30/07/2026
ተቀናሽ የማይደረጉ ወጪዎች እና ኪሳራዎች
▫️ የካፒታልነት ባህርይ ያላቸው ወጪዎች፤
▫️ የኩባንያ አክሲዮን ወይም የሽርክና ማህበር መሠረት የሆነውን ካፒታል ለማሳደግ የሚወጣ ወጪ፤
▫️ ከተቀጣሪው የወር ደመወዝ 15% (አሥራ አምስት መቶኛ) በላይ በፈቃደኝነት የሚደረግ የጡረታ ወይም የፕሮቪደንት ፈንድ መዋጮ፤
▫️ የአክሲዮን ድርሻ እና የትርፍ ድርሻ ክፍፍል፤
▫️ በመድን፣ በካሳ ወይም በዋስትና ውል መሠረት የተመለሰ ወይም ሊመለስ የሚችል ወጪ ወይም ኪሳራ፤
▫️ ማንኛውንም ሕግ ወይም ውል በመጣስ የሚጣል የገንዘብ ቅጣት ወይም የሚከፈል ካሳ፤
▫️ ግብር ከፋዩ በሂሳብ መዝገቡ የሚይዘው በወቅቱ ወጪ ያልተደረገ ነገር ግን ለወደፊት በግብር ዓመቱ ለሚከሰቱ ወጪዎች ወይም ኪሳራዎች መጠባበቂያ ይሆን ዘንድ የሚያዝ ገንዘብ ወይም የመጠባበቂያ ሂሣብ፤
▫️ ግብር ከፋዩ ለራሱ የሚያወጣው የግል ውጪ፤
▫️ በገቢ ግብር አዋጅ ወይም በውጭ ሀገር የታክስ ሕግ መሠረት የተከፈለ የገቢ ግብር ወይም ተመላሽ የሚደረግ የተጨማሪ እሴት ታክስ፤
▫️ መሥሪያ ቤቱን ወክሎ በተለያዩ ቦታዎች ለሚገኝ ተቀጣሪ ከተቀጣሪው ከመቀጠር የሚገኝ ገቢ 10% (አሥር በመቶ) በላይ የሚከፈል የኃላፊነት አበል፤
▫️ ከሚከተሉት በስተቀር ለመዝናኛ የሚወጣ ወጪ፤
ሀ. የግብር ከፋዩ የንግድ ሥራ የመዝናኛ አገልግሎት መስጠት ሲሆን፤ወይም
ለ. ተቀናሽ እንዲደረግ በሚፈቅደው ልክ በማዕድን ማውጣት፣ በማኑፋክቸሪንግ ወይም በግብርና ሥራ የተሠማራ ቀጣሪ ሠራተኞቹን ለማዝናናት የሚያወጣው ወጪ፤
▫️ ለበጎ አድራጎት ከሚሰጥ ስጦታ ውጭ የሚደረግ ስጦታ ወይም እርዳታ፤
▫️ ግብር ከፋዩ አንድን የንግድ ሥራ ሀብት ግንኙነት ላለው ሰው ሲያስተላልፍ የሚደርስ ኪሳራ፤
▫️ ማናቸውም ግብር ከፋይ ወደ ባንክ ሂሳብ ገቢ ከሚደረግ ቼክ፤ ወደ ባንክ ሂሳብ ገቢ ከሚደረግ የባንክ ድራፍት፤ ከአንድ የባንክ ሂሳብ ወደሌላ የባንክ ሂሳብ እና ወይም በኢትዮጵያ ብሔራዊ ባንክ ፈቃድ በተሰጣቸው የክፍያ መፈፀሚያ መንገዶች ገንዘብ ከማስተላለፍ ውጪ በአንድ ቀን ውስጥ ለአንድ ሰው ከብር 50,000 (ሃምሳ ሺህ ብር) በላይ በሆነ ጥሬ ገንዘብ የፈጸመው ወይም የፈጸማቸው ክፍያዎች፤