የደቡብ ወሎ ዞን ገቢዎች መምሪያ - SWZRs Office of Revenues

  • Home
  • Ethiopia
  • Dessie
  • የደቡብ ወሎ ዞን ገቢዎች መምሪያ - SWZRs Office of Revenues

የደቡብ ወሎ ዞን ገቢዎች  መምሪያ -  SWZRs Office of Revenues Contact information, map and directions, contact form, opening hours, services, ratings, photos, videos and announcements from የደቡብ ወሎ ዞን ገቢዎች መምሪያ - SWZRs Office of Revenues, Government Official, South Wollo zone, Dessie.

 # ለመላው የክርስትና እምነት ተከታዮች በሙሉ እንኳን ለፋሲካ በአል በሰላም አደረሳችሁ።          "የደቡብ  ወሎ ዞን ገቢዎች መምሪያ"  # በአሉ የደስታ፣ የሰላም ፣ የፍቅርና የመተሳ...
11/04/2026

# ለመላው የክርስትና እምነት ተከታዮች በሙሉ እንኳን ለፋሲካ በአል በሰላም አደረሳችሁ።

"የደቡብ ወሎ ዞን ገቢዎች መምሪያ"

# በአሉ የደስታ፣ የሰላም ፣ የፍቅርና የመተሳሰብ በዓል እንድሆንላችሁ ከልብ ይመኛል ።

# ይህ ታላቅ በዓል ለመላዉ ህዝባችንና ለንግዱ ማህበረሰብ ለሀገራችን ኢትዮጵያ ሰላምን፣ መተሳሰብን አንድነትን እና ፍቅርን ይዞልን እንዲመጣ ልባዊ ምኞቱን የደቡብ ወሎ ዞን ገቢዎች መምሪያ በታላቅ አክብሮት ይገልጻል ።

**መልካም የፋሲካ በዓል!**

እንኳን  ለ1447ኛው የኢድ አል-ፈጥር በዓል በሰላም አደረሳችሁ  የደቡብ ወሎ ዞን ገቢዎች መምሪያ🌙🌙ለመላው የእስልምና እምነት ተከታዮች በሙሉ፤ የረመዳን ጾምን በጸሎትና በዒባዳ አሳልፋችሁ ...
19/03/2026

እንኳን ለ1447ኛው የኢድ አል-ፈጥር በዓል በሰላም አደረሳችሁ የደቡብ ወሎ ዞን ገቢዎች መምሪያ🌙

🌙ለመላው የእስልምና እምነት ተከታዮች በሙሉ፤ የረመዳን ጾምን በጸሎትና በዒባዳ አሳልፋችሁ ለ1447ኛው የኢድ አል-ፈጥር በዓል በሰላም፣ በጤና እና በፍቅር እንኳን አደረሳችሁ!

🌙በዓላት ሁልጊዜም የደስታ፣ የቤተሰብ መገናኘትና የፍቅር መግለጫ መድረኮች ናቸው። የዞኑ ገቢዎች መምሪያም የዞናችንን የልማትና የመልካም አስተዳደር ችግሮችን ለመፍታት እና በራሳችን በምንሰበስበዉ ገቢም ለመመለስ ዘወትር ከጎናችሁ ነው።

🌙በመሆኑም መምሪያዉ በሚከተሉት ዋና ዋና ጉዳዮች ላይ የንግዱ ማህበረሰብ ከፍተኛ ጥንቃቄ እንዲያደርግ አሳስበዋል፡-

1ኛ በበዓል ዋዜማ የገበያ ቦታዎች በእጅጉ ስለሚጨናነቁ እና ፈጣን ግብይቶች ስለሚፈጸሙ፣ከሀምሳ ሽህ ብር በላይ በጥሬ ገንዘብ ግብይት እንዳይፈጽሙ: ትክክለኛዉን የዲጂታል (የኤሌክትሮኒክስ) ክፍያ አማራጮችን መጠቀም ተመራጭና አስተማማኝ መሆኑን አንዘንጋ።

2ኛ በአሉን ምክናየት በማድረግ ለሚከናወኑ ግብይቶች ደረሰኝ መስጠትዎን አይዘንጉ።

🌙 በመጨረሻም፤ የዞኑ ገቢዎች መምሪያ ለ1447ኛው የኢድ አል-ፈጥር በዓል ለመላው የእስልምና እምነት ተከታዮች የሰላም፣ የፍቅር፣ የመረዳዳት እና የደስታ በዓል እንዲሆንላችሁ ከልብ የመነጨ መልካም ምኞቱን አስተላልፏል።

🌙 ዒድ ሙባረክ

"ግብራችን ለልማታችን ለሰላማችን!!



የዞኑ ግብር ትምህርትና ኮሚኒኬሽን ስራ ሂደት

 #ይመዝገቡ፤ የነገዋን ኢትዮጵያ በድምፅዎ ያፅኑ ‼️ድጅታል ኢትዮጵያ!!
10/03/2026

#ይመዝገቡ፤ የነገዋን ኢትዮጵያ በድምፅዎ ያፅኑ ‼️
ድጅታል ኢትዮጵያ!!

09/03/2026

"በገቢ ተቋማችን ሰራተኞች ኮርተናል!"
ክቡር መንገሻ ፈንታው (ዶ.ር) የገቢዎች ቢሮ ኃላፊ

"ቅዳሜና እሁድ አገልግሎት ስለሰጣችሁን ተደስተናል። ይህን ተምሳሌታዊ ተግባር ሌሎችም ሊማሩበት ይገባል።"

የባህር ዳር ከተማ ገቢዎች ተቋም ተገልጋዮች
።።።።።።፨፨፨።።።።።።

በአማራ ክልል በየደረጃው ያሉ ግብር ከፋዮቻችን የሩብ ዓመት ግብራቸውን ሳይጨናነቁ እንዲከፍሉ ቅዳሜ እና እሁድ ሙሉቀን አገልግሎት ለመስጠት በገባነው ቃል መሰረት በገቢዎች ተቋም ታታሪ ሠራተኞቻችን ቁርጠኝነት ለግብር ከፋዬቻችን አገልግሎት የመስጠት ተግባሩ ዛሬም በስኬት ተፈፅሟል ።

በዛሬው ዕለት የካቲት 29/2018 ዓ.ም የእረፍት ጊዜያችውን በስራ በማሳለፍ ኃላፊነታችውን እየተወጡ ያሉ የባህር ዳር ከተማ ገቢዎች መምሪያ አመራርና ሰራተኞችን ክቡር መንገሻ ፈንታው (ዶ.ር) የገቢዎች ቢሮ ኃላፊ፣ ክቡር አቶ ፍቅረማርያም ደጀኔ ምክትል ቢሮ ኃላፊ እና ሌሎች የተወሰኑ የማኔጅመንት አባላት ጋር በመሆን በአካል ተገኝተው ተዘዋውረው በመጎብኝት " በገቢ ተቋማችን ሰራተኞች ኮርተናል!" ሲሉ አበረታተዋቸዋል።

ቢሮ ኃላፊው ስራውን ተዘዋውረው ሲጎበኙ በርካታ ባለጉዳዬችን አግኝተው ያወያዩ ሲሆን ግብር ከፋዬች በበኩላቸው "ቅዳሜና እሁድ አገልግሎት ስለሰጣችሁን ተደስተናል። ይህን ተምሳሌታዊ ተግባር ሌሎችም ሊማሩበት ይገባል።" ሲሉ አስተያዬታቸውን ሰጥተዋል።

አገልግሎት እየሰጡ የነበሩ ሰራተኞች በበኩላቸው "የረፍት ጊዜያችን ትተን ለደንበኞቻችን በሰጠነው አገልግሎት ደንበኞቻችን መደሰታቸውን ስለገለፁልን ከፍተኛ ደስታ ተሰምቶናል" ሲሉ አስተያዬታቸውን ገልፀዋል።

ቅዳሜና እሁድ በሁሉም የክልላችን የገቢ ተቋማት አገልግሎት በመስጠት የታለመለትን ዓላማ በማሳካት ስኬታማ ተግባር ተፈፅሟል።

ስለምናገለግላችሁ ታላቅ ኩራት ይሰማናል!
የአማራ ክልል ገቢዎች ቢሮ

"በገቢ ተቋማችን ሰራተኞች ኮርተናል!"ክቡር መንገሻ ፈንታው (ዶ.ር) የገቢዎች ቢሮ ኃላፊ"ቅዳሜና እሁድ አገልግሎት ስለሰጣችሁን ተደስተናል። ይህን ተምሳሌታዊ ተግባር ሌሎችም ሊማሩበት ይገባል...
09/03/2026

"በገቢ ተቋማችን ሰራተኞች ኮርተናል!"
ክቡር መንገሻ ፈንታው (ዶ.ር) የገቢዎች ቢሮ ኃላፊ

"ቅዳሜና እሁድ አገልግሎት ስለሰጣችሁን ተደስተናል። ይህን ተምሳሌታዊ ተግባር ሌሎችም ሊማሩበት ይገባል።"

የባህር ዳር ከተማ ገቢዎች ተቋም ተገልጋዮች
።።።።።።፨፨፨።።።።።።

በአማራ ክልል በየደረጃው ያሉ ግብር ከፋዮቻችን የሩብ ዓመት ግብራቸውን ሳይጨናነቁ እንዲከፍሉ ቅዳሜ እና እሁድ ሙሉቀን አገልግሎት ለመስጠት በገባነው ቃል መሰረት በገቢዎች ተቋም ታታሪ ሠራተኞቻችን ቁርጠኝነት ለግብር ከፋዬቻችን አገልግሎት የመስጠት ተግባሩ ዛሬም በስኬት ተፈፅሟል ።

በዛሬው ዕለት የካቲት 29/2018 ዓ.ም የእረፍት ጊዜያችውን በስራ በማሳለፍ ኃላፊነታችውን እየተወጡ ያሉ የባህር ዳር ከተማ ገቢዎች መምሪያ አመራርና ሰራተኞችን ክቡር መንገሻ ፈንታው (ዶ.ር) የገቢዎች ቢሮ ኃላፊ፣ ክቡር አቶ ፍቅረማርያም ደጀኔ ምክትል ቢሮ ኃላፊ እና ሌሎች የተወሰኑ የማኔጅመንት አባላት ጋር በመሆን በአካል ተገኝተው ተዘዋውረው በመጎብኝት " በገቢ ተቋማችን ሰራተኞች ኮርተናል!" ሲሉ አበረታተዋቸዋል።

ቢሮ ኃላፊው ስራውን ተዘዋውረው ሲጎበኙ በርካታ ባለጉዳዬችን አግኝተው ያወያዩ ሲሆን ግብር ከፋዬች በበኩላቸው "ቅዳሜና እሁድ አገልግሎት ስለሰጣችሁን ተደስተናል። ይህን ተምሳሌታዊ ተግባር ሌሎችም ሊማሩበት ይገባል።" ሲሉ አስተያዬታቸውን ሰጥተዋል።

አገልግሎት እየሰጡ የነበሩ ሰራተኞች በበኩላቸው "የረፍት ጊዜያችን ትተን ለደንበኞቻችን በሰጠነው አገልግሎት ደንበኞቻችን መደሰታቸውን ስለገለፁልን ከፍተኛ ደስታ ተሰምቶናል" ሲሉ አስተያዬታቸውን ገልፀዋል።

ቅዳሜና እሁድ በሁሉም የክልላችን የገቢ ተቋማት አገልግሎት በመስጠት የታለመለትን ዓላማ በማሳካት ስኬታማ ተግባር ተፈፅሟል።

ስለምናገለግላችሁ ታላቅ ኩራት ይሰማናል!
የአማራ ክልል ገቢዎች ቢሮ

የፊታችን ቅዳሜና እሁድ ሙሉ ቀን አገልግሎት በመስጠት ህዝባችን ለማገልገል ተዘጋጂተናል።ታዘባቸው ጣሴየአማራ ክልል ገቢዎች ቢሮ የግብር ትምህርትና ኮሙዩኒኬሽን ዳይሬክተርበአማራ ክልል በየደረጃ...
06/03/2026

የፊታችን ቅዳሜና እሁድ ሙሉ ቀን አገልግሎት በመስጠት ህዝባችን ለማገልገል ተዘጋጂተናል።

ታዘባቸው ጣሴ
የአማራ ክልል ገቢዎች ቢሮ የግብር ትምህርትና ኮሙዩኒኬሽን ዳይሬክተር

በአማራ ክልል በየደረጃው ያሉ የገቢ ተቋማት የፊታችን ሰኞ የካቲት 30 ቀን 2018 ዓ/ም በመሆኑና ግብር ከፋዮቻችን የሩብ ዓመት ግብራቸውን ከፍለው የሚያጠናቅቁበት ስለሆነ ሰኞ እለት መጨናነቅ እንዳይፈጠር እኛ የገቢ ተቋም አመራሮችና ሰራተኞች የፌታችን ቅዳሜ እና እሁድ ሙሉቀን አገልግሎት በመስጠት ለግብር ከፋዬቻችን አገልግሎት ለመስጠት የእረፍት ጊዜያችንን ሁሉ በስራ ማሳለፍ ስንወስን ታላቅ ኩራትና ክብር ይሰማል።
ስለሆነም በመጭው ቅዳሜና እሁድ ማለትም የካቲት 28 እና 29/2018ዓ.ም በአማራ ክልል በየደረጃው ያሉ የገቢ ተቋማት ክፍት መሆናቸውን በመገንዘብ ሁሉም የተቋሙ ተገልጋይ ግብር ከፋዬች በአካል በመገኘት አገልግሎት የምታገኙ መሆኑን ስንገልፅ በታላቅ ደስታ ነው።

ስለምናገለግላችሁ ታላቅ ኩራት ይሰማናል!

ግብር ለሀገር  እድገት መሠረታዊ ምንጭ ነው። ግብር  የሀገር ዋልታ ነው። መንግሥት ከዜጎች የሚሰበስበው ግብር በትምህርት፣ በጤና፣ በመንገድ ግንባታ፣ በውኃ እና በኤሌክትሪክ አገልግሎቶች ልማ...
02/03/2026

ግብር ለሀገር እድገት መሠረታዊ ምንጭ ነው።

ግብር የሀገር ዋልታ ነው። መንግሥት ከዜጎች የሚሰበስበው ግብር በትምህርት፣ በጤና፣ በመንገድ ግንባታ፣ በውኃ እና በኤሌክትሪክ አገልግሎቶች ልማት ላይ ይውላል። የሀገር ኢኮኖሚን ያሳድጋል።

አቶ አበጀ እንዳለ በደብረ ማርቆስ ከተማ በልብስ ስፌት ሙያ እና ብትን ጨርቃ ጨርቅ ሽያጭ ላይ የተሰማሩ ነጋዴ ናቸው። በዚህ የንግድ ሙያ ለ10 ዓመታት ያክል መሥራታቸውን ነው የነገሩን።

ግብር አለመክፈል ጊዜያዊ ጥቅም ቢመስልም ለሀገር የመሠረተ ልማት እድገት መሠረታዊ ምንጭ መኾኑን እረዳለሁ ነው ያሉት። የዚህ መሠረተ ልማት ተጠቃሚው ደግሞ እኔ ነኝ፤ በዚህ ልክ በመረዳት ግብር መክፈል ግዴታየ ነው ብየ በማመን የሚጣልብኝን ዓመታዊ ግብር ያለምንም ማቅማማት በወቅቱ እከፍላለሁ ብለዋል።

የደብረ ማርቆስ ከተማ አሥተዳደር ገቢዎች መምሪያ ኀላፊ ጌታቸው አለበል በበጀት ዓመቱ 2 ቢሊዮን ብር ለመሰብሰብ በማቀድ ወደ ሥራ መግባታቸውን ተናግረዋል።

በዚህም እስካሁን ባለው በመደበኛ ግብር አሰባሰብ 628 ሚሊዮን ብር ከከተማ አገልግሎት 192 ሚሊዮን ብር በአጠቃላይ 821 ሚሊዮን ብር መሰብሰብ ተችሏል ነው ያሉት፡፡

በበጀት ዓመቱ የተሰበሰበው ገቢ ከእቅዱ አንጻር ዝቅተኛ አፈጻጸም ቢኖረውም ከባለፈው ዓመት ጋር ሲነጻጸር ግን የ450 ሚሊዮን ብር ብልጫ ያሳያል ብለዋል።

በቀጣይ የባለሙያ ሥልጠና በመስጠት እና ቁርጠኛ የመሪዎችን ድጋፍ በመጠቀም የተሰጠውን እቅድ ከግብ ለማድረስም ጥረት እንደሚደረግ ተናግረዋል።

የአማራ ክልል ገቢዎች ቢሮ የግብር ትምህርት እና የኮሙዩኒኬሽን ዳይሬክተር ታዘባቸው ጣሴ የአማራ ክልል ገቢዎች ቢሮ በ2018 በጀት ዓመት 103 ቢሊዮን ብር ለመሰብሰብ አቅዶ እየሠራ መኾኑን ተናግረዋል።

እስካሁን ባለው ከታቀደው 51 ነጥብ 3 በመቶ መሰብሰቡን ገልጸዋል። ይህም ከባለፈው ዓመት ተመሳሳይ ወቅት ጋር ሲነጻጸር ከ20 ቢሊዮን ብር በላይ ብልጫ አለው ነው ያሉት።

የተመዘገበው አፈጻጸም በክልሉ የገቢ አሥተዳደር ላይ የተሻለ ቢኾንም ከፍተኛ ዕቅድ ማቀድ ብቻ ሳይኾን በሲስተም መመራት፣ ተጠያቂነትን ማጠናከር እና ኅብረተሰብን በተሳትፎ በማካተት የክልሉን የገቢ መሠረት ማሳደግ እንደሚገባ ነው የገለጹት።

ቢሮው 86 ምሥጉን ግብር ከፋዮችን በልዩ ዕውቅና ሲያበረታታ በዲሲፕሊን ግድፈት የተገኙ 133 ሠራተኞች ላይ ደግሞ ከጽሑፍ ማስጠንቀቂያ እስከ ሥራ ማሰናበት ድረስ ርምጃ መውሰዱንም አስታውቀዋል።

አሚኮ

በተሻሻለው የአማራ ብሔራዊ ክልላዊ መንግስት የከተሞች አገልግሎት ገቢ አሰባሰብና ታሪፍ መወሰኛ ደንብ ዙርያ ውይይት ተደረገ የካቲት 20/2018 ዓ.ም (አማራ ክልል ገቢዎች ቢሮ) በአማራ ክል...
27/02/2026

በተሻሻለው የአማራ ብሔራዊ ክልላዊ መንግስት የከተሞች አገልግሎት ገቢ አሰባሰብና ታሪፍ መወሰኛ ደንብ ዙርያ ውይይት ተደረገ

የካቲት 20/2018 ዓ.ም (አማራ ክልል ገቢዎች ቢሮ) በአማራ ክልል የከተማ አገልግሎት ገቢን ለማሻሻል በወጣው ረቂቅ ደንብ ላይ የገቢወች እና የከተማና መሠረተ-ልማት ቢሮ አማራርና ባለሙያዎች፣ የከተማ ከንቲቦች እንዲሁም የሚመለከታቸው አካላት የተሳተፉበት የርቀት/የዙም ስብሰባ ተካሄደ።

ክቡር መንገሻ ፈንታው (ዶ/ር) የአማራ ክልል ገቢዎች ቢሮ ሃላፊ ውይይቱን አስመልክተው ባስተላለፉት መልዕክት፤ ለከተማ አገልግሎት ገቢ መጎልበት የገቢዎች እና የከተማና መሠረተ ልማት አመራርና ባለሙያዎች ህጉን አሻሽሎ እስከ ማስፈፀም በጋራ መስራት ይገባል ብለዋል።

የከተሞቻችን ዕድገት እንዲፋጠን በክልላችን ያለውን ዝቅተኛ የከተማ አገልግሎት ገቢ አፈጻጸም ማሻሻልና ከተሞች ለሚሰጡት አገልግሎት የከተማ አገልግሎት ገቢ መክፈል የሚገባቸው አካላት ፍትሃዊ ገቢ እንዲከፍሉ ጥረት ማድረግ እንደሚገባ ጠቁመዋል።

ክቡር ሞላ መልካሙ (ዶ/ር) የከተማና መሠረተ-ልማት ቢሮ ኃላፊ በበኩላቸው፤ የንግድና ሙያ አገልግሎት ክፍያ ለመሰብሰብ የከንቲቦች ተሳትፎ ወሳኝ በመሆኑ የትኛውም የከተማ አስተዳደር በዚህ ደንብ መሠረት የሚሰበሰበው የአገልግሎት ክፍያ ለነዋሪው ሕዝብ ከሚያቀርበው የአገልግሎት ዓይነትና ጥራት ወይም ደረጃ ጋር ተመጣጣኝ ሆኖ እንዲገኝ በትጋት መሰራት ይኖርበታል ብለዋል።

ደንብ ቁጥር 220/2017 ማሻሻል ያስፈለገበት ምክንያት፤ የንግድና ሙያ አገልግሎት ክፍያ የቀመር ችግር ያለበት በመሆኑ፣ አሰራሩን ምቹና ፍትሃዊ በማድረግ ኢንቨስትመንትን ማበረታታት ተገቢ በመሆኑ፣ ክፍያው በ3 መመዘኛ መስፈርቶች መሰላቱ ከፍተኛ ዓመታዊ ገቢ ላላቸው ግብር ከፋዮች ለተጋነነ ክፍያ የሚዳርግ በመሆኑ እና ክልላዊ ፍትሃዊነትን ሊያረጋግጥ በሚችል መልኩ ማሻሻል በማስፈለጉ እንደሆነ በገቢዎች ቢሮ የገቢ ክትትልና ታክስ መረጃ አስተዳደር ቡድን ሃላፊ አቶ ስንታየሁ ታደለ አብራርተዋል።

የውይይቱ ተሳታፊ ከንቲቦች እና መምሪያ ሃላፊዎች የሰጧቸውን ግብዓቶች እንዲሁም ከሌሎች ከሚመለከታቸው አመራረች፣ ባለሙያዎች በለድርሻና አጋር አካላት ግብዓትና አስተያየት ከተሰበሰበ በኋላ ለክልሉ ምክር ቤት እንደሚቀርብ ይጠበቃል።

የደቡብ ወሎ ዞን ገቢዎች መምሪያ  የ2018  ዓ.ም   የ7  ወሩን የቁልፍ እና የአብይት ተግባሮች አፈጻጸም ገመገመ።፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨የካቲት 2018 ዓ.ምኮምቦልቻ✍️በዉይይቱ  የዞን ማኔጅመን...
25/02/2026

የደቡብ ወሎ ዞን ገቢዎች መምሪያ የ2018 ዓ.ም የ7 ወሩን የቁልፍ እና የአብይት ተግባሮች አፈጻጸም ገመገመ።፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨

የካቲት 2018 ዓ.ም
ኮምቦልቻ

✍️በዉይይቱ የዞን ማኔጅመንት አባላት፤የወረዳ/ከተማ ገቢ ጽ/ቤትሀላፊዎች፤የገቢአሰባሰብ፤የደንበኞች አገልግሎት፤የከተሞች የግብር ትምህርትና ኮሚኒኬሽን ስራ ሂደት አስተባባሪዎች በተገኙበት የተካሄደ ሲሆን ፤

✍️የ7ወሩን አፈጻጸም በመምሪያው እቅድ ዝግጅት ክትትል ግምገማ ስራ ሂደት ባለሙያ በአቶ ሀቢብ አያሌዉ ቀርቧል።

✍️በበጀት አመቱ ዞኑ ከመደበኛና ከተማ አገልግሎት 4 ነጥብ 65 ቢሊየን ብር ገቢ ለመሰብሰብ አቅዶ በ7ወሩ ውስጥ 2 ነጥብ 2 ቢሊየን ብር በመሰብሰብ አፈፃጸሙ ከአመቱ 47 ነጥብ 41 በመቶ መሰብሰብ ተችሏል።

✍️አፈጻጸሙ ከአመቱም ሆነ ከ7ወሩ አኳያ ሲታይ በጣም ዝቅተኛ እና ዞኑን የማይመጥን እንደሆነም ነዉ የተገለጸዉ።

✍️ከነጉድለቱም ቢሆን አሁን ለደረስንበት ዉጤት የተሻለ አስተዋጽኦ ያበረከቱ ወረዳና ከተሞች 10ሲሆኑ እነሱም: ሀይቅ:ወረባቦ:ቃሉ :ኩታበር:ሀርቡ:ወግድ:ተሁለደሬ:
ደጎሎ:ደሴዙሪያ:እና አምባሰል ናቸዉ።

✍️በዝቅተኛና በጣም ዝቅተኛ አፈጻጸም ያስመዘገቡ 9ወረዳናከተምችደግሞ :ቦረና:ጊምባ:ለጋምቦ:ሳይንት:ጃማ:ከላላወረዳ:መሀል ሳይንት :ወገልጤናና ደላንታ ወረዳ ናቸዉ ።ቀሪዎች በመካከለኛ ደረጃ ላይ የሚታዩ እንደሆኑም ተጠቅሷል።

✍️️በዚህም ከወረዳና ከተማም 10 የሚሆኑት የተሻለ አፈፃፀም ያላቸው የገቢ ተቋማት ለመጣው ስኬት የተቋሙ አመራርና ፈጻሚ ከአጋና ባለድርሻ አካላት ጋር በቅንጅት በመስራታቸዉ እንደሆነም ትምህርት ተወስዶበታል።

✍️የተወሰኑትም ዝቅተኛ አፈጻጸም ካስመዘገቡት ወረዳና ከተሞች በዉይይቱ ላይ የወደቁበትን እና ቀጣይ መዉጫ መንገዳቸዉንም ከቀሪ ወራት አኳያ ያላቸዉን ጸጋና ተነሳሽነት በማመላከት በቁጭት እና ባጭር ጊዜ ለዉጥ ማንጣት እንደሚችሉም ቃል ገብተዋል ።

✍️በቀጣይም በገቢ ተቋሙ መሰራት ያለባቸውንና ለዉድቀታችን ምክናየት የተባሉትን ሀሳቦች እና መዉጫ መንገዶችን በማመላከት በሁሉም የስራ ዘርፍ የማኔጅመንት አባላት በዝርዝር አመላክተዋል።

✍️ ለዚህም አፈጻጸም መቀየር በክልሉ አዘጋጅነት የተሰጠዉ ስልጠና እንደ ትልቅ መስፈንጠሪያ አቅም እንደሚሆንም ጭምር በዉይይቱ ሂደት ለማሳየት ተሞክሯል።

✍️በመጨረሻም የዞኑ ገቢዎች መምሪያ ሀላፊ አቶ አህመድ ሙሀመድ በዋና ዋና ተግባራት ላይ ዝርዝር የስራ አቅጣጫ ተሰጥቷል። መምሪያ ሀላፈዉ አክለዉ እንዳሉት :

✍️ለስራችን ዉድቀት ዋነኛዉ ምክናየቶች በተለይ ደግሞ ከዞኑ አማካይ 47.41% አፈጻጸም በታች የሆኑት ወረዳና ከተሞች :
1.ለተቋም ግንባታ ስራ : ትኩረት አለመስጠት
2.የስራ ባህላችን ደካማ መሆኑ:
3.አሰራርን በተገቢዉ ማዘመን አለመቻላችን:
4.ጥብቅ የሆነ ህግ የማስከበር ስራ በመስራት ዉስንነት መኖሩና:
5. ተግባርን ተቀናጅቶ የመፈጸም/ የተጠያቂነት አስራርን ተግባራዊ አለማድረግ ችግሮች የገጠሙን በመሆኑ አሁን ላይ ከስልጠና ያገኘነዉን አቅም በመጠቀም በየተቋማችን ያልሰለጠነዉን ሀይል አሰልጥኖ አቅም በማድረግ በቀሪ ወራቶች የተቀናጀ ስምሪት በመስጠት አፈጻጸማችን በማሻሻል የህዝባችንን የልማት ፍላጎት መመለስ እንዳለብን ሀላፊዉ አብራርተዋል ።

✍️በመጨረሻም ከቀጣይ ስራዎቻችን አኳያ:
@በቀን እቅዱ ላይ ስምሪት መስጠት:
@ያሉንን ጸጋዎች በትክክል ለይቶ ርብርብ ማድረግ:
@በቀን እቅዱ መሰረት አፈጻጸሙን መገምገም :
@ህግ የማስከበር ስራዉን ተግባራዊ ማድረግ
@በተቋሙ ቴክኖሎጅን በማዘመን ግብሩን በሲስተም መሰብሰብ እና የአገልግሎት አሰጣጡን ፈጣንና ቀልጣፋ ማድረግ :
@የገቢ ተቋሙ አመራሮች እና ሰራተኞች በስነምግባር የተሻሉ እና ግብር ከፋዪና ማህበረሰቡ በተቋሙ ላይ እምነት እንዳጥል ማድረግ:ያስፈልጋልም ብለዋል።
@በጥቅል የገቢ ተቋሙ ለሃገር እድገት ወሳኝ የሆነ ግብርና ታክስ በመሰብሰብ ቀዳሚውን ሃላፊነት መውሰድ እንዳለባቸው እና የገቢ አቅምን አሟጦ መሰብሰብ እንደሚገባ አሳስሰበዉ ዉይይቱ ተጠናቋል።

ዘገባዉ :የዞኑ ግብር ትምህርትና ኮሚኒኬሽን ስራ ሂደት :

21/02/2026

"ገቢ ለልማት" ጋዜጣ ቁጥር 193 በቅርብ ቀን!

የካቲት 13/2018 ዓ.ም (የገቢዎች ሚኒስቴር)

ውድ የገቢ ለልማት ጋዜጣ አንባቢዎች፤ እንደተለመደው «ገቢ ለልማት» ጋዜጣ ቁጥር 193 ብዙ ጠቃሚ መልዕክቶችን ይዞ በቅርቡ ይወጣል፡፡

በመሆኑም፤ ጋዜጣውን በኢሜል ጭምር እያሰራጨን ስለሆነ በኢሜል እንዲደርሳችሁ የምትፈልጉ የኢሜል አድራሻችሁን በ0116178490 (2133) በመደወል ወይም አስተያየት መስጫው ላይ በማስቀመጥ እንዲደርሳችሁ ማድረግ ትችላላችሁ፡፡

Address

South Wollo Zone
Dessie

Website

Alerts

Be the first to know and let us send you an email when የደቡብ ወሎ ዞን ገቢዎች መምሪያ - SWZRs Office of Revenues posts news and promotions. Your email address will not be used for any other purpose, and you can unsubscribe at any time.

Share