Legehida Woreda Prosperity Party/ለገሂዳ ወረዳ ብልጽግና ፓርቲ/

  • Home
  • Ethiopia
  • Dessie
  • Legehida Woreda Prosperity Party/ለገሂዳ ወረዳ ብልጽግና ፓርቲ/

Legehida Woreda Prosperity Party/ለገሂዳ ወረዳ ብልጽግና ፓርቲ/ Peblic service

27/05/2026

ትናንት፣ ዛሬና ነገ....

በሀገራችን ውስጥ በሚዛን ሊያዝ የሚገባው ነገር በትናንት፣ በዛሬና በነገ መካከል ያለው ምልከታ ነው፡፡ ትናንትን ፈፅሞ የመቀደስም ሆነ ትናንትን ፈፅሞ የማርከስ ጉዞ ሀገርን ያለ ወረት ያስቀራል።

ዛሬንና ነገን ማቃለልም ሆነ ዛሬና ነገን የሁሉም ነገር መጀመሪያ ማድረግ ሀገርን ያለ መነሻ ያስቀራል፡፡ ብልፅግና ትናንት ከዛሬና ከነገ ጋር በሚዛን የሚታይበትን መርሕ ይከተላል፡፡

• ከትናንቱ መልካሙን መውሰድ፤ እንከኑን ማረም
• ዛሬን፣ በትናንት መሠረት ላይ ገንብቶ በሚገባ መጠቀም
• ለነገ ተግባብቶ ወረት ማቆየት

ትናንትን ከዛሬና ነገ ጋር በሚዛን ለማየት እንዲቻል፣ የትናንት ቁርሾዎችን የምናክምባቸው፣በትናንትጉዞ ላይ የምንግባባባቸው ፤ ነገን በጋራ የምንተልምባቸው መንገዶችን መከተል አለብን ብሎ ያምናል፡፡

እነዚህም፡-
👉በሰከነ ምክክር አዲስ ቃል ኪዳን ማሠር ፤

ጠንካራና ቅቡልነት ያለው ሀገረ መንግሥት በፅኑ መሠረት ላይ ለመገንባት፣ ሀገራዊ መግባባትን መፍጠር እንደሚያስፈልግ ፓርቲያችን በቀዳሚነት አስቀምጧል፡፡ለዘመናት በመሠረታዊ ሀገራዊ ጉዳይ እንኳን ያላግባቡን ጉዳዮች በሀገራዊ ምክክር ምላሽ እንዲያገኙ ቁርጠኛ አቋምም አለው። ፓርቲያችን ብሔራዊ መግባባት ለሀገረ መንግሥቱ ግንባታ የማዕዘን ድንጋይ እንደሆነ ያምናል።

የፖለቲካ ማኅበረሰቡ የትናንት ቅራኔዎችን በመግባባትና በዕውቅና፣ በዕርቅና በሽግግር ፍትሕ መፍታት እንዳለበት እናምናለን፡፡ ስለዚህም በስክነትና በዕውቀት፣ ሀገራዊ ምክክሩ እንዲሠምር ሕዝባችንና የፖለቲካ ልሂቃን አዎንታዊ ሀገራዊ ድርሻቸውን እንዲወጡ ጥሪ አናቀርባለን።

በዚህ የጸና እምነታችንና መሻታችን የተነሣ የኢትዮጵያ ሀገራዊ የምክክር ኮሚሽንን በማቋቋም ሂደት እንደ ፓርቲና እንደ መንግሥት የሚጠበቅብንን አድርገናል፡፡

የሕዝብ ተሳትፎን በማረጋገጥ፣ ለኮሚሽኑ ሥራ አስፈላጊ የሆኑትን የፋይናንስ፣ የሎጀስቲክስና የመረጃ አቅርቦቶችን ያለተዐቅቦ በማሟላት፣ እንዲሁም ነጻነቱን በማክበር ባለፈው ምርጫ ዘመን ቃል የገባንውን በተግባር ፈፅመናል።

በቀጣይ አምስት ዓመታትም፡-

በኢትዮጵያ ሀገራዊ የምክክር ኮሚሽን መሪነት በሂደት የሚደረስባቸው ውሳኔዎችና ምክረ ሐሳቦች ይኖራሉ ብለን ተስፋ እናደርጋለን፡፡

እነዚህን ውሳኔዎችና ምክረ ሐሳቦች ወስደን ለሕገ መንግሥት ማሻሻያዎች፣ ለፖለቲካ ሥርዓት ማሻሻያዎች፣ ለሰብአዊ መብቶች ማሻሻያዎች እና ለቀደሙ በደሎች የመፍትሔ መንገዶች አድርገን እንደ ፓርቲና መንግሥት ለመፈጸምና ለማስፈጸም እንሠራለን።

👉በሽግግር ፍትሕ መሥመር፤ ቁርሾን መሻር ፤

በኢትዮጵያ ለዘመናት የኖሩ በደሎች፣ ቁርሾዎችና የሰብአዊ መብት ጥሰቶች አሉ፡፡ እነዚህን በተመለከተ ፈውስ የሚሰጥ ፍትሕን እና ይቅርታን ለማረጋገጥ የሽግግር ፍትሕ እንደሚያስፈልገን ፓርቲያችን ያምናል። ይህንን መሠረት በማድረግም ባለፉት ዓመታት ሕጋዊና ተቋማዊ ሥራዎች ተጀምረዋል፡፡

በቀጣይ ዓመታትም፡-

ለተፈጸሙ በደሎች እና የሰብአዊ መብት ጥሰቶች በሽግግር ፍትሕ ማዕቀፍ የወንጀል ምርመራና ክስ፣ እውነትን የማፈላለግ እና ይፋ የማውጣት ተግባር፣ በቅድመ ሁኔታ ላይ የተመሠረተ ምሕረት፣ ግለሰባዊ እና ማኅበረሰባዊ ዕርቅ ለማስፈን እንሠራለን፡፡

ይህንንም ተግባራዊ ለማድረግ ሕጋዊና ባህላዊ መንገዶችን እንጠቀማለን፤ ማካካሻና ተቋማዊ ማሻሻያን ይተገበራል።በዚህም ተጎጂዎችን ማዕከል ያደረገ የሽግግር ፍትሕ እንደ ሀገር እንዲተገበር እንሠራለን።

የብሔራዊ መግባባት፣ የዕርቅና የፍትሕ ሂደት እንዲሠምር የሀገራትን ተሞክሮ ከሀገራዊ ነባራዊ ሁኔታ ጋር አስማምተን እንጠቀማለን። እንዲሁም ባሕላዊ የግጭት አፈታትና የዕርቀ ሰላም ሥርዓቶችን እንደየአካባቢው እንተገብራለን፡፡ ይህንንም በማድረግ ሀገራዊ አንድነታችንን እና ብሔራዊ መግባባታችንን እናጠናክራለን፡፡

የሽግግር ፍትሕ ሂደት ከተፅዕኖ እና ከፖለቲካዊ ጣልቃ ገብነት ነጻ እና ገለልተኛ ሆኖ እንዲከናወን እናደርጋለን፡፡ ተአማኒነቱን እና ቅቡልነቱን ለማረጋገጥ፣ ሐቅ አፈላላጊ ኮሚሽን፣ ልዩ ዐቃቤ ሕግና ልዩ ችሎት ይቋቋምለታል፡፡

በእነዚህ ተቋማት በሚመራ ምርመራና ዳኝነት አማካኝነት እንዲከናወን በማድረግ፣ የሽግግር ፍትሕ ያስቀመጣቸውን ብሔራዊ ግቦች እንዲመታ እናደርጋለን።

👉የተሐድሶ ፕሮግራም ፤

በተለያዩ አካባቢዎች ነፍጥ አንግተው ጫካ የገቡ አካላት ወደ ሰላም መንገድ እንዲመጡ ፓርቲያችን ሲሠራ ቆይቷል፡፡ በዚህ መንገድም በሺዎች የሚቆጠሩ ታጣቂዎች የሰላም አማራጭን ተቀብለው ገብተዋል።

እነዚህ ታጣቂዎች በተሐድሶ ፕሮግራም ውስጥ እንዲያልፉ ማድረግ ይገባናል፡፡ ታጣቂ ቡድኖች እንዲበተኑ፤ ታጣቂዎች ትጥቅ እንዲያወርዱ እና ወደ ሰላማዊው መንገድ እንዲቀላቀሉ ለማድረግ የቦታ፣ የገንዘብ፣ የቴክኒክ እና የሥነ ልቦና ዝግጅት ይፈልጋል፡፡

ለዚህ ታላቅ ተግባር የሚያስፈልገውን የሰው ኃይል፣ የበጀትና የቁሳቁስ ዝግጅት በማከናወን የተሐድሶን ፕሮግራም በተሟላ መልኩ ለማከናወንና የጸና ሰላምን ለመመሥረት ፓርቲያችን ይሠራል፡፡



#ኢትዮጵያንወደተምሳሌትሀገር
#ብልፅግናፓርቲንይምረጡ

የ1447ኛው ዓመተ ሂጅራ የኢድ አል አድሃ(አረፋ) በዓል በለገሂዳ ወረዳ ወይን አምባ ከተማ በድምቀት ተከበረ======    =======      =======በወይን አምባ ከተማ እና አካባቢው ...
27/05/2026

የ1447ኛው ዓመተ ሂጅራ የኢድ አል አድሃ(አረፋ) በዓል በለገሂዳ ወረዳ ወይን አምባ ከተማ በድምቀት ተከበረ
====== ======= =======
በወይን አምባ ከተማ እና አካባቢው ያለው ህዝበ ሙስሊም በከተማው ስታድየም በመገኘት በዓሉን አክብረዋል፡፡
በበዓሉ ላይም የለገሂዳ ወረዳ ምክትል አስተዳዳሪና የግብርና ጽ/ቤት ኃላፊ አቶ ተስፋዬ ከበደ የእንኳን አደረሳችሁ መልዕክት ያስተላለፉ ሲሆን፤ ሀገራችን ኢትዮጵያ በርካታ ብሔር ብሔረሰቦች፤ የተለያዩ እምነት ተከታዮች ተከባብረው፣ ተቻችለውና ተዋደው የሚኖሩባት የብዝሀነት ተምሳሌት መሆኗን ጠቅሰው ህዝበ ሙስሊሙ በዓሉን ሲያከብር የወትሮ አንድነቱን በመመለስ፣ የዕምነቱን እሴቶች በመጠበቅ፣ የሀገር ሰላም እንዲረጋገጥ በመስራት፣ የተቸገሩ ወገኖችን በመርዳት መሆን እንዳለበት አሳስበዋል፡፡
በመጠናቀቅ ላይ ለሚገኘው የፈትህ መስጂድ ግንባታ የገቢ ማሰባሰብ ተግባር ተከናውኗል፡፡ ግንባታው እንድጠናቀቅም ሁሉም ምዕመን የአቅሙን ድጋፍ እንዲያደርግ ተጠይቋል፡፡
የኢድ ሶላት ከተሰገደ በኋላ ህዝበ ሙስሊሙ በሰላም ወደየቤቱ ተመልሷል፡፡

26/05/2026
26/05/2026
26/05/2026
የደቡብ ወሎ ዞን ዋና አስተዳዳሪ አቶ አሊ መኮንን ለዒድ አል-አድሐ በዓል የእንኳን አደረሳችሁ መልዕክት አስተላለፉውድና የተከበራችሁ የደቡብ ወሎ ዞን እንዲሁም የመላው ሀገራችን የእስልምና እ...
26/05/2026

የደቡብ ወሎ ዞን ዋና አስተዳዳሪ አቶ አሊ መኮንን ለዒድ አል-አድሐ በዓል የእንኳን አደረሳችሁ መልዕክት አስተላለፉ

ውድና የተከበራችሁ የደቡብ ወሎ ዞን እንዲሁም የመላው ሀገራችን የእስልምና እምነት ተከታዮች፤

በመጀመሪያ ለ1447ኛው ለዒድ አል-አድሃ (የዓረፋ) በዓል እንኳን በሰላም አደረሳችሁ፤ አደረሰን።

የዓረፋ በዓል የታላቁ ነቢይ ኢብራሂም (ዐ.ሰ) ለአላህ የነበራቸውን ፍጹም ታዛዥነት፣ ታማኝነትና መስዋዕትነት የምናስብበት ታላቅ የሃይማኖት በዓል ነው። ይህ ዕለት የእምነቱን አስተምህሮ መሠረት በማድረግ፣ የአንድነትና የደግነት እሴቶቻችንን የምናድስበት ልዩ አጋጣሚ ነው።

የዒድ አል-አድሃ ዋናው ፍልስፍናና ማካፈልና መረዳዳት ነው። በዓሉን ስናከብር ያለው ለሌለው በማካፈል፣ የተቸገሩትን በመደገፍ እንዲሁም አቅመ ደካሞችንና ወገኖቻችንን በማስደሰት መሆን አለበት። የእርድ ሥጋን ለሦስት ከፍሎ ለቤተሰብ፣ ለዘመድና ለችግረኞች ማዳረስ የሚለው የሃይማኖቱ አስተምህሮ በተግባር የሚገለጸው፣ ማኅበራዊ ትስስራችንን ስናጠናክርና ማዕዳችንን አብረን ስንጋራ ነው። በመሆኑም በዞናችን የሚገኘው ሕዝበ ሙስሊም የተለመደውን የቸርነትና የደግነት ባህሉን በመጠቀም፣ በዚህ በዓል ማንም ሰው ሳይከፋ በደስታ እንዲያሳልፍ የበኩሉን የተለመደ አርአያነት እንዲያሳይ አሳስባለሁ።

የደቡብ ወሎ ሕዝብ የዘመናት አብሮነት፣ መቻቻልና የአንድነት ተምሳሌት ነው። ሕዝበ ሙስሊሙ እንደ እስካሁኑ ሁሉ አሁንም ከሌሎች የሃይማኖት ወንድሞቹና እህቶቹ ጋር በመሆን ለዞናችንም ሆነ ለሀገራችን ሰላም ዘብ የመቆም ኃላፊነቱን አጠናክሮ ሊቀጥል ይገባል። ሰላም የሁሉም ነገር መሠረት በመሆኑ፣ በበዓሉ ወቅትም ሆነ ከዚያ በኋላ ሰላማችንን በጋራ መጠበቅና ማልማት ታሪካዊ ግዴታችን ነው።

በድጋሚ ለደቡብ ወሎ ዞን ሕዝበ ሙስሊም በሙሉ እንኳን ለዓረፋ በዓል በሰላም አደረሳችሁ።

በዓሉ የፍቅር፣ የሰላም፣ የብልጽግና እና የመረዳዳት ይሆንልን ዘንድ እመኛለሁ!

ዒድ ሙባረክ!

አላህ ሀገራችንንና ሕዝባችንን ይባርክ!

አሊ መኮንን
የደቡብ ወሎ ዞን ዋና አስተዳዳሪ

የለገሂዳ ወረዳ ም/አስተዳዳሪና የግብርና ጽ/ቤት ኃላፊ አቶ ተስፋዬ ከበደ ለመላው የእስልምና እምነት ተከታዮች የኢድ አል-አድሃ (አረፋ) በዓል የእንኳን አደረሳችሁ መልዕክት አስተላለፉ🕌🕌🕌🕌...
26/05/2026

የለገሂዳ ወረዳ ም/አስተዳዳሪና የግብርና ጽ/ቤት ኃላፊ አቶ ተስፋዬ ከበደ ለመላው የእስልምና እምነት ተከታዮች የኢድ አል-አድሃ (አረፋ) በዓል የእንኳን አደረሳችሁ መልዕክት አስተላለፉ
🕌🕌🕌🕌🕌🕌🕌🕌🕌
የለገሂዳ ወረዳ ምክትል አስተዳዳሪና የግብርና ጽሕፈት ቤት ኃላፊ አቶ ተስፋዬ ከበደ ለመላው ሙስሊም ማህበረሰብ ለ1447ኛው የኢድ አል-አድሃ (አረፋ) በዓል የደስታና የሰላም ምኞታቸውን ገልጸዋል።
ምክትል አስተዳዳሪው ባስተላለፉት መልዕክት፤ ኢትዮጵያ የበርካታ ብሔር ብሔረሰቦች፣ የባህል፣ የቋንቋና የእምነት እሴቶች መገኛ መሆኗን ገልጸው፣ ይህ ልዩነት ውበት ሆኖ ማህበረሰቡ ለዘመናት ተከባብሮና ተፋቅሮ መኖሩን አስታውሰዋል።
አሁን ላይ እየተፈጠሩ ያሉ ልዩነቶችን በጥልቀት አጢኖ መመልከትና የወትሮ አንድነታችንን መመለስ ለነገ የማይባል ትልቅ የቤት ሥራችን ሊሆን ይገባል፤ ያሉት አቶ ተስፋዬ ሀገራችን በለውጥ ውስጥ የምትገኝ ቢሆንም፣ ይህንን እድገት ለማደናቀፍና የሀገርን ሰላም ወደኋላ ለመመለስ የጥፋት ኃይሎች ችግር መፍጠር ከጀመሩ አምስት ዓመታትን አስቆጥረዋል። ይህንን የሰላም እጦት ለማስተካከልና የጥፋት ኃይሎች ከድርጊታቸው እንዲታቀቡ የሃይማኖት አባቶችና ሙስሊሙ ማህበረሰብ ዛሬም እንደ ትናንቱ የበኩሉን ከፍተኛ አስተዋጽኦ ሊያበረክት ይገባል።
ሀገራችን በሰላም እጦት ፈተና ውስጥ ሆናም የ2018 ሀገራዊና ክልላዊ ምርጫን ለማከናወን በርካታ የቅድመ ዝግጅት ሥራዎች ተሠርተው በአሁኑ ወቅት በ11ኛው ሰዓት ላይ እንገኛለን። በመሆኑም ምርጫው ፍጹም ሰላማዊ ሆኖ እንዲጠናቀቅ ሙስሊሙ ማህበረሰብ ታሪካዊ ድርሻውን እንዲወጣ ጥሪ አቅርበዋል።
በአሉን ስናከብር ሃይማኖታዊ ሥርዓቱ በሚፈቅደው መሠረት የተቸገሩትን፣ የታረዙትንና የታመሙ ወገኖችን በመደገፍ፣ በመጠየቅና በመንከባከብ ሊሆን እንደሚገባ ምክትል አስተዳዳሪው አሳስበዋል።
✨ ኢድ ሙባረክ! ✨

የለገሂዳ ወረዳ የእስልምና ጉዳዮች ምክር ቤት ለመላው የእስልምና እምነት ተከታዮች ለ1447ኛው የኢድ አል-አድሃ (አረፋ) በዓል ያስተላለፈፉት የእንኳን አደረሳችሁ መልዕክት =====    ==...
26/05/2026

የለገሂዳ ወረዳ የእስልምና ጉዳዮች ምክር ቤት ለመላው የእስልምና እምነት ተከታዮች ለ1447ኛው የኢድ አል-አድሃ (አረፋ) በዓል ያስተላለፈፉት የእንኳን አደረሳችሁ መልዕክት
===== ====== ======
በደቡብ ወሎ ዞን በለገሂዳ ወረዳ የእስልምና ጉዳዮች ምክር ቤት ለመላው ሙስሊም ማህበረሰብ ለ1447ኛው የኢድ አል-አድሃ (አረፋ) በዓል የእንኳን አደረሳችሁ መልዕክት አስተላልፏል።
የምክር ቤቱ ፕሬዝዳንት ሸህ ዳውድ አህመድ ለአማኞቹ ባስተላለፉት የእንኳን አደረሳችሁ መልዕክት፤ ፈጣሪ በአንድነትና በሰላም ለዚህ ታላቅ በዓል ስላደረሰን ምስጋና ይገባው ካሉ በኋላ፣ በዓሉ የደስታ፣ የሰላምና የበረከት እንዲሆን ተመኝተዋል።
ፕሬዝዳንቱ በበዓሉ መልዕክታቸው እስልምና ያስተማረንን የትጋት፣ የታጋሽነት፣ የአንድነትና የርኅራኄ እሴቶችን በዚህ የበዓል ወቅት ይበልጥ ማጠናከር ይገባል፤ በዓሉን ስናከብር በተለይም ድሆችን፣ አቅመ ደካሞችንና የተጎዱ ወገኖችን በማሰብና ደስታን በመጋራት መሆን አለበት፤ በማህበረሰቡ ውስጥ ሰላምና መረጋጋት እንዲሰፍን አብዝቶ ዱዓ ማድረግ፣ ወንድማማችነትን ማጠናከር፣ ወጣቶችን ወደ መልካም አቅጣጫ መምራትና ከማንኛውም ግጭትና ከመጥፎ ባህሪ መራቅ ያስፈልጋል ብለዋል። በወረዳው የሚገኘው ሙስሊም ማህበረሰብ የኢድ ሶላትን በየአካባቢው በአንድ ቦታ ላይ በመሰባሰብ በታላቅ ድምቀት እንዲፈጽም ጥሪ አቅረበዋል።
ምክር ቤቱ መንግስት ለበዓሉ መሳካትና ለማህበረሰቡ እያደረገ ላለው ሁለንተናዊ ድጋፍ ከልብ የመነጨ ምስጋና ያቀረበ ሲሆን፣ የለገሂዳ ወረዳ ሙስሊም ማህበረሰብ ከተጀመሩ የልማትና የሰላም ስራዎች ጎን በተጠናከረ መልኩ እንደሚቆም አረጋግጧል።
በመጨረሻም ፕሬዝዳንቱ ባስተላለፉት ጥሪ፤ በሀገራችን ኢትዮጵያ በግንቦት ወር መጨረሻ ለ7ኛ ጊዜ የሚካሄደውን ሀገራዊ የመንግስት ምርጫ አስመልክቶ፣ ህዝበ ሙስሊሙ በምርጫው ላይ በንቃት በመሳተፍ የዜግነት አሻራውን እንዲያሳርፍ አሳስበዋል።
የለገሂዳ ወረዳ የእስልምና ጉዳዮች ምክር ቤት አመራሮችና አባላት ለመላው ህዝበ ሙስሊም በድጋሚ መልካም በዓል እንዲሆን መልካም ምኞቱን ገልጿል።
🎉 ኢድ ሙባረክ! 🎉

እንኳን ለ1447ኛው የዒድ አል አድሐ በዓል አደረሰን፣ አደረሳችሁ!ስለዒድ አል-አድሐ “ዐረፋ” በዓል ስናስብ ሦስት ነገሮች ቀድመው ይታወሱናል። መስዕዋትነት፣ መታዘዝ እና መተጋገዝ። አባት ል...
26/05/2026

እንኳን ለ1447ኛው የዒድ አል አድሐ በዓል አደረሰን፣ አደረሳችሁ!

ስለዒድ አል-አድሐ “ዐረፋ” በዓል ስናስብ ሦስት ነገሮች ቀድመው ይታወሱናል። መስዕዋትነት፣ መታዘዝ እና መተጋገዝ። አባት ልጁን ለመስዕዋት ያቀረበበት፤ ልጅ የአባቱን ትዕዛዝ የፈጸመበት፤ ሙስሊሞች የመተጋገዝን እሴት ለዓለም የገለጡበት በዓል ስለሆነ “ዐረፋ” በሕዝበ-ሙስሊሙ ዘንድ ትልቅ ትርጉም አለው።

እስማኤል ለነብዩ ኢብራሂም የመጀመሪያ እና ተወዳጅ ልጃቸው ነው። አላህ (ሱ.ወ.) ይሄን ተወዳጅና የመጀመሪያ ልጅ እንዲሠዉለት ሲጠይቃቸው ታዘዙ እንጂ ወደኋላ አላሉም። ለመታዘዝ የሞከሩት ነገሩ ቀላል ሆኖ አይደለም። ልጅን ያህል ነገር መስዕዋት ማድረግ ምኑ ይቀላል? የአባትነት ስሜት ይተናነቃል። የሰይጣን ሹክሹክታ ይፈታተናል። የቤተዘመድን ወቀሳ እና የጎረቤትን አስተያየት መቋቋምም ይከብዳል። ነብዩ ኢብራሒም፥ በዚህ ሁሉ አጣብቂኝ ውስጥ አንድ ሐቅ ተገልጦላቸዋል። ከራስ ስሜት፣ ከሰው ሐሜት እና ከወዳጅ ፍላጎት የሚልቅ ታላቅ ዓላማ እንዳለ አምነዋል። ስለዚህም በፈተና ውስጥ ጸንተው ቆሙ፤ ቆራጥነታቸውም በተግባር ታየ።

ሀገር የምትገነባው ከራስ ጥቅም በላይ በሚያስቡ እና ከግላዊ ፍላጎታቸው በላይ ለመፈጸም በቆረጡ ዜጎች ነው። የሚወዱትን ነገር እንኳን ሳይቀር ለመሠዋት ዝግጁ የሆኑ ዜጎች ሲበዙላት ሀገር ትበረታለች። እስማኤላቸውን ለመስጠት የማያመነቱ ዜጎች የሞሉባት ሀገር ጽኑ ናት።

የለመድናቸው፣ የምንወዳቸው፣ የራሳችን ገንዘብ ያደረግናቸው ብዙ ነገሮች ይኖራሉ። ከእነዚህ የሚበልጥ ዓላማ ግን አለ፤ እሱም “ሀገርነት እና ሉአላዊነት” ይሰኛል። ሀገርነት የሚገነባው ከመውሰድ ይልቅ በመስጠት ነው። ሉአላዊነት የሚጸናው በፈተና ሳይወድቁ በመቆም፤ በወጀብ ሳይናወጡ መጓዝ በመቻል ነው።

የእውነት ኢትዮጵያ ሲያልፍላት ማየት የምንሻ ከሆነ ምኞታችን በተግባር ይገለጥ። የሀገር ኩስመና ካሳሰበን ለግዝፈቷ እንድከም። ያጎበጣትን የድህነት ቋጥኝ ለመሸከም ትከሻችንን እናመቻች። ጎተራዋ እንዲሞላ እጃችን አፈር ይንካ። የጠየመ ገጽዋ እንዲፈካ በሥራ ሌት-ተቀን እንሰለፍ። የተቀማ ክብሯ እስኪመለስ ድርሻችንን እንወጣ። ሀገር መውደዳችን ከልብ ከሆነ መስዕዋት ለመሆን አናመንታ።

የዐረፋ በዓል የመታዘዝና የመስዕዋት ብቻ ሳይሆን የመደጋገፍና የመተጋገዝ በዓል ጭምር ነው። በዐረፋ ከሚከናወነው እርድ አንድ ሦስተኛው ለምስኪኖች እንዲሰጥ የእስልምና አስተምህሮ ያዛል። በዐረፋ ሕዝበ-ሙስሊሙ ደስታና ሐዘኑን እየተጋራ በዓሉን ያከብራል። የዐረፋ እለት አንድም ሰው ተከፍቶ አያሳልፍም፤ በዐረፋ ሰሞን ማንም ሰው ተርቦና ተጠምቶ አያድርም። በዓሉ ትርጉም የሚሰጠው ሕዝበ-ሙስሊሙ ያለውን ተካፍሎ ሲያከብረው ነው። ሰዎች አስቸጋሪ ሁኔታን የሚሻገሩበት መፍትሄው መተሳሰብና መተጋገዝ እንደሆነ ከዐረፋ እንማራለን። ሀገርም ከፈተናዎችዋ በላይ እንድትሆን እኒህ እሴቶች ወሳኝ ናቸው።

ዐረፋ ማኅበረሰባዊ በዓል የሚባለው ለዚህ ነው። ሰዎች በግላቸው የሚያከብሩት አይደለም። ቤተሰቡ፣ ጎረቤቱ፣ ሠፈሩ፣ ከተማው የሚያከብረው በዓል ነው። ያላቸውና የሌላቸው፤ የሚችሉና የማይችሉ፤ ታላላቆችና ታናናሾች፤ ባለ ሥልጣናትና ተራ ዜጎች፣ በአንድነት የሚያከብሩት በዓል ነው። ሰው የሚኖረው በቤቱ ውስጥ አይደለም። በማኅበረሰቡ ውስጥ ነው።

ማኅበረሰባዊ ትሥሥርና ትብብር ለዜጎች እና ለሀገር ደኅንነት ወሳኝ ናቸው። ማኅበረሰባዊ ትሥሥር ስለሌሎች እንድናስብ፣ ስለሌሎች እንድንሠራ እና ስለ ሌሎች ዋጋ እንድንከፍል ያደርገናል። ራሳችንን በሌሎች ጫማ ላይ አቁመን እንድናይ ያስችለናል። የሁላችንም ሰላም፣ የሁላችንም ደኅንነት እና የሁላችንም ጥቅም ካልተከበረ በቀር የግላችንን ብቻ ልናስከብር እንደማንችል ያስገነዝበናል። ስለዚህም ማኅበራዊ ግዴታን እንደ ዜግነት ግዴታ ወስደን እንድንሠራ ያደርገናል።

ምርጫ ማኅበራዊና ዜግነታዊ ግዴታዎችን ከምንወጣባቸው የዴሞክራሲ መገንቢያ መሳሪያዎች መካከል ዋነኛው ነው። ያለ ሕዝብ ተሳትፎ ዴሞክራሲ አይሳካም። ያለ ምርጫም የሕዝብ ተሳትፎ ምሉዕ አይሆንም። የዴሞክራሲያችን መሰረት ጥንካሬው የሚለካው በተሳትፎአችን መጠን ነው።

የዘንድሮ ሀገራዊ ምርጫ ሀገረ-መንግሥታዊ ሥርዓታችን የሚጠነክርበት መሰረት ነው። የዴሞክራሲ ልምምዳችን አንድ ደረጃ ከፍ የሚልበት፤ የቀጣይ ዓመታት የሀገራችንን እጣ-ፈንታ የምንበይንበት፤ ከምንም በላይ ብዝሃ-ድምጽ የሚሰማበት የሕግ መወሰኛ ምክርቤት የምንመሰርትበት ወሳኝ አጋጣሚ ነው። በመሆኑም በዓሉን ስናከብር ዜግነታዊ ግዴታችንን ለመወጣት ብቻ ሳይሆን በካርዳችን ዴሞክራሲያዊ መብታችንን ለማረጋገጥ እየተዘጋጀን እንዲሆን ጥሪዬን አቀርባለሁ።

በድጋሚ መልካም የዐረፋ በዓል እንዲሆን እመኛለሁ!
ዒድ ሙባረክ!!

ኢትዮጵያ በልጆቿ ጥረት ታፍራና ተከብራ ለዘላለም ትኑር!!
ፈጣሪ ኢትዮጵያና ሕዝቦቿን ይባርክ!
ግንቦት 18፣ 2018 ዓ.ም

Address

Dessie

Telephone

+251922940085

Website

Alerts

Be the first to know and let us send you an email when Legehida Woreda Prosperity Party/ለገሂዳ ወረዳ ብልጽግና ፓርቲ/ posts news and promotions. Your email address will not be used for any other purpose, and you can unsubscribe at any time.

Share