ሰሜን ጎንደር ዞን ብልፅግና ፓርቲ ቅ/ጽ/ቤት North Gondar Zone Prosperity Party

  • Home
  • Ethiopia
  • Gondar
  • ሰሜን ጎንደር ዞን ብልፅግና ፓርቲ ቅ/ጽ/ቤት North Gondar Zone Prosperity Party

ሰሜን ጎንደር ዞን ብልፅግና ፓርቲ ቅ/ጽ/ቤት
North Gondar Zone Prosperity Party ኢትዮጵያ የብልፅግና ተምሳሌት ሀገር ለመሆን ቀን ከሌት እየሰራች ትገኛለች

በሰሜን ጎንደር ዞን በደባርቅ ምርጫ ክልል የደባርቅ ከተማ አስተዳደር የ31 ምርጫ ጣቢያ የአፈፃፀም ግምገማ ተካሄደ።ግንቦት 28/2018 በ31ዱ የምርጫ ጣቢያዎች ያለምንም የፀጥታ ችግር በሰላ...
05/06/2026

በሰሜን ጎንደር ዞን በደባርቅ ምርጫ ክልል የደባርቅ ከተማ አስተዳደር የ31 ምርጫ ጣቢያ የአፈፃፀም ግምገማ ተካሄደ።

ግንቦት 28/2018 በ31ዱ የምርጫ ጣቢያዎች ያለምንም የፀጥታ ችግር በሰላማዊ ፣ ዲሞክራሲያዊ እና ፍትሃዊ በሆነ መንገድ በስኬት መካሄዱ በመድረኩ ተነስቶል።

"ሚሊሻው የሕዝባዊነትን ትርጉም በተግባር ያሳየ ኃይል ነው" ኮሚሽነር አስቻለ አላምሬ  የአማራ ክልል ሚሊሻ ኮሚሽን ግንቦት 29/2018 ዓ.ም በክልል ደረጃ የሚካሄደውን የሚሊሻ 30ኛ ዓመት ...
05/06/2026

"ሚሊሻው የሕዝባዊነትን ትርጉም በተግባር ያሳየ ኃይል ነው" ኮሚሽነር አስቻለ አላምሬ

የአማራ ክልል ሚሊሻ ኮሚሽን ግንቦት 29/2018 ዓ.ም በክልል ደረጃ የሚካሄደውን የሚሊሻ 30ኛ ዓመት የምሥርታ በዓል እና የእውቅና መርሐ ግብር አስመልክቶ መግለጫ ሰጥቷል።

መግለጫውን የሰጡት የአማራ ክልል ሚሊሻ ኮሚሽን ኮሚሽነር አስቻለ አላምሬ የሚሊሻ 30ኛ ዓመት ክብረ በዓል የሚሊሻውን ታሪካዊ ተጋድሎ እና መስዋዕትነቱን ለመዘከር የታሰበ ነው ብለዋል።

በዓሉ ለሚሊሻ አባላት እና ለቤተሰቦቻቸው ክብር እና ምስጋና ለማቅረብ፤ ተቋማዊ ሪፎርም እና ዝግጁነቱን ለማረጋገጥ፤ የሕዝቡን እና የሚሊሻውን ትስስር ለማጥበቅ እና ሌሎች ዋና ዋና ዓላማዎች እንዳሉትም አንስተዋል።

ግንቦት 29/2018 ዓ.ም የአማራ ክልል ሚሊሻ የ30 ዓመታት የጀግንነት እና የሕዝባዊነት ጉዞ የሚከበርበት ልዩ ቀን እንደኾነም ገልጸዋል።

የሚሊሻ 30ኛ ዓመት ክብረ በዓል ሲባል የሚሊሻ ምስረታ ዕድሜው 30 ዓመት ነው ለማለት ሳይኾን በክልል ደረጃ የተቋቋመበትን ለመግለጽ እንደኾነም ተናግረዋል። ሚሊሻ ከንጉሠ ነገሥቱ ዘመን ጀምሮ ዘመናዊ ወታዳር ባልነበረት ወቅትም ነበር ብለዋል።

ባለፉት ሦሥት አስርት ዓመታት የክልሉ ሚሊሻ በርካታ ታሪካዊ ምዕራፎችን ማለፉንም ገልጸዋል።

ሚሊሻው መደበኛ የሥራ ድርሻውን ሳያስተጓጉል በአንድ እጁ አምራች በሌላ እጁ ደግሞ የሰላም ዘብ በመኾን "የሕዝባዊነትን ትርጉም በተግባር ያሳየ ኃይል ነው" ብለዋል።

ሀገራዊ የሉዓላዊነት ፈተናዎች እና ክልላዊ የጸጥታ ስጋቶች ባጋጠሙ ጊዜያት ሚሊሻው ከመከላከያ ሠራዊት እና ከሌሎች የጸጥታ አካላት ጋር በቅንጅት በመሰለፍ በደም እና በአጥንቱ ደማቅ ታሪክ መጻፉን ገልጸዋል።

በክልሉ አንጻራዊ ሰላም እንዲመጣ የበኩሉን ሚና ተጫውቷልም ብለዋል፡፡

ኮሚሽኑ ይህንን 30ኛ ዓመት በዓል ሲያከብር ወደፊት የክልሉን ዘላቂ ሰላም ማረጋገጥ፣ ሕገ መንግሥታዊ ሥርዓቱን ማስከበር እና የሰላም ጥሪ ተግባራት ላይ በትኩረት ለመሥራት ታሳቢ አድርጓል ነው ያሉት ሲል የዘገበው አሚኮ ነው።

የዳባት ከተማ አስተዳደር በወቅታዊ የፀጥታ ሁኔታ ከህብረተሰቡ ከተወጣጡ የህብረተሰብ ክፍሎች ጋር ውይይት አካሄደ ።  ግንቦት 27/2018 የዳባት ከተማ አስተዳደር በወቅታዊ የፀጥታ ሁኔታ ከህ...
04/06/2026

የዳባት ከተማ አስተዳደር በወቅታዊ የፀጥታ ሁኔታ ከህብረተሰቡ ከተወጣጡ የህብረተሰብ ክፍሎች ጋር ውይይት አካሄደ ።

ግንቦት 27/2018 የዳባት ከተማ አስተዳደር በወቅታዊ የፀጥታ ሁኔታ ከህብረተሰቡ ከተወጣጡ የህብረተሰብ ክፍሎች ጋር ውይይት አካሄደ ።

ዳባት በተለያዩ ወቅቶች ለሀገራችን ከፍተኛ አበርክቶ ያበረከቱ ባለሙያወችን ያፈራሽ ከተማ ናት ያሉት የዳባት ከተማ አስተዳደር ከንቲባ አቶ ሀብትሸት ሞገስ አሁን ለገጠመን የሰለም ችግር የበኩለችውን በመወጣት ዛሬም እንደትናቱ ታሪካዊ ኃላፊነታችውን እንድትወጡ ሲሉ መልክት አስተላልፈዋል ።

ህብረተሰቡ ከፀጥታ ሀይላችን ጎን በመቆም እና መንግስት ችግሩን ለመፍታት በሚወሰዳቸው እርምጃወች ሁሉ ተባባሪ መሆን አለበት ሲሉ ከንቲባው ተናግረዋል ።

እንደ ሀገር ችግሩን ለመፍታት መንግስት አልሞ እየሰራ ነው ያሉት የዳባት ወረዳ አስተዳዳሪ አቶ መርሻ ወረታ ከውስጣችን ያለውን ተላላኪ ደግሞ ማህበረሰቡ አሳልፎ መስጠት ይገባል ብለዋል ።

ዳባት ከመቸውም ጊዜ በላይ የተሻለ ልማት እየተሰራ ነው ያሉት አስተዳዳሪው ይህን ልማት ወደ ኋላ ለማስቀረት የሚሰራ ሀይልን የማስቆም ታሪካዊ ኃላፊነት አለብን ብለዋል ።

ተሳታፊ የሀገር ሽማግሌዎች መንግስት ችግሩን በንግግር እንዲፈታ እና ሰላም እንዲሰፍን መንግስትን ጠይቀዋል ።

ውይይት ከንግግር ባለፈ ተግባራዊ የሆነ ውጤት ማምጣት አለበት ያሉት የሀገር ሽማግሌዎች ህብረተሰቡም ከመንግስት ጎን በመቆም አጋዠ ሊሆን ይገባል ብለዋል ።

ሰላም ማምጣት የአንድ ወገን ድርሻ ሳይሆን የሁሉም ህብረተሰብ ክፍል የጋራ ስራ የሚመጣ ነው ያሉት የዳባት ከተማ አስተዳደር ብልፅግና ፓርቲ የፖለቲካ እና አቅም ግንባታ ዘርፍ ኃላፊ አቶ ሞላ ምስጋናው የአካባቢችን ሰላም ለመመለስ ከመቸውም ጊዜ በተለየ ህዝብ እና መንግስት በጋራ ልንሰራ ይገባል ብለዋል ።

ሰለ ሰላም ሁሉም የህብረተሰብ ክፍል ዘብ መቆም አለበት ያሉት የዳባት ከተማ አስተዳደር ብልፅግና ፓርቲ አደረጃጀት ዘርፍ ኅላፊ ወ/ሮ ማህሌት ብርሃን የተለያዩ መረጃዎች ለመንግስት በመስጠት የህዝባችን ሰለም ለመመለስ አጋዥ ልንሆን ይገባል ሲሉ መልክት አስተላልፈዋል ።

🌱 የአፈር ማዳበሪያ ችግር እንዳያጋጥም በትኩረት እየተሠራ መኾኑን የአማራ ክልል ግብርና ቢሮ አስታወቀ።በአማራ ክልል በተያዘው የምርት ዘመን 5 ነጥብ 5 ሚሊዮን በላይ ሄክታር መሬት በማረስ ...
04/06/2026

🌱 የአፈር ማዳበሪያ ችግር እንዳያጋጥም በትኩረት እየተሠራ መኾኑን የአማራ ክልል ግብርና ቢሮ አስታወቀ።

በአማራ ክልል በተያዘው የምርት ዘመን 5 ነጥብ 5 ሚሊዮን በላይ ሄክታር መሬት በማረስ ከ205 ሚሊዮን በላይ ኩንታል ሰብል ለማምረት እየተሠራ መኾኑን የአማራ ክልል ግብርና ቢሮ ምክትል ኀላፊ አጀበ ስንሻው ለአሚኮ ገልጸዋል።

ዕቅዱን ለማሳካት ደግሞ የአፈር ማዳበሪያ እና የምርጥ ዘር አቅርቦት ላይ በትኩረት እየተሠራ እንደኾነ ማብራሪያ ሰጥተዋል።

🌱🚜 ክልሉ በዚህ ዓመት፦

🚜 8 ነጥብ 6 ሚሊዮን ኩንታል የአፈር ማዳበሪያ ወደ ክልሉ ለማስገባት አቅዷል። ከዚህ ውስጥ 4 ነጥብ 6 ሚሊዮን ኩንታል የሚኾነው የክልሉ የአፈር ማዳበሪያ ዕቅድ ወደብ ላይ ደርሷል።

🚜 3 ነጥብ 7 ሚሊዮን ኩንታል የሚኾነው የአፈር ማዳበሪያ ደግሞ ወደ ክልሉ ተጓጉዞ ደርሷል። ከባለፈው ዓመት ተርፎ የነበረ 1 ነጥብ 8 ሚሊዮን ኩንታል የአፈር ማዳበሪያ ግብዓት ክልሉ ውስጥ መኖሩን አንስተዋል።

በጥቅል 5 ነጥብ 5 ሚሊዮን ኩንታል የአፈር ማዳበሪያ ለአርሶ አደሮች ለሥርጭት ቀርቧል። እስከ አሁን ባለው ጊዜም አርሶአደሮች ገዝተው የወሰዱት እና የተሠራጨው 3 ነጥብ 1 ሚሊዮን ኩንታል የአፈር ማዳበሪያ እንደኾነ ተናግረዋል።

ይህም ከአምናው ተመሳሳይ ወቅት ጋር ሲነጻጸር የተሻለ አፈጻጸም እንዳለው ነው የገለጹት። ለስርጭት የቀረበው የአፈር ማዳበሪያ አቅርቦት ቀድመው ከሚዘሩ ሰብሎች አኳያ በጥሩ የሚታይ እንደኾነም አንስተዋል።

🌱 በሌላ በኩል፦
220 ሺህ ኩንታል ምርጥ ዘር ለአርሶ አደሮች ለማቅረብ ታቅዷል።
እስከ አሁን ባለው ጊዜ 208 ሺህ ኩንታል የሰብል ምርጥ ዘር ለአርሶ አደሮች ለማሰራጨት ድልድል ተደርጓል።

72 ሺህ ኩንታል የሚኾነው የሰብል ምርጥ ዘርም ተሠራጭቷል።

ጃፓን የኢትዮጵያ ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ በሰባተኛው ጠቅላላ ምርጫ ላሳየው ሥራ ያላትን  አድናቆቷን ገለጸች። ባሕር ዳር፡ ግንቦት 26/2018 ዓ.ም (አሚኮ) በኢትዮጵያ የጃፓን ኤምባሲ ባወጣው ...
04/06/2026

ጃፓን የኢትዮጵያ ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ በሰባተኛው ጠቅላላ ምርጫ ላሳየው ሥራ ያላትን አድናቆቷን ገለጸች።

ባሕር ዳር፡ ግንቦት 26/2018 ዓ.ም (አሚኮ) በኢትዮጵያ የጃፓን ኤምባሲ ባወጣው መግለጫ የኢትዮጵያ ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ ግንቦት 24 የተካሄደውን ሰባተኛውን ጠቅላላ ምርጫ ለማደራጀት እና ለመምራት ላደረገው ከፍተኛ ጥረት አድናቆቱን ገልጿል።

ጃፓን በምርጫ ሂደቱ ላይ ለተሳተፉት እጩ ተወዳዳሪዎች፣ ድምፃቸውን ለመስጠት ለቻሉ የኢትዮጵያ ዜጎች የእንኳን ደስ አላችሁ መልዕክት አስተላልፋለች።

ጃፓን የኢትዮጵያን የዲሞክራሲ ሂደት ለመደገፍ ለብሔራዊ ምርጫ ቦርድ የገንዘብ ድጋፍ በማድረጓ የተሰማትን ደስታ ገልጻለች።

03/06/2026

7ኛው ጠቅላላ ምርጫ ሰላማዊ ሆኖ በመጠናቀቁ እንኳን ደስ አለን - የኢትዮጵያ ፖለቲካ ፓርቲዎች የጋራ ምክር ቤት

የኢትዮጵያ ፖለቲካ ፓርቲዎች የጋራ ምክር ቤት 7ኛው ጠቅላላ ምርጫ ሰላማዊ ሆኖ በመጠናቀቁ የተሰማውን ደስታ ለመላው የኢትዮጵያ ሕዝብ ገልጿል።

የፖለቲካ ፓርቲዎች፣ የፀጥታ ኃይል አካላት እንዲሁም ሕዝቡ እና ሌሎች ባለድርሻ አካላት በሙሉ ምርጫው በሰላም እንዲጠናቀቅ ለተወጡት ሀገራዊ ኃላፊነት እና ላሳዩት ፅናትም ምክር ቤቱ ያለውን ምስጋና እና አድናቆት ገልጿል።

ምክር ቤቱ በመግለጫው፣ “ልዩነቶቻችንን እና ችግሮቻችንን በዴሞክራሲያዊ መንገድ በመፈታት በምርጫው የታየውን ሰላም በማስቀጠል የበኩላችንን ሚና እንወጣ፤ ለሀገራችን ዘላቂ ሰላም በጋራ እንቁም” ሲል ጥሪውን አቅርቧል።

በደባርቅ ወረዳ በአድስጌ ቀበሌ የተቀናጀ የጤና አገልግሎት መስጫ ጤና ኬላ ግንባታ የማስመረቅና ሪቫን የመቁረጥ ስራ ተከናወነ ።                     ግንቦት 26/2018 ዓ/ም በደ...
03/06/2026

በደባርቅ ወረዳ በአድስጌ ቀበሌ የተቀናጀ የጤና አገልግሎት መስጫ ጤና ኬላ ግንባታ የማስመረቅና ሪቫን የመቁረጥ ስራ ተከናወነ ።

ግንቦት 26/2018 ዓ/ም በደባርቅ ወረዳ በአድስጌ ቀበሌ የተቀናጀ የጤና አገልግሎት መስጫ ጤና ኬላ ግንባታ የወረዳና የዞን አመራሮች በተገኙበት የማስመረቅና ሪቫን የመቁረጥ ስራ ተከናውኗል ።

በምርቃት ፕሮግራሙ ተገኝተው በፕሮግራሙ ለተሳተፉት አካላት የእንኳን ደህና መጣችሁ መልእክት ያስተላለፉት የወረዳው ዋና አስተዳዳሪ አቶ አበባው አዛናው በአድስጌ ቀበሌ የተገነባው የተቀናጀ የጤና አገልግሎት መስጫ ጤና ኬላ በአለም ባንክ የበጀት ድጋፍ በ3R-4-CACE ፕሮጀክት የተገነባውን የወረዳና የዞን አመራሮች በተገኝንበት አስመርቆ ሪቫን መቁረጥ የግንባታውን ደረጃ በልኩ አውቆ ለቀጣይ የጎደሉ ግብአቶችን አሟልቶ ማህበረሰቡ የተስተካከለ የጤና ጥበቃ አገልግሎት እንዲያገኝ ሚናው የላቀ መሆኑን አብራርተዋል ።

የተገነባው ደረጃውን የጠበቀ የጤና ኬላ ተቋም የቀበሌው ማህበረሰብ ተረክቦ በአግባቡ ሊንከባከበው እንደሚገባ ያብራሩት አቶ አበባው የተገነባው የጤና ኬላ ተቋምን ጨምሮ ግንባታው ያረፈበት ቦታ ከሶስተኛ ወገን በማፅዳት የባለቤትነት የይዞታ ህጋዊ የማረጋገጫ ደብተር ወጥቶለት የጤና ተቋሙ ደህንነት በመጠበቅ በኩል የቀበሌው ማህበረሰብና ሌላው ባለድርሻ አካላት የየበኩሉን ሚና መወጣት እንዳለበት አሳሰበዋል ።

የአድስጌ ቀበሌ ህዝብ እስካሁን ድረስ ደባርቅ ጤና ጣቢያና ሆስፒታል ድረስ በመሄድ የጤና ጥበቃ አገልግሎት ያገኝ እንደነበር ያነሱት የወረዳው የጤና ጥበቃ ፅ/ቤት ሃላፊ አቶ ሃይሌ ሞገስ የቀበሌው ህዝብ በማእከላቸው ደረጃውን የጠበቀ የጤና ኬላ ተቋም መገንባት በቅርበት የጤና ጥበቃ አገልግሎት በማግኘት ከአላስፈላጊ የጊዜ ብክነትና የኢኮኖሚ ወጭ እንደሚታደጋቸው አብራርተዋል ።

የጤና ጥበቃ አገልግሎት የሚሰጥ ደረጃውን የጠበቀ የጤና ተቋም መገንባት የቀበሌውን ማህበረሰብ ጤንነት በመጠበቅ በኩል ከፍተኛ ድርሻ እንዳለው ያብራሩት የሰሜንጎንደር ዞን የብልፅግና ፓርቲ ቅርንጫፍ ፅ/ቤት የፖለቲካ ዘርፍ ሃላፊ አቶ ሰውነት ውባለም ህዝቡ የተሳካ የጤና ጥበቃ አገልግሎት እንዲያገኝ ጤና ኬላው የሚያስፈልገውን የሰውሃይልና ግብአት በሟሟላት የቀበሌውን ህብረተሰብ ጨምሮ በምርቃት ፕሮግራም የተገኙትን የወረዳና የዞን አመራሮች የበኩላቸውን ድርሻ እንዲወጡ አሳስበዋል።

የተቀናጀ የጤና አገልግሎት መስጫ ጤና ኬላ በማእከላቸው መገንባቱ ያስደሰታቸው የቀበሌው ነዎሪዎች የተገነባው የጤና መጠበቂያ ተቋም ለቀበሌው ማህበረሰብ ውጤታማ የጤና ጥበቃ አገልግሎት እንዲሰጥ በተቋሙ የጎደሉ የህክምና ቁሳቁሶች፤የሰው ሃይልና ሌሎች ግብአቶችን እንዲሟሉ በፕሮግራሙ ለተገኙት የወረዳና የዞን አመራሮች አሳስበዋል ።

የተገነባው የተቀናጀ አገልግሎት የሚሰጥ የጤና ኬላ ከሶስተኛ ወገን ነፃ በማድረግ ህጋዊ የባለቤትነት የይዞታ ማረጋገጫ ደብተር በማሰራት በአግባቡና በእንክብካቤ እንደሚይዙት የገለፁት ነዎሪዎቹ የተገነባው የጤና መጠበቂያ ተቋም የማህበረሰቡን ጤና በመጠበቅ ሚናው የላቀና በቅርስነት ለትውልድ የሚሸጋገር በመሆኑ ህዝቡ በእንክብካቤ እንደሚይዘው ሃሳብ አስተያየታቸውን አብራርተዋል ።

03/06/2026

ሕዝቡ ሉዓላዊ የስልጣን ባለቤትነቱን በተግባር አረጋግጧል!

ግንቦት 24/2018 ኢትዮጵያውያን ከጫፍ እስከ ጫፍ በመውጣት በ7ኛው ጠቅላላ ምርጫ አዲስ ታሪክ ፅፈዋል። ይህ ታላቅ ሕዝባዊ ንቅናቄ የሀገሪቱን የዲሞክራሲ ጉዞ ለማፅናትና ለማስቀጠል ያለውን ፅኑ ፍላጎት በግልፅ ያሳየበት ታሪካዊ አጋጣሚ ሆኖ ይመዘገባል። ሕዝቡ የምርጫ ካርዱን በጥንቃቄ አስቀምጦ በመያዝ በምርጫዉ እለት ድምፅ በመስጠት ሉዓላዊ የስልጣን ባለቤትነቱን በተግባር አረጋግጧል።

የፖለቲካ ሥልጣን ምንጭ ሕዝብ ብቻ መሆኑንም ዳግም ለመላው ዓለም በማሳየት፣ ኢትዮጵያን ከፍ ማድረግ ተችሏል። በዚህ ታሪካዊ ሂደት ውስጥ ዋነኛውና ብቸኛው አሸናፊ መላው የኢትዮጵያ ሕዝብ እና ሀገራችን ኢትዮጵያ ብቻ ናቸው። መራጩ ሕዝብ ሳይሰለች ከነጋት 10:00 ሰአት ጀምሮ ረጅም ሰልፎችን በመያዝ እስከ እኩለ ሌሊት ድረስ ድምፁን የሰጠው የፓርቲዎችን ድል ለመወሰን ብቻ ሳይሆን፣ የኢትዮጵያን ሉዓላዊነትና ክብር ከፍ ለማድረግ ነው። እናቶች፣ አባቶች፣ ወጣቶች፣ አካል ጉዳተኞች፣ እድሜ ጠገብ አዛዉንቶች፣ ሙሽሮች ሳይቀሩ በነቂስ ወጥተው ዲሞክራሲን ለማፅናት ያሳዩት ትዕግስት የኢትዮጵያን ብሔራዊ አንድነትና ጥንካሬ ለዓለም ያሳየ ታላቅ የድል ምዕራፍ ነው።

የዘንድሮው የምርጫ ሂደት ሙሉ በሙሉ ሰላማዊ፣ ስልጡን እና ፍፁም ዲሞክራሲያዊ በሆነ መንገድ መጠናቀቁ ለሀገራችን ትልቅ የሞራል ድል ሲሆን ሕዝቡ ያሳየው የሰለጠነ የፖለቲካ ባህል፣ መቻቻልና እርስ በርስ የመከባበር እሴት ኢትዮጵያን ሊከፋፍሉና ሊያዳክሙ ለሚፈልጉ ሀይሎች ሁሉ ግልጽ ምላሽ የሰጠ ታሪካዊ ድል ነው። ይህ ስልጡን የዲሞክራሲ ልምምድ አካሄድ ኢትዮጵያ በዲሞክራሲ ሥርዓት ግንባታ ረገድ የደረሰችበትን ጀረጃ በተግባር ያሳየና የሀገሪቱን ገጽታ በዓለም መድረክ ከፍ ያደረገ ልዩ ክስተት ነው።

ይህ ምርጫ ለአዲሲቷና ለበለፀገችው ኢትዮጵያ ጠንካራ መሰረት በመጣል ለነገዋ የበለፀገችና የተረጋጋች ሀገር ጠንካራ መሰረት የጣለ ታላቅ የስኬት ምዕራፍ ነው። 7ኛዉ ጠቅላላ ምርጫ የልዩነት ሳይሆን የኅብረት፣ የብጥብጥ ሳይሆን የሰላም መገለጫ በመሆኑ የሀገሪቱን የነገ ተስፋ ብሩህ አድርጎታል።

በመጨረሻም በተለያዩ ጫናዎች እና ፈተናዎች ሳይበገሩ ድምፄ ዋጋ አለዉ በማለት በታላቅ ሀገራዊ ክብር ፀንተዉ በመቆም በትዕግስት እስከ ሌሊት ተሰልፈው ድምፃቸውን ለሰጡ እና የኢትዮጵያና ህዝቦቿን ታላቅነት በተግባር ላገዘፉ ዜጎች ሁሉ ታላቅ ክብርና ምስጋና ይገባቸዋል።

ኢትዮጵያ መርጣለች!
ኢትዮጵያ ለዘላለም ታሸንፋለች!



#ኢትዮጵያንወደተምሳሌትሀገር

03/06/2026
በኢትዮጵያ ዴሞክራሲን ለማጎልበት የተሠሩ ሥራዎች አበረታች ናቸው - የአፍሪካ ኅብረት ምርጫ ታዛቢ ቡድን   የአፍሪካ ኅብረት የምርጫ ታዛቢ ቡድን መሪ እና የቀድሞው የኬንያ ፕሬዚዳንት ኡሁሩ ...
03/06/2026

በኢትዮጵያ ዴሞክራሲን ለማጎልበት የተሠሩ ሥራዎች አበረታች ናቸው - የአፍሪካ ኅብረት ምርጫ ታዛቢ ቡድን

የአፍሪካ ኅብረት የምርጫ ታዛቢ ቡድን መሪ እና የቀድሞው የኬንያ ፕሬዚዳንት ኡሁሩ ኬንያታ የቡድኑን የ7ኛው ጠቅላላ ምርጫ የመጀመሪያ ግምገማ ውጤትን በተመለከተ መግለጫ በሰጡበት ውቅት፣ የኢትዮጵያ መንግሥት ዴሞክራሲን ለማጎልበት የሠራውን ሥራ እንደሚያደንቁ ገልጸዋል።

አጠቃላይ የምርጫው ሂደትም የኢትዮጵያን እና የዓለም አቀፍ ሕጎች ማዕቀፍን በተከተለ መልኩ መካሄዱን በግምገማው ማረጋገጣቸውን ጠቁመዋል።

ከቅድመ ምርጫው ጀምሮ የነበረው ሂደት አበረታች እንደነበር የገለጹት ኡሁሩ ኬንያታ፣ የአፍሪካ ኅብረት ከምርጫው ዋዜማ አንሥቶ ከሚመለከታቸው አካላት ጋር ሰፊ ውይይቶችን ሲያደርግ መቆየቱን አስታውሰዋል።

የመራጮች ትምህርት አሰጣጥ በተመለከተም ሕዝቡ እንዴት መምረጥ እንዳለበት ትክክለኛ ግንዛቤ እንዲያገኝ መደረጉን እና በምርጫው ዕለት የነበረው የተቀናጀ መናበብ ለመራጮች ምቹ ሁኔታን መፍጠሩን አስረድተዋል።

በምርጫው ሂደት ጥቅም ላይ የዋለው ቴክኖሎጂ በተለይም ለወጣቶች የፈጠረው ዕድል ከፍተኛ መሆኑን የታዛቢ ቡድኑ መሪ በመግለጫቸው አብራርተዋል።

የድምፅ መስጫ ሰዓት መራዘሙ ለመራጮች ተጨማሪ ዕድል መፍጠሩን፣ እንዲሁም ለአካል ጉዳተኞች እና ለአረጋውያን በድምፅ አሰጣጡ ሂደት ቅድሚያ መሰጠቱ የዜጎችን ተሳትፎ በእጅጉ ማነቃቃቱንም ጠቁመዋል።

በመላው ኢትዮጵያ የምርጫ አስፈፃሚዎች እና የፀጥታ አካላት የተጣለባቸውን ኃላፊነት በጥሩ ሁኔታ መወጣታቸውን፣ የመገናኛ ብዙኃንም በተመሳሳይ በከፍተኛ ኃላፊነት ስሜት ሥራቸውን ማከናወናቸውን አድንቀዋል።

ከሁሉም በላይ ደግሞ የኢትዮጵያ ሕዝብ በምርጫው ያሳየው ተሳትፎ እና ትልቁን ኃላፊነቱን በጀግንነት መወጣቱ እጅግ የሚያስመሰግን መሆኑን የአፍሪካ ኅብረት የምርጫ ታዛቢ ቡድን መሪ ኡሁሩ ኬንያታ አስታውቀዋል።

Address

Gondar

Website

Alerts

Be the first to know and let us send you an email when ሰሜን ጎንደር ዞን ብልፅግና ፓርቲ ቅ/ጽ/ቤት North Gondar Zone Prosperity Party posts news and promotions. Your email address will not be used for any other purpose, and you can unsubscribe at any time.

Share