ምክንያት በነዳጅ አቅርቦት ላይ ያጋጠመውን ችግር ለመቋቋም የሚያስችሉ ውሳኔዎችን ማሳለፉን የንግድና ቀጣናዊ ትስስር ሚኒስትር ካሳሁን ጎፌ(ዶ/ር) ገለጹ።

የንግድና ቀጣናዊ ትስስር ሚኒስትር ካሳሁን ጎፌ (ዶ/ር) በመካካለኛው ምስራቅ ያለው ጦርነትና አለመረጋጋት በሀገራችን የነዳጅ ግብይትና አቅርቦት ላይ ሊያደርስ የሚችለውን ተጽዕኖ እንዲሁም መንግሥት የሚከተላቸውን አቅጣጫዎች በተመለከተ ለኢዜአ ማብራሪያ ሰጥተዋል።

የነዳጅ አቅርቦትና ስርጭትን የሚከታተል፣ እርምጃ የሚወስድና የነዳጅ ቅድሚያ የሚሰጣቸውን ዘርፍች የሚለይ ልዩ ክፍል መቋቋሙንም ይፋ አድርገዋል።

በመካከለኛው ምስራቅ ያለው ጦርነትና አለመረጋጋት በሀገራችን የነዳጅ ግብይትና አቅርቦት ላይ ተጽዕኖ ማሳደሩን ተናግረዋል።

በጦርነቱ ምክንያት በዓለም አቀፍ ደረጃ ከጦርነቱ በፊት የአንድ በርሜል ነጭ ናፍጣ ዋጋ 80 ዶላር የነበረ ሲሆን አሁን 230 ዶላር መድረሱን ቤንዚንም ከ70 ወደ 150 ዶላር ማሻቀቡን ገልጸዋል።

ኢትዮጵያ ከመካከለኛው ምስራቅ ሀገራት ጋር የነበራት የረጅም ጊዜ የነዳጅ ግብይት ውል በጦርነቱ ምክንያት መስተጓጎሉንና አቅራቢ ሀገራቱ ምርቱን ማቅረብ እንደማይችሉ ማሳወቃቸውን አስታውሰዋል።

በዚህም ምክንያት በግዥ ሂደት ላይ የነበረ ከ180 ሺህ ሜትሪክ ቶን በላይ ነዳጅ አለመቅረቡን ጠቅሰዋል።

በጦርነቱና አለመረጋጋቱ ምክንያትም በነጭ ናፍጣ ላይ የነበረው የቀን አቅርቦት ከ9 ነጥብ 2 ሚሊዮን ሊትር ወደ 4 ነጥብብ 5 ሚሊዮን ሊትር ዝቅ ማለቱን ጠቁመዋል።

የተለያዩ ሀገራት ያጋጠማቸውን የነዳጅ አቅርቦት እጥረት ተከትሎ የተለያዩ ማህበራዊና ኢኮኖሚያዊ እቀባዎችን እያደረጉ መሆኑን ገልጸው፥ የኢትዮጵያ መንግሥት የሚከተለው መርህ ግን ከህዝቡ ጋር በመተባበር ችግሩን በጋራ ለመሻገር መሆኑን ጠቅሰዋል።

መንግሥት የተፈጠረውን የአቅርቦት እጥረት ለመቅረፍና ማህበራዊና ኢኮኖሚያዊ እንቅስቃሴዎች እንዳይገቱ ነዳጅን ከተጓዳኝ ገበያ ስለሚገዛና የዓለም የነዳጅ ዋጋ በመጨመሩ ምክንያት በሦስት እጥፍ ዋጋ እየገዛ ለማቅረብ መገደዱን ሚኒስትሩ አስረድተዋል።

ምንም እንኳን የዓለም አቀፍ የነዳጅ ዋጋ በከፍተኛ ሁኔታ ቢጨምርም፣ መንግሥት የዜጎችን ኑሮ ለመታደግ በአሁኑ ወቅት በነጭ ናፍጣ ላይ በአንድ ሊትር 95 ብር፣ በቤንዚን ላይ ደግሞ 42 ብር ድጎማ እያደረገ ይገኛል ነው ያሉት።

እስካሁን 262 ቢሊዮን ብር ገደማ ድጎማ ማድረጉን በማንሳት የተደረገ ሲሆን፣ በየወሩም ከ15 እስከ 20 ቢሊዮን ብር ለድጎማ እየተመደበ መሆኑ ጠቅሰዋል።

ያጋጠመው የነዳጅ አቅርቦት እጥረት በሀገርና በዜጎች ማህበራዊና ኢኮኖሚያዊ እንቅስቃሴ ላይ ጫና እንዳያሳድርና በፍትሐዊነት ለመምራት መንግሥት ከዛሬ ጀምሮ ተግባራዊ የሚሆን የቅድሚያ አሰጣጥ ውሳኔ ማሳለፉን ሚኒስትሩ ይፋ አድርገዋል።

በዚህም መሠረት

1. ነዳጅ የሚያጓጉዙ ተሽከርካሪዎች በማደያ የቅድሚያ ቅድሚያ እንዲሰጣቸው

2. ከፍተኛ አምራችና የኤክስፖርት ድርጅቶች በቀጥታ ፣

3. ልዩ ትኩረት የሚሹ የመንግሥትና የግል ፕሮጀክቶች በቀጥታ፣

4. የገቢና ወጪ ንግድን ጨምሮ መሠረታዊ የፍጆታ ምርቶችን የሚያጓጉዙ ተሽከርካሪዎች

5. ግብርናን የሚያዘምኑ ትራክተሮች፣

6. የከተማና ሀገር አቀፍ የብዙሃን ትራንስፖርት ተሽከርካሪዎች

7. እንዲሁም በናፍጣ የሚሰሩ የሕዝብ ማመላለሻ ተሽከርካሪዎች ነዳጅን በቅድሚያ እንዲያገኙ የሚያደርግ የቅድሚያ የነዳጅ አጠቃቀም አሠራር የሚተገበር መሆኑን ገልጸዋል።

ከዚህ ውጭ የሚደረግ የነዳጅ ስርጭት ተገቢ ባለመሆኑ እርምጃ ይወሰዳል ያሉት ሚኒስትር፥ ይህንን ውሳኔ በአግባቡ ለማስፈጸም በቅንጅት እንደሚሠራም ገልጸዋል።

በሌላ በኩል መንግሥት የፌደራልና የክልል ተቋማትን ያካተተና ስርጭቱን 24/7 የሚከታተል የሁኔታዎች ልዩ የመከታተያ ክፍል ማቋቋሙን ይፋ አድርገዋል።

ልዩ የመከታተያ ክፍሉ በማዕከል የሚመራ ሲሆን የነዳጅ አቅርቦት፣ ስርጭትና አጠቃቀምን የሚከታተል፣ ውሳኔዎችን የሚየቀርብና ቅድሚያ የሚሰጣቸውን የሚለይ መሆኑን ተናግረዋል።

በነዳጅ ግብይትና አቅርቦት ዙሪያ ሕገ-ወጥ ድርጊት የፈጸሙ የሥራ ኃላፊዎችን ጨምሮ 658 ግለሰቦች በቁጥጥር ስር የዋሉ ሲሆን፣ ከ720 ሺህ ሊትር በላይ ነዳጅ ተይዞ ለመንግሥት ገቢ ሆኗል ብለዋል።

ከህብረተሰቡ የሚከጠበቁ ተግባራትን ይፋ ያደረጉ ሲሆን በዚህም መሠረት፦

1) ነዳጅን በቁጠባ እንዲጠቀም፣

2) የታዳሽ ኃይል አማራጮችን የመጠቀም ስልትን መከተል፣

3) የእግር ጉዞ ባህልን ማጎልበት

4) አላስፈላጊ የጉዞ ፕሮግራሞችን መሰረዝና ማቆም

5) የሕዝብ ትራንስፖርትን መጠቀም

6) በነዳጅ ግብይት ላይ የሚስተዋሉ ሕገ-ወጥ ተግባራትን በማጋለጥ ረገድ ከመንግሥት ጋር ተባብሮ እንዲሠራ ጥሪ አቅርበዋል።

#ኢዜአ

31/03/2026
የአማራ ክልል ንግድና ገበያ ልማት ቢሮ  Amhara Trade And Market Development Bureau
27/03/2026

የአማራ ክልል ንግድና ገበያ ልማት ቢሮ Amhara Trade And Market Development Bureau

ወቅታዊ ሁኔታውን ምክንያት በማድረግ በምርት ላይ የዋጋ ጭማሪ እንዳይኖር ቁጥጥር እየተደረገ ነው።                   ፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨ወቅታዊ ሁኔታውን ምክንያት በማድረግ የኑሮ ው...
26/03/2026

ወቅታዊ ሁኔታውን ምክንያት በማድረግ በምርት ላይ የዋጋ ጭማሪ እንዳይኖር ቁጥጥር እየተደረገ ነው።

፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨
ወቅታዊ ሁኔታውን ምክንያት በማድረግ የኑሮ ውድነት እንዳይከሰት እየሠራ መኾኑን የአማራ ክልል ንግድ እና ገበያ ልማት ቢሮ አስታውቋል።

የአማራ ክልል ንግድ እና ገበያ ልማት ቢሮ ምክትል ኀላፊ ፈንታው ፈጠነ ኢትዮጵያ ነዳጅ ገዥ ሀገር በመኾኗ የመካከለኛው ምሥራቅ የተፈጠረው ግጭት አሉታዊ ተጽዕኖ አለው ብለዋል።

ማንኛውንም ምርት እና አገልግሎት ለማንቀሳቀስ ነዳጅ አስፈላጊ በመኾኑ ወቅታዊ ዓለም አቀፍ ሁኔታው ከኑሮ ውድነት ጋር ቀጥተኛ ግንኙነት ይኖረዋል ነው ያሉት።

የኢትዮጵያ የነዳጅ ዋጋ ከአፍሪካ ሀገራትም ኾነ ከዓለም ገበያ አኳያ ሲታይ ዝቅተኛ መኾኑን መገንዘብ ይገባል ብለዋል። የቅርብ ጊዜ የዋጋ ጭማሪውም ቢኾን አነስተኛ ጭማሪ መኾኑን ተናግረዋል። ወቅታዊ የነዳጅ ሁኔታ ለተባባሰ የምርቶች ዋጋ ጭማሪ ምክንያት እንደማይኾንም ገልጸዋል።

የነዳጅ ዋጋ ከሌሎች ሀገራት ጋር ሲነጻጸር ዝቅተኛ የኾነው መንግሥት የነዳጅ ወጭ የማኅበረሰቡን የኑሮ ውድነት እና የኑሮ ጫና እንዳያባብስ ካለው ቁርጠኝነት የተነሳ ከፍተኛ ድጎማ እያደረገ በመኾኑ ነው ብለዋል።

ነገር ግን በዓለም አቀፍ ችግሩ ምክንያት በነዳጅ እና በናፍጣ የጨመረው ዋጋ ዝቅተኛ ኾኖ እያለ በትራንስፖርት ላይ ከፍተኛ የዋጋ ጭማሪ እንደሚስተዋል አንስተዋል።

የመንግሥትን ድጎማ እና ወቅታዊ የነዳጅ ዋጋን መሠረት ያደረገ እና ተመጣጣኝ የኾነ የትራንስፖርት ዋጋ መኖር አለበት ነው ያሉት። የትራንስፖርት ጭማሪውን ለማስተካከል ከሚመለከታቸው ተቋማት ጋር በመምከር አቅጣጫ መቀመጡንም አመላክተዋል።

በኹሉም ምርቶች ላይ ዋጋ እንዳይጨመር እና የኑሮ ውድነት እንዳይባባስም ከተቋማት ጋር በቅንጅት እየተሠራ እንደኾነም አስረድተዋል።

አምራች አርሶ አደሮች በወቅታዊ ችግር ተጽዕኖ ሳይደርስባቸው ምርታቸውን ወደ መዳረሻ እንዲያደርሱ ነዳጅ ቅድሚያ እንዲያገኙ የማድረግ ሥራ እየተከናወነ መኾኑንም አንስተዋል።

የመካከለኛው ምሥራቅ ጦርነት ቢራዘም ነዳጅ ሊጠፋ ይችላል በሚል ፍራቻ ምርት የሚከዝኑ አካላት እንዳይኖሩ እየተሠራ መኾኑንም አመላክተዋል።

መንግሥት ምርቶችን ያለአግባብ ከዝነው በተገኙ አካላት ላይ ምርቱን ከመውረስ ጀምሮ ጠንካራ ሕጋዊ እና አሥተዳደራዊ እርምጃ እንደሚወሰድም አስታውቀዋል።

ጦርነቱ የሚራዘም ከኾነ መንግሥት አማራጭ መፍትሔዎችን እንደሚወስድ መረዳት ይገባል ያሉት ምክትል ኀላፊው እንደ መደበኛው ጊዜ ባይኾን እንኳን የነዳጅ አቅርቦቱ በማይቋረጥ ሁኔታ ይቀጥላል ብለዋል።

ማኅበረሰቡ የተፈጠረውን ዓለም አቀፍ ጫና በውል ተገንዝቦ ነዳጅን በቁጠባ እንዲጠቀም፣ ምርት ያለአግባብ የሚከዝኑ አካላትን የመከላከል እና የማጋለጥ ሥራውን አጠናክሮ እንዲቀጥልም አሳስበዋል።

መጋቢት 17/2018 ዓ.ም

ameco

በክልሉ የሚስተዋለውን ሕገ-ወጥ የነዳጅ ዝውውርና ንግድ ለመግታት ጥብቅ የቁጥጥርና የሕግ ማስከበር እርምጃ  መውሰድ  ተጀምሯል።           * * * * * * * * * * *የአማራ ክልል...
17/03/2026

በክልሉ የሚስተዋለውን ሕገ-ወጥ የነዳጅ ዝውውርና ንግድ ለመግታት ጥብቅ የቁጥጥርና የሕግ ማስከበር እርምጃ መውሰድ ተጀምሯል።

* * * * * * * * * * *
የአማራ ክልል ፖሊስ ዋና ጠቅላይ መምሪያ በክልሉ እየታየ ያለውን የነዳጅ እጥረት ተገን በማድረግ፣ በሕገ-ወጥ የነዳጅ ንግድና ዝውውር ላይ በተሰማሩ አካላት ላይ የማያዳግም እርምጃ መውሰድ መጀመሩን ለህዝብ ይፋ ያደርጋል ።

የአማራ ክልል ፖሊስ ዋና ጠቅላይ መምሪያ የክልሉን የፀጥታ ሁኔታ ለማባባስና የሕዝቡን ማኅበራዊ ህይወት ለማናጋት፣ ወቅታዊውን የነዳጅ እጥረት ተገን በማድረግ የሚፈጸሙ ሕገ-ወጥ ድርጊቶችን ለመከላከል ሰፊ የሕግ ማስከበር ዘመቻ እያከናወነ ይገኛል።

ፖሊስ ከሌሎች የፀጥታ አካላትና ከኅብረተሰቡ ጋር በመቀናጀት ባደረገው ከፍተኛ ክትትልና በኬላዎች ላይ በተከናወነ ፍተሻ፣ በርካታ ሕገ-ወጥ የነዳጅ ዝውውር ሙከራዎች መክሸፋቸውንና በድርጊቱ ላይ የተሰማሩ ግለሰቦችም በቁጥጥር ስር ውለው ተገቢውን የሕግ ቅጣት እንዲያገኙ መደረጉን መምሪያው ያረጋግጣል።

ይህ ሕገ-ወጥ ድርጊት በጥቂት ስግብግብ ነጋዴዎች የሚፈጸም ቢሆንም፣ በሀገርና በሕዝብ ላይ የሚያሳድረው ተፅዕኖ ግን እጅግ የከፋ ነው።

መንግሥት በከፍተኛ የውጭ ምንዛሬ ያስገባቸው የነዳጅ ምርቶች ለታለመላቸው የልማት ሥራዎች ሳይውሉ መባከናቸው አገራዊ ኪሳራን ከማስከተሉ በተጨማሪ የትራንስፖርት ዋጋ እንዲንርና የሸቀጦች ዋጋ እንዲጨምር በማድረግ የኑሮ ውድነቱን የሚያባብስ ተግባር በመሆኑ ፖሊስ ከፍተኛ ቁጥጥር ያደርጋል።

የነዳጅ እጥረት የሕዝብ ትራንስፖርትን በማሽመድመድ ዜጎች ወደ ሥራና ትምህርት እንዳይሄዱ እንቅፋት በመሆኑ ህገወጦችን ተከታትሎ ለህግ ለማቅረብ ከአጋር አካላት ጋር ተቀናጅቶ እየሰራ ይገኛል።

ከተፈቀደው የዋጋ ተመን ውጭ የዋጋ ጭማሪ የሚያደርጉ፣ ነዳጅ በመደበቅ ሰው ሠራሽ እጥረት የሚፈጥሩና ከሕገ-ወጥ ነጋዴዎች ጋር የሚተባበሩ ማደያዎች ላይ የማያዳግም አስተዳደራዊና የወንጀል ክስ እርምጃ ይወሰዳል።

ጨለማን ተገን በማድረግ ነዳጅ ወደ ተለያዩ ቦታዎች የሚያንቀሳቅሱ፣ በማከማቸት ለጥቁር ገበያ የሚያዘጋጁና በማደያዎች ላይ በኃይልም ሆነ በማግባባት ነዳጅ የሚያስቀዱ አካላት ላይ ፖሊስ ያለ ምንም ምሕረት ሕጋዊ እርምጃ ይወስዳል።

የነዳጅ እጥረቱን ተከትሎ የሕዝብን እንግልት ለግል ጥቅማቸው ማዋል የሚፈልጉ አካላትን በምንም ዓይነት ሁኔታ አንታገስም።

የክልላችን ሰላምና ኢኮኖሚያዊ ደህንነት የሚጠበቀው በጋራ በምናደርገው ጥረት በመሆኑ፣ ኅብረተሰቡ ይህን ሕገ-ወጥ ድርጊት በመጸየፍና አጠራጣሪ እንቅስቃሴዎችን ለቅርብ ፖሊስ ጣቢያ በመጠቆም የተለመደ ትብብሩን እንዲያደርግ የአማራ ፖሊስ ዋና ጠቅላይ መምሪያ ጥሪውን ያቀርባል።

በአሁኑ ወቅት ፖሊስ የኬላ ቁጥጥሩን ከወትሮው በተለየ በማጠናከር፣ የነዳጅ ሥርጭቱ ሕጋዊ መስመር መያዙን ለማረጋገጥ ሌሊትና ቀን እየሠራ እንደሚገኝ እናረጋግጣለን።


በጀግንነት መጠበቅ በሰበአዊነት ማገልገል!!

የአማራ ክልል ፖሊስ ዋና ጠቅላይ መምሪያ
ባህር ዳር ፤ መጋቢት 2018 ዓ.ም

በሀራ ከተማ የኢድ ዋዜማ የንግድ ትርኢትና ባዛር በድምቀት ተከፈ፣የሀራ ከተማ አስተዳደር ንግድና ገበያ ልማት ጽሕፈት ቤት ከፋሲካ ፕሮሞሽን ኢቨንት ጋር በመተባበር ያዘጋጁት የኢድ ዋዜማ የንግ...
10/03/2026

በሀራ ከተማ የኢድ ዋዜማ የንግድ ትርኢትና ባዛር በድምቀት ተከፈ፣

የሀራ ከተማ አስተዳደር ንግድና ገበያ ልማት ጽሕፈት ቤት ከፋሲካ ፕሮሞሽን ኢቨንት ጋር በመተባበር ያዘጋጁት የኢድ ዋዜማ የንግድ ትርኢትና ባዛር ዛሬ ከመጋቢት 1 ቀን 2018 ዓ.ም በድምቀት ተከፈተ። ለአንድ ሳምንት በሚቆየው በዚህ መድረክ ላይ የከተማው ከንቲባ ኢንጂነር ሙሐመድ ሠኢድን ጨምሮ የከተማው ከፍተኛ የሥራ ኃላፊዎችና ጥሪ የተደረገላቸው እንግዶች ተገኝተዋል።

ባዛሩን በይፋ የከፈቱት የሀራ ከተማ ከንቲባ ኢንጂነር ሙሐመድ ሠኢድ ባደረጉት ንግግር፣ መሰል የንግድ ትርኢቶች ለከተማዋ ኢኮኖሚያዊ እንቅስቃሴ ያላቸውን ፋይዳ ገልጸዋል። ከንቲባው አክለውም "ይህ ባዛር የንግድ ማኅበረሰቡንና ሸማቹን በቀጥታ የሚያገናኝ ትልቅ መድረክ ነው። በተለይ የኢድ በዓልን ምክንያት በማድረግ ነዋሪዎቻችን የሚፈልጓቸውን ምርቶች በአንድ ማዕከልና በተመጣጣኝ ዋጋ እንዲያገኙ በማድረግ ረገድ ሚናው የጎላ ነው" ያሉት ከንቲባው፣ በዓሉን ስናከብርም በመረዳዳትና መተጋገዝ ሊሆን ይገባል ብለዋል።

የንግድና ገበያ ልማት ጽሕፈት ቤት ኃላፊ ያሲን ሙሐመድ በበኩላቸው፣ የዝግጅቱ ዋና ዓለማ የገበያ መረጋጋትን መፍጠርና የንግድ ትስስርን ማጠናከር መሆኑን ገልጸዋል።

ከፋሲካ ፕሮሞሽን ጋር በመሆን ያዘጋጀነው ይህ ባዛር፣ ሸማቹ ማኅበረሰብ ያለ ደላላ ጣልቃ ገብነት ጥራት ያላቸውን ምርቶች ከአምራቾችና ከአቅራቢዎች ጋር እንዲገናኝ ያስችላል። በቆይታውም የንግድ ልውውጡ ፍትሐዊና ለነዋሪው ምቹ እንዲሆን ጥብቅ ክትትል እናደርጋለን" ሲሉ ገልጸዋል።


ይህ የኢድ ዋዜማ የንግድ ትርኢትና ባዛር መጋቢት 1 ጀምሮ ለአንድ ሳምንት ድረስ ለሕዝብ ክፍት ሆኖ የሚቆይ ሲሆን፣ የከተማዋ ነዋሪዎችና የአካባቢው ማኅበረሰብ በስፋት እየጎበኙት ይገኛሉ።

ሀራ ከተማ አስተዳደር ንግድና ገበያ ልማት ጽ/ቤት

የኢድ ዋዜማ የንግድ ትርኢትና ባዛር በሀራ ከተማ መናሀሪያ!!
10/03/2026

የኢድ ዋዜማ የንግድ ትርኢትና ባዛር

በሀራ ከተማ መናሀሪያ!!

19/02/2026

Address

Hara Gebeya

Alerts

Be the first to know and let us send you an email when ሀራ ከተማ አስተዳደር ንግድና ገበያ ልማት ጽ/ቤት posts news and promotions. Your email address will not be used for any other purpose, and you can unsubscribe at any time.

Share