Farta Woreda Road And Transport Office

Farta Woreda Road And Transport Office መንገድ ለሁሉም !!!

17/07/2026
በደቡብ ጎንደር ዞን  በ2018 በፋርጣ ወረዳ አሰተዳደር ""ቤቴን በራሴ አቅም እገነባለሁ""  በሚል ኢንሸቲቭ  ከማህበረሰቡ በተሰበሰበ ገንዘብ  የሚገነባው የቡሮ ቀበሌ የአርሶ አደር ማሰልጠ...
17/07/2026

በደቡብ ጎንደር ዞን በ2018 በፋርጣ ወረዳ አሰተዳደር ""ቤቴን በራሴ አቅም እገነባለሁ"" በሚል ኢንሸቲቭ ከማህበረሰቡ በተሰበሰበ ገንዘብ የሚገነባው የቡሮ ቀበሌ የአርሶ አደር ማሰልጠኛ ተቋም ተጠናቆ ለአገልግሎት ክፍት መሆኑን ተገለፀ።

የተሻለ የግብርና ኤክሰቴሸን ለመሰራት አንዱ የተቋሙን ደረጃ ማሻሻል ሲሆን የወረዳ አሰተዳደር በመደበው መደበኛ በጀት ሳህርና ቀበሌ የተገነባ ሲሆን በወረዳው ማህበረሰብ በተሰበሰበ የህብረተሰብ ተሳትፎ በቡሮ ቀበሌ ወጣቶችን በማደራጀት በኢተርፕራይዝ የተገነባ FTC ነው።

በደቡብ ጎንደር ዞን የፋርጣ ወረዳ ብልጽግና ፓርቲ ቅርጫፍ ጽ/ቤት የፓርቲና የመንግስትን የሚዲያ ስራዎችን ግምገማ አካሄደ።‎‎የፋርጣ ወረዳ ብልጽግና ፓርቲ ቅርጫፍ ጽ/ቤት ኃላፊ አቶ አማረ ይ...
17/07/2026

በደቡብ ጎንደር ዞን የፋርጣ ወረዳ ብልጽግና ፓርቲ ቅርጫፍ ጽ/ቤት የፓርቲና የመንግስትን የሚዲያ ስራዎችን ግምገማ አካሄደ።

‎የፋርጣ ወረዳ ብልጽግና ፓርቲ ቅርጫፍ ጽ/ቤት ኃላፊ አቶ አማረ ይሁኔ እንደገለፁት ጠንካራ የሚዲያ ሠራዊት በመገንባት የህብረተሰቡንና የመንግስትን ግኑኝነት በማጠናከር ተጠቃሚነትን ማረጋገጥ ይገባል ብለዋል።

‎የፋርጣ ወረዳ ብልጽግና ፓርቲ ቅርጫፍ ጽ/ቤት የፖለቲካ ዘርፍ ኃላፊ አቶ ደሳለኝ ካሴ እንደገለፁት የመንግስትንና የፓርቲዉን ስራ በሚዲያዉ በማስተዋወቅ ዲጅታላይዝድ በማድረግ የነቃ ተሳትፎ በመስራት የሚዲያ ሠራዊቱን ማጠናከር ይገባል ብለዋል።

‎በግምገማዉም የተገኙ ተሳታፊዎች በበኩላቸዉ በሰጡት አስተያየት የሚዲያ ሠራዊት ማፍራት የሚቻለዉ ኃላፊዎችና ባለሙያዎች ተቀናጅተዉ ሲሰሩ በመሆኑ ግንባር ቀደም ሁነን የሚዲያዉን እንቅስቃሴ በማሳደግ ጠንክረን መስራት ይጠበቅብናል በማለት ገልፀዋል።

በደቡብ ጎንደር ዞን በፋርጣ ወረዳ አስተዳደር በሶራስ ቀበሌ የሶራስና ሲና ማርያም ቤተክርስቲያን አካባቢ ተወላጆች በጋራ በመሆን  ወረዳው ባዘጋጀው  የክረምት በጎ ፈቃድ አገልግሎት ለተማሪዎች...
17/07/2026

በደቡብ ጎንደር ዞን በፋርጣ ወረዳ አስተዳደር በሶራስ ቀበሌ የሶራስና ሲና ማርያም ቤተክርስቲያን አካባቢ ተወላጆች በጋራ በመሆን ወረዳው ባዘጋጀው የክረምት በጎ ፈቃድ አገልግሎት ለተማሪዎች ደብተርና እስክብሪቶ መግዣ የሚውል ብር 100,000.00 (አንድ መቶ ሺ ብር) ድጋፍ አድርገዋል ።

ከዚህ በፈትም በዚህ አመት የዚህ ቀበሌ ተዎላጆች የሀገር ውስጥና የውጭ በጎ ፍቃደኞችን በማስተባበር በቀበሊያቸው ከመንግስት ጋር በመቀናጀት መንገድ ያሰሩ መሆኑን አስታውሰው ዛሬ ደግሞ ይህንን ማድረጋቸው ለወረዳችን ልማት ትልቅ አቅምና ከፍተኛ አስተዋፅኦ እንደለው ገልፀዋል።

በመጨረሻም ይህን ድጋፍ ላስተባበሩ፣ድጋፉ ላይ ለተሳተፉ በጎ ፍቃደኞች የወረዳ አስተዳደሩ ድጋፍ በሚደረግላቸው የነገ ትውልድ ተረካቢ ተማሪዎች፣በአጠቃላይ በማህበረሰቡ እና በወረዳ አስተዳደሩ ስም ከፍተኛ ምስጋና አቅርበው ይህን በጎ ተግባር ሌሎች በጎ ፍቃደኞችም በአረያነት ወስደው ተግባራዊ እንዲያደርጉ ጥሪ አቅርበዋል ።

"በጎነት እና አብሮነት ለኢትዮጵያ ከፍታ!"

በደቡብ ጎንደር ዞን  አስተዳደር የፋርጣ ወረዳ ብልጽግና ፓርቲ ቅርጫፍ ጸ/ቤት የ2018 በጀት አመት የፖለቲካና የድርጅት ስራዎች እቅድ አፈፃፀም ግምገማ አካሄደ።‎‎የፋርጣ ወረዳ ዋና አስተዳ...
10/07/2026

በደቡብ ጎንደር ዞን አስተዳደር የፋርጣ ወረዳ ብልጽግና ፓርቲ ቅርጫፍ ጸ/ቤት የ2018 በጀት አመት የፖለቲካና የድርጅት ስራዎች እቅድ አፈፃፀም ግምገማ አካሄደ።

‎የፋርጣ ወረዳ ዋና አስተዳዳሪ አቶ ይርጋ ጌትነት በመክፈቻ ንግግራቸዉ እንደገለፁት በጀት ዓመቱ ድልን እያሳካን ዉጤትን እያስመሰከረነ በርካታ አስተሳሰቦች ወደ ጠራ አመለካከት ለማሻገር በተሰጡ ተደጋጋሚ ውይይቶች በርካታ ድሎች ያገኘንበት ዓመት ነው ብለዋል።

‎አቶ ይርጋ አያይዘዉም ብልፅግና ፓርቲ ያሰበውን በተግባር የሚያረጋግጥ፣ በጠንካራ አባላትና ሀገር ወዳድ ህዝቦች ፓርቲ ለመሆኑ በ7ኛው ሀገራዊ እና ክልላዊ ጠቅላላ ምርጫ ትልቅ ማሳያ መሆኑን አይተናል ብለዋል።

‎የፋርጣ ወረዳ ብልፅግና ፓርቲ ቅ/ጽ/ቤት ኃላፊ አቶ አማረ ይሁኔ በበጀት ዓመቱ የተከናወኑ ጠንካራ አፈፃፀሞችን የማስቀጠል፣ ችግሮችን የመቅረፍ፣ የቀጣይ አቅጣጫዎችን የማስቀመጥ ዓመታዊ ቆይታን የሚገልፅ በዝርዝር አቅርበዋል።

‎አቶ አማረ አያይዘዉም በበጀት ዓመቱ ያስመዘገብናቸው ውጤቶች ሃገራዊ ብልፅግናን ለማረጋገጥ እንደሆነ እና የዕቅድ ዘመኑ በችግር ውስጥም የታለፈ ቢሆንም የጠላትን ሴራ ያከሸፈበት አመት እንደሆነ ገልፀዋል።

‎የፋርጣ ወረዳ ብልፅግና ፓርቲ ቅርጫፍ ጽ/ቤት የፖለቲካ ዘርፍ ኃላፊ አቶ ደሳለኝ ካሴ እንደገለፁት ያለፈው በጀት ዓመት ፓርቲው እና ከህዝቡ ጋር በመናበብ በርካታ ተግባራትን የተከናወኑበት በጀት ዓመት እንደነበረ ተናግረዋል። በመሆኑም በቀጣይ ዓመት ለምንፈፅማቸው የድርጅትና የመንግስት ተግባራት ከአባላት ቁርጠኝነት ይጠይቃል ብለዋል።

‎የፋርጣ ወረዳ ዋና አስተዳዳሪ አቶ ይርጋ ጌትነት በማጠቃለያዉ እንደገለፁት በበጀት ዓመቱ ለሀገርና ለህዝብ ሲባል የፀጥታ መዋቅሩ መስዋዕትን የከፈልንበት ቢሆንም የሀገራችን ሁለንተናዊ አንድነት ለማረጋገጥና ሀገርን ለትውልድ ለማስተላለፍ ከህዝባችን ጋር በመወያየት ሰፊ ስራ መስራት ይጠበቅብናል ብለዋል።

‎ተሳታፊዎችም በበኩላቸዉ በሰጡት አስተያየት በዓመታዊ ዕቀድ አፈፃፀሙ በርካታ የፖለቲካ ስራ በመናበብ ተሰርቷል። ስለዚህ ለሰላም ሁላችንም የድርሻችን እንወጣለን ብለዋል።

‎በመጨረሻም በበጀት ዓመቱ ጥሩ አፈፃፀም ለነበራቸው የህብረት አደረጃጀቶችና አባላት የእውቅና እና ሽልማት ተበርክቶላቸዋል።


~•~•

የፋርጣ ወረዳ ብልጽግና ፓርቲ ቅርጫፍ ጸ/ቤት  በበጀት ዓመቱ ጥሩ አፈፃፀም ለነበራቸው የህብረት አደረጃጀቶችና አባላት እውቅና እና ሽልማት   በፎቶ‎
10/07/2026

የፋርጣ ወረዳ ብልጽግና ፓርቲ ቅርጫፍ ጸ/ቤት በበጀት ዓመቱ ጥሩ አፈፃፀም ለነበራቸው የህብረት አደረጃጀቶችና አባላት እውቅና እና ሽልማት በፎቶ

27/06/2026

Address

Ethiopia, Amhara
Debre Tabor

Website

Alerts

Be the first to know and let us send you an email when Farta Woreda Road And Transport Office posts news and promotions. Your email address will not be used for any other purpose, and you can unsubscribe at any time.

Shortcuts

Share