Gondar City Water

Gondar City Water ይህ የፌስ ቡክ ገፅ የጎንደር ከተማ ውሃና ፍሳሽ አገልግሎት ጽ/ቤት በደንበኞች አገልግሎት እና በህዝብ ግንኙነት የስራ ሂደት መረጃዎች ይዳረሱበታል።

እንኳን ለ127ኛው የአድዋ የድል በዓል በሰላም አደረሳችሁ!!!      የአድዋ የድል በዓል ሲነሳ የአፍሪካውያን ብሎም የኢትዮጵያውን የይቻላል መንፈስ እንደብረት የጠነከረበትና ከነጮች ጥገኝነ...
01/03/2023

እንኳን ለ127ኛው የአድዋ የድል በዓል በሰላም አደረሳችሁ!!!
የአድዋ የድል በዓል ሲነሳ የአፍሪካውያን ብሎም የኢትዮጵያውን የይቻላል መንፈስ እንደብረት የጠነከረበትና ከነጮች ጥገኝነት መላቀቅ የሚያስችል ወኔን በተግባር የተላበስንበት አስተማሪ ታሪካችን ነው፡፡የአድዋ ድል መተባበርን፣ አንድነትንና ነጻነትን በአፍሪካውያን በተለይም በኢትዮጵያውያን ልብ ውስጥ እንደማህተም ቀርጾ ዘላለማዊ የአልሸነፍም ወኔን በተግባር ያጎናፀፈን የእምየ ምኒሊክ እና የእትጌ ጣይቱ የተጋድሎ ውጤት ነው፡፡
እድዋና አፄ ሚኒሊክ ለኢትዮጵያችን የዘመናዊ ስልጣኔ ፈር ቀዳጅ፣የአለምአቀፋዊ ግንኙነት መሰረት፣የአስተዋይነትና የብልህ አመራር ጥበብ የታየበት፣ሰብዓዊነት፣ርህራሄና በጎነት የመነጨበት ህያዊ ታሪካችን በመሆኑ እኛም የአያት ቅድመ-አያቶቻችን ታሪክ በተግባር ለመድገም ቀደምት ታሪካችን ማወቅ መመራመርና መተግበር ይጠበቅብናል፡፡አፄ ሚኒሊክን ስናስታውስ በርካታ ማህበራዊና ኢኮኖሚያዊ ጉዳዮች በአእምሯችን ይቀረፃሉ፤ከበርካታዎቹ መካከል ውሃ ኢትዮጵያ በቧንቧ ማግኘት የጀመረችበት ዘመን በእርሳቸው ዘመን ሆኖ እናገኘዋለን፡፡
ክብርና ምስጋና ለስልጣኔ ፈር ቀዳጆችና ነፃነት ላጎናፀፉን አፄ ሚኒሊክ እና ለእትጌ ጠይቱ

የጎንደር ከተማ ውኃና ፍሳሽ አገልግሎት ጽ/ቤት የደንበኞቹን ፍላጎት ለማሟላት እየጣረ ነው፤ የተቋሙ ዋና ስራ አስኪያጅ አቶ ወርቅነህ አያል እንደገለፁት ተቋሙ በርካታ ደንበኞች ያሉት ሲሆን በ...
12/01/2023

የጎንደር ከተማ ውኃና ፍሳሽ አገልግሎት ጽ/ቤት የደንበኞቹን ፍላጎት ለማሟላት እየጣረ ነው፤
የተቋሙ ዋና ስራ አስኪያጅ አቶ ወርቅነህ አያል እንደገለፁት ተቋሙ በርካታ ደንበኞች ያሉት ሲሆን በተለይም ከምንሰጣቸው የንፁህ መጠጥ ውኃ አቅርቦት በተጨማሪ የፍሳሽ ማንሻ ቫኪዮም ትራክ ተጠቅሞ የከተማዋን የፍሳሽ ቆሻሻ በማስወገድ ለግልም ሆነ ለመንግስት ድርጅቶች አገልግሎት መስጠት ለውኃ ተቋሙ ተቀዳሚ ተግባሩ ነው፡፡
አቶ ወርቅነህ አያል አክለው እንደተናገሩት አሁን ያሉት የፍሳሽ ቆሻሻ ማንሻ ተሸከርካሪዎች ከከተማው ህዝብ ቁጥርና ፍላጎት አንጻር የማይጣጣሙ ከመሆናቸውም አልፎ ለረዥም ጊዜ አገልግሎት ሲሰጡ የቆዩ በመሆናቸው በየጊዜው እየተበላሹ ደንበኞችን ማርካት አልተቻለም ብለዋል፡፡
ይህን ችግር በመጠኑም ቢሆን ለማቃለል የጎንደር ከተማ አስተዳደር ከተማ ልማትና ኮንስትራክሽን መምሪያ ለጎንደር ከተማ ውኃና ፍሳሽ አንድ የፍሳሽ ቆሻሻ ማንሻ ቫኪዮም ትራክ ከዓለም ባንክ ፕሮጀክት በተገኘ ድጋፍ መገኘቱን አቶ ወርቅነህ አያል ከጎንደር ከተማ ልማት መምሪያ ኃላፊ ከአቶ አንዷለም ሙሉ እጅ የቁልፍ ርክክብ ሲያደርጉ ገልፀዋል፡፡
ተቋማቸው ከከተማ ልማት ኮንስትራሽን መመሪያ ጋር በመቀናጀት በጋራ በመስራታቸው የውኃ ተቋሙ የተለያዩ ድጋፎችን እያገኘ ሲሆን በቀጣይም አገልግሎቱን ለማሳለጥ ትብብራቸውን አጠናክረው እንደሚቀጥሉ አቶ ወርቅነህ አያል ገልፀዋል፡፡

06/01/2023
06/01/2023

እንኩዋን ለገና በዓል በሰላም አደረሳችሁ!!

ለመላው የክርስትና እምነት ተከታዮች በሙሉ እንኩዋን ለጌታችን ለመድሃኒታችን የልደት በዓል በሰላም አደረሳችሁ!!በዓሉ የሰላም የደስታ የፍቅርና የአንድነት እንዲሆንላችሁ ይመኛል፤የጎንደር ከተማ...
06/01/2023

ለመላው የክርስትና እምነት ተከታዮች በሙሉ እንኩዋን ለጌታችን ለመድሃኒታችን የልደት በዓል በሰላም አደረሳችሁ!!በዓሉ የሰላም የደስታ የፍቅርና የአንድነት እንዲሆንላችሁ ይመኛል፤
የጎንደር ከተማ ውሃና ፍሳሽ አገልግሎት

02/01/2023

የጎንደር ከተማ ውሃና ፍሳሽ አገልግሎት ጽ/ቤት ነባሩን የመጠጥ ውሃ አቅርቦት ችግር በጊዜያዊነት እና በቋሚነት ለመፍታት ብዙ እርቀቶችን እየሄደ ቢሆንም ከዋናው የመብራት ኃይል ማሰራጫ በገጠመው ችግር ውሃን ለህብረተሰቡ ወረፍውን ጠብቆ እንዳያገኝ እያደረገው ይገኛል። በዚህም ህብረተሰቡ በችግር ላይ መሆኑ ታውቆ የሚመለከተው ክፍል መልካም ትብብራቸውን እንዲያደርጉ እየጠየቅን የጎንደር ዲስትሪክት መብራት ኃይሎች ለምታደርጉት ጥረት እናመሰግናለን !!

የጎንደር ከተማ ውሃና ፍሳሽ አገልግሎት በስሩ ለሚገኙ 11 የገጠር ቀበሌዎች የተሻለ  የውሃ አገልግሎት እንዲያገኙ በማድረግ ላይ ሲሆን በተለያየዩ ምክንያቶች አገልግሎታቸው ተቋርጦ የነበረው የ...
07/11/2022

የጎንደር ከተማ ውሃና ፍሳሽ አገልግሎት በስሩ ለሚገኙ 11 የገጠር ቀበሌዎች የተሻለ የውሃ አገልግሎት እንዲያገኙ በማድረግ ላይ ሲሆን በተለያየዩ ምክንያቶች አገልግሎታቸው ተቋርጦ የነበረው የደረስጌ ቀበሌ የእጅ ጉድጓድ ውሃ ተጠግኖ አገልግሎት መስጠት ተጀምሯል፤በሌሎች ቀበሌዎችም የሚገኙ የውሃ ተቋም የተሻለ አገልግሎት እንዲሰጡ በጎንደር ከተማ ውሃና ፍሳሽ አገልግሎት ጽ/ቤት ስር በሚገኘው የገጠር መጠጥ ውሃ ኬዝ ቲም አስተባባሪነት ተከታታይ ድጋፍና ክትትል እየተደረገባቸው ይገኛል፤ የአካባቢው ማህበረሰብም ውሃ ተቋማቱን እንዲጠብቅና ለረዥም ጊዜ አገልግሎት እንዲሰጡ ማድረግ እንዳለባቸው ኬዝ ቲሙ አስተያየቱን የሰጠ ሲሆን በቀጣይም በሌሎች የገጠር ቀበሌዎች የሚገኙ የውሃ ተቋማትን ጥገና ከማድረግ ባሻገር ተጨማሪ ግንባታ ስራ የሚያከናውን ይሆናል፤

የጎንደር ከተማ ውሃና ፍሳሽ አገልግሎት ጽ/ቤት በበጋ ወቅት ሊከሰት የሚችለውን የውሃ እጥረት ለመቀነስ በከተማው ዙሪያ ከ1930ዎቹ አካባቢ አገልግሎት ሲሰጡ የነበሩትን የሆግ፤የኮረምረምን፤የሾ...
05/11/2022

የጎንደር ከተማ ውሃና ፍሳሽ አገልግሎት ጽ/ቤት በበጋ ወቅት ሊከሰት የሚችለውን የውሃ እጥረት ለመቀነስ በከተማው ዙሪያ ከ1930ዎቹ አካባቢ አገልግሎት ሲሰጡ የነበሩትን የሆግ፤የኮረምረምን፤የሾላየን፤የዲቫኖስና የሌሎች የውሃ መገኛ ቦትዎችን በማጥናት ተጨማሪ የውሃ ምርት ለማግኘት የተቋሙ ሰራተኞችና አመራሮች ከክፍለ-ከተማ አመራሮች ጋር በትብብር በመስራት ላይ የምንገኝ ሲሆን በክልልና በራሱ በተቋሙ አቅም ደረጃ ደግሞ በአንገረብ ግድብ ታችኛው ተፋሰስ አካባቢ ጥልቀታቸው 500 ሜትር በላይ የሚሆኑ ጥልቅ የውሃ ጉድጓዶች በመቆፈር ላይ ይገኛሉ፤ ስራዎች በሚከናወኑበት የምንገኝ የህብረተሰብ ክፍሎችም ለሰራተኞች የሞራል ድጋፍ ያስፈልጋቸዋል፤

የጎንደር ከተማ ውሃና ፍሳሽ አገልግሎት ሰራተኞች የውጭ ጣልቃ ገብነትና የውክልና ጦርነት ይብቃ በማለት ሰላማዊ ሰልፉ ላይ ድምፃቸውን አሰሙ
23/10/2022

የጎንደር ከተማ ውሃና ፍሳሽ አገልግሎት ሰራተኞች የውጭ ጣልቃ ገብነትና የውክልና ጦርነት ይብቃ በማለት ሰላማዊ ሰልፉ ላይ ድምፃቸውን አሰሙ

የተከበሩ ክቡር ጠቅላይ ሚኒስትር ዶር. አብይ አህመድ የጎንደር ከተማ የመጠጥ ውሃ ችግር ትኩረት ተሰጥቶት ዘላቂ መፍትሄ እንዲሰጡን
15/10/2022

የተከበሩ ክቡር ጠቅላይ ሚኒስትር ዶር. አብይ አህመድ የጎንደር ከተማ የመጠጥ ውሃ ችግር ትኩረት ተሰጥቶት ዘላቂ መፍትሄ እንዲሰጡን

የጎንደር ከተማ ውሃና ፍሳሽ አገልግሎት ጽ/ቤት ስር የሚገኘው የሁለተኛ ከተሞች ሳኒቴሽን ፕሮግራም/ፕሮጀክት በ2014 ዓም ብቻ በከተማ አስተዳደርሩ ለሚገኙ600 በላይ ለሚሆኑ የድሃ ድሃ/ ዝቅ...
15/10/2022

የጎንደር ከተማ ውሃና ፍሳሽ አገልግሎት ጽ/ቤት ስር የሚገኘው የሁለተኛ ከተሞች ሳኒቴሽን ፕሮግራም/ፕሮጀክት በ2014 ዓም ብቻ በከተማ አስተዳደርሩ ለሚገኙ600 በላይ ለሚሆኑ የድሃ ድሃ/ ዝቅተኛ የህብረተሰብ ክፍሎች 330የውሃ ቆጣሪዎችን አከፋፈለ። ፕሮጀክቱ በ2013ዓም 350 በ2014 ዓም 330 የውሃ ቆጣሪዎችን ድጋፍ ያደረገ ሲሆን በ2015 ዓም ደግሞ የተሻለ አገልግሎት ለመስጠት በስራ ላይ ይገኛል።

ለአይራ ሆስፒታል የተሻለ የውሃ አገልግሎት በማግኘት ደንበኞቹን ማስተናገድ እንዲችል በ3/4ኛ የነበረውን የውሃ መስመር በባለ 2 ኢንች በማድረግ የመስመር ማሻሻል ስራ በውሃ ተቋማችን ሰራተኞች...
14/10/2022

ለአይራ ሆስፒታል የተሻለ የውሃ አገልግሎት በማግኘት ደንበኞቹን ማስተናገድ እንዲችል በ3/4ኛ የነበረውን የውሃ መስመር በባለ 2 ኢንች በማድረግ የመስመር ማሻሻል ስራ በውሃ ተቋማችን ሰራተኞች በመስራት ላይ

Address

ፋሲለደስ 2ኛ ደረጃ ት/ቤት
Gondar

Telephone

+251918729173

Website

Alerts

Be the first to know and let us send you an email when Gondar City Water posts news and promotions. Your email address will not be used for any other purpose, and you can unsubscribe at any time.

Contact The Organization

Send a message to Gondar City Water:

Share