South Ethiopia Region Bureau of Agriculture

  • Home
  • South Ethiopia Region Bureau of Agriculture

South Ethiopia Region Bureau of Agriculture This is the official page of the Bureau of Agriculture (South Ethiopia Regional State)
Fb where you can get all the latest info.
(1)

Detail contact information:
[email protected]
http://www.snnprboa.gov.et
https://t.me/+M8WHF-qTkSszNjM0
snnpragriculture

+251462206125

‎ሀገር ተረካቢ፣ብቁና ጤናማ ዜጋ ለማፍራት የበለፀገ የአመጋገብ ሥርዓትን መተግበር ይገባል፦አቶ አድማሱ አወቀ‎‎በክልሉ Human capital operation( HCO) ፕሮጀክት ለሚደገፉ ዞኖች...
29/05/2026

‎ሀገር ተረካቢ፣ብቁና ጤናማ ዜጋ ለማፍራት የበለፀገ የአመጋገብ ሥርዓትን መተግበር ይገባል፦አቶ አድማሱ አወቀ

‎በክልሉ Human capital operation( HCO) ፕሮጀክት ለሚደገፉ ዞኖችና ወረዳዎች ላሉ ባለሙያዎች የምግብና ሥርዓተ- ምግብ ትግበራን አስመልክቶ የግንዛቤ ማስጨበጫ ስልጠና መሰጠቱ ተመላክቷል።



‎በደቡብ ኢትዮጵያ ክልላዊ መንግስት ግብርና ቢሮ እርሻ ልማት ዘርፍ በክልሉ Human capital operation( HCO) 0ፕሮጀክት በሚደገፉ ዞኖችና ወረዳዎች ላሉ ባለሙያዎችና ባለድርሻ አካላት የሥርዓተ-ምግብ ተኮር ፣የምግብ ደህንነት ጥራትና የድኅረ -ምርት ቴክኖሎጂ አተገባበር ስልጠና መሰጠቱ ተገልጿል።

‎ሀገር ተረካቢ ፣ ብቁና ጤናማ ዜጋ ለማፍራት የበለፀገ የአመጋገብ ሥርዓትን መተግበር እንደሚገባ የክልሉ ግብርና ቢሮ ምክትል ኃላፊና የእርሻ ልማት ዘርፍ ኃላፊ አቶ አድማሱ አወቀ በስልጠና መድረኩ ባደረጉት የመክፈቻ ንግግር አመላክተዋል።

‎ኃላፊው በግብርናው ዘርፍ ምርትና ምርታማነትን መጨመር በቤተሰብ ደረጃ በሚተገበረው ሥርዓተ-ምግብ ሂደት ላይ ከፍተኛ ሚና ያለው መሆኑን ገልፀው የተመጣጠነ የአመጋገብ ሥርዓት ያለው ማህበረሰብ ከመፍጠርና ጤናውን ከመጠበቅ ባለፈ በተሰማራበት የስራ መስክ ሁሉ ውጤታማ እንዲሆን ይረዳል ብለዋል።

‎የተለያዩ ጥናቶች እንደሚያመላክቱት እንደ ሀገር 40 በመቶ የሚሆኑ ህፃናት የመቀንጨርና የመቀጨጭ አደጋ ይታይባቸዋል ያሉት አቶ አድማሱ ይህንንም ለመቀነስ በቤተሰብ ደረጃ የአመጋገብ ሥርዓታችንን በማስተካከል በትምህርቱ ፣በፓለቲካው ፣ በኢኮኖሚውና በማኅበራዊ ጉዳይ የሚታዩ ተግዳሮቶችን ለመቀነስ በጋራ መሥራት ይገባል በማለት አሳስበዋል።

‎ከምግብና ሥርዓተ-ምግብ ችግሮች ጋር ተያይዘው የሚመጡ ጉዳቶችን ለመቀነስ የግብርናው ዘርፍ የተጣለበትን የማምረት ግብ ማሳካት ተገቢ ነው አቶ አድማሱ የተመረተው ምርት ጥራቱና ደህንነቱ ተጠብቆ ተመጋቢው ጋር እስኪደርስ ድረስ የብዙ የባለድርሻ አካላት ትብብርን ይጠይቃል ብለዋል፡፡

‎የክልሉ ግብርና ቢሮ የምግብና ሥርዓተ ምግብ ከፍተኛ ባለሙያ ወ/ሮ ነፃነት ካሳ በበኩላቸው ዠhuman capital operation project (HCO) ዋነኛ ዓላማ በኅብረተሰቡ ዘንድ የሚታዩ የመቀንጨርና የመቀጨጭ ችግሮችን በመከላከል የተማሪዎችን የትምህርት አቀባበል ማሻሻል ነው ሲሉ ገልፀዋል።

‎ለዚህም በግብርናው ዘርፍ የምግብ አቅርቦትን መጨመር ለሥርዓተ-ምግብ ትግበራ ያለው ሚና የጎላ በመሆኑ ደህንነቱ የተጠበቀ እና የተሰባጠረ በአንድ ገበታ ቢያንስ 4 እንዲሁም በቀን 6 የተሻለ ይዘት ወይም ጠቀሜታ ያላቸውን ምግቦች በመጠቀም የአመጋገብ ሥርዓታችንን መጠበቅ ይገባል ብለዋል።

‎በቀጣይም ከስልጠናው የተገኘውን ግንዛቤ በመጠቀምና በፕሮጀክቱ በሚደገፉ አካባቢዎች የተመደበውን በጀት ለታለመለት ዓላማ ብቻ በማዋል የሚፈለገው ለውጥ እንዲመጣ ሊሠራ ይገባል በማለት ወ/ሮ ነፃነት ተናግረዋል።

‎የወላይታ ሶዶ ዩኒቨርሲቲ የምግብ ሳይንስና ስነ -ምግብ ተመራማሪ ዶ/ር አምስቱ ኩማ በምግብ ደህንነትና ጥራት ርዕስ የተዘጋጀ የስልጠና ሰነድ ያቀረቡ ሲሆን የክልሉ ግብርና ቢሮ ከፍተኛ የሰብል ልማት ባለሙያ አቶ ጤናው ይሁነው የድኅረ- ምርት አሰባሰብ ቴክኖሎጂን አስመልክቶ የተዘጋጀ ሰነድ አቅርበዋል።

‎ጎፋ፣አሪና ኮንሶ ዞኖች ሰሜን አሪ ፣ መሎ ኮዛና ሰገን ዙሪያ ወረዳዎች በክልሉ ካሉ ዞኖች የመቀጨጭና የመቀንጨር ችግር ይበልጥ የታየባቸው አካባቢዎች መሆናቸው በጥናት ተለይተው በhuman capital operation (HCO) እየተደገፉ እንደሆነም ተገልጿል።

‎በቀረቡ ሰነዶችና በተሠጠው ስልጠና ሰፊ ውይይት የተደረገበት ሲሆን ከቤቱ በርካታ ጥያቄዎችና ሀሳቦች ተነስተው ከቤቱ ምላሽና ማብራርያ ተሰጥቶበታል።

‎የስልጠናው ተሳታፊ ከሆኑት አንዳንዶቹ እንደገለፁት የተሰጠው ስልጠና በቀጣይ ለሚሠሩት ሥራ የተሻለ ግንዛቤ ያገኙበትና ከቤተሰባቸው ጀምሮ ተግባራዊ ማድረግ የሚያስችል አቅም እንደፈጠረላቸው ተናግረዋል።

‎በመድረኩም የክልሉ ግብርና ቢሮ የእርሻ ልማት ዘርፍ ከፍተኛ ባለሙያዎች፣ፕሮጀክቱ የሚሠራባቸው ዞኖች የግብርና መምሪያ ምክትል ኃላፊዎች እና የወረዳ ግብርና ጽ/ቤት ባለሙያዎች፣የዞንና የወረዳ የትምህርት ፣የጤና ፣የውኃና የሴቶች ተወካይና የፕሮጀክቱ ፎካሎች መሳተፋቸው ተዘግቧል።

‎በዝናቧ ጌታሁን

ተፋሰሶችን በማልማት ለአደጋ ያላቸውን ተጋላጭነት በመቀነስ አማራጭ  የገቢ ማስገኛ እንዲሆኑ እየተሰራ  ይገኛል ፦ አቶ መስፍን  ባልቻ የደቡብ ኢትዮጵያ ክልል ግብርና ቢሮ "በተፋሰሶቻችን ላይ...
29/05/2026

ተፋሰሶችን በማልማት ለአደጋ ያላቸውን ተጋላጭነት በመቀነስ አማራጭ የገቢ ማስገኛ እንዲሆኑ እየተሰራ ይገኛል ፦ አቶ መስፍን ባልቻ

የደቡብ ኢትዮጵያ ክልል ግብርና ቢሮ "በተፋሰሶቻችን ላይ የሚስተዋሉ አደጋዎችን በመቀነስ የገቢ ምንጫችንን እናሳድጋለን " በሚል መሪ ቃል ለተፈጥሮ ሃብት ልማት ባለሙያዎች የክህሎት ስልጠና መሰጠቱም ተመልክቷል

.

በክልሉ ግብርና ቢሮ የተፈጥሮ ሃብት ልማት ዘርፍ የተፈጥሮ ሃብት ልማት ዳይሬክተር እና የምክትል ቢሮ ኃላፊ ተወካይ አቶ መስፍን ባልቻ በዚህ ወቅት እንደገለጹት ባለፉት ሦስት አመታት በክልሉ የተከሰቱ የመሬት መንሸራተት አደጋዎች እጅግ አሳሳቢ ናቸው ።

በመሆኑ በየደረጃው የሚገኙ የዘርፉ ባለሙያዎች እየተከሰቱ የሚገኙ አደጋዎችን ለመቀነስ በሂደትም በዘላቂነት ለማስቀረት ሳይንሳዊ የሆነ የአሰራር ስርዓትን በመዘርጋት ሙያዊ ግዴታቸውን ሊወጡ እንደሚገባም ገልጸዋል ።

የተፈጥሮ ሃብት ልማት ሥራ የአንድ ወቅት ተግባር አይደለም ያሉት አቶ መስፍን የአፈርና ውሃ ጥበቃ ፣ ለአረንጓዴ አሻራ ችግኝ ዝግጅትና ተከላን የሁልጊዜ ተግባሮቻችን አድርገን መስራት እንደሚገባም አመልክተዋል ።

በዘርፉ የደን ልማትና እንክብካቤ ዳይሬክቶሬት አቶ ዘሪን ስዩም በበኩላቸው የደን ችግኝ ተከላና አሰተዳደር ስርዓትን በማጠናከር ከዘርፉ የሚገኘውን ኢኮኖሚያዊ ተጠቃሚነት ማሳደግ ይገባል ብለዋል።

ተፋሰሶችን ከአደጋ መንስኤነት ወደ አማራጭ የገቢ ማስገኛነት ለመቀየር በሚደረገው ጥረት ውስጥ የንብ ማነብ ስራ ወሳኝነት እንደለውም ተገልጿል ።

ዶክተር ገላዬ ስልሌ ከጋሞ ዞን ጨንቻ ከተማ እንዲሁም አቶ መሰለ ብርሃኑ ደግሞ ከጌዲኦ ዞን ገደብ ወረዳ የመጡ ሰልጣኞች ሲሆኑ ሁለቱም እንደገለጹት የተሰጣቸው ስልጠና የክህሎት ክፍተታቸውን መሙላት የሚያስችል ስልጠና ነው ብለዋል።

ለሁለት ተከታታይ ቀናት በተሰጠው የክህሎት ማጎልበቻ ስልጠና ላይ ፦ የመሬት መንሸራተት እና የአደጋ መንስኤዎችና መፍትሔዎች ፣ የመሬት መንሸራተት ክስተት መረጃ አሰባሰብና አደረጃጀት የንብ ማነብ ስራ ከተፋሰስ ልማት ስራ ጋር ማስተሳሰርና ገቢ ማሳደግ እንዲሁም በደን ችግኝ ተከላና አስተዳደር እንዲሁም በሌሎች ርዕሰ-ጉዳዮች ዙሪያ ስልጠናው ተሰጥቷል ።

በመድረኩ ከ2 መቶ 70 በላይ ለሚሆኑ የዞን ፣ የወረዳና የከተማ አስተዳደር ባለሙያዎች ተሳታፊ ሆነዋል ።

በወንድማገኝ አሰሌ

ጥራት ያላቸውን የፍየል ዝሪያዎችን ለይቶ በማዳቀል ዝሪያን ማሻሻል ለምርታማነት ዕድገት የላቀ አስተዋጽኦ እንዳለው ተገለጸ .ጥራት ያላቸውን የፍየል ዝሪያዎችን ለይቶ በማዳቀል ዝሪያን ማሻሻል ...
28/05/2026

ጥራት ያላቸውን የፍየል ዝሪያዎችን ለይቶ በማዳቀል ዝሪያን ማሻሻል ለምርታማነት ዕድገት የላቀ አስተዋጽኦ እንዳለው ተገለጸ

.

ጥራት ያላቸውን የፍየል ዝሪያዎችን ለይቶ በማዳቀል ዝሪያን ማሻሻል ለምርታማነት ዕድገት የላቀ አስተዋጽኦ እንዳለው የደቡብ ኢትዮጵያ ክልል ግብርና ምርምር ኢንስቲትዩት አስታወቀ።

በጎፋ ዞን የኡባ ደብረጸሐይ ወረዳ የማህበረሰብ አቀፍ ፍየሎች ዝሪያ ማሻሻያ ፕሮግራም ማስጀመሪያ በዛባ ቀበሌ በተካሄደበት ወቅት ተገኝተው መልዕክት ያስተላለፉት የደቡብ ኢትዮጵያ ክልል ግብርና ምርምር ኢንስቲትዩት ዋና ዳይሬክተር ዶ/ር አብዮት መብራቴ፥ ኢንስቲትዩቱ በስሩ ባሉ አምስት የምርምር ማዕከላት የማህብረሰቡን ችግር የሚፈቱ የግብርና ምርምር ሥራዎች በማከናወን ተጨባጭ ውጤት እየተመዘገበ ይገኛል ብለዋል።

በአከባቢው ካሉ የፍዬል ዝሪያዎች መካከል ጥራታቸው የተረጋገጠ፣ ለይቶ በማዳቀል ዝሪያን በማሻሻል ምርታማነትንና የአርሶና አርብቶ አደሩን የገቢ አቅማቸውን ማሳደግ እንደሚገባ ገልጸዋል።

አርሶ አደሩ ከምርምር ማዕከሉ የሚወጡ ግብዓቶችን ለይቶ በመጠቀም የግብርና ምርታማነትን ማረጋገጥ እንደሚገባውም አሳስበዋል።

የኢንስቲትዩቱ ምክትል ዳይሬክተር ዶክተር ያስን ጎኣ አርሶ እና አርብቶ አደሩ ማህብረሰብ ከአዳዲስ ቴክኖሎጂዎች ጋር እንዲተዋወቁና ተጠቃሚ እንዲሆኑ እየተከናወነ ያለው ተግባር ተጠናክሮ የሚቀጥል መሆኑን ገልጸዋል።

የሳውላ ግብርና ምርምር ማዕከል ዳይሬክተር አቶ ተፈራ አሽነ በአሁን ወቅት ማዕከሉ በጎፋ እና ባስኬቶ ዞኖች ሰፋፊ ችግር ፈቺ የምርምር ሥራዎችን እያካሄደ ሲሆን በፊየል ዝሪያ ማሻሻያው በማህበር የተደራጁ 54 አባወራዎች ተጠቃሚ እንደሚሆኑ ገልጸዋል።

የሳውላ ግብርና ምርምር ማዕከል እያካሄደ ያለው ችግር ፈቺ የምርምር ሥራ ሀገሪቱ በግብርናው ክፍለ ኢኮኖሚ ለመድረስ ላቀደችው ግብ ተስፋ የሚጥል ነው ብለዋል።

ማዕከሉ በሰብል፣ በእንስሳት ዝሪያ ማሻሻያና በሌሎችም እያከናወነ ባለው የምርምር ሥራ ተጨባጭ ውጤት እየተመዘገበ ነው ብለዋል።

የጎፋ ዞን ግብርና መምሪያ ምክትል ኃላፊ አቶ አንዳርጌ አራታ በዞኑ ከ1 ነጥብ 1 ሚሊየን በላይ ፍየል የሚገኝ ሲሆን የዝርያ ማሻሻያ ስራ መጀመሩ ለምርታማነት ዕድገት የጎላ አስተዋጽኦ አለው ብለዋል።

የዑባ ደብረጸሐይ ወረዳ ምክትል አስተዳዳሪና ግብርና ጽ/ቤት ኃላፊ አቶ ሙርተ ሙርቀና በወረዳው የተጀመረው ዝርያ ማሻሻያ ለሀገራዊ ዕድገት ተጨማሪ አቅም የሚፈጥርና ለሌማት ቱሩፋት ኢንሼቲቭ ስኬታማነት አበርክቶው የላቀ ነው ሲሉም ገልፀዋል።

ከአከባቢው ነዋሪዎች መካከል አቶ ኃይለ ተረፈ እና አቶ ተመስገን ወልልደየስ ፊዬልን በጥራት በማምረት የተሻለ ገቢ ለማግኘት ዝሪያ ማሻሻያው የተሻለ አቅም እንደሚፈጥር ተናግረዋል ሲል የዘገበው የደቡብ ኢትዮጵያ ሬዲዮና ቴሌቪዥን ድርጅት ነው።

‎ጥራቱን የጠበቀ አቮካዶ በኩታ ገጠም እርሻ በብዛት  በማምረት ለሀገር ውስጥና  ለውጭ ገበያ ለማቅረብ በልዩ ትኩረት ይሠራል :-ክቡር ዶ/ር መሪሁን ፍቅሩ ‎ክቡር ዶክተር መሪሁን ፍቅሩ ይህን...
28/05/2026

‎ጥራቱን የጠበቀ አቮካዶ በኩታ ገጠም እርሻ በብዛት በማምረት ለሀገር ውስጥና ለውጭ ገበያ ለማቅረብ በልዩ ትኩረት ይሠራል :-ክቡር ዶ/ር መሪሁን ፍቅሩ

ክቡር ዶክተር መሪሁን ፍቅሩ ይህንን የተናገሩት የክልሉ ብሔራዊ የአቮካዶ ልማት ፕሮግራም (NADP) ሥራ ማስጀመሪያ መድረክ በንግግር በከፈቱበት ወቅት ነው።



ጥራቱን የጠበቀ አቮካዶ በኩታ ገጠም እርሻ በብዛት በማምረት ለሀገር ውስጥና ለውጭ ገበያ ለማቅረብ በልዩ ትኩረት ይሠራል ሲሉ በደቡብ ኢትዮጵያ ክልላዊ መንግስት ‎በምክትል ርዕሰ -መስተዳድር ማዕረግ የዲላ ክላስተር አስተባባሪና የክልሉ ግብርና ቢሮ ኃላፊ ክቡር ዶ/ር መሪሁን ፍቅሩ አሳሰቡ።

‎አቮካዶ ለዘመናት በሀገራችን በተለያዩ አካባቢዎች ሲለማ የነበረ ተክል ቢሆንም ትኩረት ባለማግኘቱና በምርምር የተሻሻሉ ምርታማና የተሻለ የዘይት ይዘት ያላቸው ዝርያዎችን ለይተን ማልማት ባለመቻላችን ያለንን ዕምቅ የመልማት ሳንጠቀም ኖረናልም ብለዋል።

‎ዶ/ር መሪሁን አክለውም በቀጣይ ጊዜያት እንደ ሀገር በጠቅላይ ሚኒስትራችን ድጋፍ ይህ ፕሮግራም (NADP) የሚሠራ ሲሆን በክልላችን ለ15 ዓመታት በአቮካዶ ልማት ላይ የሚተገበር በመሆኑ ከፍተኛ የማምረት አቅም ካላቸው አካባቢዎች በተጨማሪ በሁሉም ዞኖች ተግባራዊ ይደረጋል ብለዋል።

‎አቮካዶ ላይ መሥራት ደቡብ ኢትዮጵያን ማሻገር ነው ያሉት ኃላፊው በስፋትና በጥራት በማምረት ፣ገበያን በማረጋጋት በከተማ ያለው የኅብረተሰብ ክፍል ገጠሩን በመናፈቅ ንፁህ አየር የምናገኝበት የፍራፍሬ ገነት በመፍጠር የአርሶ አደሩን ተጠቃሚነት ለማጎልበት መሥራት ይጠበቅብናል ብለዋል።

‎በቀጣይም የተሻለ ይዘት ያለው አቮካዶ በመምረጥ፣ አዳቃይ ባለሙያዎችን በማሰልጠን፣ በእንዳስትሪ ልማቱ የተሠማሩ የግል ባለሀብቶችን በማሳተፍ፣ አመራሩና ባለሙያው በመቀናጀት ሞዴል ችግኝ ጣቢያዎችን ለማፍራት ቢሮው በማድረግ በትኩረት መሥራት እንደሚገባም ዶ/ር መሪሁን አስታውቀዋል።

‎በዕለቱም የክልሉ ግብርና ቢሮ ምክትል ኃላፊና የእርሻ ልማት ዘርፍ ኃላፊ አቶ አድማሱ አወቀ የዛሬው መድረክ ዋነኛ ዓላማ በክልላችን አቮካዶን በስፋትና በብቃት በማምረት ከምግብነትና ከእንዳስትሪ ግብአትነት ባሻገር የውጭ ምንዛሪ ገቢን ለማሳደግ በሚያስችሉ መርሆች ላይ ለመምከር እንደሆነ ገልፀዋል።

‎ብሔራዊ የአቮካዶ ልማት ፕሮግራም እንደ ሀገር ከ38 ቢሊየን ብር በላይ ከመደበኛ በጀት ተመድቦ ለ15 ዓመታት በመቆየት የሚሠራ ሲሆን ከዚህ ቀደም በቢሮው ችግኝ በማፍላትና በማቅረብ ሲደግፉ የነበሩ ፕሮግራሞችና ፕሮጀክቶች በመቀናጀት የተሻለ ሥራ የሚሠራ መሆኑን ተናገግረዋል።

‎የክልሉ ብሔራዊ አቮካዶ ልማት ፕሮግራም (NADP)ማናጀር ወ/ሮ አበበች ደሳለኝ የፕሮግራሙን ዓላማ ፣በቀጣይ በፕሮግራሙ ሊሠሩ የታቀዱ ሥራዎችንና በፕሮግራሙ የሚደገፉ ወረዳዎችን አስመልክቶ የተዘጋጀውን ሰነድ አቅርበዋል።

‎የአቮካዶ ተክል ከሌሎች ፍራፍሬዎች ልዩ የሚያደርገው በየትኛውም እድሜ ክልል ለሚገኙ ሰዎች ከፍተኛ ጠቀሜታ ያለው ምግብ ከመሆኑ ባሻገር ለምግብ ዘይትና ለስነ ውበት ያለው አስተዋፅኦ የጎላና እጅግ ተፈላጊ የሆነ የፍራፍሬ ዓይነት በመሆኑ ልዩ ትኩረት ተሰጥቶ ይሠራበታል ብለዋል።

‎ፕሮግራሙ በክልሉ በሚገኙ ከፍተኛ አቮካዶ የማምረት አቅም ባላቸው አካባቢዎች (በወላይታ፣ጋሞ፣ጌዴኦ፣ ጎፉ፣አሪ ፣ደ/ኦሞ፣ ባስኬቶ ዞኖች ውስጥ በሚገኙ 7 ዞኖችና 12 ወረዳዎች ላይ እንደሚሠራ ተገልጿል።

‎በዕለቱም ከቤቱ በርካታ አስተያየቶችና ጥያቄዎች የተነሡ ሲሆን ከመድረኩም ምላሽና ማብራሪያ ተሰጥቶበታል።

‎በመድረኩም የክልሉ ግብርና ቢሮ ሴክተር ማናጅመንት አባላት፣ የፕሮግራሞና ፕሮጀክት አስተባባሪዎች የቢሮው እርሻ ዘርፍ ከፍተኛ ባለሙያዎች፣ፕሮግራሙ ከሚሠራባቸው ዞኖች(ከ7ቱ ዞኖች) ግብርና መምሪያ ኃላፊዎች፣ከ12ቱ የፕሮግራሙ ወረዳ አስተዳደሪዎችና የወረዳ ግብርና ጽ/ቤት ኃላፊዎች መሳተፋቸው ተዘግቧል ።

‎በዝናቧ ጌታሁን

በአርሶ  አደሮቾ የመስክ ላይ ትምህርት ቤት በቀሰሙት ዕውቀት  ምርታማ በሆኑ ሴት አርሶ አደሮች  ማሳ የአርሶ አደሮች የመስክ ቀን በዓል ተከበረ የእስሳትና ዓሳ ሃብት ልማት ዘርፍን  ምርታማ...
27/05/2026

በአርሶ አደሮቾ የመስክ ላይ ትምህርት ቤት በቀሰሙት ዕውቀት ምርታማ በሆኑ ሴት አርሶ አደሮች ማሳ የአርሶ አደሮች የመስክ ቀን በዓል ተከበረ

የእስሳትና ዓሳ ሃብት ልማት ዘርፍን ምርታማነት ለማሳደግ በሚደረገው ሁሉ - አቀፍ ርብርብ ውስጥ የአርሶ አደሮች የመስክ ላይ ትምህርት ቤት አስተዋጽኦ ከፍተኛ መሆኑ ተገለጸ

19-24-2018 ዓ.ም # ዲላ

በደቡብ ኢትዮጵያ ክልል ጋሞ ዞን አርባ ምንጭ ዙሪያ ወረዳ ጫኖ ዶርጋ ቀበሌ 35 ሴት አርሶ አደሮች በመስክ ላይ አተገባበር ዙሪያ የወሰዱትን የክህሎት ስልጠና በመጠቀም ከፍተኛ ውጤት ማስገኘት መቻላቸውን ነው በመስክ በዓሉ መመልከት የተቻለው ።

የአርባ ምንጭ ዙሪያ ወረዳ ግብርና ጽህፈት ቤት ኃላፊ አቶ መርዶክዮስ ከርባ እንደገለጹት የአርሶ አደሮች የመስክ ላይ ትምህርት ቤት የሚሰጠውን ትምህርት የቀሰሙት ሴት አርሶ አደሮች ምርታማነታቸውን ማሳደግ ችለዋል ።

የአርሶ አደሮች የመስክ ላይ ትምህርት ቤት አዲስ የኤክስቴንሽን አቀራረብ ስልት ሲሆን ይህም ዘመኑን የዋጀ በመሆኑ ተመራጭና ውጤታማ ነው ብለዋል።

ዶክተር ኤሊያስ አቢዩ የግብርና ትራንስፎርሜሽን ኢንስቲትዩት ከፍተኛ ባለሙያ ሲሆኑ ምርትና ምርታማነት በማሳደግ ገበያን ተደራሽ ለማድረግ በሚደረገው ጥረት ውስጥ የአርሶ አደሮች የመስኮ ላይ ትምህርት ቤት አስተዋጽኦ ከፍተኛ መሆኑን አመልክተዋል ።

ዛሬ በጋሞ ዞን የተካሄደው በመስክ ላይ የሚሰጠውን ትምህርት ቀስመው ውጤት ማስገኘት የቻሉ ሴት አርሶ አደሮች በክልሉ እንዲሁም በአገር አቀፍ ደረጃ ከፍተኛ ልምድ የሚቀሰምበት መሆኑንም ገልጸዋል ።

በደቡብ ኢትዮጵያ ክልል ግብርና ቢሮ የእንስሳትና ዓሳ ሃብት ልማት ሴክተር ፕሮግራም ከፍተኛ ባለሙያ የሆኑ ወይዘሮ ተናኜ ወርቅ አሰፋ በበኩላቸው " እኔ ሴት ነኝ" ብለው የአርሶ አደሮች የመስክ ላይ ትምህርት ቤት የሚሰጠውን የዕውቀትና የክህሎት ማበልጸጊያ ስልጠና የወሰዱ ሴት አርሶ አደሮች ተሞክሮ እጅግ ደስ የሚያሰኝ ነው ብለዋል።

በዕለቱ የመስክ ጉብኝት ከተካሄደባቸው ሴት አርሶ አደሮች መካከል አልማዝ ቦላ እና ገነቷ ይገኙበታል ፤ ሁለቱም ሴት አርሶ አደሮች እንደገለጹት በአርሶ አደሮች የመስክ ላይ ትምህርት ቤት የሚሰጠውን የሚሰጠውን ዕውቀት በመቅሰማችን በሕይወታችን ላይ ከፍተኛ ለውጥ መምጣቱን ተመልሰክል ።

ሁለቱም ሴት አርሶ አደሮች እንደገለጹት የተሰጣቸውን ስልጠና በመጠቀም ከሃሳ በላይ ዶሮዎች እያረቡ የሚገኙ ሲሆኑ ኢኮኖሚያዊ ተጠቃሚ መሆን ችለዋል ።

በወንድማኝ አሰሌ

"ከዝናብ ጥገኝነት የተላቀቀና ሁሉንም የውኃ ፀጋዎች የሚጠቀም ዘመናዊ ግብርና ዕውን ለማድረግ በትኩረት እየተሠራ ይገኛል።" ክቡር ዶክተር መሪሁን ፍቅሩከ255 ሚሊየን 414 ሺህ በላይ በጀት ...
27/05/2026

"ከዝናብ ጥገኝነት የተላቀቀና ሁሉንም የውኃ ፀጋዎች የሚጠቀም ዘመናዊ ግብርና ዕውን ለማድረግ በትኩረት እየተሠራ ይገኛል።" ክቡር ዶክተር መሪሁን ፍቅሩ

ከ255 ሚሊየን 414 ሺህ በላይ በጀት ለሚገነባው የጋልዳ አነስተኛ የመስኖ አውታር የቦታ ርክክብ፣ የሰነድ መፈራረም እና የመሠረት ድንጋይ የማስቀመጥ መርሃ-ግብር በወላይታ ዞን ኦፋ ወረዳ ተካሂዷል።



በደቡብ ኢትዮጵያ ክልላዊ መንግሥት ግብርና ቢሮ የተሳትፏዊ ግብርናና የአየር ንብረት ለውጥ ሽግግር ፕሮግራም (PACT) በወላይታ ዞን ኦፋ ወረዳ ጋልዳ ቀበሌ በፀሐይ ኃይል የሚደገፍ የአነስተኛ መስኖ አውታር ግንባታ ፕሮጀክት የቦታ ርክክብ መርሃ-ግብር ተካሂዷል።

የግንባታ ፕሮጀክቱን የግንባታ መግባቢያ ሰነድ በመፈረም ሥራውን የተረከበው የወላይታ ውኃ ሥራዎች ኢንተርፕራይዝ መሆኑ ተመልክቷል።

በደቡብ ኢትዮጵያ ክልል በምክትል ርዕሰ-መስተዳድር ማዕረግ የዲላ ክላስተር አስተባባሪና የክልሉ ግብርና ቢሮ ኃላፊ ክቡር ዶክተር መሪሁን ፍቅሩ በመርሃ-ግብሩ እንደገለፁት ከዝናብ ጥገኝነት የተላቀቀ እና ሁሉንም የውኃ ፀጋዎች አሟጦ የሚጠቀም ዘመናዊ ግብርና ዕውን ለማድረግ በትኩረት እየተሠራ ይገኛል።

ክቡር ዶክተር መሪሁን ፍቅሩ አክለውም ውኃ ላይ መሥራት ህይወትን ማስቀጠል መሆኑን አንስተው የጋልዳ መስኖ አውታር ግንባታ ሲጠናቀቅ የአካባቢውን ኅብረተሰብ የልማት ተሳትፎ በማሳደግ ኢኮኖሚያዊ ተጠቃሚነትን እንደሚያረጋግጥ ተናግረዋል።

የወላይታ ሶዶ ውኃ ሥራዎች ኮንስትራክሽን ኢንተርፕራይዝ ተግባሩን በተረከበበት አግባብ ጥራቱን ጠብቆ በተያዘው ጊዜ አለያም ቀደም ብሎ እንዲያስረክብ፤ የፕሮጀክቱ አማካሪ የሆነው የደቡብ ኢትዮጵያ ዲዛይን ግንባታ ቁጥጥር ኢንተርፕራይዝ ተግባሩን በመቆጣጠር፣ በመከታተልና በመደገፍ ጥራቱን ጠብቆ እንዲጠናቀቅ በማድረግ እንዲያጠናቀቁ አደራ ብለዋል።

ክቡር ዶክተር መሪሁን የጋልዳ አነስተኛ የመስኖ አውታር ግንባታ የእስከ አሁን ተግባራትን በባለቤትነት የመሩ እና የሚመሩ በክልሉ ግብርና ቢሮ ምክትል የቢሮ ኃላፊና የተፈጥሮ ሀብት ልማት ዘርፍ ኃላፊ ክቡር አቶ አንደኛ ሽናሌን እና የተሳትፏዊ ግብርናና የአየር ንብረት ሽግግር ፕሮግራም (PACT) ማናጀር አቶ ተገኝ ዳንኤልን ላበረከቱት አስተዋፅዖ አመስግነዋል።

የወላይታ ዞን ዋና አስተዳዳሪ ክቡር ረዳት ፕሮፌሰር ሳሙኤል ተሰማ የጋልዳ አነስተኛ መስኖ አውታር ግንባታ የአካባቢውን ኅብረተሰብ የልማት ጥያቄ የመለሰና በመስኖ ልማት በአብነትነት የሚጠቀስ የመስኖ ማዕከል ለመፍጠር እንደሚያስችል አብራርተዋል።

በክልሉ ግብርና ቢሮ የተሳትፏዊ ግብርናና የአየር ንብረት ሽግግር ፕሮግራም (PACT) ማናጀር አቶ ተገኝ ዳንኤል የጋልዳ አነስተኛ የመስኖ አውታር ግንባታ ሥራ በሚቀጥሉት ስምንት ወራት ውስጥ ተጠናቆ ለአገልግሎት ይበቃል ተብሎ ይጠበቃል ብለዋል።

በፀኃይ ኃይል የሚደገፈውና ከ255 ሚሊየን 414 ሺህ ብር በላይ ወጪ የሚገነባው የጋልዳ አነስተኛ መስኖ አውታር 115 ሔክታር መሬት በማልማት 104 ቤተሰቦችን ተጠቃሚ ያደርጋል።

የወላይታ ውኃ ሥራዎች ኢንተርፕራይዝ ባለቤትና ሥራ አስኪያጅ ኢንጂነር ሀብታሙ ፋንታ በፀሐይ ኃይል የሚደገፈውን የጋልዳ አነስተኛ መስኖ አውታር ግንባታ ሥራን ጥራትና ደረጃውን ጠብቆ ለማጠናቀቅ ሙሉ አቅም እንዳለው ጠቁመው በተያዘው ጊዜ ውስጥ አጠናቀን እናስረክባለን ብለዋል።

የደቡብ ኢትዮጵያ ዲዛይን ግንባታና ቁጥጥር ኢንተርፕራይዝ ዋና ሥራ አስኪያጅ ኢንጂነር ካሳሁን ሀብተጊዮርጊስ በበኩላቸው ተቋማቸው ረጅም ልምድና የመፈፀም አቅም እንዳለው ተናግረው ፕሮጀክቱ የጥራት ደረጃውን ጠብቆ እንዲጠናቀቅ በቁርጠኝነት እንሠራለን ብለዋል።

በቦታ ርክክብ መርሃ-ግብሩ ክቡር ዶክተር መሪሁን ፍቅሩ፣ የወላይታ ዞን ዋና አስተዳዳሪ ክቡር ረዳት ፕሮፌሰር ሳሙኤል ተሰማ እና በሚኒስትር ማዕረግ የኢፌዴሪ የህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት የመንግሥት የልማት ድርጅቶች ቋሚ ኮሚቴ ሰብሳቢ ክቡር አቶ መለሰ መናን ጨምሮ የግብርና ሴክተር ማኔጅመንት አባላት የወላይታ ዞን እና የኦፋ ወረዳ ከፍተኛ የፓርቲና የመንግሥት አመራሮች፣ የሀይማኖት አባቶች፣ የሀገር ሽማግሌዎች እንዲሁም የጋልዳ ቀበሌ ነዋሪዎች መሳተፋቸው ተዘግቧል።

በአያሌው ዘነበ

"የእንስሳት ምርታማነትን ለማሳደግ በምርምር የወጡ ተክኖሎጅዎችን መጠቀም  ይገባል!" ዶ/ር አብ. ዮት መብራቴየደቡብ ኢትዮጵያ ግብርና ምርምር ኢንስቲትዩት የእንስሳት ምርታማነትን የሚያሳድጉ ...
24/05/2026

"የእንስሳት ምርታማነትን ለማሳደግ በምርምር የወጡ ተክኖሎጅዎችን መጠቀም ይገባል!" ዶ/ር አብ. ዮት መብራቴ

የደቡብ ኢትዮጵያ ግብርና ምርምር ኢንስቲትዩት የእንስሳት ምርታማነትን የሚያሳድጉ ስምንት የቴክኖሎጂ ፓኬጅ ጥንቅሮችን ለጥቅም ማዘጋጀቱን አስታውቋል።



በግብርናው ዘርፍ ዘላቂ ልማት ለማረጋገጥ መንግሥት ለእንስሳትና ዓሣ ሀብት ልማት የትኩረት መስክ ቀዳሚ ትኩረት ሰጥቶ እየሠራ ይገኛል።

ዘርፉ ለሥራ ዕድል ፈጠራ፣ ለኢኮኖሚያዊ ጠቀሜታ እንዲሁም ለሥርዓተ-ምግብ ዋስትና የሚያበረክተውን ጉልህ አስተዋፅዖ ታሳቢ በማድረግም ነው የሌማት ትሩፋት ኢኒሼቲቭ ተቀርፆ እየተተገበረ የሚገኘው።

በእንስሳትና ዓሣ ሀብት ልማት ዘርፍ የምርታማነት እምርታ ለማስመዝገብ በምርምር የተደገፈ የቴክኖሎጂ ውጤቶችን መጠቀም ግድ እንደሚል የመስኩ ምሁራን ይገልፃሉ።

ከዚሁ እውነት በመነሳት ነው የደቡብ ኢትዮጵያ ግብርና ምርምር ኢንስቲትዩት በስምንት የተለያዩ የዘርፉ የትኩረት መስኮች ለበርካታ ዓመታት ምርምር ተደርጐ ውጤታማነታቸው የተረጋገጡ ቴክኖሎጃዎችን የአተገባበር ፓኬጅ አዘጋጅቶ ጥቅም ላይ እንዲውሉ ያቀረበው።

የኢንስቲትዩቱ ዋና ዳይሬክተር ዶ/ር አብዮት መብራቴ እንደገለፁት የእንስሳት ምርትና ምርታማነት ለማስደግና በአጭርጊዜ እምርታ ለማምጣት ለተያዘው ውጥን የማይተካ ሚና ያላቸው ለመሆኑ ታትመው በሌሎችም አማራጮች ለተጠቃሚዎች የማድረስ ሥራ እየተሠራ ነው ። የተቀረፁ የቴክኖሎጂ አጠቃቀም ፓኬጆችን ለኤክስቴንሽን የማስተላለፍ ሥራ በቀጣይ ይከናወናል ያሉት ዋና ዳይሬክተሩ የኤክስቴንሽን አካላት በቴክኖሎጂ አጠቃቀም የአርቢውን ኅብረተሰብ አቅም በስልጠና በመገንባት ውጤት ማስመዝገብ እንደሚጠበቅባቸው ማስታወቃቸው ተዘግቧል።

የአጠቃቀም ፓኬጆቹ በተለይ ከእንስሳት መኖ ጋር ተያያዥ የሆኑ ችግሮችን ለመፍታት የአካባቢ ግብኣት በመጠቀም ሳይንሳዊ ምርምር ስርዓት ተከትሎ ያፈለቃቸውን ውጤታማ ተክኖሎጂ ፓኬጆች፡ በአልፋ አልፋ መኖ አመራረት አያያዝና አጠቃቀም፣ ከአካባቢ ግብዓት የፍየል መኖ አዘገጃጀትና አጠቃቀም፣ የሎህማን ብራውን እንቁላል ጣይ የዶሮ ዝርያ አረባብ ዘዴ፣ አፈር አልባ አረንጓዴ መኖን (Hydroponic feed) አዘጋጅቶ ለዶሮ መኖነት በመጠቀም የእንቁላል ምርታማነትና ጥራት ማሻሻል፣ የደሾና ላብ ላብ መኖዎች አመራረት፣ አያያዝና አጠቃቀም፣ የኑግ ዘር ኬክን ከደረቅ ግራዋ ቅጠል ጋር በግ ለማሞከት መጠቀም፣ በአርሶ አደር ጀረጃ የቦባንስ ብራውንና የሎህማን ብራውን የዶሮ ዝርያዎች ምርታማነት ማሻሻልና የእርግብ አተርን ለምርምር ጠቀሜታ ያላቸውን ዶሮዎች ምርታማነት ማሻሻል ፓኬጆች ጥልቅ የምርምር ሥራዎች ውጤት ላይ ተመሥርተው የተቀረፁ በመሆናቸው አርሶ/ አርብቶ አደሩም ሆነ ሌሎች በመስኩ የተራማራ አካላት ሁሉ ተጠቃምነት ለማረጋገጥ በምደረገው ስርጸት ህደት የሚመለከተው አባላት ሁሉ አስፈላግውን ድጋፍ ማድረግ እንደሚገባ እንደሚገባ አቶ መከተ ግርማ የኢንስቲትዩቱ የእንስሳት ምርምር ዳይሬክተር ማሳሰባቸው ተዘግቧል።

በአያሌው ዘነበ

"በአፈር ማዳበሪያ ሂሳብ አያያዝና ኦዲት አሠራር ዙሪያ የተሰጠው ስልጠና የኅብረት ሥራ ማኅበራት ዕድገትና ተወዳዳሪነትን ያሻሽላል'' አቶ ታምራት ደልቦ ለሁለት ተከታታይ ቀናት በአፈር ማዳበሪ...
23/05/2026

"በአፈር ማዳበሪያ ሂሳብ አያያዝና ኦዲት አሠራር ዙሪያ የተሰጠው ስልጠና የኅብረት ሥራ ማኅበራት ዕድገትና ተወዳዳሪነትን ያሻሽላል'' አቶ ታምራት ደልቦ

ለሁለት ተከታታይ ቀናት በአፈር ማዳበሪያ ሂሳብ አያያዝና ኦዲት አሠራር ዙሪያ ሲሰጥ የቆየው ስልጠና መጠናቀቁ ተጠቁሟል።



የደቡብ ኢትዮጵያ ክልል ኅብረት ሥራ ልማት ኤጀንሲ በአፈር ማዳበሪያ ሂሳብ አያያዝና ኦዲት እንዲሁም በማኅበራት ዕድገትና ተወዳዳሪነት ማሻሻያ ላይ ለክልል፣ ለዞን፣ ለወረዳ እና ለከተማ አስተዳደር ባለሙያዎች የተዘጋጀ ስልጠና ሰጥቷል።

ለሁለት ቀናት በቆየው ስልጠና በክልሉ ኅብረት ሥራ ልማት ኤጀንሲ የማኅበራት ደህንነት ጥበቃ ዳይሬክቶሬት ዳይሬክተር በአቶ ዘካሪያስ ዘውጋ እና በማኅበራት ማደራጃና ማስፋፊያ ዳይሬክቶሬት ዳይሬክተር በአቶ ቶንጃ ቶማ ለስልጠናው የተዘጋጁ ሰነዶች ቀርበው ትንታኔ ተሰጥቶባቸዋል።

በምክትል ዋና ዳይሬክተር ማዕረግ የግብርና ምርት አቅርቦትና ግብይት ዳይሬክቶሬት ዳይሬክተር ክቡር አቶ ታምራት ዴልቦ መድረኩን ባጠቃለሉበት ወቅት መንግሥት የአፈር ማዳበሪያ አቅርቦትን በማሳደግ የአርሶ አደሩን ፍላጎት ለማርካት በትኩረት እየተሠራ ይገኛል ብለዋል።

የአፈር ማዳበሪያ በከፍተኛ የውጪ ምንዛሬ በመንግሥት ድጎማ ወደ ሀገር የሚገባ ሀብት መሆኑን ያመለከቱት ክቡር አቶ ታምራት ግብይቱ በጥብቅ የሂሳብ አያያዝና ኦዲት ሥርዓት ሊፈፀም ይገባልም ብለዋል።

በክልሉ የአፈር ማዳበሪያ ግብይት እጅ በእጅ ክፍያ እንዲፈፀም አቅጣጫ መቀመጡን ተከትሎ ሥራው እየተፈፀመ እንደሚገኝ ያመለከቱት ክቡር አቶ ታምራት የሽያጭ ገንዘብን በወቅቱ ወደ ባንክ የማስገባት እና ሪፖርት ማቅረብ እንዲሁም የሀብት ቁጥጥርና የፋይናን ኦዲትና ሪፖርት ማቅረብ ከቡድን መሪዎችና ሰልጣኝ ባለሙያዎች ይጠበቃል ብለዋል።

የኅብረት ሥራ ሪፎርም ተግባር በክልሉ እየተከናወነ መሆኑን ክቡር አቶ ታምራት አንስተው የማኅበራትና የኅብረት ሥራ መዋቅር በአመለካከት የመገንባት፣ አደረጃጀትን የማጠናከር፣ የማኅበራትን ተወዳዳሪነት በማጠናከር ወደ ኤክስፖርት ገበያ ማስገባት፣ የሰው ኃይል እጥረት በአዲሱ የሥራ ምዘናና ደረጃ ዕድገት (JEG) ጥናት መሠረት የመሙላት ሥራ በማከናወን የገጠር ትራንስፎርሜሽንን ለማረጋገጥ ርብርብ እንደሚደረግ አስረድተዋል።

የኦዲት ሥራን ለመደገፍ ከክልል ማዕከል ድጋፋዊ ክትትል ቡድን ወደ ዞኖች ወርዶ አፈፃፀምን እንደሚገመግም ጠቁመው አስፈላጊው ቅድመ-ዝግጅት በዩኒየኖችና መሠረታዊ ኅብረት ሥራ ማኅበራት እንዲከናወን አሳስበዋል።

በክልሉ ግብርና ቢሮ የኮሚዩኒኬሽን ዘርፍ ኃላፊ አቶ ፈቃዱ በየነ በበኩላቸው የተሰጠው ስልጠና በክልሉ የአፈር ማዳበሪያ ሂሳብ አያያዝና ኦዲት ተግባራት አፈፃፀም ሂደት እና ውጤታማነት ላይ የሚስተዋሉ ተግዳሮቶችን ለመቅረፍ እንደሚያስችል ገልፀዋል።

በመድረኩ ተሳታፊዎች የተሰጡ አስተያዬቶችና ጠቃሚ ግብዓት የተወሰደባቸው መሆኑን ያነሱት አቶ ፈቃዱ ህግን ያልተከተለ አሠራርን በማንም ይፈፀም በማን ተቀባይነት ስለሌለው በአሠራር እንዲታረም ይደረጋል ብለዋል።

ለመድረኩ በቀረቡ ሰነዶች ላይ ሰልጣኞች አስተያዬትና ጥያቄ ሰንዝረዋል፤ ለተሰነዘሩ ጥያቄዎችም ከቤቱና ከመድረክ ምላሽና ማብራሪያ ተሰጥቷል።

በስልጠናው የተሳተፉ ባለሙያዎች በሂሳብ አያያዝ እና በኦዲት የሚያጋጥማቸውን ተግዳሮት ለመቅረፍ የሚያስችል ግንዛቤ መጨበጣቸውንና በተጠያቂነት ተልዕኮን ለመፈፀም በቁርጠኝነት እንደሚሠሩ አረጋግጠዋል።

በስልጠናው የጨበጡትን ግንዛቤና ክህሎት በቀጣይ ተግባር ላይ በማዋል ለተቋማዊ ግብ ስኬት እንደሚያውሉ ገልፀው የአቅም ግንባታ ስልጠናው ተጠናክሮ እንዲቀጥል ጠይቀዋል።

በስልጠናው ላይ በምክትል ዋና ዳይሬክተር ማዕረግ የግብርና ምርት አቅርቦትና ግብይት ዳይሬክቶሬት ዳይሬክተርና የዋና ዳይሬክተር ተወካይ ክቡር አቶ ታምራት ዴልቦን ጨምሮ ከክልል፣ ከዞን፣ ከሪጅዮ-ፓሊስ፣ ፈርጅ አንድና ፈርጅ ሁለት ከተማ አስተዳደሮች እንዲሁም ከወረዳዎች የተውጣጡ የዘርፉ ቡድን መሪዎች እና የአፈር ማዳበሪያ ሂሳብ አያያዝና ኦዲት ባለሙያዎች መሳተፋቸው ተዘግቧል።

በአያሌው ዘነበ

  በወይዴ ሙልአቴ ቀበሌከ5 ሄ/ር በላይ የኩታ ገጠም እርሻ ላይ በመደበኛ መስኖ እየለማ የሚገኝ የጥቅል-ጎመን እና የሽንኩርት ማሣ በምስል👇👇👇
23/05/2026

በወይዴ ሙልአቴ ቀበሌ
ከ5 ሄ/ር በላይ የኩታ ገጠም እርሻ ላይ በመደበኛ መስኖ እየለማ የሚገኝ የጥቅል-ጎመን እና የሽንኩርት ማሣ በምስል👇👇👇

የአፈርን ጤንነት መጠበቅ የሰውንና የእንስሳትን ደኅንነት መጠበቅ ነው:-አቶ አንደኛ ሽናሌ‎‎በደቡብ ኢትዮጵያ ክልላዊ መንግስት ግብርና ቢሮ በተፈጥሮ ሀብት ልማት ዘርፍ የአፈር  ጤንነትና ለም...
22/05/2026

የአፈርን ጤንነት መጠበቅ የሰውንና የእንስሳትን ደኅንነት መጠበቅ ነው:-አቶ አንደኛ ሽናሌ

‎በደቡብ ኢትዮጵያ ክልላዊ መንግስት ግብርና ቢሮ በተፈጥሮ ሀብት ልማት ዘርፍ የአፈር ጤንነትና ለምነት ማሻሻያ ዳይሬክቶሬት የስልጠናና የንቅናቄ መድረክ አካሂዷል።



‎"ለም አፈር ለበለፀገች ደቡብ ኢትዮጵያ መሠረት ነው " በሚል መሪ ቃል በክልሉ ካሉ ከሁሉም ዞኖችና ወረዳዎች ከተውጣጡ የአፈር ጤንነትና ለምነት ማሻሻያ ዳይሬክተሮችና ቡድን መሪዎች ጋር የስልጠናና የንቅናቄ መድረክ ተካሂዷል።

‎የክልሉ ግብርና ቢሮ ምክትል ኃላፊና የተፈጥሮ ሀብት ልማት ዘርፍ ኃላፊ አቶ አንደኛ ሽናሌ ለምርትና ምርታማነት መሠረት የሆነውን የአፈርን ጤንነት መጠበቅ የሰውንና የእንስሳትን ደኅንነት መጠበቅ ነው ብለዋል።

‎በአፈር ውስጥ ያሉ ማዕድናት ጤናማ ካልሆኑ የአፈርን ደህንነት መጠበቅ አይቻልም ያሉት ኃላፊው ለዚህም ቨርሚ ኮምፖስት በማዘጋጀት ፣የተፈጥሮ ማዳበሪያን ከሰው ሠራሽ ማዳበሪያ ጋር አቀናጅቶ መጠቀም እንደሚገባ አሳስበዋል።

‎በክልሉ ያለውን የኑሮ ውድነት ችግር በመቅረፍና የምግብ ዋስትናን ለማረጋገጥ ምርታማነትን የሚቀንሱ ተግዳሮቶችን በመለየት የአፈር ለምነትን የሚጨምሩ የተለያዩ የመፍትሔ አማራጮችን መጠቀምና መደገፍ እንደሚገባ አመላክተዋል።

‎አቶ አንደኛ አክለውም በክልሉ የአፈርን ጤንነት በመጠበቅ አሲዳማነትን ለመቀነስ ከተለያዩ ፕሮጀክቶች ጋር በመቀናጀት በርካታ ተግባራት መከናወናቸውን ገልፀው በዘርፉ የሚታየውን ችግር በመቅረፍ ምርትና ምርታማነትን ለማሳደግ በየደረጃው ያለው አካል በትኩረት መሥራት እንዳለበት አሳስበዋል።

‎የቢሮው የተፈጥሮ ሀብት ልማት ዘርፍ የአፈር ጤንነትና ለምነት ማሻሻያ ዳይሬክተር ወ/ሮ ዝናሽ አበበ የዘርፉን የንቅናቄ ሰነድ በማቅረብ ሰፊ ገለፃ አቅርበዋል።

‎የአፈርን ለምነት ከሚቀንሡና የአሲዳማነት መጠን እንዲጨምር ከሚያደርጉ ነገሮች ዋነኞቹ የአፈር የላይኛው ክፍል በዝናብና በተለያዩ ምክንያት መታጠብና መወገድ ሲሆን ይህንንም ችግር ለመቅረፍ መሬቱን በኖራ ማከም አንዱና ዋነኛው አማራጭ መሆኑን ተናግረዋል።

‎አሲዳማ መሬት ከ50-100 ምርት የሚቀንስ ሲሆን በኖራ የታከመ መሬት ከ100 በመቶ በላይ የምርት መጠን ይጨምራል ያሉት ወ/ሮ ዝናሽ በክልሉ በአሲዳማነት የተጠቃ መሬት 326 ሺህ 507 ሄ/ር መሬት ሲሆን ባለፉት 12 ዓመታት በተሠራው ሥራ 14 ሺህ 970 ሄ/ር መሬት በኖራ ታክሞ ያገገመ መሆኑን ተናግረዋል።

‎በዕለቱም የጋሞ ፣ የወላይታ ፣የጌዴኦ ፣የኮንሶና አሪ ዞኖች የአፈር ለምነት ዳይሬክተሮችና የወላይታ ሶዶ አፈር ላባላቶሪ ሥራስኪያጅ በዘርፉ የተሠሩ ሥራዎችን ያመላከተ ሰነድ አቅርበዋል።

‎በቀረቡ ሰነዶችም ከቤቱ ለተነሡ ጥያቄዎችና ሀሳቦች ከመድረኩ ምላሽና ማብራርያ ተሰጥቶበታል

‎በመድረኩም የቢሮው የተፈጥሮ ሀብት ልማት የአፈር ጤንነትና ለምነት ማሻሻያ ዳይሬክቶሬት ከፍተኛ ባለሙያዎች ፣ የሦስቱ ሪጅዮ ፖሊስ ከተማ አስተዳደር መምሪያ ኃላፊዎች፣ ከሁሉም ዞኖችና ወረዳዎች የተውጣጡ የአፈር ጤንነትና ለምነት ማሻሻያ ዳይሬክተሮችና ቡድን መሪዎች መሳተፋቸው ተዘግቧል።

‎በዝናቧ ጌታሁን

Address

Dilla, Ethiopia

Alerts

Be the first to know and let us send you an email when South Ethiopia Region Bureau of Agriculture posts news and promotions. Your email address will not be used for any other purpose, and you can unsubscribe at any time.

Contact The Organization

Send a message to South Ethiopia Region Bureau of Agriculture:

  • Want your organization to be the top-listed Government Service?

Share