Jor Woreda Government Communication Affair Office

Jor Woreda Government Communication Affair Office Jor woreda Government communication affair office

ጷጉሜ 3 የጽናት ቀን "በትውልድ ቅብብሎሽ የፀናች ሀገር ኢትዮጵያ" በሚል መሪ ሀሳብ በጋምቤላ ከተማ ዋናው አደባባይ በደማቅ ሁኔታ እየተከበረ ነው። ጷጉሜ 3 /2018 ዓ/ም(የጋምቤላ ከተማ ...
08/09/2026

ጷጉሜ 3 የጽናት ቀን "በትውልድ ቅብብሎሽ የፀናች ሀገር ኢትዮጵያ" በሚል መሪ ሀሳብ በጋምቤላ ከተማ ዋናው አደባባይ በደማቅ ሁኔታ እየተከበረ ነው።

ጷጉሜ 3 /2018 ዓ/ም(የጋምቤላ ከተማ አስተዳደር የመንግስት ኮሙኒኬሽን ጉዳዮች ጽህፈት ቤት)

ጷጉሜ 3 የጽናት ቀን "በትውልድ ቅብብሎሽ የጸናች ሀገር ኢትዮጵያ" በሚል መሪ ሀሳብ በጋምቤላ ከተማ ዋናው አደባባይ ላይ የክልሉ ርዕሰ መስተዳደር ክብርት ወይዘሮ አለሚቱ ኡሞድን ጨምሮ የክልል እና የከተማ አስተዳደሩ ከፍተኛ አመራሮች እና መላው የከተማው ነዋሪዎች እንዲሁም የጸጥታ አካላት በተገኙበት በተለያዩ መርሃ ግብሮች በደማቅ ሁኔታ እየተከበረ ይገኛል።

06/09/2026
05/09/2026
የጆር ወረዳ አጠቃላይ አመራሮች ጨምሮ የወረዳ ትምህርት ጽ/ቤት ባላሙያዎች፣ ርዕሳነ መምህራንና ሱፔርቫይዘሮች የተገኙውበት በ2019 ዓ/ም  ተማሪዎችን ወደ ትምህርት ቤት ለማምጣት የተዘጋጀ የ...
04/09/2026

የጆር ወረዳ አጠቃላይ አመራሮች ጨምሮ የወረዳ ትምህርት ጽ/ቤት ባላሙያዎች፣ ርዕሳነ መምህራንና ሱፔርቫይዘሮች የተገኙውበት በ2019 ዓ/ም ተማሪዎችን ወደ ትምህርት ቤት ለማምጣት የተዘጋጀ የትምህርት ንቅናቄ ሰነድ ዙሪያ ላይ ውይይት ተካሄደ ።

ከጆር ወረዳ መንግስት ኮሙኬሸን ጉዳዮች ጽ/ቤት (ነሐሴ 29/2018 ዓ/ም)
====================

የጆር ወረዳ አጠቃላይ አመራሮች ጨምሮ የወረዳ ትምህርት ጽ/ቤት ባላሙያዎች፣ ርዕሳነ መምህራንና ሱፔርቫይዘሮች የተገኙውበት በ2019 ዓ/ም ተማሪዎችን ወደ ትምህርት ለማምጣት የተዘጋጀ የትምህርት ንቅናቄ ሰነድ ዙሪያ ላይ ውይይት ተካሄደ ።

የንቅናቄ ሰነድ ያቀረቡ በክልል ትምህርት ቢሮ የጎልማሶች ትምህርት ባላሙያ የሆኑት አቶ አብዮት ኡክድ እንደገለፁት የዚህ ሰነድ ዋና ዓላማ የተማሪዎችን ውጤት ለማሻሻል እና መጠነ ማቋረጥን በዘላቂነት ለመቅረፍ የትምህርት ባለድርሻ አካላት እና የወላጆች ከአሁኑ ሰዓት ጀምሮ ትኩረት ሰጥተው እንዲሰሩ ለማድረግ መሆኑ ተገልፁዋል።

በተለይ ሁሉም የትምህርት ባለድርሻ አካላት ማለትም ማህበረሰቡ፣ መምህራኖች፣ ተማሪዎቹም፣ ወላጅ መምህር ህብረት አካላት፣ የወረዳ አመራሩ ጨምሮ የተማሪዎች ውጤትን ለማሻሻል በቅንጅት ሊሰሩ እንደሚገባ አቶ አብዮት ኡክድ አሰረድቷዋል ።

በትምህርት ንቅናቄ መድረክ የክልሉ ኤች አይ ቪ ኤድስ ኢጀንስ ኃላፊ አቶ ኡጁሉ ኡጁሉ ፣ የጆር ወረዳ ም/አሰተዳደሪና ፑብ/ሠር/ሰ/ሀ/ል/ጽ/ቤት ኃላፊ አቶ ኡኬሎ ዋዲ ፣ የጆር ወረዳ ብልጽግና ፓርቲ ጽ/ቤት ኃላፊ አቶ ኡዋር ኡጁሉ ፣የዞኑ ፑብ/ሠር/መምሪያ ባለሙያ አቶ አሽናፊ ዲዱሙ ፣ የወረዳ የትምህርት ጽ/ቤት ኃላፊ አቶ ኡፔድ ኡቻላ እና ባለሙያዎች፣ ርዕሳነ መምህራን፣ ሱፔርቫይዘሮች የተሳተፉ ሲሆን፤ ያለፉ ዓመት የትምህርት አፈፃፀምንም ገምግመዋል።

የጆር ወረዳ ም/አሰተዳደሪና ፑብ/ሠር/ሰ/ሀ/ል/ጽ/ቤት ኃላፊ አቶ ኡኬሎ ዋዲ በበኩላቸው እንደገለፁት የዚህ መድረክ ዋና ዓላማ በዘንድሮው 2019 ዓ/ም በሁሉም ትም/ቤቶች የመማር ማስተማር ሥራ ወቅቱ ጠብቆ ለመጀመርና ዕድሜያቸው ለትምህርት የድረሱ ህፃናቶቹ ወደ ትምህርት ቤት ለማምጣት ያለመ መሆኑ ገልፁዋል ።

የክልሉ ኤች አይ ቪ ኤድስ ኢጀንስ ኃላፊ አቶ ኡጁሉ ኡጁሉ እንደተናገሩት የተማሪዎች ከትምህርት ገበታ መቅረት እና ትምህርት ማቋረጥ የትምህርት ሥርዓቱን ውጤታማነትና ጥራት የሚፈታተኑ በወረዳ ሆነ በሁሉም ወረዳዎች ስር የሰደዱ ማህበራዊና ኢኮኖሚያዊ ማነቆዎች መሆናቸውን ተናግረዋል።

የዛሬው የትምህርት ንቅናቄም እነዚህን ተግዳሮቶች ለመቋቋም የአጭር እና የረጅም ጊዜ መፍትሔዎችን በማቀናጀት በትኩረት አቅጣጫዎች ላይ ተወያይቶ መፍትሔ ለማምጣት መሆኑን ጠቁመዋል ::

በ2019 የትምህርት ዘመን በትምህርቱ ዘርፍ ያሉትን ችግሮች በዘላቂነት ለመቅረፍ እና የትምህርት ቤቶችን ማህበረሰብ ተሳትፎ ለማጠናከር የታቀዱ ውይይቶች እና የንቅናቄ ሥራዎች ተጠናክረው እንደሚቀጥሉ ተናግረዋል።

አቶ ኡጁሉ አክሎው እንደገለፁት የተማሪዎችን ውጤት ለማሻሻል እና መጠነ ማቋረጥን በዘላቂነት ለመቅረፍ የትምህርት ባለድርሻ አካላት እና የወላጆች ትኩረት ወሳኝ ማህበረሰቡ በቅንጅት መስራት እንደሚገባቸው አሳስበዋል።

በመድረኩ ላይ የተሳተፉ ተወያዮችም በበኩላቸው በሰጡት አስተያየት፤ በየጊዜው እያጋጠመ ያለውን የተማሪዎች መቋረጥ እና ውጤት መቀነስ ለመግታት ማህበረሰቡ ከትምህርት ቤት አመራሮች እና ከመንግስት አካላት ጋር በንቃት መተባበር እንዳለበት አንስተዋል።

Address

Gambella
Gambela

Website

Alerts

Be the first to know and let us send you an email when Jor Woreda Government Communication Affair Office posts news and promotions. Your email address will not be used for any other purpose, and you can unsubscribe at any time.

Shortcuts

Share