12/09/2022
ይህ ተአምር ሳታነቡና ሼር ሳታደርጉ አትለፉ
የፃድቃኔዋ ማርያም ተዓምር ስሜ ወለተ ማርያም ይባላል በአዲስ አበባ ልዩ ስሙ ቄራ አባባቢ ነው የተወለድኩት በ12 ዓመቴ በአፄ ዘርዓ ያዕቆብ 1ኛ ደረጃ ትምህርት ቤት የአራተኛ ክፍል ትምህርቴን እየተከታተልኩ የጌታችን የኢየሱስ ክርስቶስ የልደት በዓል/ገና/ ካሳለፍኩኝ በኋላ በማይታወቅ ሁኔታ ድንገት ሁለቱም ዓይኖቼ ማየት ተሳናቸው። ቤተሰቦቼ አዲስ አበባ ውስጥ አሉ ከሚባሉ የዓይን እስፔሻሊስት ሀኪሞች ዘንድ ገንዘባቸውን ጨረሱ እንጂ መፍትሄ አላገኙም ነበር። እኔ ማየት ተስኖኝ ቤተሰቦቼ ዙሪያው ገደል በሆነባቸውና ግራ በተጋባንበት ወቅት
የእመቤታችን አማላጅነት ከጭንቅ ታደገን። ቤተሰቦቼ በተፈጠረብኝ ነገር በጣም ተረብሸው ነበር። እኔም ዓይኔ ጠፍቶ እንደት እንደምሆን ተጨንቄና አዝኜ ነበር። ሌትም ቀንም አለቅስ ነበር። በሀኪም መፍትሄ ያጡት ቤተሰቦቼ የተለያዩ የጠበል ቦታዎች እየወሰዱኝ እጠመቅ ነበር። ለውጥ ግን ማምጣት አልቻልኩም። በእንደዚህ ዓይነት ሁኔታ ላይ እያለሁ አባቴ ለታናሽ ወንድሙ ለአጎቴ ስለእኔ ሁኔታ በጭንቅ ሲነግረው አጎቴ ባጋጠመኝ አደጋ አዝኖ ጊዜ ሳያጠፋ የአባቴ እህት ከሆነችው አክስቴ ጋር ሆነው በታህሳስ 21 ወደ ፃድቃኔ ማርያም ገዳም ይዘውኝ መጡ። በሰው እየተመራሁ ወደ ገዳሙ ምሽት ላይ ደረስን።
ተዓምረ ማርያም ሰምተን ኪዳን አድርሰን ከጨረስን በኋላ ሁሉም ምእመናን እንደሚያደርገው ወደ ጠበል ቦታ በቤተሰቦቼ አማካኝነት ሄጄ ተጠመኩኝ። በወቅቱ ጠበሉ ገና ሰውነቴ ላይ ሲያርፍ ተሰማኝ ሰላምና የመረጋጋት ስሜት መቼም አረሳውም። ተጠምቄ ከወጣሁ በኋላ እምነቱን ዓይኔን ተቀባብቼና ጠበሉን ጠጥቼ ወደ ማረፊያ ቦታችን ሄድን። ትንሽ አረፍ እንዳልኩ ዓይኔን በጣም አሳከከኝ የሆነ ነገር ዓይን ወደ ውጪ ሲገፈው ታወቀኝ። በቃ ዓይ ተጎልጉሎ የወጣ መስሎኝ ተረበሽኩ አለቀስኩ ሁኔታየን ያስተዋለች አክስቴ ጊዜ ሳታጠፋ ወደ ዋሻ ይዛኝ ገባች። ይሁን እንጂ ፋታ ከማግኘት ይልቅ ዓይኔን በጣም ይቆረቁረኝ ጀመረ። የሚቆረቁረኝ ነገር ምን እንደሆነ አክስቴ ዓይኔን ገልጣ ብታይልኝም ምንም ነገር አላገኘችም።
በእንደዚህ ዓይነት ሁኔታ ጥቂት ደቂቃዎች ካለፉ በኋላ ድንገት ዓይኔ ለሶስት ጊዜ ብርት ጭልም እያለ በመጨረሻ ከፊት ለፊቴ የነበረው የእመቤቴን ሥዕል በደንብ ለማየት ቻልኩኝ።
ወዲያው እንባዬ እየፈሰሰ ለአክስቴ ዓይኔ እያየ ነው ብየ ነገርኳት። አክስቴ የምታየው ነገር ከቁጥጥር ውጪ ስለሆነባት እያለቀሰችና እየጮኸች የእመቤታችንን ድንቅ ተአምር በተሰበሰበው ሕዝበ ክርስቲያን አይተውና ሰምተው ወዲያው በእንባ እመቤታችንን ማመስገን ጀመሩ። የጸሎት ቦታው በአንድ ጊዜ በደስታና በለቅሶ ተሞላ፤ እመቤታችን ቅድስት ድንግል ማርያም በአንድ በእለተ ቀኗ ዓይኔን ብርሃን መለሰችልኝ። በጨለማ ሂጄ በብርሃን ተመለስኩኝ። አይቼ የመጣሁትን ቦታ እንዳመሰግን አደረገችኝ እንደገናም ፈጠረችኝ። እንደ ጓደኞቼ ትምህርቴን እንድቀጥል አደረገችኝ
ምስጋና ይድረሳት
የእህታችንን ዓይን ያበራች ለእኛም መልካም የሆነውን ብርሃን ታብራልን እሷን መድኃኒት አድርጎ የሰጠን ልጇ መድኃኔአለም ክብሩ ለዘለዓለም ይሁን። እመቤታችን ቅድስት ድንግል ማርያም በተቸገርንበትና መልስ ባጣንበት ነገር ሁሉ ከጎናችን ትሆን ዘንድ መልካም ፈቃድ ይሁን አሜን