የድሬዳዋ ፍትህ ፀጥታና ህግ ጉዳዮች ቢሮ Diredawa Justice Security and Law Affairs Office

  • Home
  • Ethiopia
  • Dire Dawa
  • የድሬዳዋ ፍትህ ፀጥታና ህግ ጉዳዮች ቢሮ Diredawa Justice Security and Law Affairs Office

የድሬዳዋ ፍትህ ፀጥታና ህግ ጉዳዮች ቢሮ  Diredawa Justice Security and Law Affairs Office Contact information, map and directions, contact form, opening hours, services, ratings, photos, videos and announcements from የድሬዳዋ ፍትህ ፀጥታና ህግ ጉዳዮች ቢሮ Diredawa Justice Security and Law Affairs Office, Government Organization, Dire Dawa.

25/04/2026
 #እንኳን ለኢየሱስ ክርስቶስ የትንሣኤ ፋሲካ በዓል በሰላም አደረሳችሁ ::የድ/ዳ/አስ/ፍትህ ፀጥታና ህግ ጉ/ቢሮ::::::::::::::::::::[[[[[]]]]]:::::::::::::::::::...
11/04/2026

#እንኳን ለኢየሱስ ክርስቶስ የትንሣኤ ፋሲካ በዓል በሰላም አደረሳችሁ ::
የድ/ዳ/አስ/ፍትህ ፀጥታና ህግ ጉ/ቢሮ
::::::::::::::::::::[[[[[]]]]]::::::::::::::::::::
እንኳን ለኢየሱስ ክርስቶስ የትንሣኤ ፋሲካ በዓል በሰላም አደረሳችሁ እያለ በዓሉ የሰላም የደስታ የተቸገሩ ወገኖችን በመርዳት በመደጋገፍ በአብሮነት የምናሳልፈው በዓል እንዲሆን የድ/ዳ/አስ/ፍትህ ፀጥታና ህግ ጉ/ቢሮ ከልብ ይመኛል ።
በድጋሚ መልካም የትንሳኤ ፋሲካ በዓል
:::::::::::::::::======:::::::::::::::::
የድ/ዳ/አስ/ፍትህ ፀጥታና ህግ ጉ/ቢሮ

እንኳን ለ2018 ዓ.ም የኢየሱስ ክርስቶስ ትንሳኤ (ፋሲካ) በዓል በሰላም አደረሳችሁ።::::::::::መላው የክርስትና እምነት ተከታይ ወገኖቼ፥ በዐብይ የጾም ወር ለወገኖቻችሁ በፍቅር ከፈፀማ...
11/04/2026

እንኳን ለ2018 ዓ.ም የኢየሱስ ክርስቶስ ትንሳኤ (ፋሲካ) በዓል በሰላም አደረሳችሁ።
::::::::::
መላው የክርስትና እምነት ተከታይ ወገኖቼ፥ በዐብይ የጾም ወር ለወገኖቻችሁ በፍቅር ከፈፀማችሁት ሰብዓዊ ተግባር ባሻገር በጸሎት እና በስግደት ያለፉት እነዚያ ቀናት፥ በዕለት ተዕለት ህይወታችን ማየት የምንፈልገው ጤናማ ስኬት፥ ያለ ብርቱ ጥረት፥ ድካም እና መስዋዕትነት ሊመጣ እንደማይችል ማስተማሪያ እንደሆኑ አልጠራጠርም።

ሳይወድቁ መነሳት፥ ምሽትን ሳያልፉ ንጋትን ማየት አይታሰብምና፤ መላው የአስተዳደራችን ነዋሪዎች የግል ልዩነቶቻችንን ወደጎን ትተን፥ የጋራ መኖሪያችን ለሆነችው 'ትንሿ ኢትዮጵያ' ድሬዳዋ ሁለንተናዊ እድገት እና ትንሳኤ በመትጋት፥ ቤተሰባዊ ኃላፊነታችንን እንድንወጣ ወንድማዊ ጥሪዬን እያቀረብኩ፥ የትንሳኤ በዓል የፍቅር፥ የአብሮነት፥ የበጎነት እና የብልፅግና እንዲሆንላችሁ እመኛለሁ።

መልካም በዓል

Hordooftoota Amantaa Kiriistiyaanaa maraaf Baga ayyaana Faasikaa bara 2018tiin Nagayaan isin gahe.

Lammiilee too kanneen Hordooftoota Amantaa Kiristiyaanaa taataan hundi keeysan, keeysattu ji'oottan lamaan dabraniif sirna Kadhannaa, Soomaa fi Sagadaa keessatti, hojii namoomaa gaggaarii gaggeeysitaniin daran, jiruu teenya tan guyyaa-guyyaa keeysatti milkaa'ina fayya qabeessa ta'e kan argachuu barbaannu dadhabinaa, ciminaa, dhama'iinsaa fi wareegama tokkoon malee goonkuma arkachuu kan hin dandeenye tahuu Ji'ootta barumsa nuuf kennan tahuun shakkii qabu.

Goonkuma osoo hin kufne ka’uun, osoo halkan hin bariine hafuun hinyaadamu; tanaafJiraattonni Bulchiinsa keenyaa hundi garaa garummaa dhuunfaa keenya moggaatti dhiifnee, Iddoo jireenya hunda keenyaa tan taate "Itiyoophiyaa xiqqoo" Dirree Dhawaa teenyaaf guddina waloo fi Badhaadhina isiitiif cimnee carraaquun itti-gaafatamummaa keenyaa abbummaan akka bahaannu waamicha koo dhiheeysaa Ayyaanni "Tinsaa'ee" kan Jaalalaa, kan Danoomaa, kan Toluummaa fi Badhaadhinaa akka isiniif tahuun hawwa.

Ayyaana Gaarii!

11/04/2026
 #ዜና | የስቅለት በዓል በኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተ-ክርስቲያን ተከበረ።::::::::::::::የስቅለት በዓል ዛሬ ከማለዳው ጀምሮ በድሬዳዋ በሚገኙ የክርስትና ኃይማኖት ተከታዮች ዘን...
10/04/2026

#ዜና | የስቅለት በዓል በኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተ-ክርስቲያን ተከበረ።
::::::::::::::
የስቅለት በዓል ዛሬ ከማለዳው ጀምሮ በድሬዳዋ በሚገኙ የክርስትና ኃይማኖት ተከታዮች ዘንድ በስግደት፣ በዝማሬ፣ በፀሎት እና በንስሃ ታስቦ ውሏል።

በድሬዳዋ ደብረሰላም መድኃኔዓለም ካቴድራል በተከናወነው ሃይማኖታዊ ስነ-ስርዓት ላይ የአስተዳደሩ ከንቲባ ከድር ጁሃር ጨምሮ የአስተዳደሩ ከፍተኛ የመንግስት አመራሮች ለህዝበ ክርስትያኑ የማዕድ ማጋራት አካሂደዋል።

የወረዳ 05 አስተዳደር ጽ/ቤት ከስግደት ለሚመለሱ የክርስትና እህት ወንድሞቻቸው ማዕድ በማዘጋጀት አጋርተዋል።

በትናንትናው እለት የጸሎተ ሐሙስ ‘ሕፅበተ እግር" ስነ ስርዓት በእምነቱ ተከታዮች ዘንድ መከበሩ የሚታወስ ሲሆን የፊታችን እሁድ የትንሳኤ በዓል በመላው የክርስትና እምነት ተከታዮች ዘንድ በተለያዩ ዝግጅቶች የሚከበር ይሆናል።
/- Dire tv አማርኛ:-/

22/03/2026
  የድሬዳዋ አስተዳደር ከንቲባ፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡ የድሬዳዋ አስተዳደር ከንቲባ የተከበሩ  አቶ ከድር ጁሀር 1447ኛው የኢድ አልፈጥር በአል አስመልክቶ ያስተላለፉት መልዕክት ፡፡፡፡፡...
19/03/2026


የድሬዳዋ አስተዳደር ከንቲባ
፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡
የድሬዳዋ አስተዳደር ከንቲባ የተከበሩ አቶ ከድር ጁሀር 1447ኛው የኢድ አልፈጥር በአል አስመልክቶ ያስተላለፉት መልዕክት
፡፡፡፡፡፡፡
#እንኳን ለ1447ኛው የኢድ አል-ፊጥር ረመዳን በዓል፥ በሰላም እና በጤና አደረሰን/አደረሳችሁ።

ያሳለፍነው የረመዳን ጾም ወር ፥ ዋነኛ ሥርዓቶች ከሆኑት የፀሎት እና የስግደት መንፈሳዊ ተግባራት በተጨማሪ ፥ በብዙ የበረከት ሥራዎች የታጀበ ወር ነበር።

ዘንድሮ የረመዳን ወር እና የክርስትና ዕምነት ተከታዮች ዐቢይ ጾም በተመሳሳይ ቀን በመጀመራቸው ፥ ከጥንትም 'በትንሿ ኢትዮጵያ' #ድሬዳዋ ህብረተሰብ ውስጥ የኖረው የፍቅር እና አብሮነት ውብ እሴት፥ በይበልጥ ደምቆ መታየቱ የማይካድ ሀቅ ነው።

የነገዋ የኢድ ዕለት፥ በረመዳን የጾም ወር የፈፀምናቸውን የአንድነት፥ የእዝነት፥ የመረዳዳት እና ሌሎች በርካታ መልካም እሴቶች አጠንክረን፥ በቀጣይ የዕለት ተዕለት ኑሯችን ውስጥ ለማስቀጠል ለራሳችን ቃል የምንገባበት ልዩ ቀን ናት።

'ረመዳን ሙባረክ' ተባብለን የጀመርነውን የጾም፥ ፀሎት እና ስግደት ወር በሰላም እንድንጨረስ ለረዳን ፈጣሪ ምስጋና እያቀረብኩ፥ ለመላው የእስልምና እምነት ተከታይ ወገኖቼ ይህ በዓል የፍቅር፥ የመረዳዳት እና የአብሮነት እንዲሆንላችሁ እመኛለሁ።
ኢድ ሙባረክ
::::::

የድሬዳዋ አስተዳደር ከንቲባ

10/03/2026

Address

Dire Dawa

Website

Alerts

Be the first to know and let us send you an email when የድሬዳዋ ፍትህ ፀጥታና ህግ ጉዳዮች ቢሮ Diredawa Justice Security and Law Affairs Office posts news and promotions. Your email address will not be used for any other purpose, and you can unsubscribe at any time.

Share