የከምባታ ዞን መንግሥት ኮሙኒኬሽን ጉዳዮች መምሪያ

  • Home
  • Ethiopia
  • Durame
  • የከምባታ ዞን መንግሥት ኮሙኒኬሽን ጉዳዮች መምሪያ

የከምባታ ዞን መንግሥት ኮሙኒኬሽን ጉዳዮች መምሪያ የዞናችን ሕዝቦች በላቀ መረጃ በልጽገው የጋራ ውሳኔ ሰጪነታቸውን ማረጋገጥ
(1)

የፓርቲያችን አባላትና ደጋፊዎች ከመለው ህዝብና ከሚመለከታቸው ባለድርሻዎች ጋር በመሆን 7ኛው ሀገራዊ ምርጫ ፍጹም ሰላማዊና ስኬታማ ሆኖ እንዲጠናቀቅ ላበረከቱት ግንባር ቀደም ተሳትፎ አቶ ተክ...
03/06/2026

የፓርቲያችን አባላትና ደጋፊዎች ከመለው ህዝብና ከሚመለከታቸው ባለድርሻዎች ጋር በመሆን 7ኛው ሀገራዊ ምርጫ ፍጹም ሰላማዊና ስኬታማ ሆኖ እንዲጠናቀቅ ላበረከቱት ግንባር ቀደም ተሳትፎ አቶ ተክሌ ስዩም ምስጋናቸውን አቀረቡ!

የከምባታ ዞን ብልጽግና ፓርቲ ቅ/ጽ/ቤት ኃላፊ አቶ ተክሌ ስዩሞ 7ኛው ሀገራዊ ምርጫ በሰላም እንዲጠናቀቅ ሚናቸውን ለተወጡ ለፓርቲው አባላትና ደጋፊዎች እንዲሁም በምርጫ ሂደቱ ለተሳተፉ ተቋማትና አካላት በሙሉ ምስጋናቸውን አቅርበዋል፣

ምርጫ የዲሞክራሲያዊ ሥርዓት አንዱ መገለጫና በህዝብ የተመረጠ መንግስት ለመመሠረት ትልቅ መሣሪያ ነው፣ ይህ ሂደት ለ7ኛ ዙር በሀገራችን በተካሄደበት በዚህ ወቅት በዞናችን የሚገኙ የፓርቲያችን አባላትና ደጋፊዎች፣ የሚመለከታቸው በሙሉ ከምርጫ ቅስቀሳ እስከ ድምጽ መስጫ ቀን ድረስ ላደረጉት ጠንካራ ተሳትፎ አቶ ተክሌ ስዩም ልባዊ ምስጋናቸውን አቅርበዋል፣

የብልጽግና ፓርቲ 'ኢትዮጵያን ወደ ተምሳሌት ሀገር!' በሚል መሪ ሀሳብ የምርጫ ቅስቀሳውን ሀገረ መንግስትና ብሔረ መንግስት ግንባታ እውን ለማድረግ ሁለንተናዊ ብልጽግናን ለማረጋገጥ በመደመርና እሳቤ በማህበራዊ፣ በኢኖሚያዊና በፖለቲካው በሁሉም ዘርፎች የኢትዮጵያን ሁለንተናዊ ብልጽግናን ለማረጋገጥ ፓርቲው ትኩረት አድርጎ እየሰራ መሆኑንም ይህም በሰላምና በዲሞክራሲያዊ ህደት የሚረጋገጥ ይሆናልም ነው ያሉት፣

ሰላም ለሁሉም እንቅስቃሴያችን ዋና ነገር በመሆኑ በምርጫ ህደት ውስጥ ለሰላም የተሰጠው ትኩረት ተጠናክሮ መቀጠል እንዳለበት፣ የመደመር፣ የመተባበርና የመደጋገፍ ባህል ማጎልበት፣ ከነጠላ ትርክት ይልቅ ገዥና አሰባሳቢ ትርክት ለማስፈን ትኩረት በመስጠት በልማትና በዲሞክራሲያዊ ሥርዓት ግንባታችን የአስተሳሰብ የበላይነት እንዲያገኝ ትኩረት እንደሚሰጥም በመልዕክታቸው ገልጸዋል፣

በመጨረሻም 7ኛ ሀገራዊ ጠቅላላ ምርጫ በሰላምና በውጤታማነት ግቦቹን ያሳካ እንዲሆን ያልተገደበ ድጋፋችሁን ያበረከታችሁ አመራር አካላት፣ የፓርቲው አባላትና ደጋፊዎች፣ ፀጥታ አስከባሪ አካላት እና በምርጫው ህደት ውስጥ ለተሳተፉ በሙሉ አቶ ተክሌ ስዩም ልባዊ ምስጋናቸውን አቅርበዋል፣

ከምባታ ዞን ብልጽግና ፓርቲ ጽ/ቤት

የከምባታ ዞን ዋና አስተዳዳሪ የተከበሩ አቶ አረጋ እሸቱ የሰባተኛው ጠቅላላ ምርጫ በሰላም መጠናቀቅን አስመልክቶ የምስጋና መልዕክት አስተላለፉ‎‎በከምባታ ዞን በሁሉም የምርጫ ጣቢያዎች ሰባተኛ...
02/06/2026

የከምባታ ዞን ዋና አስተዳዳሪ የተከበሩ አቶ አረጋ እሸቱ የሰባተኛው ጠቅላላ ምርጫ በሰላም መጠናቀቅን አስመልክቶ የምስጋና መልዕክት አስተላለፉ

‎በከምባታ ዞን በሁሉም የምርጫ ጣቢያዎች ሰባተኛው ሀገራዊና ክልላዊ ምርጫ ሒደት ፍፁም ሰላማዊ በሆነ መልኩ በመጠናቀቁ የከምባታ ዞን ዋና አስተዳዳሪ አቶ አረጋ እሼቱ ለመራጩ ሕዝብና በምርጫው ሂደት ለተሳተፉ አካላት ሁሉ የምስጋና መልዕክት አስተላልፈዋል።

ዋና አስተዳዳሪው በመልዕክታቸው ግንቦት 24 ቀን 2018 ዓ/ም የከምባታ ዞን መራጭ ሕዝብ ከሌሊቱ 11 ሰዓት ጀምሮ በየምርጫ ጣቢያው በመሰለፍ ከ12 ሰዓት ጀምሮ እስከ ድምፅ አሰጣጥ ሒደት ፍፃሜ ድረስ በሁሉም የምርጫ ጣቢያዎች በመገኘት ተወካዮቻቸውን በመምረጥ ለሀገራቸው ዕድገትና ለዴሞክራሲያዊ ሥርዓቱ መጠናከር አስተዋጽኦ የሚያበረክተውን ድምፃቸውን በሰላማዊ መንገድ መስጠታቸውን ገልጸዋል።

‎በምርጫው ዕለት በአብዛኛዎቹ የምርጫ ጣቢያዎች የነበረውን ዝናብና ቅዝቃዜ ተቋቁመውና "ኢትዮጵያ እየመረጠች" መሆኗን ለዓለም ሕዝብ በአደባባይ በማሳየት ጭምር ለሚቀጥሉት አምስት ዓመታት ኢትዮጵያን ይመራል ብለው ያመኑትን ፓርቲ በነቂስ ወጥተው በመምረጥ የሚያኮራ ተግባር ፈፅመዋል ብለዋል።

የሀገራችንን ዴሞክራሲያዊ ሒደት በተጨባጭ በመደገፍ ከጅምር እስከ ፍፃሜ ወኪሉን ለመምረጥ በምርጫው ላይ ለተሳተፈው ሕዝብ፣ አድናቆትም ምስጋናም ያቀረቡት ዋና አስተዳዳሪው ዜጎች በሠላም እንዲመርጡ እያንዳንዱ ምርጫ ጣቢያና መላ ዞኑ ሰላማዊ እንዲሆን በትጋት ለሰሩ የፀጥታ አካላት፣ በየምርጫ ጣቢያዎች የምርጫውን ሒደት ላስተባበሩ ብሎም ለመሩ አመራሮች፣ ለሲቪክ ማኅበራት ተወካዮች፣ ለምርጫ አስፈጻሚዎች፣ ታዛቢዎች እንዲሁም ለመላው የዞኑ ሕዝብ የላቀ ምስጋና አቅርበዋል።

‎በመጨረሻም በቅድመ ምርጫ እና በምርጫው ዕለት የተስተዋለው የሕዝቡ የዳበረ የዴሞክራሲ ባህል፣ የአንድነት መንፈስ እና የሕግ የበላይነት እሴት መገለጫ መሆኑን የገለፁት ዋና አስተዳዳሪው በድኅረ ምርጫ ወቅትም በተመሳሳይ ሁኔታ መቀጠል እንዳለበት አስገንዝበዋል።

‎የምርጫው ዕለት የነበረው መደማመጥ፣ ሀገራዊ ተቆርቋሪነት፣ ትብብርና ሰላማዊ ተሳትፎ ከዚህ በኋላ በሚኖሩ መሰል ሀገራዊ፣ ክልላዊና ዞናዊ የልማት ጥሪዎችና ሌሎች ጉዳዮችም ተጠናክሮ እንዲቀጥል ጥሪ አቅርበዋል።

ፈጣሪ ኢትዮጵያንና ሕዝቦቿን አብዝቶ ይባርክ

‎ኢትዮጵያ መርጣለች፣ አሸንፋለች!!

‎አቶ አረጋ እሸቱ
‎የከምባታ ዞን ዋና አስተዳዳሪ

02/06/2026
‎ሰባተኛው ጠቅላላ ምርጫ ያለምንም የፀጥታ ችግር በሰላማዊ ሁኔታ መጠናቀቁን የከምባታ ዞን ሠላምና ፀጥታ መምሪያ አስታወቀ።‎‎የከምባታ ዞን ሠላምና ፀጥታ መምሪያ ኃላፊ አቶ መልካሙ ማቴዎስ የ...
02/06/2026

‎ሰባተኛው ጠቅላላ ምርጫ ያለምንም የፀጥታ ችግር በሰላማዊ ሁኔታ መጠናቀቁን የከምባታ ዞን ሠላምና ፀጥታ መምሪያ አስታወቀ።

‎የከምባታ ዞን ሠላምና ፀጥታ መምሪያ ኃላፊ አቶ መልካሙ ማቴዎስ የምርጫውን መጠናቀቅ አስመልክቶ በሰጡት መግለጫ በዞኑ ሁሉም አካባቢዎች ምርጫው ያለምንም የፀጥታ ችግር በሠላም ተጠናቅቋል ብለዋል።

‎በዞኑ አምስት የምርጫ ክልሎችና 306 የምርጫ ጣቢያዎችና በጠምባሮ ምርጫ ክልል 31 የምርጫ ጣቢያዎች በድምሩ 337 የምርጫ ጣቢያዎ መኖራቸው ያስታወቁት ኃላፊው በሁሉም የምርጫ ጣቢያዎች የድምፅ ቆጠራ ተጠናቅቆ ኮሮጆዎች ወደ የምርጫ ክልሎች ተጠቃልለው መግባታቸውን ተናግረዋል።

‎ከምርጫው ሰላማዊነት ጋር በተያያዘ ዜጎች ድምጻቸውን ዴሞክራሲያዊ መብታቸውን ተጠቅመው በነጻነት መምረጣቸውንም ኃላፊው ጠቁመዋል።

‎ለዚህም ከቅድመ ምርጫ ጀምሮ እስከ ድኅረ ምርጫ ድረስ ያለውን የምርጫ ሒደት በተናበበ መልኩ ሥራዎችን በጋራ መሥራት በመቻሉ የመጣ ውጤት ስለመሆኑም አቶ መልካሙ ማቴዎስ በመግለጫቸው አመላክተዋል።

‎የምርጫው ሰዓት መራዘም ተከትሎ እንደዞን ያለው ሁኔታ በተረጋጋ መልኩ እንዲካሔድ ተደርጓል።

‎ምርጫው ሠላማዊ ሆኖ እዲጠናቀቅ የባለድርሻ አካላት ሚና በተለይም ከህዝቡ ጋር በቅንጅት የተሰሩ ሥራዎች ውጤታማ ናቸው ያሉት አቶ መልካሙ ማቴዎስ ከፖለቲካ ፓርቲዎች የጋራ ምክር ቤትና የሲቪል ማህበራት የምርጫ አፈጻጸሙን በመከታተል ረገድ የጎላ ድርሻ እንደነበራቸውም ገልፀዋል።

‎ምርጫው ያለምንም የፀጥታ ችግር ሠላማዊ ሆኖ እንዲጠናቀቅ አበርክቶ ላደረጉ የፀጥታው መዋቅር፣ የፀጥታው ግብረ ኃይል፣ ፖሊስ፣ ሚሊሻና መላው ሕዝብ ምስጋና አቅርበዋል።

በድህረ ምርጫ ወቅት የሚከናወኑ ዋና ዋና ተግባራት ምንድናቸው?7ኛው ጠቅላላ ምርጫ በትናንትናው ዕለት በስኬት መጠናቀቁን ተከትሎ፣ ሀገራችን በአሁኑ ወቅት አዲስ የፖለቲካ፣ ማኅበራዊ እና ኢኮኖ...
02/06/2026

በድህረ ምርጫ ወቅት የሚከናወኑ ዋና ዋና ተግባራት ምንድናቸው?

7ኛው ጠቅላላ ምርጫ በትናንትናው ዕለት በስኬት መጠናቀቁን ተከትሎ፣ ሀገራችን በአሁኑ ወቅት አዲስ የፖለቲካ፣ ማኅበራዊ እና ኢኮኖሚያዊ አቅጣጫ የሚቀረጽበት ወሳኝ የድህረ ምርጫ ምዕራፍ ላይ ትገኛለች፡፡

ይህ ወቅት የምርጫ ሂደት የመጨረሻው ምዕራፍና የሕዝብ ድምፅ ወደ ተግባራዊ መንግሥታዊ ሥራ የሚቀየርበት ወሳኝ ድልድይ ነው፡፡

በዚህ ወሳኝ የድህረ ምርጫ ምዕራፍ የሚከናወኑ ዋና ዋና ተግባራት የሚከተሉት ናቸው፦

በየምርጫ ጣቢያው የተሰጡ ድምፆች በግልጽነት ተቆጥረውና ተረጋግጠው በብሔራዊ ምርጫ ቦርድ በኩል ጊዜያዊ እና የመጨረሻ ውጤቶች ለሕዝብ ይፋ ይደረጋሉ፡፡

በተያያዥም የሀገር ውስጥ እና ዓለም አቀፍ ታዛቢዎች በሂደቱ ላይ ያስተዋሏቸውን ጠንካራና ደካማ ጎኖች የያዘ ይፋዊ መግለጫ እና ምክረ-ሀሳብ ያቀርባሉ፡፡

በሂደቱ ወይም በውጤቱ ላይ ቅሬታ ያላቸው ተፎካካሪ ፓርቲዎች ወይም የግል እጩዎች ያቀረቧቸውን አቤቱታዎች የምርጫ ቦርድ እና ፍርድ ቤቶች መርምረው ሕጋዊ ውሳኔ የሚሰጡበት ወቅት በመሆኑ፣ ማንኛውም ውዝግብ በሰላማዊና በሕጋዊ መንገድ ብቻ እንዲፈታ ይደረጋል፡፡

በተጨማሪም የምርጫ አስፈጻሚው አካል የሰው ኃይል፣ የቴክኖሎጂ እና የበጀት አጠቃቀሙን የሚገመግምበት ሲሆን፣ ሂደቱ በሰላማዊ መንገድ የፖለቲካ ሥልጣን ሽግግር የሚከናወንበት የሕግ የበላይነት መገለጫ ነው፡፡(EBC)

02/06/2026
ሰባተኛው ጠቅላላ ምርጫ የተረጋጋ፣ ሰላማዊ፣ ዴሞክራሲያዊ እና በዓለም አቀፍ መስፈርቶች መሰረት ደረጃውን የጠበቀ ሆኖ ተጠናቋል፡- ኢሰመኮሰባተኛው ጠቅላላ ምርጫ የተረጋጋ፣ ሰላማዊ፣ ዴሞክራሲያ...
02/06/2026

ሰባተኛው ጠቅላላ ምርጫ የተረጋጋ፣ ሰላማዊ፣ ዴሞክራሲያዊ እና በዓለም አቀፍ መስፈርቶች መሰረት ደረጃውን የጠበቀ ሆኖ ተጠናቋል፡- ኢሰመኮ

ሰባተኛው ጠቅላላ ምርጫ የተረጋጋ፣ ሰላማዊ፣ ዴሞክራሲያዊ እና በዓለም አቀፍ መስፈርቶች መሰረት ደረጃውን የጠበቀ እንደሆነ ባደረገው ምልከታና ክትትል ማረጋገጡን የኢትዮጵያ ሰብዓዊ መብቶች ኮሚሽን (ኢሰመኮ) አስታወቀ፡፡

የኮሚሽኑ ዋና ኮሚሽነር አቶ ብርሃኑ አዴሎ በሰጡት መግለጫ፤ ኮሚሽኑ በምርጫው ሂደት ላይ ታዛቢ ባለሙያዎችን በማሰማራት ሂደቱን በቅርበት ሲከታተል መቆየቱን ገልጸዋል።

በዚህም ምርጫው የተረጋጋ፣ ሰላማዊ፣ ዴሞክራሲያዊ እና በዓለም አቀፍ መስፈርቶች መሰረት ደረጃውን የጠበቀ መሆኑን ኮሚሽኑ ባደረገው ምልከታና ክትትል ማረጋገጡን ጠቅሰዋል።

ከዚህ በተጨማሪም ለምርጫው ሂደት የሚያስፈልጉ ቁሳቁሶች በሙሉ በተገቢው መልኩ ተሟልተው መቅረባቸውን ጠቁመዋል።

በምርጫው ዕለት በምርጫ ጣቢያዎች ላይ የታዩትን ረጃጅም ሰልፎች በተመለከተ፣ ኮሚሽኑ ለቦርድ ጥቆማ ማቅረቡን ጠቅሰው፤ ቦርዱም በቀረበለት ጥቆማ መሰረት የማስተካከያ እርምጃዎችን መውሰዱን ምባራራታቸውን ኢዜአ ዘግቧል።

ኮሚሽኑ በቀጣይም በድህረ-ምርጫ ሂደቶች ላይ ተከታታይ ክትትል እንደሚያደርግና በሂደቱ የሚያገኛቸውን ማናቸውንም ግኝቶች ለሕዝብ ይፋ እንደሚያደርግ አስታውቀዋል።

(EBC)

ሕዝቡ ሕጋዊ ካልሆኑ ከማንኛውም ምንጮች ከሚወጡ መረጃዎች ራሱን እንዲጠብቅ ምርጫ ቦርድ አሳሰበ የኢትዮጵያ ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ መራጮች በትላንትናው ዕለት ግንቦት 24 ቀን 2018 ዓ.ም በከፍ...
02/06/2026

ሕዝቡ ሕጋዊ ካልሆኑ ከማንኛውም ምንጮች ከሚወጡ መረጃዎች ራሱን እንዲጠብቅ ምርጫ ቦርድ አሳሰበ

የኢትዮጵያ ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ መራጮች በትላንትናው ዕለት ግንቦት 24 ቀን 2018 ዓ.ም በከፍተኛ ንቃት እና ትዕግሥት ድምፃቸውን ስለሰጡ አመስግኗል።

በምርጫ ሕጉ መሠረት ውጤት በቦርዱ ይፋ እስከሚሆን ድረስም በትዕግሥት እንዲጠብቁ እና ሌሎች አካላትም ያልተረጋገጡ መረጃዎችን ከማሰራጨት እንዲቆጠቡ፤ ሕዝቡም ከመሰል መረጃዎች ራሱን እንዲጠብቅ ቦርዱ አሳስቧል። (EBC)

በሰባተኛው ጠቅላላ ምርጫ ህዝቡ በዴሞክራሲ ባህል ግንባታ ላይ ያለውን ተሳትፎ ያሳየበት እንደነበር ተመላከተ (ሆሳዕና፣ግንቦት 25/2018)የማዕከላዊ ኢተዮጵያ ክልል የፖለቲካ ፓርቲዎች የጋራ ...
02/06/2026

በሰባተኛው ጠቅላላ ምርጫ ህዝቡ በዴሞክራሲ ባህል ግንባታ ላይ ያለውን ተሳትፎ ያሳየበት እንደነበር ተመላከተ

(ሆሳዕና፣ግንቦት 25/2018)የማዕከላዊ ኢተዮጵያ ክልል የፖለቲካ ፓርቲዎች የጋራ ምክር ቤት የሰባተኛው ጠቅላላ ምርጫ ድምጽ አሰጣጥ ሂደት መጠናቀቁን አስመልክቶ ለመገናኛ ብዙሃን መግለጫ ሰጥቷል።

የማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል የፖለቲካ ፓርቲዎች የጋራ ምክር ቤት ሰብሳቢ አቶ ደምስ ገብሬ ለመገናኛ ብዙሀን በሰጡት መግለጫ እንደገለጹት በሰባተኛው ጠቅላላ ምርጫ ህዝቡ በዴሞክራሲ ባህል ግንባታ ላይ ያለውን ተሳትፎ ያሳየበት እንደነበር ተናግረዋል።

ህዝቡ በነቂስ ወጥቶ በመሳተፍ በሰላማዊ መንገድ ድምጹን ሲመርጥ መዋሉን ተናግረዋል ።

በክልሉ ትላንት በተካሔደው ጠቅላላ ምርጫ ላይ 17 የፖለቲካ ፓርቲዎች መሳተፋቸውን የገለጹት አቶ ደምስ ምርጫው ከታወጀበት ጊዜ ጀምሮ የጋራ ምክር ቤቱ የላቀ ጥረት ሲያደርግ መቆየቱን ጠቁመዋል።

ምርጫ ለሀገረ መንግስት ግንባታ የጎላ አስተዋጽኦ እንደሚያበረክት የተናገሩት ሰብሳቢው ለዚህም የጋራ ምክር ቤቱ ምርጫው ሰላማዊ፣ዴሞክራሲያዊ እና ተአማኒነት ያለው ሆኖ እንዲጠናቀቅ በትኩረት ሲሰራ እንደነበር አስታውሰዋል።

ተፎካካሪ ፓርቲዎች የሀገሪቱን እና ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ ያወጣውን ህግ እየተከተሉ መሄድ ተገቢ መሆኑን አብራርተዋል።

የጋራ ምክር ቤቱ በየጊዜው የሚፈጠሩ ችግሮችን በውይይት እየፈታ መምጣቱን ጠቅሰዋል።

በትላንትናው ጠቅላላ ሀገራዊ ምርጫ ህዝቡ በነጻነት ወጥቶ በተረጋጋና ሰላማዊ በሆነ መንገድ ድምጽ ሲሰጥ መዋሉን አቶ ደምስ በመግለጫቸው ጠቅሰዋል።

ምርጫ ሊያደናቅፍ የሚችል ችግር አለመግጠሙን የተናገሩት ሰብሳቢው ይህ ደግሞ ህዝቡ የሚፈልገውን ፓርቲ በነጻነት እንዲመርጥ አስችሎታል ሲሉም አብራርተዋል።

ህዝቡ የምርጫው ሂደት ሰላማዊ እንዲሆን ላደረገው የላቀ ጥረት አቶ ደምስ ምስጋና አቅርበዋል።

የጋራ ምክር ቤቱ ምክትል ሰብሳቢ አቶ በረከት ከድር በበኩላቸው ሰባተኛው ጠቅላላ ምርጫ በዋና ዋና መመዘኛዎች ሲታይ ሰላማዊ፣ፍትሀዊ እና ተአማኒነት ያለው ምርጫ ነው ብለዋል።

በክልሉ ለመጀመሪያ ጊዜ የተካሔደ ምርጫ ነው ያሉት አቶ በረከት በገዢው ፓርቲ ፣በተፎካካሪ ፓርቲዎች እንዲሁም በመንግስት በኩል ምርጫውን ለማካሔድ የነበረው ዝግጅት ውጤታማ መሆኑን ጠቅሰዋል።

የምርጫው ሂደት ሰላማዊ እንደነበር የተናገሩት አቶ በረከት በክልሉ 15 የፖለቲካ ፓርቲዎች እና 5 የግል እጩዎች መሳተፋቸውን አስረድተዋል።

ምርጫ የዲሞክራሲ ስርአት ግንባታ መሰረት ነው ያሉት ምክትል ሰብሳቢው ዜጎች በመረጡት መንግስት የመተዳደር መብትን የሚያረጋግጥ ስለመሆኑም ጠቅሰዋል።

ዜጎች በምርጫ የሚያደርጉት ንቁ ተሳትፎ ለሰላም፣ ለልማት እና ለዴሞክራሲ ስርዓት ግንባታ የሚኖረው አበርክቶ ከፍተኛ መሆኑን አቶ በረከት በመግለጫቸው አብራርተዋል።

ክልሉን የተሞክሮ ማዕከል ለማድረግ የተጀመረው ጥረት ውጤታማ ነው ያሉት ምክትል ሰብሳቢው የሰላም እና የተረጋጋ የፖለቲካ ባህል ግንባታ ተምሳሌት መሆኑን ተናግረዋል።

በክልሉ በሁሉም አካባቢዎች በ35 የምርጫ ክልሎች የፖለቲካ ፓርቲዎች የጋራ ምክር ቤት ማቋቋም በመቻሉ ለምርጫው ስኬታማነት የጎላ አበርክቶ እንደነበረው ጠቅሰዋል።

Central Ethiopia Regional Government Communication Affairs bureau

Address

Karl Henz Street
Durame

Alerts

Be the first to know and let us send you an email when የከምባታ ዞን መንግሥት ኮሙኒኬሽን ጉዳዮች መምሪያ posts news and promotions. Your email address will not be used for any other purpose, and you can unsubscribe at any time.

Contact The Organization

Send a message to የከምባታ ዞን መንግሥት ኮሙኒኬሽን ጉዳዮች መምሪያ:

Share