Andabet Woreda Culture and Tourism Office

Andabet Woreda Culture and Tourism Office Contact information, map and directions, contact form, opening hours, services, ratings, photos, videos and announcements from Andabet Woreda Culture and Tourism Office, Government Organization, Debre Tabor.

ይካቲት 23/2015 ዓ.ምበአንዳቤ ወረዳ የ127ኛው የአድዋ የድል በዓል በደመቀ ሁኔታ ተከብሮ ዋለበደቡብ ጎንደር ዞን በአንዳቤ ወረዳ የ127ኛው የአድዋ የድል በዓል "አድዋ የጀግንነት፣ የአ...
03/03/2023

ይካቲት 23/2015 ዓ.ም

በአንዳቤ ወረዳ የ127ኛው የአድዋ የድል በዓል በደመቀ ሁኔታ ተከብሮ ዋለ

በደቡብ ጎንደር ዞን በአንዳቤ ወረዳ የ127ኛው የአድዋ የድል በዓል "አድዋ የጀግንነት፣ የአንድነትና የነፃነት ቀን!" በሚል መሪቃል በደመቀ ሁኔታ ተከብሮ ውሏል። በበዓሉም የተለያዩ የወረዳችን ማህበረሰብ፣የአባት አርበኞች፣ የሀይማኖት አባቶች፣ የጸጥታ አካላት እንዲሁም መምህራንና ተማሪዋች የተገኙ ሲሆን በለተያዩ መነባንብ፣ ሽለላ፣ ድራማና በልዩልዩ ዝግጅቶች ተከብሮ ውሏል። በውይይቱም የአድዋ በዓል ምንነትና ጠቀሜታው:የንባብ ባህልን ማሳደግና የአፍመፍቻ ቀቋንቋ በዓልን ማክበርና መናገር የሚል ሰነድ በወረዳው ባህልና ቱሪዝም ጽ/ቤት ኃላፊ በአቶ ያለው አመራ ቀርቦ ውይይት የተደረገ ሲሆን የቀደሙት አባቶቻችን በመስዋትነት ነፃነቷን ጠብቀው የቆዩንን ከእነክብሯና ነፃነቷ ተጠብቃ ለቀጣዩ ትውልድ ማስረከብ የሁሉም ሀላፊነት በመሆኑ ታሪካችንና ቅርሳችን እንዲሁም ባህላዊ ትውፊታችንን በመጠበቅ በ127ኛው የአድዋ የድል በዓል ኢትየጵያዊያኖች ፋሺስት ኢጣሊያንን ድል ሲያደርጉ በአለም ህዝብ ዘንድ የጥቁሮች አፍሪካውያን ድል አድራጊነት የነፃነት ጮራ ያበሰረ ሲሆን ለኢትዮጵያውያን የህብረብሄራዊ አንድነትና በአለም ዘንድ ከፍ ብላ እንድትታይና አዲስ ታሪክ የተፃፈበት ሆኖ አልፏል። በፋሺስት ኢጣሊያን ወረራ ወቅት የሐይማኖት አባቶች ከፈተኛ ድርሻ የወሰዱ ሲሆን የኢትዮጵያዊን አርበኞች፣ ወጣቶችና ሴቶች ለሀገራቸው ሲሉ እንዳሁኑ ዘመናዊ መሳሪያ ሳይኖር በጦር በጎራዴ ትልቅ መስዋት በመክፈል ተፋልመው ሀገራቸውን ነፃ አውጥተዋል።
የኢትዮያን ጠላቶች አሁንም ገና ያልጠፉ ስለሆነ ከአባቶቻችን ታሪክ በመማር ኢትዮጵያን ማስከበርና ታሪካችንና ባህላችን አስጠብቀን ለቀጣይ ትውልድ ማስተላለፍ )በሚያስችል ሁኔታ 127ኛው የአዋድል የድል በዓል በደመቀ ሁኔታ ተከብሮ ውሏል

"አድዋ የኢትዮጵያውያን ህብረት የአፍሪካ የነፃነት ጮራ!!!"

የአንዳቤት ወረዳ ባህልና ቱሪዝም ጽ/ቤት

02/03/2023
ይካቲት 5/2015 ዓ.ምበአንዳቤት ከተማ የቅዱስ ገብርኤል ህንፃ ቤተክርስቲያን ተጠናቆ ተመረቀበኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተክርስቲያን በደቡብ ጎንደር ዞን ሀገረ ስብከት በአንዳቤት ከተማ ...
12/02/2023

ይካቲት 5/2015 ዓ.ም

በአንዳቤት ከተማ የቅዱስ ገብርኤል ህንፃ ቤተክርስቲያን ተጠናቆ ተመረቀ

በኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተክርስቲያን በደቡብ ጎንደር ዞን ሀገረ ስብከት በአንዳቤት ከተማ የቅዱስ ገብርኤል ህንፃ ቤተክርስቲያን ተጠናቆ ብጹህ አቩነ እንድሪያስ የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተክርስቲያን የሊቃውንት ጉባኤ ሰብሳቢ፣የሀገረስብከት ሀላፊዎች፣ ከተለያየ ቦታ የመጡ ሊቃውንተ ቤተክርስቲያንና ልዩልዩ እንግዶችና ምዕመንና ምዕመናት በተገኙበት የቅዱስ ገብርኤል ህንፃ ቤተክርስቲያን ተጠናቆ በሀይማኖታዊ ስርዓት በዝማሬ፣በቅኔና በስብከተ ወንጌል ክዋኔ በዛሬውለት በደመቀ ሁኔታ ተመርቋል።
የዚህ ህንጻ ቤተክርስቲያን ምረቃም ለየት የሚያደርገው ቤተክርስቲያኗ በገጠማት ፈተና ሱባኤ ተይዞ በተወሰነ መልኩ ጥያቄዋ የተመለሰበት ቀን ነው በመሆኑም እንደስከአሁ አንድነታችን አስጠብቀን ቅርሶችንና ትውፊቶችን ጠብቀን ለትውልድ እንድናስተላልፍ በማለት ለዚህ ህንጻ ቤተክርስቲያን አስተዋፅኦ ያደረጋችሁ ሁሉ እንኳን ደስ አላችሁ።

የአንዳቤት ወረዳ ባህልና ቱሪዝም ጽ/ቤት

ጥር 25/5/2015.ዓ.ምበደቡብ ጎንደር ዞን ሀገረ ስብከት በመካነ-ኢየሱስ ከተማ የ ቅዱስ መርቆርዮስ አመታዊ የንግስ በዓል ከክልልና ከዞን ያሉ ከፍተኛ አመራሮች፣የአጎራባች ወረዳ የመንግስት...
02/02/2023

ጥር 25/5/2015.ዓ.ም

በደቡብ ጎንደር ዞን ሀገረ ስብከት በመካነ-ኢየሱስ ከተማ የ ቅዱስ መርቆርዮስ አመታዊ የንግስ በዓል ከክልልና ከዞን ያሉ ከፍተኛ አመራሮች፣የአጎራባች ወረዳ የመንግስት የስራ ኃላፊዋችና ተወላጆች፣ ብጹህ አቡነ እንድሪያስ፣ ከተለያየ ቦታ በመጡ ሊቃውንተ ቤተክርስቲያን እና ምዕመንና ምዕመናት እንዲሁም ልዩልዩ እንግዶች በተገኙበት ሃይማኖታዊ ስርዓቱንና ትውፊቱን በጠበቀ መልኩ ያለምንም የፀጥታ ችግር በተለያዩ ዝማሬዎችና ጨዋታዎች እንዲሁም የፈረስ ጉግስ ጨዋታዎችን በመከወን የቅዱስ መርቆርዮስ አመታዊ የንግስ በዓል በደመቀ ሁኔታ ተከብሮ ውሏል።

ይህንን በዓል በጥሩ ሁኔታ ለማክበር አስተዋፅኦ ላደረጋችሁ ሁሉ ቤተክርስቲያኗ ምስጋና ታቀርባለች!!!

የአንዳቤት ወረዳ ባህልና ቱሪዝም ጽ/ቤት

ጥር 21/5/2015.ዓ.ምበደቡብ ጎንደር ዞን ሀገረ ስብከት በአንዳቤት ወረዳ በአንዳቤት ከተማ የደብረ ሐይል ቅዱስ ኡራኤል አመታዊ የንግስ በዓል በዛሬው እለትም ታቦተህጉ ወደ ባህረ ጥምቀቱ ...
29/01/2023

ጥር 21/5/2015.ዓ.ም

በደቡብ ጎንደር ዞን ሀገረ ስብከት በአንዳቤት ወረዳ በአንዳቤት ከተማ የደብረ ሐይል ቅዱስ ኡራኤል አመታዊ የንግስ በዓል በዛሬው እለትም ታቦተህጉ ወደ ባህረ ጥምቀቱ በአማረ መልኩ ወርዷል ስለሆነም በ22/5/2015 ዓ.ም የንግስ በዓሉ በደመቀ ሁኔታ ይከበራል ስለዚህ ሁሉም ኦርቶዶክሳዊያን እንዲገኙና በዓሉን እንዲያከብሩ ሲሉ የደብሩ አስተዳዳሪዎች መልዕክት አስተላልፈዋል።

የአንዳቤት ወረዳ ባህልና ቱሪዝም ጽ/ቤት

ጥር 18/5/2015.ዓ.ምበደቡብ ጎንደር ዞን ሀገረ ስብከት በአንዳቤት ወረዳ በስሜት ሾላየ ቀበሌ የሰሚ ቅዱስ ጊዮርጊስ አመታዊ የንግስ በዓል  ከተለያየ ቦታ በመጡ ሊቃውንተ ቤተክርስቲያን እ...
26/01/2023

ጥር 18/5/2015.ዓ.ም

በደቡብ ጎንደር ዞን ሀገረ ስብከት በአንዳቤት ወረዳ በስሜት ሾላየ ቀበሌ የሰሚ ቅዱስ ጊዮርጊስ አመታዊ የንግስ በዓል ከተለያየ ቦታ በመጡ ሊቃውንተ ቤተክርስቲያን እና ምዕመንና ምዕመናት በተገኙበት ሃይማኖታዊ ስርዓቱንና ትውፊቱን በጠበቀ መልኩ ያለምንም የፀጥታ ችግር በተለያዩ ዝማሬዎችና ጨዋታዎች በመከወን በደመቀ ሁኔታ ተከብሮ ውሏል።

የከርሞ ሰው ይበለን!!!

የአንዳቤት ወረዳ ባህልና ቱሪዝም ጽ/ቤት

ጥር 17/5/2015.ዓ.ምበደቡብ ጎንደር ዞን ሀገረ ስብከት በአንዳቤት ወረዳ በስሜት ሾላየ ቀበሌ የሰሚ ቅዱስ ጊዮርጊስ አመታዊ የንግስ በዓል ከድራሩ ጀምሮ በደመቀሁኔታ እየተከበረ ሲሆን ታቦ...
25/01/2023

ጥር 17/5/2015.ዓ.ም

በደቡብ ጎንደር ዞን ሀገረ ስብከት በአንዳቤት ወረዳ በስሜት ሾላየ ቀበሌ የሰሚ ቅዱስ ጊዮርጊስ አመታዊ የንግስ በዓል ከድራሩ ጀምሮ በደመቀሁኔታ እየተከበረ ሲሆን ታቦተ ህጉም ወደ ማደሪያ ቦታው በሰላም ወረዷል።
ስለሆነም በነገው እለት ለሚከበረው የሰሚ ቅዱስ ጊዮርጊስ የንግስ በዓል በተለየ ሁኔታ ስለሚከበር ማንኛውም ኦርቶዶክሳዊያን መምጣት የሚችል በዓሉን እንዲያከብር የቤተክርስቲያንኒቱ አስተዳዳሪዎች መልዕክታቸውን አስተላልፈዋል።

የአንዳቤት ወረዳ ባህልና ቱሪዝም ጽ/ቤት

ጥር 11/2015 ዓ.ም    እንኳን ለብርሃነ ጥምቀቱ በሰላም አደረሳችሁ!!  ለመላው የክርስትና እምነት ተከታዮች እንኳን ለጌታችንና ለመድሃኒታችን ለኢየሱስ ክርስቶስ የጥምቀት በዓል በሰላም ...
18/01/2023

ጥር 11/2015 ዓ.ም

እንኳን ለብርሃነ ጥምቀቱ በሰላም አደረሳችሁ!!

ለመላው የክርስትና እምነት ተከታዮች እንኳን ለጌታችንና ለመድሃኒታችን ለኢየሱስ ክርስቶስ የጥምቀት በዓል በሰላም አደረሳችሁ እያለ የአንዳቤት ወረዳ የባህልና ቱሪዝም ጽ/ቤት መልካም ምኞቱን ይገልፃል።
የጌታችንና የመድሃኒታችን የኢየሱስ ክርስቶስ የጥምቀት በዓል ከማይዳሰሱ ቅርሶች አንዱ ሲሆን በየአመቱ በደመቀ ሁኔታ በመላው ኦርቶዶክስ ተዋህዶ እምነት ተከታዮች ጥር 11 በድምቀት ይከበራል።
በመሆኑም የአንዳቤት ወረዳ የባህልና ቱሪዝም ጽ/ቤት ኃላፊ አቶ ያለው አመራ ለመላው የክርስትና እምነት ተከታዮች እንኳን ለብርሃነ ጥምቀቱ በሰላም አደረሳችሁ በማለት የዘንድሮው በዓል ለየት የሚያደርገው ያልፋሉ ያልተባሉ ችግሮች ከሞላጎደል አልፈው ለዚህቀን ደርሰናል። ስለሆነም ይህ የጥምቀት በዓል ጌትታችንና መድሀኒታችን ብርሀነ መለኮቱን የገለጸበትና አንድነቱንና ሶስትነቱን ያሳየበት በመሆኑ በሁሉም አካባቢ በድምቀት የሚከበር ታላቅ በዓል ነው በማለት በዓሉ የሰላም፣የጤና የፍቅር በዓል ይሁንላችሁ ይሁንልን ሲሉ መልእክታቸውን አስተላልፈዋል። በአሉንም ስናከብር ኢትዮጵያዊ ባህላችንና አለባበሳችን እንዲሁም ሃይማኖታዊ አስተምሮቱን በጠበቀ መልኩ ያለው ለሌለው በማካፈል፣ በመረዳዳትና በመደጋገፍ ሊሆን እንደሚገባ በመጠቆም በዓሉንም ስናከብር አካባቢያችንና ቤታችንን በንቃት መጠበቅና መጠንቀቅ አለብን ሲሉ መልእክታቸውን አስተላልፈዋል።

መልካም የጥምቀት በዓል!!!

የአንዳቤት ወረዳ የባህልና ቱሪዝም ጽ/ቤት

ጥር 8/5/2015 ዓ.ምየጥምቀትን በዓል ትውፊቱንና ስርዓቱን ጠብቆ እንዲከበር ለማድረግ ከባለድርሻ አካላት ጋር የምክክር መድረክ ተካሄደበደቡብ ጎንደር ዞን በአንዳቤት ወረዳ የአንዳቤት ወረዳ...
16/01/2023

ጥር 8/5/2015 ዓ.ም
የጥምቀትን በዓል ትውፊቱንና ስርዓቱን ጠብቆ እንዲከበር ለማድረግ ከባለድርሻ አካላት ጋር የምክክር መድረክ ተካሄደ

በደቡብ ጎንደር ዞን በአንዳቤት ወረዳ የአንዳቤት ወረዳ ባህልና ቱሪዝም ጽ/ቤት በአንዳቤት ከተማ የጥምቀትን በዓል ትውፊቱንና ስርዓቱን ጠብቆ ያለምንም የፀጥታ ችግር በድምቀትና በስርዓት እንዲከበር ለማድረግ ከባለድርሻ አካላት ጋር የምክክር መድረክ ተካሄደ። በውይይቱም የወረዳው ዋና አስተዳዳሪ አቶክብሮም አለምነውና የባህልና ቱሪዝም ጽ/ቤት ኃላፊና ባለሙያወች፣የቤተክህነት ኃላፊዎችና የሐይማኖት መሪዎች፣ የከተማ ልማትና የመዘጋጃ ኃላፊዎችእና የጸጥታ አካላት እንዲሁም የናታኔምና የቅዱስ ጊዮርጊስ የምንጣፍ አንጣፊ ማህበር በተገኙበት የጥምቀትን በዓል ትውፊቱንና ስርዓቱን ጠብቆ እንዲከበር ለማድረግ የጋራ የምክክር መድረክ አካሂዷል። በዚህም ውይይት የነበሩ ጥንካሬዎችንና ድክመቶችን በመገምገም ለቀጣይም ይህን በዓል በድምቀት ለማክበር ሁሉም አጋር አካላት የየድርሻውን እንዲወስድ የጋራ አቅጣጫ ተቀምጧል።

የአንዳቤት ወረዳ ባህልና ቱሪዝም ጽ/ቤት

ታህሳስ 28/2015 ዓ.ም    እንኳን ለብርሃነ ልደቱ በሰላም አደረሳችሁ!!  ለመላው የክርስትና እምነት ተከታዮች እንኳን ለጌታችንና ለመድሃኒታችን ለኢየሱስ ክርስቶስ የልደት በአል በሰላም ...
06/01/2023

ታህሳስ 28/2015 ዓ.ም

እንኳን ለብርሃነ ልደቱ በሰላም አደረሳችሁ!!

ለመላው የክርስትና እምነት ተከታዮች እንኳን ለጌታችንና ለመድሃኒታችን ለኢየሱስ ክርስቶስ የልደት በአል በሰላም አደረሳችሁ እያለ የአንዳቤት ወረዳ ባህልና ቱሪዝም ጽ/ቤት መልካም ምኞቱን ይገልፃል።
የጌታችንና የመድሃኒታችን የኢየሱስ ክርስቶስ የልደት በአል በየአመቱ ታህሳስ 28 እና 29 ቀን በመላው የኦርቶዶክስ ተዋህዶ እምነት ተከታዮች በድምቀት ይከበራል።
በመሆኑም የአንዳቤት ወረዳ ባህልና ቱሪዝም ጽ/ቤት ሃላፊ አቶ ያለው አመራ ለመላው የክርስትና እምነት ተከታዮች እንኳን ለብርሃነ ልደቱ በሰላም አደረሳችሁ በማለት በአሉ የጤና፣የፍቅርና የሰላም ይሁንላችሁ ይሁንልን ሲሉ መልእክታቸውን አስተላልፈዋል።
በአሉንም ስናከብር ሃገራችን ያለችበትን ነባራዊ ሁኔታ ግምት ውስጥ በማስገባት ኢትዮጵያዊ ባህላችንና ሃይማኖታዊ አስተምሮቱን በጠበቀ መልኩ ያለው ለሌለው በማካፈል፣ በመረዳዳትና በመደጋገፍ ሊሆን እንደሚገባ በመጠቆም ሃገራችን ባጋጠማት ችግር በጦርነት ምክንያት አካባቢያቸው ለቀው ተፈናቅለው በችግር ላይ የሚገኙ የህብረተሰብ ክፍሎችንና የሃገርን ሉአላዊነት ለማስከበር ግንባር ላይ የሚገኙ የፀጥታ አካላትን በማሰብ እንዲሁም ሳንዘናጋ ከወትሮው በተለየ አካባቢያችንን በንቃት መጠበቅና መጠንቀቅ አለብን ሲሉ አሳስበዋል።

መልካም የልደት በዓል!!!
የአንዳቤት ወረዳ ባህልና ቱሪዝም ጽ/ቤት

ታህሳስ 27/2015 ዓ.ምበአንዳቤት ከተማ ለአገልግሎት ሰጭ ተቋማት ስልጠና ተሰጠበደቡብ ጎንደር ዞን በአንዳቤት ወረዳ በአንዳቤት ከተማ ለሚገኙ የሆቴልና የምግብ ቤት ባለቤቶች እንዲሁም ከቁር...
05/01/2023

ታህሳስ 27/2015 ዓ.ም

በአንዳቤት ከተማ ለአገልግሎት ሰጭ ተቋማት ስልጠና ተሰጠ

በደቡብ ጎንደር ዞን በአንዳቤት ወረዳ በአንዳቤት ከተማ ለሚገኙ የሆቴልና የምግብ ቤት ባለቤቶች እንዲሁም ከቁርስ ቤቶችና ከወረዳው ግብረ ኃይል ኮሚቴዎች በተገኙበት በ26/4/2015 ዓ.ም ለአገልግሎት ሰጭ ተቋማት ስለ አሰራሩና መመሪያ ዙሪያ ስልጠና ተሰጥቷል። በዚህ ውይይትም ወረዳው የቱሪስት መዳረሻ ሲሆን ነገር ግን ጎብኝዎች ሲመጡ የሆቴልና የቁርስቤቶች የአገልግሎት አሰጣጥና የሽንት ቤት ፅዳት ችግር እየገጠመ ስለሆነ ይህንን ለማስተካከል ያለመ የስልጠናና መድረክ ተካሂዷል።
ለቀጣይም ይህ ግብረ ሀይል እየተንቀሳቀሰ ችግሮችን እየለየ የሚያስተካክል ሲሆን በማያስተካክል የአገልግሎት ዘርፍ ላይ እርምጃ የሚወስድ ይሆናል።
ይህንን ውይይት እንዲሳካ ለማድረግ እና የከተማውን ውበት ለማስጠበቅ እገዛ ያደረጉ የአንዳቤት ከተማ መሪ መዘጋጃ ሲሆን በተቋሙ ስም ላቅ ያለ ምስጋናችን እናቀርባለን።

የአንዳቤት ወረዳ ባህልና ቱሪዝም ጽ/ቤት

Address

Debre Tabor

Website

Alerts

Be the first to know and let us send you an email when Andabet Woreda Culture and Tourism Office posts news and promotions. Your email address will not be used for any other purpose, and you can unsubscribe at any time.

Share