Đổ Thạch Số 1

Đổ Thạch Số 1 ጠቃሚና ሚስጥራዊ መረጃወይም ጥቆማ ካለ በውስጥ መስመር ይጠቁሙን

14/07/2023

👉 የንግድ ስራ ፈቃድ ሳይኖራቸው በሕገወጥ መንገድ እየነገዱ የተገኙት እና በወንጀል የተከሰሱት 1ኛ/ግርማቸው እያሱ መንግስቱ 2ኛ/ባያቸው እያሱ መንግስቱ ለእያንዳንዳቸው የሚታሰብ በ7 አመት ፅኑ እስራት እና በብር=3000 እንዲቀጡ ተወሰነ፦
➤ ተከሳሽዎች በዋና ወንጀል አድራጊነት ተካፋይ በመሆን ሕዳር 21 ቀን2015ዓ/ም በግምት ከለሊቱ 9:00 ሰአት ሲሆን 1ኛ/ተከሳሽ ሸፌር በመሆን የታርጋ ቀጥር ኮድ1 አ.ማ - 41748 በሆነ ባጃጅ 2ኛ/ተከሳሽን አሳፍሮ ከሽዋ ዳቦ ወደጊወርጊስ አደባባይ እያሽከረከረ በመምጣት ላይ እንዳለ በፀጥታ ኃይል ተይዘው ሲፈተሹ በሕገወጥ መንገድ የተጫነ 1ኛ/7 ጀሪካ ባለ 25 ሌትር ቤንዚል 2ኛ/5 ጀሪካ ባለ30 ሌትር ቤንዚል ጠቅላላ ዋጋው ብር=18,616 የሆነው ነዳጅ ተይዞ የጎንደር ከተማ አስተዳደር 3ኛ ፓሊስ ጣቢያ በሰው እና በእግዚቪት ማሰረጃ አስደግፎ ምርመራ አጣርቶ ለማእከላዊ ጎንደር ዞን ፍትህ መምርያ የኢኮኖሚ ነክ ወንጀል ጉዳዮች የስራ ሒደት በመላክ የዞን ዐቃቤ ሕግ የተላከለትን መዝገብ መርምሮ በተከሳሽዎች ላይ1ኛ/ክስ የንግድ ምዝገባ ፈቃድ አዋጅ ቁጥር 980/2008 አንቀፅ 22/1/እና49/2/እና የኢፌዲሪ የወንጀል ሕግ አንቀፅ 32/1/ሀ/ የተመለከተውን በመጥቀስ2ኛ/ ክስ ደግሞ የንግድ ዉድድር እና የሸማችዎች ጥበቃ አዋጅ ቁጥር 813/20.6 አንቀፅ 24/1/ሀ/ለ/አንቀፅ 43/4/5/የተመለከተውን በመጥቀስ ሁለት ክስ መስርቶ ለማእከላዊ ጎንደር ዞን ከፍተኛ ፍ/ቤት በማቅረብ ጉዳዩ በክርክር ቆይቶ ሰኔ 15 ቀን 2015ዓ/ም በዋለው የወንጀል ችሎት ተከሳሽዎች በዐቃቤ ሕግ በኩል የቀረበባቸውን ማስረጃ ማስተባበል ባለመቻላቸው ጥፋተኛ ሆነው በመገኘታቸው ለያንዳንዳቸው የሚታሰብ በ7 አመት ፅኑ እስራት እና በብር=3,000 እንዲቀጡ ፍ/ቤቱ ወስኗል።በሕገወጥ መንገድ የተያዘው ነዳጅ ለመንግስት ውርስ ተደርጓል።
መረጃው
የጎንደር ከተማ ፖሊስ መምሪያ የታ/ወ/ምርመራ ዋና ክፍል ነው

08/07/2023

🛑 በሐሰተኛ መታወቂያ የመገልገል ወንጀል የተከሰሰው ፋሲካው አየልኝ አዳነ በ2 አመት ከ5 ወር ፅኑ አስራት እና በብር=2,000 እንዲቀጣ ተወሰነ፦
➤ ተከሳሽ የካቲት 13 ቀን/2015ዓ/ም በግምት ከምሽቱ 2:00 ሰአት ሲሆን ጎንደር ከተማ ቀበሌ 17 ልዩ ቦታ አውቶፓርኮ በፀጥታ ኃይል ድንገተኛ ፍተሻ ሲደረግ በዞብል ክፍለ ከተማ ቀሐ እየሱስ ቀበሌ ጽ/ቤት የነዋሪ መታወቂያ የተሰጠ በማስመሰል ሐሰተኛ መታወቂያ ይዞ እየተገለገለ በመገኘቱ የጎንደር ከተማ 4ኛ ፓሊስ ጣቢያ በተከሳሹ ላይ ምርመራ አጣርቶ ለማእከላዊ ጎንደር ዞን ፍትህ መምርያ የሙስና ወንጀል ጉዳዮች የስራ ሒደት በመላክ የዞን ዐቃቤ ሕግ መዝገቡን መርምሮ አዋጅ ቁጥር 881/2007 አንቀፅ 23/3/የተመለከተውን ጠቅሶ ክስ መስርቶ ለማእከላዊ ጎንደር ዞን ከፍተኛ ፍ/ቤት በማቅረብ ጉዳዩ በክርክር ቆይቶ ሰኔ 16 ቀን2015ዓ/ም በዋለው የወንጀል ችሎት ተከሳሽ ባቀረበው የመከላከያ ምስክር የዐቃቤ ሕግን ክስና ማስረጃ ማሰሰተባበል/መከላከል ባለመቻሉ ጥፋተኛ ሆኖ በመገኘቱ ፍ/ቤቱ በ2 አመት ከ5 ወር ፅኑ እስራት እና በብር=2,000 እንዲቀጣ ወስኗል።

02/07/2023

👉 በሕገ ወጥ መንገድ የጦር መሳርያ ይዞ በመገኘት የተከሰሰው ዳንኤል ደጀን አማረ በ6 አመት ከ6 ወር ፅኑ እስራት እና በብር=2,000 እንዲቀጣ ተወሰነ፦
➤ ተከሳሽ ጥር 2 ቀን 2015ዓ/ም ከምሽቱ 12:30 ሲሆን ጎንደር ከተማ አይራ ተብሎ ከሚጠራው አካባቢ በመኪና ተሳፍሮ በመሔድ ላይ እንዳለ የፀጥታ ኃይሉ ደንገተኛ ፍተሻ ሲያደርግ 889 የቱርክ ሽጉጥ ጥይት ይዞ በመገኘቱ የጎንደር ከተማ አስተዳደር 3ኛ ፓሊስ ጣቢያ ምርመራ አጣርቶ ለማዐከላዊ ጎነደር ዞን ፍትህ መምርያ በመላክ የዞን ዐቃቤ ሕግ የተላከለትን መዝገብ መርምሮ የጦር መሳርያን ለመቆጣጠር እና ለማስተዳደር የወጣውን አዋጅ ቁጥር 1177/2002 አንቀፅ 4/1/ እና 22/3/የተመለከተውን በመጥቀስ ክስ መስርቶ ለማእከላዊ ጎንደር ዞን ከፍተኛ ፍ/ቤት በማቅብ ጉዳዩ በክርክር ቆይቶ በ30/9/2015ዓ/ም በዋለው የወንጀል ችሎት ተከሳሽ ባቀረበው የመከላከያ ማስረጃ የዐቃቤ ሕግን ክስና ማስረጃ ማስተባበል ባለመቻሉ ጥፋተኛ ሆኖ በመገኘቱ በ6 አመት ከ6 ወር ፅኑ እስራት እንዲቀጣ ተወስኗል።
በእግዚቪት የተያዙት 889 የቱርክ ሽጉጥ ጥይት በውርስ ለመንግስት ገቢ ሆኗል።

በአማራ ፖሊስ ኮሌጅ ለ10ኛ ዙር የሠለጠኑ የፖሊስ አባላት 20ኛ አመታቸዉን አከበሩ፡፡ በ1995 ዓ.ም ከሁሉም የክልሉ አካባቢዎች ተመልምለው በቀደመው የአማራ ፖሊስ ማሰልጠኛ ተቋም በአሁኑ ፖ...
07/06/2023

በአማራ ፖሊስ ኮሌጅ ለ10ኛ ዙር የሠለጠኑ የፖሊስ አባላት 20ኛ አመታቸዉን አከበሩ፡፡

በ1995 ዓ.ም ከሁሉም የክልሉ አካባቢዎች ተመልምለው በቀደመው የአማራ ፖሊስ ማሰልጠኛ ተቋም በአሁኑ ፖሊስ ኮሌጅ የ10ኛ ዙር/ኮርስ ስልጠናን የተከታተሉት ሠልጣኞች ስራ ከጀመሩ ሃያ/20/ አመት ሞልቷቸዋል፡፡
ያኔ ስልጠናውን የተከታተሉ ምልምሎች ዛሬ በተቋሙ ከፍተኛ የአመራር እርከን የሚያገለግሉትን ጨምሮ ከተቋሙ ወጭ በተለያዩ ተግባራት ተሰማርተው ይገኛሉ። ትላንትን ለማስታወስ ነገን ለማጠናከር አንድነትን ለማጉላት ያለመ የኮርሱ የጋራ መድረክ ተሰናድቷል የበአሉ ዝግጅት አስተባባሪ ዋና ሳጅን ትእግስት መልሰዉ እንደገለፁት በስራ ላይ ያሉትን ፣ከተቋሙ የለቀቁትን፣ በሀገር ዉስጥም በዉጭም የሚገኙ የኮርሱ ሠልጣኞችን በማህበራዊ መገናኛ በማሰባሰብ ዝግጅቱን ማክበር መቻላቸዉን ዋና ሳጅን ትእግስት ገልፀዋል፡፡

ዝግጅቱን በፖሊስ ኮሌጁ የማክበር አላማዉም ተቋማዊ ፍቅርን ለማጠናከርና ኮርሱን አሰልጥነዉና ፖሊሳዊ ሳይንስን አስተምረዉ በስራ ብቁ ያደረጉ በስነምግባር አንፀዉ የሠልጣኞችን የህይወት ጉዞ ዉጤታማ እንዲሆን ላደረጉ አሠልጣኞችና መምህራንን በአካል ምስጋና ለማቅረብ ታስቦ እንደሆነም ዋና ሳጅን ትእግስት አስረድተዋል፡፡
አባላቱ በበኩላቸው ዝግጅቱ የ20 ዓመት የህይወት ጉዟቸውንና ተቋማዊ አበርክቷቸውን መለስብለው እንዲቃኙ ከማስቻሉም በላይ አንድነትን በማጠናከር የመረዳዳትና የመተጋገዝ ልምድን ለማስቀጠል ማቀዳቸውን አንስተዋል፡፡
ዝግጅቱ በፎቶ ኢግዚቨሽን፣ የሰለጠኑባቸውን ቦታና መማሪያ ክፍሎች በመጎብኘት፣ በደብረ ማርቆስ ጨሞጋ ረጫ፣በፖናል ውይይትና በሌሎች የመዝናኛ መርሀ ግብሮች የቀድሞ አሰልጣኞች ፣የማሠልጠኛዉ ሀላፊ የነበሩት ኮማንደር አድማሱ መኮነን ጨምሮ ጥሪ የተደረገላቸዉ እንግዶች ተገኝተዋል፡፡
ዘጋቢ፦ረ/ኢ/ር ምህረትአብ እስጢፋኖስ

👋በህይወት ስትኖር ማወቅ ያለብህ 3 ነገሮች !     1⃣ የምትፈልገውን ሳይሆን የሚገባህን ነው የምታገኘው።    2⃣ ለብዙ ሰው የሚያስፈልገውን ስታደርግ የምትፈልገውን ሁሉ ታገኛለህ ።   ...
12/05/2023

👋በህይወት ስትኖር ማወቅ ያለብህ 3 ነገሮች !

1⃣ የምትፈልገውን ሳይሆን የሚገባህን ነው የምታገኘው።
2⃣ ለብዙ ሰው የሚያስፈልገውን ስታደርግ የምትፈልገውን ሁሉ ታገኛለህ ።
3⃣ ስትፈልገዉ ያጣከውን ሲፈልግህ ታገኘዋለህ ።

መልካም ቀን ተመኘን 🙏

11/09/2022
የአማራ ልዩ ኀይል የአንደኛ ዙር ኮማንዶ አባላት ተመርቀዋልሐምሌ 28/2014 ዓ.ምለአማራ ህዝብ ብሎም ለኢትዮጵያ አሌንታ የሚሆኑ ለመጀመሪያ ጊዜ የአማራ ልዩ ኀይል ኮማንዶ አባላት ተመርቀዋል...
04/08/2022

የአማራ ልዩ ኀይል የአንደኛ ዙር ኮማንዶ አባላት ተመርቀዋል

ሐምሌ 28/2014 ዓ.ም
ለአማራ ህዝብ ብሎም ለኢትዮጵያ አሌንታ የሚሆኑ ለመጀመሪያ ጊዜ የአማራ ልዩ ኀይል ኮማንዶ አባላት ተመርቀዋል። በስነ-ስርዓቱ ይልቃል ከፋለ (ዶ.ር) የአማራ ክልል ርዕሰ መስተዳድር፣ ጀኔራል አበባው ታደሰ የኢፌዲሪ መከላከያ ሰራዊት ምክትል ኢታማዦር ሹም፣ የፌደራል ፖሊስ ምክትል ኮሚሽነር ጀኔራል ዘላለም መንግስቴን ጨምሮ የክልሉ ከፍተኛ የስራ ኀላፊዎችና ከፍተኛ የፖሊስ መኮንኖች ተገኝተው መርቀዋል።

የአማራ ክልል ፖሊስ ኮሚሽን ይጠቀምበት የነበረውን አርማ ቀየረ።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።የክልላችን ፖሊስ እያደረገ ካለው ሪፎርም ጋር የሚመጥን አርማ በማስፈለጉ ከዚህ በፊት ይጠቀምበ...
13/05/2022

የአማራ ክልል ፖሊስ ኮሚሽን ይጠቀምበት የነበረውን አርማ ቀየረ
።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።
የክልላችን ፖሊስ እያደረገ ካለው ሪፎርም ጋር የሚመጥን አርማ በማስፈለጉ ከዚህ በፊት ይጠቀምበት የነበረውን አርማ መቀየሩን በይፋዊ የቴሌግራም ገፁ ይፋ አድርጓል

በም/ኮ/ር ካሳሁን ፀጋው ሞት  ጥልቅ ሀዘን ተሰመቶናል ለወዳጅ ዘመዶቹና ለስራ ባልደረቦቹ መጽናናትን እንመኛለን//የጎንደር ከተማ አስተዳደር ፖሊስ መምሪያመጋቢት 14/2014ዓም
23/03/2022

በም/ኮ/ር ካሳሁን ፀጋው ሞት ጥልቅ ሀዘን ተሰመቶናል ለወዳጅ ዘመዶቹና ለስራ ባልደረቦቹ መጽናናትን እንመኛለን//
የጎንደር ከተማ አስተዳደር ፖሊስ መምሪያ
መጋቢት 14/2014ዓም

የአስቸኳይ ጊዜ አዋጅ ተነሳየሚኒስትሮች ምክር ቤት ለስድስት ወር ተደንግጎ የነበረው የአስቸኳይ ጊዜ አዋጅ እንዲነሳ ወሰነ። ምክር ቤቱ ዛሬ ረቡዕ ጥር 18 ቀን 2014 ዓም ባካሄደው ስብስባ፤...
27/01/2022

የአስቸኳይ ጊዜ አዋጅ ተነሳ

የሚኒስትሮች ምክር ቤት ለስድስት ወር ተደንግጎ የነበረው የአስቸኳይ ጊዜ አዋጅ እንዲነሳ ወሰነ።
ምክር ቤቱ ዛሬ ረቡዕ ጥር 18 ቀን 2014 ዓም ባካሄደው ስብስባ፤ የአስቸኳይ ጊዜ አዋጁ የተፈጻሚነት ጊዜ እንዲያጥር ያደረገው አዋጁን ማውጣት “የግድ አስፈላጊ እንዲሆን አድርጎ የነበረው ሁኔታ የተቀየረ በመሆኑና ስጋቱን በመደበኛው የሕግ ማስከበር ስራ መከላከልና መቆጣጠር የሚቻልበት ደረጃ ላይ በመድረሱ፣ ውሳኔውን ማስተላለፉን ጠቅላይ ሚኒስትር ጽሕፈት ቤት አስታውቋል።

በጎንደር ከተማ የጥምቀት በዓል በሰላም ተከብሯል። በታሪካዊቷ ጎንደር ከተማ በመከበር ላይ የሚገኘው የጥምቀት በዓል ካደሩበት ጥምቀተ ባህር በሰላም ወደ አጥቢያ ቤተክርስቲያናቱ ገብተዋል። ታቦ...
19/01/2022

በጎንደር ከተማ የጥምቀት በዓል በሰላም ተከብሯል።

በታሪካዊቷ ጎንደር ከተማ በመከበር ላይ የሚገኘው የጥምቀት በዓል ካደሩበት ጥምቀተ ባህር በሰላም ወደ አጥቢያ ቤተክርስቲያናቱ ገብተዋል።

ታቦታቱ ወደ አጥቢያ ቤተክርስቲያን በሰላም እንዲገቡ የከታማዋ የፀጥታ ኀሎች እና ሰላም ወዳዱ የጎንደር ከተማ ህዝብ የነበራቸው ተሳትፎ ጉል ነበር።

የዘንድሮውን የጥምቀት በዓል በጎንደር ከተማ ለማክበር በነቂስ ከታደው የከተማዋ ምዕመናን በተጨማሪ ከተለያዩ ሀገራት የመጡም ኢትዮጵያዊያን እና የውጭ ሀገር ዜጎች ለበዓሉ ልዩ ድምቀት የሰጡት ሲሆን በጥምቀተ ባህሩ ላይም የክልሉን ርዕሰ መስተዳድር ጨምሮ የፌደራልና የክልል የስራ ኀላፊዎች እንዲሁም አርቲስቶች እና የሰባአዊ መብት ተማጋቾች ተገኝተዋል።

የነበረውን የትራፊክ መጨናነቅ የከተማዋ የትራፊክ ፖሊሶችም ባደረጉት ጉልህ ተሳትፎ ያለምንም የትራፊክ አደጋ እና ያለምንም የፀጥታ ችግር በዓሉ በሰላም ተከብሯል።
ለመላው ህዝባችን እንኳን ደስ ያለን እያልን ቀጣይ ስራዎቻችንም እንዲህ በአንድነት እያሳካን የጠላቶቻችን አንገት እንደምናስደፋ እናምናለን

ለቀድሞ የኢትዮጵያ ሰራዊት አባላት ጥሪ ቀረበየአገር መከላከያ ሚኒስቴር ለቀድሞ የኢትዮጵያ ሰራዊት አባላት ጥሪ አቅርቧል፡፡በኢትዮጵያ እየተደረገ ያለውን ሃገርን የማፍረስ ሴራ በማክሸፍ አገርን...
05/11/2021

ለቀድሞ የኢትዮጵያ ሰራዊት አባላት ጥሪ ቀረበ

የአገር መከላከያ ሚኒስቴር ለቀድሞ የኢትዮጵያ ሰራዊት አባላት ጥሪ አቅርቧል፡፡

በኢትዮጵያ እየተደረገ ያለውን ሃገርን የማፍረስ ሴራ በማክሸፍ አገርን የማዳን ዘመቻ ላይ ባላቸው እውቀት ልምድ እና አቅም ከአገር መከላከያ ሠራዊት ጎን በመሰለፍ ይህ አፍራሽ ሃይል እስኪደመሰስ ድረስ የበኩላቸውን ድርሻ ለመወጣት ባላቸው ተነሳሽነት ከሀገር መከላከያ ጎን በመቆም አቅማቸውና እውቀታቸው የፈቀደውን አስዋፅኦ ለማበርከት ጥያቄ አቅርበዋል፡፡

በዚሁ መሠረት ይህንን ተልዕኮ መወጣት የሚያስችል አካላዊ ሁኔታ ፣ የጤና ፣ የስነ – አእምሮ ዝግጁነት ፣ እውቀት እና ልምድ ያላቸውን አባላት ከዚህ በታች የተቀመጠውን መስፈርት ለሚያሟሉ የቀድሞ የሀገር መከላከያ ሠራዊት አባላት የወጣ መስፈርት እንደሚከተለው ቀርቧል፡-

1. አጠቃላይ መስፈርቶች

1.1. የኢፌዴሪ ሀገ – መንግስትን የተቀበሉ ፣

1.2. በህዝቦች ሉአላዊነትና አንድነት የሚያምኑ እና በፅናት ለማገልገል ሙሉ ፍቃደኝነት ያላቸው ፣

1.3. ከማንኛውም የፖለቲካ ድርጅቶች ወገናዊነት ነፃ የሆኑ ፣

1.4. በወንጀል ይሁን በፍታብሄር ተከሶ የፍርድ ቤት ክርክር የሌለባቸው

1.5. መከላከያ የሚያሰማራቸው የጦር ክፍሎች ሁሉ ተዘዋውረው ለመስራት ሙሉ ፍቃደኛ የሆኑና የአካል ብቃት ያላቸው ፣

1.6. ለእግረኛ አዋጊ መኮንኖች ፣ ሻለቃ አመራርና ከዚያ በላይ ሃላፊነት የነበራቸው ፣

1.7. በየትኛውም የማዕረግ ደረጃ ላይ በየማሰልጠኛ ማዕከላት አሰልጣኝ የነበሩ እና ማስረጃ ማቅረብ የሚችሉ ፣

1.8. የሜካናይዝድ እና የቡድን መሳሪያ አመራርና ምድብተኛ የነበሩ ፣

1.9. የጤንነት ሁኔታን በተመለከተ

– የአይን ፣ የአፍንጫ ፣ የጆሮ ፣ የጥርስ ፣ የከንፈር ፣ ችግር የሌለባቸው ፣

– ከቲቢ ፣ ከሚጥል በሽታ ፣ ከስኳር ፣ ከደም ግፊት ፣ ከኪንታሮት ፣ከእንቅርት በሽታዎች ነፃ የሆኑ እና ለእንቅስቃሴ አስቸጋሪ የሆነ አካላዊ ችግር የሌለባቸው ( የማያነክስ ) ፣

1.10. የትምህርት ሁኔታ ማቀድ ፣ ማሠልጠን ፣ የስልጠና ዶክሜንት ማዘጋጀት የሚያስችል የትምህርት ዝግጅት ያለው፣

1.11. በሚመለመልበት አካባቢ ከቀበሌ ፣ ከመስተዳድር እና ከፖሊስ
ከወንጀል ነፃ ስለመሆናቸው የፅሁፍ ማስረጃ ማቅረብ የሚችሉ ፣

1.12. የቀድሞ ጦር ሠራዊት አባል ስለመሆናቸው ማስረጃ ማቅረብ የሚችሉ ፡፡

2. ዕድሜን በተመለከተ፡-

2.1. ከወታደር እስከ ከፍተኛ የበታች ሹም ያሉ ከ55 ዓመት ያልበለጡ ፣
2.2. መስመራዊ መኮንኖች ከ60 አመት ያልበለጡ ፣

2.3. ከሻለቃ በላይ ያሉ ከፍተኛ መኮንኖች ከ64 ዓመት ያልበለጡ መሆን አለባቸው፡፡

3. የምልመላ ቦታና ጊዜ ፡-

-ለአዲስ አበባ ተመዝጋቢዎች በየክፍለ ከተማቸው ሲሆን

– ለክልል ተመዝጋቢዎች በየአካባቢያችሁ ባሉ የቀበሌ ፣ የወረዳ

አስተዳደርና የፀጥታ ወይም ሚሊሻ ፅ/ቤት በአካል በመቅረብ መመዝገብ ይቻላል

– የምዝገባ ጊዜው ከህዳር 01 ቀን 2014 ዓ/ም እስከ ህዳር 15 ቀን 2014 ዓ/ም ድረስ ይሆናል፡፡

– በሁሉም የምዝገባ ጣቢያዎች ዝርዝር መስፈርቶች ተለጥፎ የሚገኙ መሆኑ ተገልጿል፡፡

አካባቢዎን ይጠብቁ!

ወደ ግንባር ይዝመቱ!

መከላከያን ይደግፉ!

Address

BELEKO
Gondar
0918032118

Telephone

+251918032118

Website

Alerts

Be the first to know and let us send you an email when Đổ Thạch Số 1 posts news and promotions. Your email address will not be used for any other purpose, and you can unsubscribe at any time.

Contact The Organization

Send a message to Đổ Thạch Số 1:

Share