Welqait Tegede Tellemt Amhara Scholars Association

Welqait Tegede Tellemt Amhara Scholars Association This is legally registered association founded on Yekatit 22/2012 E.C.

በዛሬዉ ቀን ሰኔ 7/2016 ዓ/ም የማህበሩ የምንግዜም አምባሳደር ከሆኑት ወ/ሮ ጥሩወርቅ ሰረበ የተገኘ ድጋፍ በዓይነት፦ለወልቃይት ጠገዴ ሰቲት ሁመራ ዞን ጤና መምርያ ስማቸዉ ግደይ የሚከተሉ...
14/06/2024

በዛሬዉ ቀን ሰኔ 7/2016 ዓ/ም የማህበሩ የምንግዜም አምባሳደር ከሆኑት ወ/ሮ ጥሩወርቅ ሰረበ የተገኘ ድጋፍ በዓይነት፦

ለወልቃይት ጠገዴ ሰቲት ሁመራ ዞን ጤና መምርያ ስማቸዉ ግደይ የሚከተሉት ዝርዝር የህክምና ቁሳቁስ አስረክበናል።

✔️6 የደም ግፊት መለኪያ/BP Apparatus
✔️3 የሙቀት መለኪያ/No Touch Infrared Thermometer
✔️5 የደም ኦክስጅን መጠን መለኪያ/Pulse Oximeter

ናቸዉ።

በርክክቡ የምሁራን ማህበሩ ከፍተኛ አመራሮች በአካል ተገኝተናል።
****ወጠጠአምማ***

በአማራ ክልል ወልቃይት ጠገዴ ሰቲት ሁመራ ዞን የ8ኛ ክፍል ፈተና ዛሬ መሰጠት እንደተጀመረ ዞኑ አስታውቋል።በአካባቢው አንጻራዊ ሰላም በመኖሩ ትምህርታቸውን በአግባቡ ሲከታተሉ የነበሩ 5 ሺህ...
11/06/2024

በአማራ ክልል ወልቃይት ጠገዴ ሰቲት ሁመራ ዞን የ8ኛ ክፍል ፈተና ዛሬ መሰጠት እንደተጀመረ ዞኑ አስታውቋል።

በአካባቢው አንጻራዊ ሰላም በመኖሩ ትምህርታቸውን በአግባቡ ሲከታተሉ የነበሩ 5 ሺህ 197 የ8ኛ ክፍል ተማሪዎች ፈተናውን በመውሰድ ላይ ይገኛሉ ነው የተባለው።

በዞኑ 108 ትምህርት ቤቶች ላይ ፈተናው እየተሰጠ እንደሚገኝም የወልቃይት ጠገዴ ሰቲት ሁመራ ዞን ትምህርት መምሪያ ኀላፊ ገብረማርያም መንግሥቴ ገልጸዋል።

በ2015 የትምህርት ዘመን የ8ኛ ክፍል ፈተና ከወሰዱ ተማሪዎች ከ70 በመቶ በላይ ወደ ቀጣይ ክፍል ማለፋቸውን ያስታወሱት የመምሪያ ኀላፊው በ2016 የትምህርት ዘመን በአዲስ መልክ ለመጀመሪያ ጊዜ እየተሰጠ በሚገኘው የ8ኛ ክፍል ፈተና ተማሪዎች የተሻለ ውጤት እንዲያስመዘግቡ መሠራቱን ተናግረዋል።

ተማሪዎች በፈተናው ውጤታማ እንዲኾኑ ከፈተና በፊት የማካካሻ ትምህርት እና አጋዥ ጥያቄዎችን በማዘጋጀት ለተማሪዎች በመስጠት ድጋፍ ሲሰጥ መቆየቱንም አንስተዋል።

ለተማሪዎች እየተሰጠ የሚገኘው ፈተና በዞኑ በሚገኙ ከተማ አሥተዳደሮች እና ወረዳዎች ያለምንም የጸጥታ ችግር እየተከናወነ ነው።

የፈተና አሰጣጡ ከኩረጃ የጸዳ እንዲኾን "በአንድ ወንበር አንድ ተማሪ" በማስቀመጥ ፈተናው እየተሰጠ እንደሚገኝ እና የፈተና አሰጣጡ ሂደት ጥንቃቄ የተሞላበት መኾኑን በመፈተኛ ትምህርት ቤቶች በመገኘት ማረጋገጣቸውን አቶ ገብረማርያም መንግሥቴ ተናግረዋል።

***አንጎትኛ***ወልቃይት ጠገዴ አማራ ማህበረሰብየስርግ ስነ ስርዓት መኃላ/ባህላዊ ቃልኪዳንየሴት ሙሽራ ሽማግሌ ተወካይ፦ ምንድን ነው ውላችን?የወንድ ሙሽራ ሽማግሌ ተወካይ፦ አንጎትኛየሴት ሙ...
09/06/2024

***አንጎትኛ***

ወልቃይት ጠገዴ አማራ ማህበረሰብ
የስርግ ስነ ስርዓት መኃላ/ባህላዊ ቃልኪዳን

የሴት ሙሽራ ሽማግሌ ተወካይ፦ ምንድን ነው ውላችን?
የወንድ ሙሽራ ሽማግሌ ተወካይ፦ አንጎትኛ

የሴት ሙሽራ ሽማግሌ ተወካይ፦ አጤ ይሙት መንግስት ይሙት?
የወንድ ሙሽራ ሽማግሌ ተወካይ፦ አጤ ይሙት መንግስት ይሙት

ቃል በአንጎትኛ ታሰረ
ፍቅር በተዋህዶ ከበረ

ድንቅ መፅኃፍ በልማት ሙሉ አለማየሁ

****ወጠጠአምማ****

በወልቃይት ጠገዴ ሰቲት ሁመራ ዞን 2015 ዓ/ም ማለፍያ ነጥብ በማስመዝገብ ወደ ከፍተኛ ትምህርት ተቋማት ያለፉ 39 ተማሪዎች ለእያንዳንዳቸዉ 2,560 ብር ከወልቃይት ጠገዴ ተወላጅ በሰሜን ...
01/06/2024

በወልቃይት ጠገዴ ሰቲት ሁመራ ዞን 2015 ዓ/ም ማለፍያ ነጥብ በማስመዝገብ ወደ ከፍተኛ ትምህርት ተቋማት ያለፉ 39 ተማሪዎች ለእያንዳንዳቸዉ 2,560 ብር ከወልቃይት ጠገዴ ተወላጅ በሰሜን አሜሪካ ወ/ሮ ጥሩወርቅ ሰረበ የተገኘ ሙሉድጋፍ ሽልማት/ማበረታቻ ተደርጓል።

ከሁለት ወር በፊት በዞኑ ከፍተኛ ዉጤት ያስመዘገቡ 2 ወንድ እና 2 ሴት ተማሪዎች ለእያንዳንዳቸዉ ላፕቶፕ መሸለማችን ይታወሳል።

የሁሉጊዜ የማህበሩ አጋር የሆኑት ወ/ሮ ጥሩወርቅ በማህበሩ ስም እንደወትሮዉ ከልብ እናመሰግናለን።

*ወጠጠአምማ*

***ወጠጠአምማ***ከወልቃይት ጠገዴ ጠለምት የተፈናቀለ ማህበረሰብ ማን ነው?ጥናታዊ ፅሁፍሚያዝያ 13/2016 ዓ/ም
21/04/2024

***ወጠጠአምማ***

ከወልቃይት ጠገዴ ጠለምት የተፈናቀለ ማህበረሰብ ማን ነው?

ጥናታዊ ፅሁፍ
ሚያዝያ 13/2016 ዓ/ም

በወ/ጠ/ሰ/ሁመራ ዞን 2015 የትምህረት ዘመን የ12ኛ ክፍል መልቀቂያ ፈተና ከፍተኛ ውጤት ያመጡ ተማሪዎች1.አስረሱ ምስጋናው/ተፈጥሮ ሳይንስ _530*ማክሰኞ ገበያ2.ተመስገን አቡሆይ/ማህበራ...
01/04/2024

በወ/ጠ/ሰ/ሁመራ ዞን 2015 የትምህረት ዘመን የ12ኛ ክፍል መልቀቂያ ፈተና ከፍተኛ ውጤት ያመጡ ተማሪዎች

1.አስረሱ ምስጋናው/ተፈጥሮ ሳይንስ _530*ማክሰኞ ገበያ
2.ተመስገን አቡሆይ/ማህበራዊ ሳይንስ_361*ማክሰኞ ገብያ
3.ሂወት ሲሳይ /ተፈጥሮ ሳይንስ_431*ዳንሻ
4.ሜሮን ገዜ ኪዳን/ማህበራዊ ሳይንስ_305*ሁመራ

ወጠጠአምማ

በአብክመ ትምህርት ቢሮ የወልቃይት ጠገዴ ሰቲት ሁመራ ዞን የትምህርት መምርያ የ9 ወር ስራ አፈፃፀም ግምገማ ከወረዳ ሱፐርቫይዘሮች፣ ርዕሰ መምህራን፣ የቡድን መሪዎች እና ጽ/ቤት ኃላፊዎች በ...
01/04/2024

በአብክመ ትምህርት ቢሮ የወልቃይት ጠገዴ ሰቲት ሁመራ ዞን የትምህርት መምርያ የ9 ወር ስራ አፈፃፀም ግምገማ ከወረዳ ሱፐርቫይዘሮች፣ ርዕሰ መምህራን፣ የቡድን መሪዎች እና ጽ/ቤት ኃላፊዎች በወፍአርግፍ ከተማ ከመጋቢት 21-22/2016 ዓ/ም አካሂዷል።

የወልቃይት ጠገዴ ጠለምት አማራ ምሁራን ማህበር በያዝነዉ ዐመት በትምህርት ዙርያ የተሰሩ ስራዎች አጭር ማብራሪያ አቅርቧል።

ማህበሩ በ2015 ዓ/ም የ12ኛ ክፍል ተፈጥሮ ሳይንስ እና ማህበራዊ ሳይንስ ከፍተኛ ዉጤት ያመጡ ሁለት ወንድ እና ሁለት ሴት ተማሪዎች hp core i5 ላፕቶፕ ሽልማት ሸልሟል።

ይህን የላፕቶፕ ሽልማት እና በቀጣይ የምንገልፃቸዉ ሌሎች የትምህርት ቤት ድጋፎች ሙሉ ድጋፍ ያደረጉልን ነዋሪነታቸዉ በሰሜን አሜሪካ ያደረጉት የወልቃይት ጠገዴ ተወላጅ ወ/ሮ ጥሩወርቅ ሰረበ ናቸዉ።

ወ/ሮ ጥሩወርቅ በትምህርቱ ዘርፍ በርካታ ድጋፎች በማድረግ ይታወቃሉ። ይህም ማህበሩ እንደወትሩ በያዝነዉ ዐመት ላደረጉት በጎ ተፅዕኖ ከፍ ያለ ምስጋና ያቀርባል።

የጠገዴ ወረዳ ትምህርት ጽ/ቤት ለምሁራን ማህበሩ የምስጋና እና ምስክር ወረቀት አበርክቷል። እናመሰግናለን።

ሽልማቱ በየአመቱ በቀጣይነት የሚከናወን ይሆናል።

*የማህበረሰባችን ዘርፈብዙ ችግሮች ለመፍታት እንተጋለን!*

የወልቃይት ጠገዴ ጠለምት አማራ ምሁራን ማህበር
ሁመራ

***ወጠጠአምማ***ታራካችን በወያኔ እጅ በወደቀበት ዘመን ፅኑ፣ ዘመን ተሻጋሪ ዕይታ በመያዝ ይሄን ዳግማዊ አያናይዝጊ/ደጃዝማች አያናይዝጊ ዘወልቃይት፤ በአፄ ፋሲል ጎንደር ዘመነ መንግስት በ...
09/02/2024

***ወጠጠአምማ***
ታራካችን በወያኔ እጅ በወደቀበት ዘመን ፅኑ፣ ዘመን ተሻጋሪ ዕይታ በመያዝ ይሄን ዳግማዊ አያናይዝጊ/ደጃዝማች አያናይዝጊ ዘወልቃይት፤ በአፄ ፋሲል ጎንደር ዘመነ መንግስት በድንቅ ኪነ ህንፃ ጥበብ የታነፀዉ ቤተ ሞሎ ቤተ መንግስት በማህበሩ ሎጎ እንዲቀመጥ የማህበሩ አባላት ብዙ ደክመናል።

አሁን ታሪኩ በዚህ ደረጃ ከፍ ብሎ ለማየት ስለበቃን ኩራት ይሰማናል።

ዘጋቢ፡- "የዘመን መስታወት" ቤተ ሞሎ ቤተ - መንግስት ወልቃይት ጠገዴ

4HP Laptops !በቅድምያ የከበረ ምስጋና ለውድ  Tiruwork Serebe ይሁንልን!በትናንትናው ዕለት ማህበራችን በሀገረ አሜሪካ ከምትኖረው ውድ እህታችን ጥሩወርቅ ሰረበ በ2015 ዓ/ም...
18/01/2024

4HP Laptops !

በቅድምያ የከበረ ምስጋና ለውድ Tiruwork Serebe ይሁንልን!

በትናንትናው ዕለት ማህበራችን በሀገረ አሜሪካ ከምትኖረው ውድ እህታችን ጥሩወርቅ ሰረበ በ2015 ዓ/ም የ12ኛ ክፍል የዩኒቨርስቲ መግቢያ ወጤት በወልቃይት ጠገዴ ሰቲት ሁመራ ዞን ለሶስት ከፍተኛ ውጤት ላመጡ ተማሪዎቻችና አንድ በልዩ ሁኔታ የማበረታቻ ሽልማት ለ Laptop መግዣ የሚሆን በለገሰችው ገንዘብ መሰረት :- .....

Core i5, 16GB RAM, 512GB SSD, 8th generation 4 HP laptops ገዝቷል በቅርቡ ወደ ውጤታማ ተማሪዎቻችን እጅ ይደርሳል!

ክብርና ምስጋና ለውድ የዘወትር ድጋፍ አድራጊ በተለይ በትምህርትና ተማሪዎች ዙሪያ የማበረታታት ጉዳይ የላቀ ተነሳሽነት ያላት ክብርት እህታችን ይሁን!!! በወጣ ይተካ! እግዚአብሔር ካንቺ ጋር ይሁን!
ማህበራችን ላደረግሽው በጎ ስራ ሁሉ ሁሌም ከልብ ያመሰግናል!

#ኑትውልድእናበረታታ!

የሀዘን መልዕክትየማህበሩ መስራች እና አባል የነበረዉ ወንድማችን ንጋት ተክሌ ከዚህ ዐለም በሞት ተለይቶናል። የወንድማችን ህልፈተ ህይወት ልብ ሰባሪ እና አስደንጋጭ ነው። ንጋት ሠዉ አክባሪ፣...
12/01/2024

የሀዘን መልዕክት

የማህበሩ መስራች እና አባል የነበረዉ ወንድማችን ንጋት ተክሌ ከዚህ ዐለም በሞት ተለይቶናል። የወንድማችን ህልፈተ ህይወት ልብ ሰባሪ እና አስደንጋጭ ነው። ንጋት ሠዉ አክባሪ፣ ታታሪ፣ ደፋር እና ቁርጠኛ ሠዉ ነበር።

የካቲት 22/2012 ከማህበሩ መመስረት ግዮን ሆቴል ባደረግነዉ ስብሰባ ታሪካዊ ኃላፊነቱ የተወጣ ወንድም ነበር።
ጥቅምት 24/2013 ከአአ ወደ ግንባር በመሄድ ዘምቷል።
ኃዘኑ መራር ነው።

በዛሬው ዕለት 03/05/2016 ዓ/ም በደብረ ሊባኖስ ገዳም የቀብር ስነስርዓቱ ተፈፅሟል።

ፈጣሪ የወንድማችን ነብስ በአፀደ ገነት ያኑርልን።
ለቤተሰቡ፣ ወዳጅ ቤተሰብ እና የማህበሩ አባላት ፈጣሪ መፅናናቱን ይስጠን።

12/12/2023
ጥቅምት 30ማይካድራ የአማራ ጭፍጨፋ 3ኛ ዐመት መታሰብያ
10/11/2023

ጥቅምት 30
ማይካድራ የአማራ ጭፍጨፋ
3ኛ ዐመት መታሰብያ

Address

Gondar

Telephone

+251921128030

Website

Alerts

Be the first to know and let us send you an email when Welqait Tegede Tellemt Amhara Scholars Association posts news and promotions. Your email address will not be used for any other purpose, and you can unsubscribe at any time.

Contact The Organization

Send a message to Welqait Tegede Tellemt Amhara Scholars Association:

Share