CERS TVET Bureau - የማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል ቴክኒክና ሙያ ትምህርትና ስልጠና ቢሮ

  • Home
  • Ethiopia
  • Durame
  • CERS TVET Bureau - የማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል ቴክኒክና ሙያ ትምህርትና ስልጠና ቢሮ

CERS TVET Bureau - የማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል ቴክኒክና ሙያ ትምህርትና ስልጠና ቢሮ This page is dedicated to sharing info about skill, knowledge, technology, innovation & job creation

05/08/2025
የአንድ ጀምበር የሰባት መቶ ሚሊዮን ሀገራዊ ችግኝ ተከላ አካል የሆነው የችግኝ መትከል ዘመቻ  ተከናወነ፡፡‎‎‎”በመትከል ማንሰራራት” በሚል መሪ ቃል የሰባተኛው ዓመት ግብ የአንድ ጀምበር ሰ...
31/07/2025

የአንድ ጀምበር የሰባት መቶ ሚሊዮን ሀገራዊ ችግኝ ተከላ አካል የሆነው የችግኝ መትከል ዘመቻ ተከናወነ፡፡


‎”በመትከል ማንሰራራት” በሚል መሪ ቃል የሰባተኛው ዓመት ግብ የአንድ ጀምበር ሰባት መቶ ሚሊዮን ችግኝ ተከላ አካል የሆነው የችግኝ ተከላ ዘመቻ በሾኔ ፖሊ ቴክኒክ ኮሌጅ በተሳካ ሁኔታ ተከናውኗል፡፡

👉‎በችግኝ ተከላው ዘመቻ ላይ የማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል ቴክኒክና ሙያ ትምህርት ሥልጠና ቢሮ ከፍተኛ የሥራ ኃላፊዎች፣ የሾኔ ከተማ አስተዳደር የሥራ ኃላፊዎች፣ የሾኔ ፖሊ ቴክኒክ ኮሌጅ ዲኖች፣ የማኔጅመንት አባላትና አጠቃላይ የኮሌጁ ማኅበረሰብ ተገኝተዋል፡፡

👉‎የሾኔ ፖሊ ቴክኒክ ኮሌጅ ዲን አቶ ተሻለ ተካልኝ በችግኝ ተከላው ወቅት ተገኝተው እንዳሉት በሀገር አቀፍ ደረጃ ሰባት መቶ ሚለዮን፣ በክልላችን ስምንት ነጥብ ስድሰት ሚሊዮን፣ በዞናችን አንድ ነጥብ ሁለት ሚሊዮንና በኮሌጃችን ሶስት ሺህ አምስት መቶ ችግኞች በላይ ይተከላሉ ብለዋል፡፡

👉‎ችግኝ መትከል ነገን ከማረጋገጥ ባለፈ የህልውናችንን መሰረት በቤተሰብ ደረጃ መበልጸግን መነሻ ያደረገ ነው ያሉት ኃላፊው ሁሉም ዜጋ በነፍስ ወከፍ የተከለውን ችግኝ መንከባከብ እንዳለበት አጽንዖት ሰጥተው ተናግረዋል፡፡

👉‎በዛሬው ዕለትም መላ ኢትዮጵያውያን በአንድ ጀምበር በአረንጓዴ ዐሻራው ዓለም የሚደነቅበት ተዓምር የሠራንበት ታሪካዊ ዕለት በመሆኑ አጠቃላይ የኮሌጃችንን ማኅበረሰብ የዚህ ሁነት ተሳታፊ መሆኑ እጅግ የምያስመሰግነው ነው በማለት መልዕክታቸውን አስተላልፈዋል፡፡

👉‎በችግኝ ተከላው ዘመቻ ወቅት የተገኙት የማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል ቴክኒክና ሙያ ትምህርትና ሥልጠና ቢሮ ኃላፊ ኢ/ር ሰለሞን ፈርሻ በበኩላቸው የችግኝ ተከላው ዛሬ ላይ ቆመን ለነገ ትውልድ የምንሰራው ሥራ ከመሆኑ ባሻገር ለዘለቄታዊ ብልጽግና ዋሰትና ነው ብለዋል፡፡

👉‎ሥነ - ምህዳሩን የጠበቀ፣ በተከታታይ ክትትል የለማ፣ ከአየር ንብረት ብክለት ነጻ የሆነ፣ ለወደፊት ለትውልዱ ምቹ የሆነ ሀገር ማስረከብ የምንችለው ችግኝ ስንተክል ነው ብለዋል፡፡

👉‎የሚተከሉ ችግኞች ከአከባቢው የማደግና የመበልጸግ እሳቤን መሰረት ያደረገና በዕውቀት ላይ ተመስርቶ ነገን ከግናዛቤ ያስገባ ኃላፊነትን መወጣት እንዲሚገባም ተናግረዋል፡፡

👉‎የምድረ ገቢውን ውበት መጠበቅ የሚችሉ፣ለምግብነት የሚያገለግሉና ኢኮኖሚን የሚያመነጩ ችግኞችን መትከል ወቅቱ የሚፈልገውን ፋይዳ ከማሰገኘታቸው ባሻገር ብልጽግናችንን እንድናረጋግጥ የማይተካ ሚና እንዳለው ምክትል ቢሮ ኃላፊው አውስተዋል፡፡

👉‎የሾኔ ከተማ አስተዳደር ከንቲባ አቶ አበራ በዶሬ በችግኝ ተከላው ወቅት በሾኔ ፖሊ ቴክኒክ ኮሌጅ የተገኙ ሲሆን ችግኞችን መትከል የዜግነት ድርሻን መወጣት እንደሆነ ገልጸው ከመትከል ባሻገርም የተተከሉ ችግኞችን ዘውትር ክትትል በማድረግ መንከባከብ ያስፈልጋል ብለዋል፡፡

👉‎በአንድ ጀምበር ሰባት ሚሊዮን በላይ ችግኞችን በሀገር አቀፍ ደረጃ በመትከል ኢትዮጵያውያን ታሪክ የሚሰሩበት ዕለት ከመሆኑም ባሻገር የምንተክለው ችግኝ ውበት፣ ምግብ፣ጥላና እሰትንፋስ በመሆኑ ሁሉም ዜጋ በመሰጠት የተተከሉ ችግኞችን መንከባከብ እንዳለበት የችግኝ ዘመቻው ተሳታፊዎች ገልጸዋል፡፡

👉‎በችግኝ ተከላው ዘመቻ ወቅት የማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልለ ቴክኒክና ሙያ ትምህርትና ሥልጠና ቢሮ ምክትልና የቴክኖሎጂ ሽግግርና ኢንደስትሪ ኤክስቴንሽን ዘርፍ ኃላፊ አቶ ይስሃቅ ማሶሬ፣ የቢሮ ኃላፊ አማካሪ አቶ ነስር ያሲን እና የሃዲያ ዞን ሳይንስና ቴክኖሎጂ መምሪያ ኃላፊ ወ/ሮ ገነት ሙሉጌታ ተገኝተዋል፡፡

ፍሬዉ ሀይሉ

31/07/2025

👍👌

ፈጣንና ዘላቂነት ያለው የኢኮኖሚ ዕድገት ለማምጣት እና ድህነትን ለመቅረፍ የቴክኒክና ሙያ ትምህርትና ስልጠና ተቋማት ሚና የጎላ መሆኑ ተገለፀ።ሐምሌ 23/2017 ዓ.ምዱራሜ።የማዕከላዊ ኢትዮጵ...
30/07/2025

ፈጣንና ዘላቂነት ያለው የኢኮኖሚ ዕድገት ለማምጣት እና ድህነትን ለመቅረፍ የቴክኒክና ሙያ ትምህርትና ስልጠና ተቋማት ሚና የጎላ መሆኑ ተገለፀ።

ሐምሌ 23/2017 ዓ.ም
ዱራሜ።

የማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል የቴክኒክና ሙያ ትምህርትና ስልጠና ቢሮ ክልላዊ የዲፈረንሼሽን ጥናት ቫሊዴሽን ወርክሾፕ በዱራሜ ከተማ እያካሔደ ይገኛል።

መድረኩን በይፋ ያስጀመሩት የማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል ቴክኒክና ሙያ ትምህርትና ስልጠና ቢሮ ኃላፊ አቶ አሰፋ ደቼ በሀገር ዘላቂ ልማትና ድህነትን የማስወገድ እቅድ የቴክኒክና ሙያ ትምህርትና ስልጠና ዓላማ በኢኮኖሚያዊና ማኅበራዊ ዘርፎች ፍላጎት ላይ የተመሰረተ ትምህርት እና ስልጠና በመስጠት ዜጎችን ተጠቃሚ ማድረግ መሆኑን ተናግረዋል።

ፈጣንና ዘላቂነት ያለው የኢኮኖሚ እድገት ለማምጣት እና ድህነትን ለማስወገድ የቴክኒክና ሙያ ትምህርትና ስልጠና ተቋማት ተግባቢ ክህሎትን የተላበሰ ተግባራዊ ክህሎትና ብቃት ያለው ተፈላጊ የሰው ኃይል በማፍራት ለዘርፉ ስትራቴጂክ ዕቅድ መሳካት የበኩላቸውን አስተዋጽኦ ሊያበረክቱ እንደሚገባም አሳስበዋል።

የማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል ቴክኒክና ሙያ ትምህርትና ስልጠና ቢሮ ምክትል የቢሮ ኃላፊና የተቋማት አቅም ግንባታና ጥራት ማረጋገጫ ዘርፍ ኃላፊ ኢንጂነር ሰለሞን ፈርሻ የቴክኒክና ሙያ ተቋማትን ዘመኑ የደረሰበት ደረጃ ላይ ለማድረስ ተቋማቱን በሥራ ገበያ ፍላጎት መቃኘትና በሥራ ገበያው ተፈላጊ የሆኑ የሙያ ስልጠናዎችን እንዲሰጡ ማድረግ ይገባል ብለዋል።

በክልሉ ወቅታዊ የቴክኒክና ሙያ ተቋማት ቁመና የስልጠና ፕሮግራሞች ተመሳሳይነት የበዛባቸው ከሥራ ፍላጎት ገበያው ጋር ያልተጣጣመ እና የስልጠናው ሁኔታ ሁሉንም ዓይነት የሙያ መስኮች የሚነካካ ቢሆንም በአንዱም የሙያ መስክ የልህቀት ማዕከል መሆን አለመቻላቸውን የገለፁት ኢንጂነር ሰለሞን የስልጠና ሒደታቸውም የቴክኒክና ሙያ ትምህርትና ስልጠና ማዕቀፍ ከሚፈቅደው ውጪ በንድፈ ሀሳብ ስልጠናዎች የተሞሉ መሆናቸውን ተናግረዋል።

በመሆኑም እነዚህን ምክንያቶች መነሻ በማድረግ የዲፈሬንሼሽን ወይም የስልጠና መስኮችን በሙያ መስመር ለያይቶ በአካባቢ ፀጋ እና በሥራ ፍላጎት መሰረት ማጥናት ድግግሞሽን ለማስቀረትና ብቁ ሰልጣኞችን ለማፍራት እንደሚያግዝም ኃላፊው አብራርተዋል።

የማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል ቴክኒክና ሙያ ትምህርትና ሥልጠና ቢሮ ’’ከመስፈንጠር ከፍታ ወደ ላቀ እምርታ’’  በሚል መሪ ሀሳብ የብልጽግና ቤተሰብ አበላት የምዘና መድረክ  አካሄደ።‎‎     ...
29/07/2025

የማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል ቴክኒክና ሙያ ትምህርትና ሥልጠና ቢሮ ’’ከመስፈንጠር ከፍታ ወደ ላቀ እምርታ’’ በሚል መሪ ሀሳብ የብልጽግና ቤተሰብ አበላት የምዘና መድረክ አካሄደ።

‎ ሐምሌ 22 ቀን 2017 ዓ/ም
‎ ዱራሜ

‎የማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል ቴክኒክና ሙያ ትምህርትና ስልጠና ቢሮ የብልጽግና ቤተሰብ አበላት ምዘና የቢሮው ከፍተኛ የሥራ ኃላፊዎች፣ የዘርፍ አስተባባሪዎች፣ ዳይሬክተሮችና የብልጽግና ቤተሰብ አባላት በተገኙበት ተካሄዷል፡፡

‎የምዘና መድረኩን የቢሮው ምክትልና የተቋማት አቅም ግንባታና ጥራት ማረጋገጫ ዘርፍ ኃላፊ አ/ር ሰለሞን ፈርሻ የመሩት ሲሆን በ2017 ዓ.ም የስራ ዘመን የተከናወኑ የመንግሥትና የፓርቲ ሥራዎች በውጤት የታጀቡ እንደነበሩ በማብራራት የመወያያ መነሻ ሀሳቦች አቅርበዋል።

‎በበጀት ዓመቱ ከዕቅድ ምዕራፍ ጀምሮ በቂ ዝግጅት በማድረግ፣የውይይት እና የግንኙነት አግባብ በማጠናከር÷ የአባላት ተሳትፎ በማሳደግ የህዝብ ተጠቃሚነት ለማረጋገጥ የሚያስችሉ የተለያዩ ስኬታማ ተግባራት ማከናወናቸው በመድረኩ ተመልክቷል።

‎ይህን መነሻ በማድረግ የአባላት ምዘና የተካሄደ ሲሆን ምዘናው አባላቱን ለቀጣይ ተልእኮ በሚያዘጋጅ አግባብ ተከናውኗል።

የመድረኩ ተሳታፊዎችም ራሳቸው በ2018 የበጀት ዓመት ለላቀ ተልእኮ ዝግጁ ሆነው እንዲቀርቡ የሚያግዝ መማማርን÷መገነባባትን እና መተራረምን መሰረት ያደረገ የምዘና ሂደት እንደነበር እና በቀጣዩ ጊዜ የላቀ ውጤት ለማስመዝገብ የሚያግዛቸው መሆኑ አብራርተዋል።


‎በመጨረሻም በጋራ መድረክ ማጠቃለያ የተደረገ ሲሆን የቢሮው ምክትልና የስልጠናና የተቋማት እቅም ግንባታና ዘርፍ ኃላፊ ኢ/ር ሰለሞን ፈርሻ ቀጣዩ የሥራ ዘመን በተግባር አፈጻጸም ከምንጊዜም በላይ የላቀ ውጤት ለማስመዝገብ የምንሰራበት መሆኑ ለዚህ ደግሞ መነሻ የሚሆን ጥራት ያለው ዕቅድ መዘጋጀቱ አክለዉ ገልፀዋል።

የማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል ቴክኒክና ሙያ ትምህርትና ሥልጠና ቢሮ የብልጽግና ቤተሰብ አበላት ምዘና ተጀመረ።‎‎     ሐምሌ 22 ቀን 2017 ዓ/ም‎     ዱራሜ‎‎የማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል ...
29/07/2025

የማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል ቴክኒክና ሙያ ትምህርትና ሥልጠና ቢሮ የብልጽግና ቤተሰብ አበላት ምዘና ተጀመረ።

‎ ሐምሌ 22 ቀን 2017 ዓ/ም
‎ ዱራሜ

‎የማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል ቴክኒክና ሙያ ትምህርትና ስልጠና ቢሮ የብልጽግና ቤተሰብ አበላት ምዘና በቢሮ ኃላፊ ቢሮ እየተከሄደ ይገኛል።

‎መድረኩን እየመሩ የሚገኙት የቢሮ ምክትል ኃላፊ እና የስልጠናና የተቋማት አቅም ግንባታ ዘርፍ ኃላፊ ኢንጂነር ሰለሞን ፈርሻ ለምዘናዉ መነሻ እንዲሆን ከበጀት ዓመቱ የክላስተርና የቢሮዉን ጥንካሬ እና ጉድለቶችን የያዘ ሀሳብ አንስተዋል።

‎የ2017 ዓ.ም የመንግሥትና የፓርቲ ሥራዎች አፈጻጸም ጠንካራ ጎኖችና መሻሻል የሚገባቸው ጉድለቶችን በማንሳት ያብራሩት ም/ቢሮ ኃላፊው አባላት ምዘናውን ፍጹም በሆነ ንቁ ተሳትፎ መከታተል እንዳለባቸው አብራርተዋል።

‎የምዘና መድረኩም የማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል ቴክኒክና ሙያ ትምህርትና ሥልጠና ቢሮ ም/ቢሮ ኃላፊና የቴክኖሎጂ ሽግግርና ኢንደስትሪ ኤክስቴነሽን ዘርፍ ኃላፊ አቶ ይስሃቅ ማሶሬና የቢሮ ኃላፊ አማካሪ አቶ ነስሩ ያሲን በተኙበት ቀጥሏል።

27/07/2025
4 ቀን ቀረው!ሐምሌ 24 ፣2017 700 ሚሊዮን ችግኝ በአንድ ጀንበር። እንዘጋጅ!4 days to go!July 31, 2025   will attempt planting 700 million seedl...
27/07/2025

4 ቀን ቀረው!

ሐምሌ 24 ፣2017 700 ሚሊዮን ችግኝ በአንድ ጀንበር። እንዘጋጅ!

4 days to go!

July 31, 2025 will attempt planting 700 million seedlings in one day. Let’s get ready as the count down begins.

#አረንጓዴዐሻራ

የማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል ሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት የማህበራዊ ዘርፍ ቋሚ ኮሚቴ የቴክኒክና ሙያ ትምህርትና ስልጠና ቢሮ የ2017 በጀት ዓመት ዕቅድ አፈጻጸምን ገምግሟል።ሀምሌ 10/2017 ...
17/07/2025

የማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል ሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት የማህበራዊ ዘርፍ ቋሚ ኮሚቴ የቴክኒክና ሙያ ትምህርትና ስልጠና ቢሮ የ2017 በጀት ዓመት ዕቅድ አፈጻጸምን ገምግሟል።

ሀምሌ 10/2017 ዓ. ም

የማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል ምክር ቤት የማህበራዊ ጉዳዮች ቋሚ ኮሚቴ ሰብሳቢ አቶ ግዛቸው ዋሌራ ተቋሙን በገመገመበት ወቅት እንደገለፁት ተቋሙ ለተለያዩ ሰልጣኞች የአጭር ጊዜ ስልጠና እየሰጠ ያለበትን አግባብ ተጠናክሮ ሊቀጥል ይገባል ብለዋል።

ለሀገር ውስጥና ለውጪ ሀገር የስራ ስምሪት እየተሰጠ የሚገኘዉ ስልጠና አበራታች በመሆኑ የሰለጠነ የሰው ሀይልን ለማፍራት የሚደረገውን ጥረት እንዲያጠናክሩም አሳስበዋል።

በፈጠራና ክህሎት ተግባር ችግር ፈቺ ስራዎችን በመስራት የህብረተሰቡን ተጠቃሚነት የበለጠ ለማሳደግ መስራት አለባቸውም ብለዋል።

ከበጀት አመቱ መጀመሪያ አንቶ የሴተሩ ባለሙያዎችና አመራሮች በአዳዲስ እሳቤዎች ዙሪያ አቅም ከመገንባት አኳያ የተከናወኑ ተግባራትም አበረታች መሆናቸው ተመላክቷል::

በበጀት አመቱ የተከናወኑ ተግባራት በጥልቀት የተገመ ገመ ሲሆን በርካታ ጥንካሬዎች እና ጥቂት ዉስንነቶች የነበሩበት በድምሩ ስኬታማ የበጀት አመት የነበረ መሆ ኑ ተገምግሟል::

16/07/2025
የውጭ ሃገር የሥራ ዕድል...በሥራና ክህሎት ሚንስቴር የውጪ ሃገር ሥራ ስምሪት በሰለጠነ እና በከፊል የሰለጠነ የሰው ሃይል የዜጎችን መብት፣ ደህንነት እና ጥቅም አስጠብቆ በማሰማራት ትልቅ ስ...
16/07/2025

የውጭ ሃገር የሥራ ዕድል...

በሥራና ክህሎት ሚንስቴር የውጪ ሃገር ሥራ ስምሪት በሰለጠነ እና በከፊል የሰለጠነ የሰው ሃይል የዜጎችን መብት፣ ደህንነት እና ጥቅም አስጠብቆ በማሰማራት ትልቅ ስኬት መመዝገቡ ይታወቃል።

አሁንም ህጋዊ የውጪ ሃገር ሥራ ስምሪት በሰለጠነ የሰው ሃይል በተለያዩ የሞያ ዘርፎች በቁጥር ከፍተኛ የሆነ የሰው ሃይል ይፈለጋል።

በመሆኑም ከዚህ በታች በተዘረዘሩት የሞያ ዘርፎች መሰማራት የምትፈልጉ በሙሉ ከታች በተቀመጠው ሊንክ በመግባት ፎርሙን ሞልታችሁ የእድሉ ተጠቃሚ እንድትሆኑ ስንል እናሳውቃለን።

Driving & Transportation
1. Light Vehicle Driver
2. Heavy Vehicle Driver (e.g., Grader Operator)
3. House Driver
4. Trolley Operator

Security & Safety
5. Security Guard
6. CCTV Surveillance Operator
7. Office Security Personnel
8. Plumber
9. Electrician
10. HVAC Technician
11. AC Technician
12. Pumper

Domestic & Facility Services
13. Housekeeper
14. House Maid
15. House Cleaner
16. Housekeeping Supervisor
17. Houseman
18. Caretaker
19. Steward
20. Laundry Attendant
21. Bellman

Hospitality & Food Services
22. Receptionist
23. Waiter/Waitress
24. Barista
25. Sous Chef
26. Pastry Chef / Dessert Chef
27. Garde Manger Chef
28. Arabica Cuisine Chef
29. Kitchen Assistant
30. Private Cook
31. Room Attendant
32. Hotel Assistant Manager

Healthcare & Caregiving
33. Nurse
34. Junior Nurse
35. Home Care Nurse
36. Private Nurse
37. Junior Midwife / Clinical Nurse
38. Elderly Care Assistant
39. Live-in Support Assistant
40. Neonatal Intensive Care Unit (NICU) Nurse
41. Junior Physiotherapist

Childcare Services
42. Babysitter
43. Childcare Worker

Beauty & Salon Services
44. Hairdresser
45. Hairstylist
46. Beauty Therapist
47. Salon Manager
48. Nail Technician
49. Nail Art Instructor
50. Massage Therapist
51. Makeup Artist

Agriculture & Farming
52. Indoor Farmer
53. General Farm Worker

Administrative & Marketing
54. Junior Administrative Assistant
55. Junior Marketing Assistant
56. Junior Account Manager
57. Sales Representative
58. Purchaser

Skilled Labor
59. Construction Worker
60. Laborer
61. Tailor
62. Storekeeper
63. Supervisor

Retail & Customer Services
64. Cashier
65. Promoter

https://forms.gle/TF5BcYBtrhwkyjR59

መልካም ዕድል!

የሥራ ባለቤት

Address

Durame

Telephone

+251913163063

Website

Alerts

Be the first to know and let us send you an email when CERS TVET Bureau - የማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል ቴክኒክና ሙያ ትምህርትና ስልጠና ቢሮ posts news and promotions. Your email address will not be used for any other purpose, and you can unsubscribe at any time.

Contact The Organization

Send a message to CERS TVET Bureau - የማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል ቴክኒክና ሙያ ትምህርትና ስልጠና ቢሮ:

Share