Zinabu Wolde

Zinabu Wolde Gedeo Zone Chief Administrator
Researcher and Lecturer at Dilla University
(1)

06/06/2026
የመደመር እሳቤን መሠረት ያደረገ፣ የጌዴኦ "የአንድነት ምዕራፍ"፣ በህዝባችን ውስጥ መረዳት ለምችሉ ፖለቲካዊ፣ ኢኮኖሚያዊ እና ማህበራዊ ለውጥ አምጥቷል:: ይህ ደግሞ መነሻ ነው፣ ይቀጥላል::...
05/06/2026

የመደመር እሳቤን መሠረት ያደረገ፣ የጌዴኦ "የአንድነት ምዕራፍ"፣ በህዝባችን ውስጥ መረዳት ለምችሉ ፖለቲካዊ፣ ኢኮኖሚያዊ እና ማህበራዊ ለውጥ አምጥቷል:: ይህ ደግሞ መነሻ ነው፣ ይቀጥላል:: ከጊዜ ጋር አብሮ መፍጠን፣ ዕይታን ከአካባቢ እስሬኝነት ከፍ አድርጎ ለማየት ይረዳል::
Viva #ጌዴኦ

03/06/2026
የተከልነው ችግኝ ብቻ አይደለም፣ የህባችን እሴት የሆነውን፦ ቅንነት፣ መልካምነት፣ አብሮነት እና አንድነት ነው።ይህ የጌዴኦ ህዝብ እሴት ነው::Aggakenni agguni!!!
03/06/2026

የተከልነው ችግኝ ብቻ አይደለም፣ የህባችን እሴት የሆነውን፦
ቅንነት፣ መልካምነት፣ አብሮነት እና አንድነት ነው።
ይህ የጌዴኦ ህዝብ እሴት ነው::
Aggakenni agguni!!!

 #ልዩ ምስጋናለመላው የዞናችን ህዝብ፣ ለወጣቶች፣ ለፓርቲያችን አባላትና ደጋፊዎች፣ ለአመራሮቻችን፣ ለፀጥታ አካላት፣ ለሚዲያ ተቋማትና ለምርጫው ስኬት የበኩላችሁን የተወጣችሁ በሙሉ የሥራችን ...
02/06/2026

#ልዩ ምስጋና

ለመላው የዞናችን ህዝብ፣ ለወጣቶች፣ ለፓርቲያችን አባላትና ደጋፊዎች፣ ለአመራሮቻችን፣ ለፀጥታ አካላት፣ ለሚዲያ ተቋማትና ለምርጫው ስኬት የበኩላችሁን የተወጣችሁ በሙሉ

የሥራችን መከናወን ብቻችንን ልሳካ ይቅርና በፍጹም ልታሰብ የማይችል ነው፤ ሆኖም አብረን ተቀናጅተንና ተደጋግፈን በውጤት የታጀበ ተግባር ፈጽመናል። የዚህ ሚስጥሩ ምንም ሳይሆን ተደማምጠን እና ተከባብረን ህዝባችንን መሠረት ባደረጉ ተግባር ላይ የሰነበትን አንድ ቤተሰብ በመሆናችን ነው።

የተወዳደሩት ፓርቲዎች ቢሆኑም ያሸነፈችው ግን ኢትዮጵያ ሀገሬ ናት፤ ምርጫው ሠላማዊ ሆኖ የተጠናቀቀው ሰላምን የሚያደፈርሱ አካላት ስላልነበሩ ሳይሆን የኛ አንድነትና መተሳሰር ስለበጠ ነውና ሁላችሁም እንኳን ደስ ያላችሁ!

በጌዴኦ ዞን በርካታ ፕሮጀክቶችን አሳክተን በየአቅጣጫው የመሠረተ ልማት ጭላንጭሎች አሳይተን ዛሬ ለምርጫው ቀን መብቃታችን የህዝባችን ጽኑ ተሳታፊነትና ቀናነት ተጨምሮበት ስለሆነ በዚህ አጋጣሚ ለጌዴኦ ህዝብ ያለኝን አድናቆትና ምስጋና እገልጻለሁ።

የዘንድሮ ምርጫ እንደ ሀገርም ታሪካዊና በብዙ ነገር ለየት ያለ ሲሆን በተለይም በርካታ ፓርቲዎችና የግል እጩዎች መሳተፋቸው፣ የመድብለ ፓርቲ ስርዓቱ እንዲጎለብት ገዢው ፓርቲ መወዳደሪያ ሜዳውን ያሰፋበት እና ከምንም በላይ ሠላማዊ፣ ነፃ፣ ፍትሃዊና ዲሞክራሲያዊ ምርጫ እንዲሆን ብዙ ጥረት የተደረገበት ልዩ የምርጫ አመት ነው ማለት ይቻላል። ይህ ሁኔታ በራሱ ግብ ባለመሆኑና ብቻውን በቂ ባለመሆኑ በየደረጃው ኃላፊነት ያለን አካላት የምጠበቅብንን እንድንወጣ አደራ ማለት ፈልጋለሁ።

በቀጣይም ህዝባችንን ይዘን ብዙ ድሎችን እንደምናስመዘግብ ዛሬ ይበልጥ እርግጠኛ መሆን ችያለሁና ምስጋናዬ በያላችሁበት ይድረሳችሁ።

ሠላማችሁም የበዛ ይሁን!!!

02/06/2026

‎በዞኑ ምርጫው ዴሞክራሲያዊ ፣ ፍትሃዊና ሰላማዊ ሆኖ በመጠናቀቁ ዋና አስተዳዳሪ ዝናቡ ወልዴ(ዶ/ር) ምስጋና አቀረቡ

‎(ዲላ ግንቦት 25/2018 ዓ/ም) በጌዴኦ ዞን 7ኛው ሀገራዊና ክልላዊ ምርጫ ዴሞክራሲያዊ ፣ ፍትሃዊና ሰላማዊ ሆኖ በመጠናቀቁ የዞኑ ዋና አስተዳዳሪ ዝናቡ ወልዴ(ዶ/ር) ለመላው ለዞኑ ህዝብ ምስጋና አቅርበዋል ።

‎ይህ 7ኛው ሀገራዊና ክልላዊ ምርጫ የኢትዮጵያን አሸናፊነት ያረጋገጠ መሆኑን አስተዳዳሪው በምስጋና መልዕክታቸው ገልጸዋል ።

‎በዞኑ የምርጫ ሂደት ከጀመረበት ጊዜ አንስቶ ህዝቡ በሰላማዊ መንገድ ተሳትፎ በማድረግ በባለቤትነት መብቱን መጠቀም መቻሉን ነው አስተዳዳሪው የገለጹት ።

‎በተለይም ግንቦት 24 የተከናወነ የመጨረሻ የድምጽ አሰጣጥ ሂደት በሰላም እንዲጠናቀቅ የበኩላቸውን ኃላፊነት ለተወጡ ባለድርሻ አካላት ዶክተር ዝናቡ ምስጋና አቅርበዋል ።

‎የጸጥታ አካላት ፣ የምርጫ አስፈጻሚዎች ፣ ገለልተኛ ታዛቢዎች ፣ ወጣቶች ፣ አመራሮች እና ሌሎችም ባለድርሻዎች አካላት ሚናቸው ከፍተኛ እንደነበረ አንስቶ በዞኑ ህዝብ ስም አመስግነዋል ።

‎የምርጫ ድምጽ ቆጠራ ሂደት ተጠናቆ የምርጫ ቦርድ ውጤቱን እስከሚያሳውቅ ድረስ ህብረተሰቡ የተለያዩ የአሉባልታ ወሬዎችን እንዳይሰማ አስተዳዳሪው ጥሪ አቅርበዋል ።

‎@የጌዴኦ ዞን የመንግስት ኮሙኒኬሽን አገልግሎት !

01/06/2026
ሰላማችው የበዛ ይሁን ውድ ማህበራዊ ሚዲያ ተጠቃምዎች!!ይህ ከታች የምትመለከቱት መረጃ ለዘመናት በዞናችን የከሰሩ እና የቀነጨሩ አንቅ ነን ባዮች የፌበረኩት የሀሴት መረጃ ነው:: ይህ አይነት...
01/06/2026

ሰላማችው የበዛ ይሁን ውድ ማህበራዊ ሚዲያ ተጠቃምዎች!!ይህ ከታች የምትመለከቱት መረጃ ለዘመናት በዞናችን የከሰሩ እና የቀነጨሩ አንቅ ነን ባዮች የፌበረኩት የሀሴት መረጃ ነው:: ይህ አይነት ክስተት በዞናችን የለምም አይኖርምም፣ ህዝባችን ጨዋ እና በሥራ የምያምን ህዝብ ነው:: የቀን ጉዳይ ነው፣ ሁሉም በውሼት የተካኑ የእጃቸውን የምያገኙበት ጊዜ ሩቅ አይደለም::

በድጋሚ የተሰጠ መግለጫየኢትዮጵያ ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ ዛሬ ሰኞ ግንቦት 24 ቀን 2018 ዓ.ም. ከማለዳ 12:00 ሰዓት ጀምሮ እስከ ምሽት 12:00 ሰዓት የ7ኛውን ጠቅላላ ምርጫ ድምፅ የማስ...
01/06/2026

በድጋሚ የተሰጠ መግለጫ

የኢትዮጵያ ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ ዛሬ ሰኞ ግንቦት 24 ቀን 2018 ዓ.ም. ከማለዳ 12:00 ሰዓት ጀምሮ እስከ ምሽት 12:00 ሰዓት የ7ኛውን ጠቅላላ ምርጫ ድምፅ የማስፈጸም ሂደት ላይ እንደነበር ይታወቃል። ቦርዱ በሥምሪት ላይ ያለው የክትትል ቡድኑ ያቀረበለትን ሪፖርት ተመልክቶ የሚከተለውን ወሥኗል።

በኢትዮጵያ የምርጫ፣ የፖለቲካ ፓርቲዎች ምዝገባና የምርጫ ሥነ-ምግባር ዐዋጅ 1162/2011 አንቀጽ 49(4) መሠረት ቦርዱ የምርጫው ነፃና ፍትሐዊነት ይበልጥ ያሰፍናል ብሎ ካመነ የድምፅ መስጫ ሰዓቱን ሊያራዝም እንደሚችል በግልጽ ይደነግጋል። በመሆኑም የድምፅ መስጫ ሂደት ባልተጠናቀቀባቸው የምርጫ ጣቢያዎች ላይ ድምፅ የመስጠት ሂደቱ እስከ ዕኩለ ለሊት 6:00 ሰዓት ድረስ የተራዘመ መሆኑን ቦርዱ ያሳውቃል።

ማሳሰቢያ: የተመዘገቡ መራጮች መርጠው የተጠናቀቁባቸው ጣቢያዎች ላይ አስፈጻሚዎች የድምፅ ቆጠራ ሂደቱን እንዲያከናውኑ ቦርዱ ያስታውሳል።

Address

Gedeo , Ethiopia, Wolaita Sodo, Ethiopia, Arba Mintch, Ethiopia , Addis Ababa
Dila
1000

Alerts

Be the first to know and let us send you an email when Zinabu Wolde posts news and promotions. Your email address will not be used for any other purpose, and you can unsubscribe at any time.

Share