19/09/2024
የዲላ ከተማ ፓሊስ አስ/ር ጽ/ቤት ከ5ቱም ቀበሌ ከ15 ቀጠና ለተመረጡ ገለልተኛ አማካሪ ቡድን እና ማህበረሰብ ደኅንነትን ፓትሮል (ቅኝት) ዙሪያ የተዘጋጀ ሥልጠና ተሰጠ ።
ዲላ መስከረም 9/2017 ዓ.ም የዲላ ከተማ ፓሊስ ህዝብ ግንኙነት
በስልጠናው መክፈቻ ንግግር ያደረጉት የዲላ ከተማ ፓሊስ አዛዥ ኢ/ር እድገት ህርባዬ ከ5ቱም ቀበሌ ከ15 ቀጠና ለተመረጡ ገለልተኛ አማካሪ ቡድን እና ማህበረሰብ ደህንነት ፓትሮል (ቅኝት) ዙሪያ የዲላ ከተማ ፓሊስ ጽ/ቤት በተዘጋጀው ስልጠና እንኳን ቀሰላም መጣችሁ ከበዓሉ በኃላ የዲላ ከተማን ሰላምና ደህንነት በቀጣይነት ከማረጋገጥ አንፃር ፓሊስ ከማህበረሰቡ ጋር የጠበቀ ግንኙነት በመፍጠር የህዝቡን ተሳትፎ በማሳደግ የከተማዋን ሰላም አስተማማኝ ደረጃ ማድረስ ለሁሉም ነዋሪ ለአከባቢው ፓሊስ ነው እናንተም የዛሬ ሰልጣኞች ነገ ለአከባቢያችሁ የሰላም አምባሳደር ፓሊስ ናችሁ ተቀናጅቶ ለመስራት ሥልጠናው አስፈላጊ እንደሆነ ገልፀዋል በዕለቱ ተገኝተው ለሰልጣኞች ስልጠና የሰጡ የዲላ ከተማ ፓሊስ ማህ/አቀ/የቅድመ ወንጀል መከላከል ኮሚኒቲ ኦፊሰር በድን መሪ ም/ኮ/ር አበባ አክሊሉ ናቸው ።
በመድረኩ ተገኝተው መልዕክት ያስተላለፉት የጌዴኦ ዞን ፓሊስ መምሪያ ማህ/አቀ/ወንጀል መከላከል ዲቨዥን ማስተባበሪያ ኃላፊ ኢ/ር ቦጋለ ገመደ ፓሊስና ህብረተሰብ ,ህብረተሰብና ፓሊስ ተቀናጅተው ወንጀልን በመቀነስ መስራቱ ጌዴኦ ዞን ከሁሉም ዞኖች የሰላም አምባሳደር ዞን መሆኑን ከ ደቡብ ኢት/ያ ክልል መንግስት ይህን ማረጋገጫ ሰቶናል ስለዚህ የከተማችን ሰላምና ደኅንነት መረጋገጥ ለከተማው እድገት ማህበራዊና ፓለቲካዊ ፋይዳ እንዳለው ኢ/ር ቦጋለ ገመደ አሳውቀዋል ።
በመቀጠልም የዲላ ከተማ አስ/ር ሰላምና ፀጥታ ጽ/ቤት ኃላፊ አቶ አዲሱ ከበደ የፀጥታ ኃይሎች የህብረተሰቡን ሰላምና ደኅንነት ከማስጠበቅ አልፈው በልማት ፣በበጎ ፈቃድ አገልግሎት ፣ የማህበረሰብ አቀፍ አገልግሎት መስጫ ማዕከል ግንባታ ማሳያ ተግባሮች ናቸው ብለዋል ።
የዛሬው ስልጠና የዲላ ከተማ ፓሊስ ጽ/ቤት መስጠቱ ለምንሥራ ሥራ ጉልበት ይሰጠናል አሉ።