Gofa Zone Revenue Department

Gofa Zone Revenue Department ይህ የጎፋ ዞን ገቢዎች መምሪያ ፌስቡክ ገፅ ነው ስለ ግብር እና ታክስ ጉዳዮች ወቅታዊ እና ትክክለኛ መረጃ እንድደርስዎ ገፁን ላይክ እና ለወዳጅ ጎደኛ ያጋራ ❗️❗️

24/05/2026

“ግብር ከፋዩ 'በኔ ታማኝነት ሀገር እየተገነባ ነው' በሚል ሀገርን የመውደድ እሳቤ ግብሩን በታማኝነት እና በወቅቱ የመክፈል ባህሉን ሊያሳድግ ይገባል”
- ወ/ሮ ዓለምነሽ ደመቀ (የደቡብ ኢትዮጵያ ክልል የገቢዎች ቢሮ ኃላፊ)

ግንቦት 16/2018 ዓ.ም (የገቢዎች ሚኒስቴር)

የደቡብ ኢትዮጵያ ክልል የገቢዎች ቢሮ በክልሉ ያለውን ትልቅ የገቢ አቅም አሟጥጦ ለመጠቀም የሚያስችሉ ስራዎችን እያከናወነ እንደሚገኝ የቢሮው ኃላፊ ወ/ሮ ዓለምነሽ ደመቀ ገለጹ።

ቢሮው የተለያዩ የሪፎርም ስራዎችን ማከናወኑን የገለጹት የቢሮ ኃላፊዋ የታክስ ሕግ ማሻሻያዎችን በማድረግ እና የሰው ኃይል የመፈጸም አቅምን ለማሳደግ የሰው ኃይል የሪፎርም ስራዎችን የማከናወን ተግባር ቀዳሚው እንደነበር ተናግረዋል።

በክልሉ ባሉ 138 የታክስ ማእከላትን ጨምሮ የታክስ አሰባሰብ ስርዓቱን በቴክኖሎጂ የማስደገፍ እና የማዘመን ሰፊ ስራ መሰራቱን ገልፀው በዚህም ግብር ከፋዩ ያለበት ቦታ በመሆን በቀላሉ ግብሩን እንዲከፍል እና ገቢ የመሰብሰብ አቅም እንዲያድግ ያስቻለ ነው ብለዋል።

ክልሉ እንደአዲስ ከተዋቀረ በኋላ ባሉት ዓመታት የገቢ አፈጻጸሙ እያደገ መምጣቱን የገለጹት ወ/ሮ ዓለምነሽ በ2016 በጀት ዓመት 13 ቢሊየን የነበረው የገቢ አቅም በ2018 በጀት ዓመት 32.4 ቢሊየን ለመሰብሰብ በማቀድ በአስር ወራት ውስጥ ብቻ 25.5 ቢሊየን መሰብሰብ መቻሉን ገልጸዋል። አፈጻጸሙም ከ2017 በጀት ዓመት ተመሳሳይ ወቅት ጋር ሲነጻጸር የ11 ቢሊየን ብር ብልጫ እንዳለውም አሳውቀዋል።

የታክስ ሕግ ማስከበርን ጋር ተያይዞ ክልሉ ቅድሚያ የሚሰጠው የግብር ከፋዩን የታክስ ግንዛቤ ለማስጨበጥ ስራ መሆኑን የጠቀሱት ኃላፊዋ ነገር ግን ከዚህ አልፈው የታክስ ሕግ ጥሰትን በሚፈጽሙት ላይ ሕግ የማስከበር ስራዎችን እያከናወነ እንደሚገኝ ገልጸዋል።

የክልሉ ገቢ የመሰብሰብ አቅም እንዲያድግ የገቢዎች ሚኒስቴር የታክስ ኢንፎርሜሽን ቴክኖሎጂ ልማት ስራዎች እንዲሁም የሰው ኃይል አቅም ማጎልበት ላይ ድጋፍ እያደረገ እንደሆነ ገልጸው በቀጣይም የበለጠ ተቀራርበው እንደሚሰሩ ያላቸውን እምነት ገልጸዋል።

ወ/ሮ ዓለምነሽ ለግብር ከፋዩ ባስተላለፉት መልእክትም ግብር ከፋዩ በኔ ታማኝነት ሀገር እየተገነባ ነው በሚል ሀገርን የመውደድ እሳቤ እንዲንቀሳቀስ እና ታክስን ማጭበርበር እራስንም፤ ሀገርንም የሚጎዳ ተግባር መሆኑን በመገንዘብ ግብርን በታማኝነት እና በወቅቱ በመክፈል ተቋሙ ገቢን በተገቢው ልክ ሰብስቦ ለሀገር ልማት ለማዋል ከሚያደርገው ጥረት ጎን እንዲሰለፍ ጥሪ አቅርበዋል።

ፎቶ:- የትናየት እንዳያፍሩ

 በደምባ ጎፋ ወረዳ ገቢዎች ጽህፈት ቤት ብቁ አመልካቾችን ለመቅጠር አዲስ የስራ ማስታወቂያ አውጥቷል።  በዚህም መሠረት ተፈላጊ መስፈርቶችን የምታሟሉ አመልካቾች በተገለጸው ጊዜና ቦታ በመቅረ...
20/05/2026



በደምባ ጎፋ ወረዳ ገቢዎች ጽህፈት ቤት ብቁ አመልካቾችን ለመቅጠር አዲስ የስራ ማስታወቂያ አውጥቷል።

በዚህም መሠረት ተፈላጊ መስፈርቶችን የምታሟሉ አመልካቾች በተገለጸው ጊዜና ቦታ በመቅረብ እንድታመለክቱ ይጠየቃል።

የሆቴል ክፍል ይዞታ ክፍያ ምንድነው?በከተሞች ውስጥ ሆቴሎች እና ሌሎች የእንግዳ ማረፊያዎች የአልጋ/የመኝታ አገልግሎት ሲሰጡ፣ በአንድ ቀን በሚያገኙት የእያንዳንዱ አልጋ/መኝታ ክፍል ገቢ ላይ...
14/05/2026

የሆቴል ክፍል ይዞታ ክፍያ ምንድነው?

በከተሞች ውስጥ ሆቴሎች እና ሌሎች የእንግዳ ማረፊያዎች የአልጋ/የመኝታ አገልግሎት ሲሰጡ፣ በአንድ ቀን በሚያገኙት የእያንዳንዱ አልጋ/መኝታ ክፍል ገቢ ላይ ተሰብስቦ የሚከፈል ገቢ ነው፡፡

ይህ ገቢ የማዘጋጃ ቤታዊ ገቢ ሲሆን የሚወሰነውና የሚሰበሰበውም በክልሉ መስተዳደር ምክር ቤት የወጣውን ደንብ ቁጥር 100/2018 መሰረት አድርጎ ነው፡፡

የሆቴል ክፍል ይዞታ የሚከፍሉት በክልላችን በሚገኙ ከተሞች በሆቴሎች እና በሌሎች የአልጋ/የመኝታ አገልግሎት የሚጠቀሙ ማንኛውም ግለሰቦች ሲሆኑ በአንድ ቀን የአንድ አልጋ ክፍል ክፍያ 1,000.00(አንድ ሺህ ብር) እና ከዚያ በላይ ሲሆን ነው፡፡

የማስከፈያ ምጣኔው ከ2% እስከ 3% ሆኖ ከተሞች ከራሳቸው ተጨባጭ ሁኔታ አንፃር በምክር ቤቶቻቸው የሚያስወስኑት ይሆናል፡፡

የክፍያው መሠረት የሚሆነው የመኝታው የአንድ ቀን አገልግሎት ዋጋ ሲሆን ስሌቱ የሚጣለምው በሚከራየው አልጋ ክፍል ዋጋ ላይ በመቶኛ ሲሆን ከታክስ በፊት ባለው ዋጋ ላይ ነው፡፡ ለሆቴል ክፍል ይዞታ ክፍያ በተሰላው ዋጋ ላይ ሌላ ተጨማሪ ታክስ አይሰላም፡፡

👉ገቢው የሚሰበሰብበት ሁኔታ፡-

•አገልግሎቱን የሚሰጡ ግለሰቦች ወይም ድርጅቶች ከተገልጋዩ ይሰበስባሉ፡፡
•በየወሩ የተሰበሰበውን ገቢ ወሩ ባለቀ በ 30 ቀናት ውስጥ ለሚመለከተው አካል ማሳወቅና መክፈል ይኖርባቸዋል፡፡
•ክፍያውን በወቅቱ ባላሳወቁ እና ባልከፈሉ ላይ የዘገየበት ቅጣትና ወለድ ይታሰባል፡፡

👉🏾 ከክፍያ ነጻ የሆኑ አካላት

1. የመንግሥት ሠራተኞችና ኃላፊዎች፦ ለመንግሥታዊ ሥራ አገልግሎት በሚጠቀሙበት ጊዜ ብቻ፡፡
2. ታዳጊዎች፦ ዕድሜያቸው ከ18 ዓመት በታች የሆኑ ጎብኚዎች፡፡
3. ለረጅም ጊዜ የሚቆዩ ቱሪስቶች ፦ ለመዝናኛና ለቱሪስት አገልግሎት በተከታታይ ከ30 ቀናት በላይ የሚቆዩ ከሆነ፣ ከ30ኛው ቀን በኋላ ያለው ቆይታ ከክፍያ ነፃ ይሆናል፡፡

👉🏾 ለምን ይጠቅማል?
ይህ ገቢ የማዘጋጃ ቤታዊ ገቢ በመሆኑ፣ ለከተሞቻችን መሠረተ ልማት መሳለጥና ለጽዳት ስራዎች ከፍተኛ እገዛ ያደርጋል፡፡ በመሆኑም ሁሉም የሆቴል ባለቤቶች በፋይናንስ መዋቅር በተዘጋጀው ደረሰኝ እና የገቢ ኮድ መጠቀም አለባቸው፡፡

13/05/2026

የደረጃ "ለ" ግብር ከፋዮች ዓመታዊ ግብር የሚከፍሉት በሚከተለው አኳኋን ይሆናል፣

ከተያዘው የግብር ዓመት በፊት ማለትም የ2017 ግብር ዘመን በነበረው የከፈሉትን ግብር 25%(ሃያ አምስት በመቶ) ከሐምሌ ወር መጨረሻ ጀምሮ በሚቆጠር በየሶስት ወሩ የሶስት ወሩ በተጠናቀቀ በ30 (ሰላሳ) ቀናት ውስጥ አስቀድመው መክፈል ይኖርባቸዋል፡፡
በዚህ መሠረት፡-
👉የመጀመሪያ ዙር ክፍያ ጊዜ ከህዳር 01 እስከ 30 ይሆናል፣
👉የሁለተኛ ዙር ክፍያ ጊዜ የካቲት 01 እስከ 30 ይሆናል፣
👉የሶስተኛ ዙር ክፍያ ጊዜ ከግንቦት 01 እስከ 30 ሲሆን በየግብር ዓመቱ ሐምሌ ወር መጨረሻ ሊከፍሉ ከሚገባው ግብር ላይ በየሶስት ወሩ የከፈሉት ተቀንሶ ቀሪውን ይከፍላሉ፡፡

የደረጃ "ለ" ግብር ከፋዮች የሂሳብ መዝገብ መያዝ ግዴታ የለለባቸው ሲሆን በፍቃደኝነት መያዝ ይችላሉ፡፡ የያዙት የሂሳብ መዝገብ ተቀባይነት ካገኘ የሚከፍሉት ግብር በሂሳብ መዝገባቸው ሠንጠረዥ ሐ መሰረት ይሆናል፡፡

ከላይ የተጠቀሰው ቢኖርም ለመጀመሪያ ጊዜ የገቢ ግብር የሚከፍሉ አዲስ ግብር ከፋዮች የመጀመሪያውን የግብር ዓመት በተመለከተ ዓመታዊ ግብር የሚከፍሉት በሚከተለው አኳኋን ይሆናል፤

ሀ) የደረጃ "ሀ" አዲስ ግብር ከፋዮች ዓመታዊ ገቢያቸውን ማስታወቅ ባለባቸው ጊዜ በግብር ዓመቱ ሊከፍሉት የሚገባውን ግብር መክፈል አለባቸው፡፡

ለ) የደረጃ "ለ" አዲስ ግብር ከፋዮች ከሐምሌ 1 ቀን እስከ ሐምሌ 30 ቀን ባለው ጊዜ ዉስጥ ግብሩን መክፈል አለባቸው::

በታክስ አስተዳደር ማሻሻያ ረቂቅ አዋጅ ላይ ውይይት ተካሄደግንቦት 04/2018 ዓ.ም (የገቢዎች ሚኒስቴር)ከ2008 ዓ.ም ጀምሮ አገልግሎት በመስጠት ላይ ያለው የታክስ አስተዳደር አዋጅ ቁጥር...
12/05/2026

በታክስ አስተዳደር ማሻሻያ ረቂቅ አዋጅ ላይ ውይይት ተካሄደ

ግንቦት 04/2018 ዓ.ም (የገቢዎች ሚኒስቴር)

ከ2008 ዓ.ም ጀምሮ አገልግሎት በመስጠት ላይ ያለው የታክስ አስተዳደር አዋጅ ቁጥር 983/2008ን ማሻሻል የሚያስችል ውይይት ተካሄድ፡፡

በመድረኩም የገቢዎች ሚኒስትር ዓይናለም ንጉሴ የታክስ አስተዳደር አዋጅ ቁጥር 983/2008 ላለፉት አሥር ዓመታት በታክስ አስተዳደር ሂደት ዋንኛ የህግ ማዕቀፍ ሆኖ አገልግሏል ብለዋል፡፡

ሆኖም በእነዚህ ዓመታት የታክስ አስተዳደር ተግባራት ላይ ማነቆ የሆኑ ጉዳዮች መስተዋላቸውን የገለጹት ሚኒስትሯ አዋጁን እንደገና ፈትሾ ማሰተካከያ ማድረግ ተገቢ መሆኑን ተናግረዋል፡፡

በገንዘብ ሚኒስቴር የታክስ ጉዳዮች አማካሪ አቶ ዋሲሁን አባተ በረቂቅ አዋጁ የተደረጉ ዋና ዋና ማሻሻያዎችን ያብራሩ ሲሆነ ከዚህም መካከል የታክስ ምስክር ወረቀት አሰጣጥ፣ የግልግል ስርዓትን እንደ አንድ የታክስ ውሳኔ አለመግባባት መፍቻ ዘዴ መጠቀም፣ የታክስ ውሳኔ ማስታወቅያ የሚታረምበት ስርዓት፣ የታክስ ውሳኔ ማስታወቂያ ላይ ማሻሻያ ማድረጊያ እና ይግባኝ ማቅረቢያ የጊዜ ገደብን የተመለከቱ ጉዳዮች እንደሚገኙ ገልጸዋል፡፡

በውይይት መድረኩ የስራ ኃላፊዎች እና ከፍተኛ ባለሙያዎች የተሳተፉ ሲሆን የተሰጡ ግብዓቶችን በማካተት የአዋጁን ማሻሻያ ሥራ በአጭር ጊዜ ለማጠናቀቅ መስራት እንሚገባም ስምምነት ላይ ተደርሷል፡፡

የሆቴል ክፍል ይዞታ ክፍያ ምንድነው?በከተሞች ውስጥ ሆቴሎች እና ሌሎች የእንግዳ ማረፊያዎች የአልጋ/የመኝታ አገልግሎት ሲሰጡ፣ በአንድ ቀን በሚያገኙት የእያንዳንዱ አልጋ/መኝታ ክፍል ገቢ ላይ...
12/05/2026

የሆቴል ክፍል ይዞታ ክፍያ ምንድነው?

በከተሞች ውስጥ ሆቴሎች እና ሌሎች የእንግዳ ማረፊያዎች የአልጋ/የመኝታ አገልግሎት ሲሰጡ፣ በአንድ ቀን በሚያገኙት የእያንዳንዱ አልጋ/መኝታ ክፍል ገቢ ላይ ተሰብስቦ የሚከፈል ገቢ ነው፡፡

ይህ ገቢ የማዘጋጃ ቤታዊ ገቢ ሲሆን የሚወሰነውና የሚሰበሰበውም በክልሉ መስተዳደር ምክር ቤት የወጣውን ደንብ ቁጥር 100/2018 መሰረት አድርጎ ነው፡፡

የሆቴል ክፍል ይዞታ የሚከፍሉት በክልላችን በሚገኙ ከተሞች በሆቴሎች እና በሌሎች የአልጋ/የመኝታ አገልግሎት የሚጠቀሙ ማንኛውም ግለሰቦች ሲሆኑ በአንድ ቀን የአንድ አልጋ ክፍል ክፍያ 1,000.00(አንድ ሺህ ብር) እና ከዚያ በላይ ሲሆን ነው፡፡

የማስከፈያ ምጣኔው ከ2% እስከ 3% ሆኖ ከተሞች ከራሳቸው ተጨባጭ ሁኔታ አንፃር በምክር ቤቶቻቸው የሚያስወስኑት ይሆናል፡፡

የክፍያው መሠረት የሚሆነው የመኝታው የአንድ ቀን አገልግሎት ዋጋ ሲሆን ስሌቱ የሚጣለምው በሚከራየው አልጋ ክፍል ዋጋ ላይ በመቶኛ ሲሆን ከታክስ በፊት ባለው ዋጋ ላይ ነው፡፡ ለሆቴል ክፍል ይዞታ ክፍያ በተሰላው ዋጋ ላይ ሌላ ተጨማሪ ታክስ አይሰላም፡፡

👉ገቢው የሚሰበሰብበት ሁኔታ፡-

•አገልግሎቱን የሚሰጡ ግለሰቦች ወይም ድርጅቶች ከተገልጋዩ ይሰበስባሉ፡፡
•በየወሩ የተሰበሰበውን ገቢ ወሩ ባለቀ በ 30 ቀናት ውስጥ ለሚመለከተው አካል ማሳወቅና መክፈል ይኖርባቸዋል፡፡
•ክፍያውን በወቅቱ ባላሳወቁ እና ባልከፈሉ ላይ የዘገየበት ቅጣትና ወለድ ይታሰባል፡፡

👉🏾 ከክፍያ ነጻ የሆኑ አካላት

1. የመንግሥት ሠራተኞችና ኃላፊዎች፦ ለመንግሥታዊ ሥራ አገልግሎት በሚጠቀሙበት ጊዜ ብቻ፡፡
2. ታዳጊዎች፦ ዕድሜያቸው ከ18 ዓመት በታች የሆኑ ጎብኚዎች፡፡
3. ለረጅም ጊዜ የሚቆዩ ቱሪስቶች ፦ ለመዝናኛና ለቱሪስት አገልግሎት በተከታታይ ከ30 ቀናት በላይ የሚቆዩ ከሆነ፣ ከ30ኛው ቀን በኋላ ያለው ቆይታ ከክፍያ ነፃ ይሆናል፡፡

👉🏾 ለምን ይጠቅማል?
ይህ ገቢ የማዘጋጃ ቤታዊ ገቢ በመሆኑ፣ ለከተሞቻችን መሠረተ ልማት መሳለጥና ለጽዳት ስራዎች ከፍተኛ እገዛ ያደርጋል፡፡ ሁሉም የሆቴል ባለቤቶች በፋይናንስ መዋቅር በተዘጋጀው ደረሰኝ እና የገቢ ኮድ በመጠቀም ግዴታቸውን እንዲወጡ እናሳስባለን፡፡

የደረጃ "ሀ" ግብር ከፋዮች ቅድመ ግብር ክፍያ፦በፌዴራል የገቢ ግብር ማሻሻያ አዋጅ ቁጥር 1395/2017 አንቀጽ 89 መሠረት፤ የደረጃ "ሀ" ግብር ከፋዮች ቅድመ ግብራቸዉን (1/4ኛ) ክፍያ...
12/05/2026

የደረጃ "ሀ" ግብር ከፋዮች ቅድመ ግብር ክፍያ፦

በፌዴራል የገቢ ግብር ማሻሻያ አዋጅ ቁጥር 1395/2017 አንቀጽ 89 መሠረት፤ የደረጃ "ሀ" ግብር ከፋዮች ቅድመ ግብራቸዉን (1/4ኛ) ክፍያ ሲፈጽሙ በሩብ ዓመቱ ተቀናሽ የተደረገባቸው 3% ቅድመ ግብር (Withholding) ታሳቢ ይደረጋል።

በጎፋ ዞን ገቢዎች መምሪያ የ2018 በጀት ዓመት የዘጠኝ ወራት የዕቅድ አፈፃፀም ግምገማና የምክክር መድረክ አካሄደ።‎‎ሣውላ፦ሚያዝያ 30/2018 ዓ/ም‎‎በጎፋ ዞን ገቢዎች መምሪያ የ2018 ...
08/05/2026

በጎፋ ዞን ገቢዎች መምሪያ የ2018 በጀት ዓመት የዘጠኝ ወራት የዕቅድ አፈፃፀም ግምገማና የምክክር መድረክ አካሄደ።

‎ሣውላ፦ሚያዝያ 30/2018 ዓ/ም

‎በጎፋ ዞን ገቢዎች መምሪያ የ2018 በጀት ዓመት የዘጠኝ ወራት ዞን አቀፍ የዕቅድ አፈፃፀም ግምገማና የምክክር መድረክ የጎፋ ዞን ዋና አስተዳደር በተገኙበት ከሁሉም መዋቅር ከመጡ አስተባባሪ አካላትና አመራሮች በተገኙበት አካሄደ።

‎የጎፋ ዞን ዋና አስተዳዳሪ ኢንጂነር ዳግማዊ አየለ በአፈፃፀም ግምገማ መድረኩ ተገኝተው እንደተናገሩት ገቢን አሟጦ መሰብሰብ የማህበረሰብ የመልማት ጥያቄዎችን በየጊዜው ለመመለስ የምናደርገው ተግባር ነው ብለዋል።

‎አክለውም ሆኖም ግን የገቢ አሰባሰባሰባችን ከዘልማዳዊ አሰራር ያልወጣ ዘውትር ታማኝ በሆኑ ግብር ከፋዮች ላይ ብቻ የተንጠለጠለ ነው በማለት ተናግረዋል።

‎በገቢ አሰባሰባችን ግብር ሳይከፍሉ የሚሰሩ እና የትውውቅ ድርሻ አለን ብለው የሚያስቡና ህገ-ወጥነትን የተላመዱ ከአንዳንድ ባለሙያዎች ጋር በመመሳጠር የማይከፍሉ ነጋዴዎች መኖራቸውን ያሳያል ብለዋል።

‎በየመዋቅሩ የመሬት መጠቀሚያ የግብር አሰባሰባችንን በጊዜ እና በወቅት መሰብሰብና ማህበረሰቡን ከዕዳ ነፃ ከማድረግ አኳያ እጅግ በጣም ክፍተቶች ያሉበትና እስከ ዛሬ ድረስ አሟጦ መሰብሰብ አለመቻሉን ተናግረዋል።

‎ኢንጂነር ዳግማዊ አያይዘው እንዳሉት በእጃችን ያሉ ሀብቶችን ስትራቴጅካዊ በሆነ መንገድ ከመሰብሰብና ከተቀመጠላቸው ዓላማ አንፃር ለመጠቀም በየጊዜው የአሰራር ስርዓትን ተከትሎ መስራት ያስፈልጋል ብለዋል።

‎የጎፋ ዞን ገቢ መምሪያ ኃላፊ አቶ ሙሉቀን ጉጃ በበኩላቸው እንዳሉት የ2018 በጀት ዓመት የዘጠኝ ወር ዕቅድ አፈፃፀም ግምገማ በዞን አቀፍ እንዲደረግ የተፈለገበት ዓላማ የገቢ አሰባሰባችንን ክፍተት በመለየት የቀጣይ አቅጣጫ ለማስቀመጥ ተፈልጎ እንደሆነ ተናግረዋል።

‎አቶ ሙሉቀን በተጨማሪ እንደተናገሩት ባለፉት ዘጠኝ ወራት ከጠቅላላ ገቢ 1,568,897,532 ብር ለመሰብሰብ ታቅዶ ገቢ ብር 1,421,975,266 በመሰብሰብ የዕቅዱን 90.64 በመቶ ማሳካታቸውን ተናግረዋል።

‎አክለውም የበጀት ዓመቱ የዘጠኝ ወር ዕቅድ አፈፃፀም ካለፈው ተመሳሳይ ወቅት ጋር ሲነፃፀር በገንዘብ 492,205,021.85 ሲሆን 52.93 በመቶ ዕድገት ተመዝግቧል ብለዋል።

‎በቴክኖሎጂ አጠቃቀም ላይ የገቢ አመራርና ባለሙያ የQR ኮድ ያለው የደረት ባጅና ማንነትን የሚገልፅ መታወቅያ ተሰርቶለት በትዕዛዝ መስክ ስራውን ይሰራል በማለት ተናግረዋል።

‎ የነጋዴው ማህበረሰብም የሚያሳትሙትን ደረሰኞች በQR ኮድ እንድያሳትሙ በማድረግ ህገ-ወጥነትን በማስቀረት የምንፈልገውን የተቀናጀ ልማት እንሰራለን ብለዋል።

‎በመድረኩ ተሳታፊ የሆኑ የመዋቅሮች አስተዳዳሪዎችና የገቢ መምሪያና ጽ/ቤት ኃላፊዎች በሰጡት አስተያዬት እንደተናገሩት የገቢ አሰባሰባችንን ከማሳደግ አንፃር ዘርፈ ብዙ የማነቆ ችግሮች ያሉ ስሆን አንደኛው ችግር የአሰራ ስርዓትን ያለመጠበቅ የክትትልና ቁጥጥር ስራችን ደካማ የመሆን ችግሮች አሉብን ብለዋል።

‎በመጨረሻም የገቢ አሰባሰብ ስርዓትን ማዘመን ፤ህገ-ወጥነትን መከላከል፤የመሬት መጠቀሚያ ግብር አሟጦ መሰብሰብ እና ቀሪ ተግባራትን በቀሪ ጊዜያት በመሰብሰብ ውጤት ለማስመዝገብ የስራ ስምሪትና የቀጣይ አቅጣጫን በማስቀመጥ መድረኩ ተጠናቋል።

የደቡብ ኢትዮጵያ ክልል ገቢዎች ቢሮ የዘጠኝ ወራት የሥራ አፈጻጸም ግምገማ ከዞን እና ሪጂዮፖሊስ ከተሞች ጋር በበይነ መረብ ውይይት አካሄደአርባ ምንጭ –ሚያዚያ 29/2018 ዓ.ም የደቡብ ኢት...
07/05/2026

የደቡብ ኢትዮጵያ ክልል ገቢዎች ቢሮ የዘጠኝ ወራት የሥራ አፈጻጸም ግምገማ ከዞን እና ሪጂዮፖሊስ ከተሞች ጋር በበይነ መረብ ውይይት አካሄደ

አርባ ምንጭ –ሚያዚያ 29/2018 ዓ.ም

የደቡብ ኢትዮጵያ ክልል ገቢዎች ቢሮ በበጀት ዓመቱ የዘጠኝ ወራት የዕቅድ አፈጻጸም ላይ ከዞን እና ከሪጂዮፖሊስ ከተማ አስተዳደር የሥራ ኃላፊዎች ጋር በበይነ-መረብ (Virtual) የታገዘ የውይይት መድረክ አካሄደ።

በመድረኩ ላይ የክልሉ፣ የዞን እና የከተማ አስተዳደር የገቢዎች ቢሮ የሥራ ኃላፊዎችና ባለሙያዎች የተሳተፉ ሲሆን፣ ባለፉት ዘጠኝ ወራት የታዩ ጥንካሬዎችና ድክመቶች ላይ ጥልቅ ግምገማ ተደርጓል።

በተለይም የገቢ አሰባሰብ ሥርዓቱን ይበልጥ ቀልጣፋ ለማድረግና የተቀመጠውን ግብ ለማሳካት በሚያስችሉ ቀጣይ አቅጣጫዎች ላይ ሰፊ ውይይት ተካሂዷል።

የቢሮው ከፍተኛ የሥራ ኃላፊዎች በመድረኩ ማጠቃለያ ላይ እንደገለጹት፤ በቀሩት ጥቂት ወራት የታቀደውን ዓመታዊ የገቢ ግብ ለማሳካት በየደረጃው የሚገኙ የዘርፉ መዋቅሮች በቁርጠኝነት መስራት እንዳለባቸው አሳስበዋል።

በገቢ አሰባሰብ ሂደት ላይ የሚታዩ ክፍተቶች፣ የታክስ ስወራን መከላከል እና የግብር ከፋዮችን ቁጥጥር ማሳደግ በሚቻልባቸው መንገዶች ላይ ትኩረት ተሰጥቷል።

በተለይም የሪጂዮፖሊስ ከተሞችና ዞኖች ያላቸውን የገቢ አቅም በሥራ ላይ በማዋል የክልሉን የልማት ፍላጎት መደገፍ የሚያስችል ገቢ እንዲሰበሰብ ጥሪ ቀርቧል።

ዲጂታል ታክስሚያዚያ 28/2018 ዓ.ም (የገቢዎች ሚኒስቴር)
06/05/2026

ዲጂታል ታክስ

ሚያዚያ 28/2018 ዓ.ም (የገቢዎች ሚኒስቴር)

የ5 ዓመታት ሀገራዊ የታክስ ገቢ አሰባሰብ ዕድገትሚያዚያ 28/2018 ዓ.ም (የገቢዎች ሚኒስቴር)አስተማማኝ የልማት አቅም እንፈጥራለን !
06/05/2026

የ5 ዓመታት ሀገራዊ የታክስ ገቢ አሰባሰብ ዕድገት

ሚያዚያ 28/2018 ዓ.ም (የገቢዎች ሚኒስቴር)

አስተማማኝ የልማት አቅም እንፈጥራለን !

Address

Gofa
Gofa

Telephone

+251903283881

Website

Alerts

Be the first to know and let us send you an email when Gofa Zone Revenue Department posts news and promotions. Your email address will not be used for any other purpose, and you can unsubscribe at any time.

Contact The Organization

Send a message to Gofa Zone Revenue Department:

Share