Dire Traffic Police-ድሬ ትራፊክ ፖሊስ

Dire Traffic Police-ድሬ ትራፊክ ፖሊስ ድሬ ከትራፊክ አደጋ የፀዳች እንድትሆን ተግተን እንሰራለን።

  ሰዓዳ መሀመድበድሬዳዋ ፖሊስ ጠቅላይ መምሪያ የመንገድ ትራፊክ ቁጥጥር ዳይሬክቶሬት ዳይሬክተር​እንኳን ለዚህ ታላቅ ክብርና ማዕረግ በበቃት አበቃሽ!ለመላው የድሬዳዋ ህዝብና ለከተማዋ ሰላምና...
29/05/2026

ሰዓዳ መሀመድ

በድሬዳዋ ፖሊስ ጠቅላይ መምሪያ የመንገድ ትራፊክ ቁጥጥር ዳይሬክቶሬት ዳይሬክተር

​እንኳን ለዚህ ታላቅ ክብርና ማዕረግ በበቃት አበቃሽ!

ለመላው የድሬዳዋ ህዝብና ለከተማዋ ሰላምና ደህንነት የምታበረክቺው አስተዋጽኦ ለዚህ ከፍተኛ ሃላፊነት ስላበቃሽ የተሰማንን ታላቅ ደስታ እየገለጽን፣ እንኳን ደስ አለሽ እንላለን።

በምድብ ስራሽ ሁሉ መልካም የስራ ዘመንና ስኬት እንዲሆንልሽ ከልብ እንመኛለን!

የመንገድ ትራፊክ ቁጥጥር ዳይሬክቶሬት

 "153 ኛው ሳምንት የድሬ ትራፊክ ፖሊስ አባላት ሳምንትዊ የስፖርት እንቅስቃሴ                      #በፎቶ🚶‍♂️🚶‍♀️       🚶‍♂️🚶‍♀️           🚶‍♂️🚶‍♀️ 👍...
29/05/2026


"153 ኛው ሳምንት የድሬ ትራፊክ ፖሊስ አባላት ሳምንትዊ የስፖርት እንቅስቃሴ
#በፎቶ
🚶‍♂️🚶‍♀️ 🚶‍♂️🚶‍♀️ 🚶‍♂️🚶‍♀️
👍👍👍ድሬ ትራፊክ ፖሊስ 👍👍👍

23/05/2026


በስህተት ወደ አካውንቱ የገባለትን 50 ሺህ ብር የመለሰው የድሬዳዋ ወጣት

​በዛሬው ዘመን የታማኝነት እና የቅንነት መገለጫ የሆኑ ሰዎችን ማግኘት እጅግ ብርቅ እየሆነ በመጣበት በዚህ ወቅት፣ በድሬዳዋ ከተማ የታየ አንድ እውነተኛ ታሪክ የብዙዎችን ቀልብ ስቧል።

በስህተት ወደ ባንክ አካውንቱ የገባለትን ከፍተኛ የገንዘብ መጠን ያለምንም ማንገራገር ለባለቤቱ የመለሰው ወጣት አሽከርካሪ፣ ለብዙዎች አርአያ የሚሆን ተግባር ፈጽሟል።

​የድሬዳዋ የሌሊት ታክሲ አሽከርካሪዎች ማህበር አባል የሆነው ወጣት እዩኤል ሙልጌታ ፣ በዕለቱ እንደማንኛውም ቀን የዕለት ተዕለት ሥራውን እያከናወነ ነበር። ሆኖም ግን ባልተጠበቀ ሁኔታ ወደ ንግድ ባንክ አካውንቱ 50,000 (ሀምሳ ሺህ) ብር ገቢ መደረጉን የሚገልጽ የዓይነት መልዕክት (SMS) ይደርሰዋል። ወጣቱ እዩኤል ይህ ገንዘብ ከማንም የሚጠብቀው እንዳልሆነና በስህተት የገባ መሆኑን ለመረዳት ጊዜ አልወሰደበትም።

​ይህን ገንዘብ በስህተት ወደ እዩኤል ሙሉጌታ አካውንት ያስገባችው በዱባይ የምትኖር ሳናይት አበጋዝ የተባለች ግለሰብ ናት። ሳናይት በሀገር ውስጥ ለሚገኙ ዘመዶቿ አስቸኳይ እርዳታ ለማድረስ አስባ ገንዘቡን ስትልክ፣ በቁጥር መሳሳት ምክንያት ገንዘቡ ቀጥታ ወደ ወጣት እዩኤል አካውንት ሊገባ ችሏል።
በወቅቱ ገንዘቡ የደረሳቸው መስሏት የነበሩት ሳናይትና ቤተሰቦቿ፣ በኋላ ላይ ስህተት መፈጠሩን ሲረዱ ከፍተኛ ድንጋጤና ጭንቀት ውስጥ ወድቀው ነበር።

​ወጣት እዩኤል ግን የገንዘቡን መግባት ካወቀበት ቅጽበት ጀምሮ ሕሊናው የሰውን ንብረት ለመውሰድ አልፈቀደም። "የሰው ሀቅ የሰው ነው፤ በላቤ ያልሰራሁበትን ገንዘብ አልነካም" በማለት ወዲያውኑ ወደ ባንክ በመሄድ ተገቢውን ማጣራት አድርጓል። በመጨረሻም ሙሉ ገንዘቡን በስህተት ወደላከችው ወደ ሳናይት አበጋዝ አካውንት በታማኝነት እንዲመለስ አድርጓል።

​ይህንን ያልተጠበቀ ታማኝነት የተመለከቱት ባለቤቷ ሳናይት እና ቤተሰቦቿ፣ በወጣቱ ተግባር እጅግ በማድነቅ ምስጋና አቀርበዋል ።

​ይህ የእዩኤል ተግባር ግላዊ ጥንካሬ ብቻ ሳይሆን፣ እርሱ የሚገኝበት ማህበር መገለጫም ጭምር ነው። ባለፉት ጥቂት ዓመታት ተደራጅቶ ወደ ሥራ የገባው የድሬ የሌሊት ታክሲ አሽከርካሪዎች ማህበር፣ አባላቱ በሚያሳዩት መልካም ስነ-ምግባር የከተማዋ ኩራት እየሆነ መጥቷል።

​ማህበሩ በተለይ በሌሊት ጉዞ ወቅት በታክሲዎች ውስጥ ጠፍተው እና ተረስተው የሚቀሩ ውድ ንብረቶችን፣ ስልኮችንና ገንዘቦችን በጥንቃቄ ጠብቆ ለባለቤቶቹ በመመለስ ይታወቃል።

​እነዚህ ወጣቶች በምሽት ለከተማዋ ነዋሪዎችና እንግዶች ደህንነቱ የተጠበቀ የትራንስፖርት አገልግሎት ከመስጠት ባለፈ፣ በባህሪያቸውና በታማኝነታቸው የድሬዳዋን በጎ ገጽታ በከፍተኛ ደረጃ እየገነቡ ይገኛሉ። ወጣት እዩኤልም የዚህ መልካም ስም ማረጋገጫ ሆነዋል ።
===================
የድሬዳዋ ፖሊስ ጠቅላይ መምሪያ ትክክለኛ፣ ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
#በፌስቡክ:-👇
📌በአማረኛ :-https://www.facebook.com/profile.php?id=100071007202116

📌በኦሮምኛ :-https://www.facebook.com/profile.php?id=100068806916386

📌ስፖርት :-https://www.facebook.com/profile.php?id=100063887688997

📌ዩትዩብ፦https://youtube.com/?feature=shared

📌በቴሌግራም ቻናላችን
👉https://t.me/direpoli

📌ቲክቶክ፦https://www.tiktok.com/?_t=8fY2fIbUgSs&_r=1

፡፡


ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን

 "151 ኛው ሳምንት የድሬ ትራፊክ ፖሊስ አባላት ሳምንትዊ የስፖርት እንቅስቃሴ                      #በፎቶ🚶‍♂️🚶‍♀️       🚶‍♂️🚶‍♀️           🚶‍♂️🚶‍♀️ 👍...
15/05/2026


"151 ኛው ሳምንት የድሬ ትራፊክ ፖሊስ አባላት ሳምንትዊ የስፖርት እንቅስቃሴ
#በፎቶ
🚶‍♂️🚶‍♀️ 🚶‍♂️🚶‍♀️ 🚶‍♂️🚶‍♀️
👍👍👍ድሬ ትራፊክ ፖሊስ 👍👍👍

"ከመካኒኮች እስከ ኮሪደር ልማት ተጠቃሚዎች፤ የትራፊክ ደህንነት ግንዛቤ የማሳደግ ስራ ተከናወነ"በተለያዩ የህብረተሰብ ክፍሎች ላይ ያተኮረ የትራፊክ ደህንነት ግንዛቤ ማስጨበጫ መርሃ ግብር ተ...
12/05/2026

"ከመካኒኮች እስከ ኮሪደር ልማት ተጠቃሚዎች፤ የትራፊክ ደህንነት ግንዛቤ የማሳደግ ስራ ተከናወነ"

በተለያዩ የህብረተሰብ ክፍሎች ላይ ያተኮረ የትራፊክ ደህንነት ግንዛቤ ማስጨበጫ መርሃ ግብር ተከናውነዋል ።

​በተለያዩ የሙያ ዘርፎች ለተሰማሩ ባለሙያዎችና ለህብረተሰብ ክፍሎች የትራፊክ ደህንነትን የተመለከተ የግንዛቤ ማስጨበጫ ስራ ተከናወነ።

በመርሃ ግብሩም ​ለተሽከርካሪ መካኒኮች ወይም ባለሙያዎቹ ባሉበት የስራ ቦታ በመገኘት፣ ስለ ትራፊክ አደጋ አስከፊነት ሰፊ ማብራሪያ ተሰጥቷል።

በተለይም ተሽከርካሪዎችን ለሙከራ በሚያነቃንቁበት ወቅት "እችላለሁ" በሚል መተማመን ብቻ ያለ መንጃ ፈቃድ መንዳት የሚያስከትለውን የህግና የደህንነት ጉዳት በሚመለከት ጥብቅ ማሳሰቢያ ተሰጥቷል።

​ በአስተዳደሩ ከፍተኛ ወጪ የተገነቡ የኮሪደር ልማት ስራዎች ለተሽከርካሪ ክፍት መሆናቸውን ተከትሎ፤ ፎቶ ለመነሳትና ለመዝናናት የሚመጡ ዜጎች ለደህንነታቸው ሲባል ከመኪና መንገድ ውጪ እንዲሆኑና አስፈላጊውን ጥንቃቄ እንዲያደርጉ የግንዛቤ ማሳደጊያ መልዕክት ተላልፏል።

የፍቅር ተባባሪ ታክሲ ባለንብረቶች ማህበር አባላት ደም በመለገስ ​ሰብአዊነታቸውን በተግባር አረጋገጡ  ።​የፍቅር ተባባሪ ታክሲ ባለንብረቶች ማህበር አባላት ''ደም መለገስ ህይወትን ማዳን ነ...
09/05/2026

የፍቅር ተባባሪ ታክሲ ባለንብረቶች ማህበር አባላት ደም በመለገስ ​ሰብአዊነታቸውን በተግባር አረጋገጡ


​የፍቅር ተባባሪ ታክሲ ባለንብረቶች ማህበር አባላት ''ደም መለገስ ህይወትን ማዳን ነው" በሚል መሪ ቃል ዛሬ ባከናወኑት የበጎ አድራጎት መርሃ ግብር 44 ዩኒት ደም ለግሰዋል።

የማህበሩ ሊቀመንበር አቶ ደረጀ ድሪባ ማህበሩ በቀጣይም የሌሊት ታክሲ ማህበር አርአያነትን በመከተል የትራንስፖርት አገልግሎት ከመስጠት ባለፈ፣ ከፀጥታ አካላት ጋር በቅንጅት በመስራት የከተማዋን ሰላምና ደህንነት ለማረጋገጥ እንደሚተጋ ገልጸዋል። በተለይም አጠራጣሪ እንቅስቃሴዎችን በወቅቱ ለፖሊስ በማሳወቅ፣ የወንጀል መከላከል ስራው ላይ እንደ አንድ የፀጥታው አካል በመቆጠር የዜግነት ድርሻቸውን ለመወጣት ዝግጁ መሆናቸውን አቶ ደረጀ ድሪባ አረጋግጠዋል።

​ማህበሩ በማህበራዊ አገልግሎት ዘርፍ ያለውን ተሳትፎ አጠናክሮ የቀጠለ ሲሆን፣ በዛሬው እለት የለገሱት ደም በሆስፒታሎች ለሚገኙና አስቸኳይ የደም እርዳታ ለሚያስፈልጋቸው ወገኖች ህይወት መትረፍ ትልቅ አስተዋጽኦ ይኖረዋል።

​ይህ አርአያነት ያለው ተግባር በማህበሩ አባላት ዘንድ ያለውን መረዳዳትና ለወገናቸው ያላቸውን ክብር የሚያሳይ ነው።

በትምህርት ቤቶች ላይ ያተኮረ የትራፊክ ደህንነት ግንዛቤ ፈጠራ ተካሄደ​ዛሬ በቀንጨራ፣ በሀሎቡሳ፣ በሁሉልሞጆ እንዲሁም በዋሂል 1ኛ እና 2ኛ ደረጃ ትምህርት ቤቶች በመገኘት ለተማሪዎችና ለመም...
29/04/2026

በትምህርት ቤቶች ላይ ያተኮረ የትራፊክ ደህንነት ግንዛቤ ፈጠራ ተካሄደ

​ዛሬ በቀንጨራ፣ በሀሎቡሳ፣ በሁሉልሞጆ እንዲሁም በዋሂል 1ኛ እና 2ኛ ደረጃ ትምህርት ቤቶች በመገኘት ለተማሪዎችና ለመምህራን ሰፊ የግንዛቤ ማስጨበጫ ትምህርት ተሰጥቷል።

​ዋና ዓላማው ተማሪዎች መንገዶችን እንዴት በጥንቃቄ መጠቀም እንዳለባቸው፣​የትራፊክ አደጋ አስከፊነት፡ በአደጋ የሚጠፋውን የሰው ህይወትና የአካል ጉዳትን ለመከላከል የሚያስችሉ ጥንቃቄዎች ማስገንዘብ ነው ።
​ትውልድን ከአደጋ በመታደግ ረገድ የትምህርት ቤቶች ሚና ከፍተኛ በመሆኑ፣ ይህ የግንዛቤ ፈጠራ ስራ ተጠናክሮ የሚቀጥል ይሆናል።

​"ደህንነቱ የተጠበቀ መንገድ ለሁሉም!"

 "150 ኛው ሳምንት የድሬ ትራፊክ ፖሊስ አባላት ሳምንትዊ የስፖርት እንቅስቃሴ                      #በፎቶ🚶‍♂️🚶‍♀️       🚶‍♂️🚶‍♀️           🚶‍♂️🚶‍♀️ 👍...
24/04/2026


"150 ኛው ሳምንት የድሬ ትራፊክ ፖሊስ አባላት ሳምንትዊ የስፖርት እንቅስቃሴ
#በፎቶ
🚶‍♂️🚶‍♀️ 🚶‍♂️🚶‍♀️ 🚶‍♂️🚶‍♀️
👍👍👍ድሬ ትራፊክ ፖሊስ 👍👍👍

በሳቢያን 2ኛ ደረጃ ትምህርት ቤት የመንገድ ደህንነት የግንዛቤ ማስጨበጥ ስራ ተከናወነ​በድሬዳዋ ፖሊስ ጠቅላይ መምሪያ የትራፊክ ቁጥጥር ዳይሬክቶሬት፤ በሳቢያን 2ኛ ደረጃ ትምህርት ቤት ለ9ኛ...
20/04/2026

በሳቢያን 2ኛ ደረጃ ትምህርት ቤት የመንገድ ደህንነት የግንዛቤ ማስጨበጥ ስራ ተከናወነ

​በድሬዳዋ ፖሊስ ጠቅላይ መምሪያ የትራፊክ ቁጥጥር ዳይሬክቶሬት፤ በሳቢያን 2ኛ ደረጃ ትምህርት ቤት ለ9ኛ ክፍል (K፣ L እና M) ተማሪዎች ሰፊ የግንዛቤ ማስጨበጥ ትምህርት ሰጠ።

​በትምህርት ቤቱ የጂኦግራፊ መምህር የሆኑት መምህር ደጀኔ መኮንን ባመቻቹት በዚህ መድረክ ላይ ተማሪዎች ስለ መንገድ ደህንነት ዝርዝር ትምህርት እንዲያገኙ ተደርጓል። መምህሩ ባስተላለፉት መልዕክት፤ የግንዛቤ ማስጨበጫ ስራው በዘርፉ ባለሙያዎች መሰጠቱ ተማሪዎች በቂና ጠንካራ እውቀት እንዲያካብቱ ትልቅ እገዛ እንደሚያደርግ ገልጸዋል።

​የድሬዳዋ ፖሊስ ጠቅላይ መምሪያ የትራፊክ ቁጥጥር ዳይሬክቶሬት በበኩሉ፤ የተማሪዎችን የመንገድ ደህንነት እውቀት ማጎልበት የሁሉንም አካላት ርብርብ የሚሻ ተግባር መሆኑን በመጠቆም መልዕክቱን አስተላልፏል።

 "149 ኛው ሳምንት የድሬ ትራፊክ ፖሊስ አባላት ሳምንትዊ የስፖርት እንቅስቃሴ                      #በፎቶ🚶‍♂️🚶‍♀️       🚶‍♂️🚶‍♀️           🚶‍♂️🚶‍♀️ 👍...
17/04/2026


"149 ኛው ሳምንት የድሬ ትራፊክ ፖሊስ አባላት ሳምንትዊ የስፖርት እንቅስቃሴ
#በፎቶ
🚶‍♂️🚶‍♀️ 🚶‍♂️🚶‍♀️ 🚶‍♂️🚶‍♀️
👍👍👍ድሬ ትራፊክ ፖሊስ 👍👍👍

Address

Dire Dawa

Telephone

+251947290437

Website

Alerts

Be the first to know and let us send you an email when Dire Traffic Police-ድሬ ትራፊክ ፖሊስ posts news and promotions. Your email address will not be used for any other purpose, and you can unsubscribe at any time.

Contact The Organization

Send a message to Dire Traffic Police-ድሬ ትራፊክ ፖሊስ:

Share