25/05/2026
በሰዎች ህይወት ላይ ተስፋን ለመዝራት፣ በህመም ምክንያት አልጋ ላይ ያሉ ወገኖችን ለመታደግ እና የደም እጥረትን ለመቅረፍ ደብረ ብርሃን ደም ባንክ እና አጣዬ ሆስፒታል ከሌሎች ባለድርሻ አካላት ጋር በመተባበር ያዘጋጁትን የደም ልገሳ ጥሪ በመቀበል በከፍተኛ ማህበራዊ ኃላፊነት እና በበጎ ፈቃደኝነት ደማችሁን ለለገሳችሁ የአጣዬ ከተማ በጎ ፈቃደኛ ደም ለጋሽ ንቁ ተሳታፊዎች እና አስተባባሪዎች በሙሉ ደስታችንን እና ታላቅ አክብሮታችንን እንገልጻለን።
"ደም መለገስ ህይወትን መለገስ ነው!"
እናንተ ዛሬ በፈቃደኝነት የለገሳችሁት እያንዳንዱ ጠብታ ደም፣ በሆስፒታሎች ውስጥ በህመም ምክንያት ለሚሰቃዩ፣ በወሊድ ምክንያት ደም ለሚፈሳቸው/ለሚያጥራቸው እናቶች፣ በአደጋ ምክንያት አስቸኳይ ህክምና ለሚያስፈልጋቸው ወገኖች አዲስ የተስፋ ብርሃን ነው።
ይህ የበጎ አድራጎት ተግባራችሁ ዘላቂ ሆኖ እንዲቀጥል የዘወትር ምኞታችን ነው።
ስለ እያንዳንዱ የህይወት ስጦታችሁ እናመሰግናለን!