06/09/2026
✈️ በደቡብ ኦሞ ዞን ዲመካ ከተማ እየተገነባ ያለው መለስተኛ የአውሮፕላን ማረፊያ በፍጥነት እየተሠራ ነው
በደቡብ ኢትዮጵያ ክልል በግንባታ ሂደት ላይ ከሚገኙ አራት መለስተኛ የአውሮፕላን ማረፊያዎች መካከል፣ በደቡብ ኦሞ ዞን በዲመካ ከተማ እየተገነባ ያለው መለስተኛ የአውሮፕላን ማረፊያ አንዱ ነው።
ፕሮጀክቱን በተያዘው ዕቅድ መሠረት ለማጠናቀቅ ሥራው በፍጥነትና በትኩረት እየተከናወነ ይገኛል።
የደቡብ ኢትዮጵያ ክልል መንገዶች ባለሥልጣን ዋና ዳይሬክተር ኢንጂነር እድሬ እርኮ፣ ፕሮጀክቱ በተያዘው ዕቅድ መሠረት በፍጥነት እየተከናወነ መሆኑን ገልጸው፣ በቀጣይም ሥራው በትኩረት በማስቀጠል በታቀደለት ጊዜ እንዲጠናቀቅ እየተሠራ መሆኑን ጠቁመዋል።
© SERA Communication