የባስኬቶ ዞን ወጣቶች ክንፍ ማህበራዊ ሚዲያ ገጽ

የባስኬቶ ዞን ወጣቶች ክንፍ ማህበራዊ ሚዲያ ገጽ ይህ የባስኬቶ ዞን ወጣቶች ክንፍ ይፋዊ የማህበራዊ ድህረገጽ ነዉ ይከተሉ ወቅታዊ የሆኑ መረጃዎችን ያግኙ።

21/08/2026
የማርበርግ ቫይረስ በሽታን ለመከላከልና ለመቆጣጠር በባስኬቶ ዞን ላስካ ከተማ አስተዳደር ለማህበረሰቡ ግንዛቤ የማስጨበጥ ሥራ እየተሰራ መሆኑ ተገለፀ።‎‎ላስካ: ህዳር 20/2018 ዓ/ም (ላስ...
29/11/2025

የማርበርግ ቫይረስ በሽታን ለመከላከልና ለመቆጣጠር በባስኬቶ ዞን ላስካ ከተማ አስተዳደር ለማህበረሰቡ ግንዛቤ የማስጨበጥ ሥራ እየተሰራ መሆኑ ተገለፀ።

‎ላስካ: ህዳር 20/2018 ዓ/ም (ላስካ ኮሙኒኬሽን)
‎በባስኬቶ ዞን ላስካ ከተማ አስተዳደር በሁሉም የከተማዋ መግቢያ እና መውጫ በሮች ላይ የማርበርግ ቫይረስ በሽታን ለመቆጣጠርና ቅድሚያ መከላከል የሚያስችሉ የመከላከያ መንገዶችን ለማህበረሰቡ ግንዛቤ የማስጨበጥ ሥራ እየተሰራ መሆኑ ተገለጿል።

‎የባስኬቶ ዞን ጤና መምሪያ ኃላፊ ወ/ሮ ፍሬሕይወት ቃናኦ የማርበርግ ቫይረስ በሽታን ለመቆጣጠርና ለመከላከል በጤና ሚኒስቴር የወጡ መግለጫዎችን ማህበረሰቡ ተግባራዊ በማድረግ ራሳቸውንና ቤተሰቦቻቸውን ልከላከሉ እንደሚገባቸው በአጽንዖት ገልጸዋል።

ወ/ሮ ፍሬሕይወት ‎አያይዘውም በሽታው የተከሰተበት አካባቢ አጎራባች በመሆኑ ልዩ ጥንቃቄ በማድረግ ቫይረሱ ወደ ዞናችን እንዳይዛመት በሚደረገው ጥረት ሁሉም የህብረተሰብ ክፍሎች ጉልሁን ሚና መወጣት እንዳላቸው አስገንዝበዋል።

‎የላስካ ከተማ አስተዳደር ጤና ጥበቃ ጽ/ቤ ኃላፊ አቶ ፍሬው ደለለኝ የማርበርግ ቫይረስ በሽታ እንዳይዛመት ሁላችንም በመረባረብ በሁሉም የከተማ አስተዳደሩ መግቢያ እና መውጫ በር ላይ ስለ ማርበርግ ቫይረስ በሽታ አስከፊነት እንዲሁም ለመቆጣጠርና ቅድሚያ መከላከል በምያስችሉ የመከላከያ መንገዶች ዙሪያ ለማህበረሰቡ ግንዛቤ የማስጨበጥ ስራ እየተሰራ መሆኑን አስገንዝበዋል።

የላስካ ከተማ አስተዳደር ‎እና የላስካ ዙሪያ ወረዳ የወጣቶች ክንፍ አደረጃጀቶች በጋራ በመሆን በከተማይቱ የመግቢያና የመውጫ በሮች ላይ የእጅ መታጠቢያዎችን በማዘጋጀትና ስለ በሽታው አስከፊነት ማህበረሰቡን
ግንዛቤ በማስጨበጥ ወደ ከተማዋ የሚከትሙ የህበረተሰብ ክፍሎች ራሳቸውንና ሌሎችን ከቫይረሱ እንዲታደጉ ከማስቻል ረገድ ጉልህ አስተዋጽኦ አበርክቶዋል።

‎የላስካ ከተማ አስተዳደር እና የላስካ ዙሪያ ወረዳ የትራፊክ ፖሊሶችም በርካታ አሽከርካሪዎች ቫይረሱ በተገኘበት አጎራባች ዞን ተሣፋሪዎችን አሳፍረው የትራንስፎርት አገልግሎት የሚሰጡ በመሆናቸው ቫይረሱ በቀላሉ እንዳይዛመት በሚደረገው ጥረት ጥብቅ ክትትል እያደረጉ እንደሚገኙ ገልጸዋል።

‎በመጨረሻም ቫይረሱ ልጆችን ያለ ወላጅ፣ ወላጆችን ደግሞ ያለ ጧሪ ልያስቀር የሚችል አደገኛ ወረርሽን በመሆኑ ማህበረሰባችን ይህንን በመገንዘብ አስፈላጊውን ጥንቃቄ ማድረግ እንዳለባቸውም ጥሪ ቀርቧል


ህዳር 20/2018 ዓ/ም
‎ ላስካ

በባስኬቶ ዞን ብልጽግና ፓርቲ ቅ/ጽ/ቤት በአዲስ መልክ  የተመደቡ አመራሮች የሥራ ርክክብ አደረጉህዳር 20/2018 ዓ.ም #ላስካ| በባስኬቶ ዞን ብልጽግና ፓርቲ ቅ/ጽ/ቤት በአዲስ መልክ  የ...
29/11/2025

በባስኬቶ ዞን ብልጽግና ፓርቲ ቅ/ጽ/ቤት በአዲስ መልክ የተመደቡ አመራሮች የሥራ ርክክብ አደረጉ

ህዳር 20/2018 ዓ.ም

#ላስካ| በባስኬቶ ዞን ብልጽግና ፓርቲ ቅ/ጽ/ቤት በአዲስ መልክ የተመደቡ አመራሮች የሥራ ርክክብ አድርገዋል።

የባስኬቶ ዞን ብልጽግና ፓርቲ ቅርንጫፍ ጽ/ቤት ኃላፊና የመንግስት ዋና ተጠሪ አቶ አለምብርሃን ካሣሁን ስርዓትን በማስቀጠል ሂደት ላይ ጤናማ ሽግግር አስፈላጊ መሆኑን ተናግረዋል።

በገጠር እና ከተማ የተጀማመሩ የልማት ሥራዎችን፣ አዳጊ የልማት ጥያቄዎች እና የመልካም አስተዳደር ችግርን ደረጃ በደረጃ ለመፍታት በቅንጅት እንደሚሰሩ ጠቁመዋል።

ሕዝብን ማገልገል ፈተና የበዛበት ነገር ግን በአግባቡ ላገለገለ ሰው ዕድለኝነትም ጭምር እንደሆነ የገለፁት የመንግሥት ዋና ተጠሪ አቶ አለምብሃን ፈተናን በብልሃት ማለፍ እንዳለባቸውም አብራርተዋል።

የቀድሞው የዞኑ ብልጽግና ፓርቲ ቅ/ጽ/ቤት ኃላፊ የነበሩና በአሆኑ የዞኑ ንግድና ኢንዱስትሪ ልማት መምሪያ ኃላፊ ኢንጂነር ዘማች ካንሶ ስልጣንን ለታለመለት ለሕዝብ አገልግሎት መጠቀም እና ለሕዝብ አገልጋይ መሆን እንደሚያስፈልግ ገልጸዋል።

ዞናችን በጎ ተግባርን በማከናወን በክልል ደረጃ የተመሰገነ መሆኑን ጠቁመው በሌሎች የተለያዩ ተግባር ቀዳሚ መሆን አለብን ሲሉ አክለው አብራርተዋል።

በስተመጨረሻ በዞን ማዕከል ያሉ አስተባባሪ አካላት የሥራ ርክክብ በማድረግ፤ ሁሉም በተመደቡበት የተሳካ ጊዜ እና
መልካም የአገልግሎት ጊዜ እንዲሆንላቸው ተመኝተዋል ።

የባስኬቶ ዞን መንግሥት ኮሙዩኒኬሽን አገልግሎት
ህዳር 20/2018 ዓ.ም
ላስካ

እጅግ ልብ ሰባሪ የሀዘን መገለጫ 😭😭😭 ወጣት መ/ር ትግሉ መለሰ  ሰዉ አክባሪ ፣ ታታሪ ፣ አስተዋይ እና ትጉህ ነበርክ    ገና በለጋ ዕድሜህ ሞት ተመኝህ እጅግ በጣም አሳዛኝ ፤ፈጣሪ ነፍስ...
24/11/2025

እጅግ ልብ ሰባሪ የሀዘን መገለጫ 😭😭😭
ወጣት መ/ር ትግሉ መለሰ ሰዉ አክባሪ ፣ ታታሪ ፣ አስተዋይ እና ትጉህ ነበርክ
ገና በለጋ ዕድሜህ ሞት ተመኝህ እጅግ በጣም አሳዛኝ ፤
ፈጣሪ ነፍስህን በአፀደ ገነት ከደጋጎች አጠገብ ያሳርፍ።
ለመላዉ ቤተሰቦቹ እና ለሥራ ባልደረቦቹ መጽናናትን እንመኛለን 😭😭😭😭😭😭😭

በላስካ ዙሪያ ወረዳ በሣሣ እና በሱባ ሁለተኛ ደረጃ ት/ቤት 20ኛውን የብሄር ብሄረሰቦችን ቀን "የዲሞክራሲያዊ መግባባት ለህብረ ብሄራዊ  አንድነት"በሚል መሪ ቃል በደመቀ መልኩ ተከበረ።ላስካ...
24/11/2025

በላስካ ዙሪያ ወረዳ በሣሣ እና በሱባ ሁለተኛ ደረጃ ት/ቤት 20ኛውን የብሄር ብሄረሰቦችን ቀን "የዲሞክራሲያዊ መግባባት ለህብረ ብሄራዊ አንድነት"በሚል መሪ ቃል በደመቀ መልኩ ተከበረ።

ላስካ፣ህዳር 15/2018ዓ.ም(ዙሪያ ወረዳ ኮሙኒኬሽን)

የላስካ ዙሪያ ወረዳ ብልፅግና ፓርቲ ቅ/ጸ/ቤት ወጣቶች ክንፍ ከላስካ ዙሪያ ወረዳ ት/ቤቶች ጽ/ቤት በጋራ በመተባበር በሣሣ ሁለተኛ ደረጃ ት/ቤት የብሄር ብሄረሰቦችን ቀን በተለያዩ ኩነቶች ተከብሯል።

የላስካ ዙሪያ ወረዳ ብልፅግና ፓርቲ ቅ/ጽ/ቤት ወጣቶች ክንፍ ኃላፊ አቶ ሳሙኤል ግርማ ኢትዮጵያ የብዝኃ ቋንቋ፣ ብዝኃ ባህልና ብዝኃ ማንነት ሀገር መሆኗን ገልፀው ትውልዱ ስለሀገራችን ኢትዮጵያ በጥልቀት የሚገነዘቡበት እንደሆነ ገልፀዋል።

ኢትዮጵያውያን የብዝሃ ባህል፣ ታሪክ፣ እሴትና የተፈጥሮ መስህብ መሆናቸውን ለዓለም የሚያስተዋውቁበት መድረክ እንደሆነ መገንዘብ ያስፈልጋል ብለዋል፡፡

የላስካ ዙሪያ ወረዳ ት/ቤቶች ጽ/ቤት ም/ኃላፊ አቶ መምሩ መለሰ ሕገ-መንግስታዊ ሥርዓቱን ለማስረፅ፣ ብሔር-ብሔረሰቦች በማንነታቸው እንዲኮሩና እንዲቀራረቡ ብሎም በበዝኃነት ውስጥ የተጠናከረ ህብረ-ብሔራዊ አንድነት እንዲጎላ ለማድረግ እንደሆነ ገልፀዋል።

አክለው በትምህርት ቤቶች እንድህ አይነት ፕሮግራሞች መካሄዳቸው ስለሀገራችን ኢትዮጵያ እንዲሁም ስለብሄር ብሄረሰቦች ጠንቅቀው የምያውቁበት እንደሆነ ገልፀዋል።

ህብረ ብሄራዊነት ለኢትዮጵያዊያን ተፈጥሯችን፣ ውቤታችንና የጥንካሬአችን ምንጭ እንደሆነ መመልከት ተችሏል።

ሀገር ተረካቢ ተማሪዎች ስለ ብሄር ብሄረሰቦች እኩልነት፣ስለሀገር ፍቅር ጠንቅቀው የምያውቁበት ህብረ ብሄራዊ አንድነትን የምያጠናክሩበት እንደሆነ ነው የተጠቀሰው።

በፕሮግራሙ በሁለት ትምህርት ቤቶች ዕለቱን በተመለከተ የጥያቄና መልስ ውድድር የተካሄደ ሲሆን ለአሸናፍ ተማሪዎች የማበረታቻ ሽልማት ተበርክቶላቸዋል።

ህዳር 15/2018 ዓ.ም
ላስካ
የላስካ ዙሪያ ወረዳ መንግሥት ኮሙዩኒኬሽን አገልግሎት

‎ከወባ በሽታ የፀዳች ኢትዮጵያን ዕውን ለማድረግ የአመራሩንና የህብረተሰቡ ተሳትፎ ጉልህ ሚና እንዳለው ተገለፀ።‎‎ላስካ፡ ህዳር 05/2018 ዓ.ም‎‎የባስኬቶ ዞን ጤና መምሪያ ከወባ በሽታ የ...
14/11/2025

‎ከወባ በሽታ የፀዳች ኢትዮጵያን ዕውን ለማድረግ የአመራሩንና የህብረተሰቡ ተሳትፎ ጉልህ ሚና እንዳለው ተገለፀ።

‎ላስካ፡ ህዳር 05/2018 ዓ.ም

‎የባስኬቶ ዞን ጤና መምሪያ ከወባ በሽታ የፀዳች ኢትዮጵያን ለማየት የአመራሩንና የህብረተሰቡ ተሳትፎ ጉልህ ሚና አለው በሚል የንቅናቄ መድረክ አካሂዷል።

‎የዜጎችን ጤና በመጠበቅ የበለፀገች ኢትዮጵያ ዕውን ለማድረግ ከወባ የፀዳ አከባቢ ለመፍጠር በቅንጅት መስራት እንደሚገባ የባስኬቶ ዞን የመንግስት ዋና ተጠሪ ኢንጂነር ዘማች ካንሶ አስገንዝበዋል።

‎ቀጣይነት ያለው ድጋፍና ክትትል በማድረግ፤ ለህብረተሰቡ የጠራ ግንዛቤ በመፍጠር የወባ በሽታን ለመግታት፤ በትኩረት ተግባራትን መምራት እንደሚገባ ኢ/ር ዘማች ተናግረዋል።

‎የወባ ወረርሽን በሀገሪቱ ኢኮኖሚ ላይ የሚያሳድረው ተጽዕኖ ከፍተኛ መሆኑን የገለፁት የባስኬቶ ዞን ህዝብ ምክር ቤት ዋና አፈ ጉባኤ የተከበሩ አቶ ማርቆስ ልፋቱ የወባ በሽታን ለመከላከል ሁሉም የህብረተሰብ ክፍል የድርሻውን እንዲወጣ መልዕክታቸውን አስተላልፈዋል።

‎መከላከልን መሰረት ያደረገ ፖልስ በመከተል እየተባባሰ የመጣውን የወባ በሽታ ለመግታት እየተሰራ እንደሚገኝ የገለፁት የዞኑ ጤና መምሪያ ኃላፊ አቶ ሙሉቀን ፍሬው የወባ ወረርሽን በመከላከልና በመቆጣጠር ጤናማ ማህበረሰብ ለመፍጠር የሚከናወኑ ተግባራት ተጠናክረው እንደሚቀጥሉ ተናግረዋል።

‎የወባ በሽታን ለመከላከል ባለድርሻ አካላት ማህበረሰቡን በማስተባበር እንዲሰሩ አቶ ሙሉቀን መልዕክታቸውን አስተላልፈዋል።

‎የወባ ንቅናቄ መድረክ ሰነድ በባስኬቶ ዞን ጤና መምሪያ በሽታ መከላከልና ጤና ማጎልበት ሥራ ሂደት ባለሙያ በሆኑት በአቶ አለማየሁ ዘነበ ቀርቦ ምክክር ተደርጎበታል።

‎ "ወባን ማጥፋት ከእኔ ይጀምራል"!
‎ ህዳር 05/2018 ዓ.ም
‎ ላስካ

የብልፅግና ፓርቲ ምክትል ፕሬዝዳንት እና የፓርቲው ፅ/ቤት  ኃላፊ ክቡር አቶ አደም ፋራህ እና የኢፌዴሪ ከተማ እና መሠረተ ልማት ሚኒስቴር ሚኒስትር  ክብርት ወ/ሮ ጫልቱ ሳኒ በ10ኛው የኢት...
14/11/2025

የብልፅግና ፓርቲ ምክትል ፕሬዝዳንት እና የፓርቲው ፅ/ቤት ኃላፊ ክቡር አቶ አደም ፋራህ እና የኢፌዴሪ ከተማ እና መሠረተ ልማት ሚኒስቴር ሚኒስትር ክብርት ወ/ሮ ጫልቱ ሳኒ በ10ኛው የኢትዮጵያ ከተሞች ፎረም ለመከፋል የአፋር ክልል ርዕሰ መዲና ሰመራ ከተማ ገብተዋል።

እንግዶቹ የሱልጣን አሊ ሚራህ አየር ማረፊያ ሲደርሱ የአፋር ክልል ርዕሰ መስተዳድር ክቡር ሃጂ አወል አርባ እና የክልሉ ከፍተኛ አመራሮች ደማቅ አቀባባል አድርገውላቸዋል።

‎ከወባ በሽታ የፀዳች ኢትዮጵያን ዕውን ለማድረግ የአመራሩንና የህብረተሰቡ ተሳትፎ ጉልህ ሚና እንዳለው ተገለፀ።‎‎ላስካ፡ ህዳር 05/2018 ዓ.ም(ባስኬቶ ዞን ኮሙኒኬሽን)‎‎የባስኬቶ ዞን ጤ...
14/11/2025

‎ከወባ በሽታ የፀዳች ኢትዮጵያን ዕውን ለማድረግ የአመራሩንና የህብረተሰቡ ተሳትፎ ጉልህ ሚና እንዳለው ተገለፀ።

‎ላስካ፡ ህዳር 05/2018 ዓ.ም(ባስኬቶ ዞን ኮሙኒኬሽን)

‎የባስኬቶ ዞን ጤና መምሪያ ከወባ በሽታ የፀዳች ኢትዮጵያን ለማየት የአመራሩንና የህብረተሰቡ ተሳትፎ ጉልህ ሚና አለው በሚል የንቅናቄ መድረክ አካሂዷል።

‎የዜጎችን ጤና በመጠበቅ የበለፀገች ኢትዮጵያ ዕውን ለማድረግ ከወባ የፀዳ አከባቢ ለመፍጠር በቅንጅት መስራት እንደሚገባ የባስኬቶ ዞን የመንግስት ዋና ተጠሪ ኢንጂነር ዘማች ካንሶ አስገንዝበዋል።

‎ቀጣይነት ያለው ድጋፍና ክትትል በማድረግ፤ ለህብረተሰቡ የጠራ ግንዛቤ በመፍጠር የወባ በሽታን ለመግታት፤ በትኩረት ተግባራትን መምራት እንደሚገባ ኢ/ር ዘማች ተናግረዋል።

‎የወባ ወረርሽን በሀገሪቱ ኢኮኖሚ ላይ የሚያሳድረው ተጽዕኖ ከፍተኛ መሆኑን የገለፁት የባስኬቶ ዞን ህዝብ ምክር ቤት ዋና አፈ ጉባኤ የተከበሩ አቶ ማርቆስ ልፋቱ የወባ በሽታን ለመከላከል ሁሉም የህብረተሰብ ክፍል የድርሻውን እንዲወጣ መልዕክታቸውን አስተላልፈዋል።

‎መከላከልን መሰረት ያደረገ ፖልስ በመከተል እየተባባሰ የመጣውን የወባ በሽታ ለመግታት እየተሰራ እንደሚገኝ የገለፁት የዞኑ ጤና መምሪያ ኃላፊ አቶ ሙሉቀን ፍሬው የወባ ወረርሽን በመከላከልና በመቆጣጠር ጤናማ ማህበረሰብ ለመፍጠር የሚከናወኑ ተግባራት ተጠናክረው እንደሚቀጥሉ ተናግረዋል።

‎የወባ በሽታን ለመከላከል ባለድርሻ አካላት ማህበረሰቡን በማስተባበር እንዲሰሩ አቶ ሙሉቀን መልዕክታቸውን አስተላልፈዋል።

‎የወባ ንቅናቄ መድረክ ሰነድ በባስኬቶ ዞን ጤና መምሪያ በሽታ መከላከልና ጤና ማጎልበት ሥራ ሂደት ባለሙያ በሆኑት በአቶ አለማየሁ ዘነበ ቀርቦ ምክክር ተደርጎበታል።

‎ "ወባን ማጥፋት ከእኔ ይጀምራል"!
‎ ህዳር 05/2018 ዓ.ም
‎ ላስካ

Address

Felege Niway

Alerts

Be the first to know and let us send you an email when የባስኬቶ ዞን ወጣቶች ክንፍ ማህበራዊ ሚዲያ ገጽ posts news and promotions. Your email address will not be used for any other purpose, and you can unsubscribe at any time.

Shortcuts

Share