የደ/ብርሃን ሪጂዮ ፖሊታንት ከተማ አስተዳደር ገቢዎች መምሪያ

  • Home
  • Ethiopia
  • Debre Birhan
  • የደ/ብርሃን ሪጂዮ ፖሊታንት ከተማ አስተዳደር ገቢዎች መምሪያ

የደ/ብርሃን ሪጂዮ ፖሊታንት ከተማ አስተዳደር ገቢዎች መምሪያ የደ/ብርሃን ሪጂዮ ፖሊታንት ከተማ አስተዳደር ገቢዎች መምሪያ

የደ/ብርሀን ከተማ ገቢዎች መምሪያ ከ 2 ቢሊዬን ብር በላይ  ወይም የእዱን 71.46 %ሰብሰቧል።በቀን 11/09/2018 ዓ.ም  እንደ መምሪያ  የገቢ እቅድ አፈፃፀም  የክልል ገቢዋች ቢሮ የ...
19/05/2026

የደ/ብርሀን ከተማ ገቢዎች መምሪያ ከ 2 ቢሊዬን ብር በላይ ወይም የእዱን 71.46 %ሰብሰቧል።
በቀን 11/09/2018 ዓ.ም እንደ መምሪያ የገቢ እቅድ አፈፃፀም የክልል ገቢዋች ቢሮ የድጋፍ ቡድን ፤ የመምሪያ ማኔጅመንት ፤የከፍለ ከተማ ሀላፊ እና የገቢ አሰባሰብ የሰራ ሂደት አስተባባሪዎች በተገኙበት ተገመገመ።
የመምሪያው እቅድ ክትትል የስራ ሂደት አሰተባባሪ አቶ ገዛህኝ ነገሰ አሰከ 10/09/2018 ከክፍለ ከተማ አስከ መምሪያ የተከናወኑ ተግባራት በዝርዝር በእጥርት እና ጥንካሬ ሪፖርት ቀረቦ ሰፊ ግምገማ ተደርጎል።
የክልል ገቢዎች ቢሮ የድጋፍ ቡድን ከሪፖርቱ በመነሳት በቀሪ ወራት የበጀት ዓመት የገቢ ዕቅድን ሊያሳኩ የሚችሉ ተግባራትን ቆጥሮ መስጠት፣ ትኩረት ሚደረግባቸውን ተግባራት ከመምሪያሪያ እስከ ክፍለ-ከተማ ለይቶ መስራት እና ተግባራትን በስራ ክፍፍል እና በቅንጅት መምራት እንደሚጠበቅ ተናግረዋል።
ዳግም ውሳኔ ያልተወሰነላቸውን መወሰን እና የተወሰነላቸውን ግብር ከፋዮች በማስከፈል እንደሚገባ ተናግረዋል፡፡
የተጨማሪ እሴት ታክስ ተመዝጋቢዎች ወርሃዊ ሪፖርት እንዲያደርጉ በቂ ክትትል ማድረግ እና ጠንካራ የደረሰኝ ክትትል ስራ በመስራት ችግር ያለባቸውን 50ሺ ብር አስተዳደራዊ ቅጣት በመቅጣት ለግብር ህጉ ተገዥ እንዲሆኑ የማድረግ ስራ መስራት እንደሚገባ ተናግርዎል፡፡
ውዝፍ ግብር ያለባቸውን ግብር ከፋዮች መረጃ በማጥራት ማስጠንቀቂያ መስጠት፣ ድርጅት በማሸግ፣ አካውንት በማገድ፣ ሃብት ንብረት በመያዝ ተቆራርጦ ገቢውን መሰብሰብ በቀሪ ወራት የሚጠበቅ እንደሆነ እና
ግብራቸውን ያልከፈሉ የንግድ ትርፍ እና ኪራይ ገቢ ፣ ቅድም ግብር ወይም 25 በመቶ ያልከፈሉ የደረጃ "ሀ" እና "ለ" ግብር ከፋዮችን እና አማራጭ አነስተኛ ግብር ወይም 2.5 በመቶ መክፈል የሚገባቸውን ግብር ከፋዮች ተከታትሎ ማስከፈል እንደሚገባ የስራ አቅጣጫ ተሰቷል።የመምሪያው ም/ሀላፊ አቶ ወንደሰን ተገኝ የክልሉ የድጋፍ ቡድን የተሰጡ አሰተያየቶችን በመቀበል እና ዝቅተኛ አፈፃፀም ያላቸውን የገቢ ኮዶችን በመለየት ትኩረት በሰጠት መሰራት ይገባል ብለዎል።
የመምሪያው ሀላፊ አቶ አበባየሁ ምገሰ ሲያጠቃልሉ ያልተሰበሰቡ የገቢ አርዓሰቶች እና ዝቅተኛ አፈፃፀም ያላቸውን ተግባራት ከሂደት እና ምክንያት ከመቁጠር በመውጣት በቀሪ ወራት ከፍተኛ ርብርብ በማድረግ እቅዱን ለማሳካት መስራት እንደሚገባ የስራ አቅጣጫ ሰጥተዎል።

አስከ 28/08/2018  1.99ቢሊየን ብር ወይም የእቅዱን 68.05% ተሰበሰበ።ሚያዝያ 29/2018 ዓ.ም  የደ/ብርሀን ከተማ ገቢዋቾ መምሪያ  የ2018 በጀት ዓመት እስከ ሚያዝያ 28/08...
07/05/2026

አስከ 28/08/2018 1.99ቢሊየን ብር ወይም የእቅዱን 68.05% ተሰበሰበ።
ሚያዝያ 29/2018 ዓ.ም የደ/ብርሀን ከተማ ገቢዋቾ መምሪያ የ2018 በጀት ዓመት እስከ ሚያዝያ 28/08/2018 እቅድ አፈፃፀም ግምገማ መድረክ ከክፍለ ከተሞች የማኔጅመንት እና የመምሪያ ማኔጅመንት አባላት ጋር ግምገማ አካሄዷል።
የደ/ብርሀን ከተማ ገቢዋች መምሪያ ኃላፊ አቶ አበባየሁ ሞገስ በመድረኩ ላይ እንደገለጹት በቀሪ 2 ወራት ጠንካራ ክትትል ናድጋፍ ስራ በመስራት እቅድን ማሳካት ይኖርብናል ብለዋል።
በቀሪ ወራት ዝቅተኛ አፈፃፀም ያላቸውን የገቢ ምንጮችን በመለየት የታቀደውን የገቢ እቅድ ለማሳካት የገቢ ተቋሙ አመራሮች እና ሰራተኞች በቁርጠኝነት መስራት እንደሚኖርባቸው ገልፀዋል፡፡
ለገቢ አሰባሰብ ስራችን አጋር እና ባለድርሻ ከሆኑ አካላት ጋር ውይይቶችን ማድረግ እና የደረሰኝ አቆራረጥ ላይ ክትትል የማድረግ ስራ በቀጣይም መሰራት እንዳለበት ገልጸዋል፡፡
የመምሪያው ገቢዎች ምክትል ኃላፊ አቶ ወንደሰን ተገኝ እንደተናገሩት ከክፍለ ከተማ አሰከ መምሪያ ዝቅተኛ አፈፃፀም ያላቸውን የገቢ አርዕስቶችን በመለየት በተለይ ደግሞ የከተማ አገልግሎት ገቢ እንደ ከተማ በሚፈለገው መንገድ እየሄደ እንዳለሆነ ገልፀው በቀሪ ወራት ተግባራትን ቆጥሮ በመስጠት እና በመቀበል እቅዱን ለማሳካት መሰራት ይኖርበታል ብለዋል፡፡
ቴክኖሎጅ መጠቀም የግብር ፍትሃዊነትን ለማረጋገጥ እና ዘላቂ ገቢ እንዲኖር የሚያደርግ ዋና መሳሪያ ስለሆነ ገቢ ተቋሙ በትኩረት የሚሰራበት ጉዳይ እንደሆነም ተናግረዋል፡፡
በመድረኩ የመምሪያው የእቅድ ዝግጅት የስራ ሂደት የሆኑት አቶ ገዛህኝ ነገሰ ያለፉት ወራት የተግባራት አፈፃፀም ባቀረቡበት ወቅት እንደተናገሩት በ2018 በጀት ዓመት ከመደበኛ እና ከተማ አገልግሎት ገቢ በድምሩ 2.92. ቢሊዮን ብር ለመሰብሰብ አቅዶ እየሰራ እንደሆነ እና ባለፉት ወራት በታክስ አሰባሰቡ ዙሪያ አበረታች ውጤት እየተመዘበ እንደሚገኝ ገልጸዋል፡፡
እስከ ሚያዝያ 28/2018 ዓ.ም ከመደበኛ እና ከተማ አገልግሎት ገቢ በድምሩ 2.92 ቢሊዮን ለመሰብሰብ ታቅዶ 1.99 ቢሊየን ብር የተሰበሰበ መሆኑን ገልፀዋል።

04/05/2026
የደ/ብርሀን ከተማ ገቢዎች  መምሪያ አሰከ 12/08/2018  1.88 ቢሊዮን  ብር ሰበሰበ። አቶ አባየሁ  ሞገስ  የገቢዎች መምሪያ ኃላፊ  እንደመምሪያ  የተሰሩ ተግባራትን  በዝርዝር   በ...
21/04/2026

የደ/ብርሀን ከተማ ገቢዎች መምሪያ አሰከ 12/08/2018 1.88 ቢሊዮን ብር ሰበሰበ።
አቶ አባየሁ ሞገስ የገቢዎች መምሪያ ኃላፊ እንደመምሪያ የተሰሩ ተግባራትን በዝርዝር በእጥርትና ጥንካሬ የክፍለ ከተሞችን የገቢ አፈፃፀማቸውን በሚያሳይ መልኩ ሪፖርት ያቀረቡ ሲሆን በግምገማው ላይ የተሳተፉ ከክፍለ ከተማ አሰከ መምሪያ የማንጅመንት አባላት በተገኙበት ሰፊ ውይይት ተደርጎል።
አቶ ወንደሰን ተገኝ የመምሪያው ም/ኃላፊ የገቢ አፈፃፀሙ በተፈለገው መንገድ እየሄደ እንዳልሆነ ገልፀው በቀጣይ ቀሪ ወራት በግዜ የለኝም መንፈስ ለገቢ አሰባሰቡ ትኩረት መሰጠት ያለበት መሆኑን ገልፀዎል።
አቶ አበባየሁ ሞገስ በ2018 በጀት አመት መደበኛ ገቢ 1.7ቢሊዮን ብር ለበመሰብሰብ ታቅዶ የተሰበሰበ 1.37ቢሊዮን አፈፃፀም 77.04% አገልግሎት ገቢ እ 1.15ቢሊዮን ለሰብሰብ ታቅዶ የተሰበሰበ 511.3 ሚሊየን አፈፃፀም 44.3% መሆኑን ገልፀው የመደበኛው ገቢ አሰባሰቡ የተሻለ እንደሆነ በመግለፀ የአገልግሎት ገቢው አፈፃፀሙ ዝቅተኛ ስለሆነ በልዩ ስምሪት መሰራት እንዳለበት አሳስበዎል።
አቶ በድሉ ውብሸት የደብረብርሀን ከተማ ከንቲባ ሲያጠቃልሎ ገቢ መሰብሰብ ከተማን ለማልማት የማይተካ ሚና ያለ ው እንደሆነ ገልፀው ከተወሰኑ ሳምንታት ወዲህ አየተሰበሰበ ያለው ገቢ ሲታይ ከተማውን እና የገቢ ተቋም ባለሞያውን የማይመጥን እንደሆነ በመግለፅ በቀጣይ ቀሪ ወራት ከተማውን ሊመጥን የሚችል ገቢ በመሰብሰብ የተጀመሩ የልማት ስራዎችን በማጠናቀቅ ህብርተሰቡን የልማት ተጠቃሚ ማድረግ እንጀሚገባ ገልፀዎል።

በ9 ወሩ 1. 87 ቢሊዮን ብር ገቢ ተሰበሰበየደብረ ብርሀን ከተማ አሰተዳዱር ገቢዎች መምሪያ  በ2018 በጀት ዓመት 2.9ቢሊዮን ብር  ለመሰብሰብ አቅዶ እስከ ሚያዝያ  09/2018 ዓ.ም ከ...
20/04/2026

በ9 ወሩ 1. 87 ቢሊዮን ብር ገቢ ተሰበሰበ
የደብረ ብርሀን ከተማ አሰተዳዱር ገቢዎች መምሪያ በ2018 በጀት ዓመት 2.9ቢሊዮን ብር ለመሰብሰብ አቅዶ እስከ ሚያዝያ 09/2018 ዓ.ም ከመደበኛገቢ 1.36 ቢሊዮን አፈፃፀም 76.8 % እና ከከተማ አገልግሎት ገቢ 510.06 ሚሊዬን ብር አፈፃፀም 44.3% መሰብሰብ መቻሉን የአወሳሰንአሰባሰብናክትትል የስራ ሂደት አሰተባባራ አቶ ብርቅነህ ደሳለኝ ገለጹ፡፡
ከተማው የሚያመነጨውን ገቢ በመሰብሰብ የከተማው ህዝብ የሚያነሳቸውን የልማትና የመልካም አስተዳደር ጥያቄዎች ምላሽ ለማሰጠት እየሰራ ይገኛል ብለዋል።
የ በ2018 ዓ.ም ከመደበኛ እና ከከተማ አገልግሎት ገቢ በድምሩ 2. 9 ቢሊዮን ብር ለመሰብሰብ አቅዶ እስከ ሚያዝያ 09/2018 ዓ.ም ከመደበኛ ገቢ እና ከከተማ አገልግሎት ገቢ በድምሩ 1 .87 ቢሊዮን ብር ወይም የእቅዱን 64.03% መሰብሰብ እንደተቻለ ተናግረዋል፡፡
የተሰበሰበው ገቢ ከባለፈው ዓመት ተመሳሳይ ወቅት ከተሰበሰበው ገቢ አኳያ ሲነፃፀር 606 304 979 ብር ወይም 49.1% እድገት እንዳለው ገልፀዋል፡፡

እንኳን ለጌታችን  ለመደኃኒታችን እየሱስ ክርስቶስ የትንሳኤ በዓል በሳላም አደርሳችሁ አቶ አበባየሁ ሞገስ  የደ/ብርሀን ከተማ  ገቢዎች  መምሪያ  ኃላፈ  ለተቋሙ  ሰራተኞች፣ ለግብር ከፋዮች...
11/04/2026

እንኳን ለጌታችን ለመደኃኒታችን እየሱስ ክርስቶስ የትንሳኤ በዓል በሳላም አደርሳችሁ
አቶ አበባየሁ ሞገስ የደ/ብርሀን ከተማ ገቢዎች መምሪያ ኃላፈ
ለተቋሙ ሰራተኞች፣ ለግብር ከፋዮችና ለገቢ አሰባሰብ ስራው ስኬት ለሚተጉ አጋር ና ባለድርሻ አካላት በሙሉ
የትንሳኤው በዓል የሰላም ፧የፍቅር እና የመተሳስብ በዓል እንዲሆን መልካም ምኞታቸውን ገልፀዋል።

የደ/ብርሀን ከተማ ገቢዎችመምሪያ እስከ 14/07/ 2018  ከ  1.7 ቢሊየን ብር በላይ ገቢ ሰበሰበ።መጋቢት 15/2018 ዓ.ም  የደ/ብርሀን ከተማ ገቢዎች መምሪያ የ2018 በጀት አመት ገ...
24/03/2026

የደ/ብርሀን ከተማ ገቢዎችመምሪያ እስከ 14/07/ 2018 ከ 1.7 ቢሊየን ብር በላይ ገቢ ሰበሰበ።
መጋቢት 15/2018 ዓ.ም የደ/ብርሀን ከተማ ገቢዎች መምሪያ የ2018 በጀት አመት ገቢ አሰባሰቡን የከተማው የመምሪያ አመራሮች ፣ የመምሪያ የገቢ ስራ ሂደት አስተባባሪዎች ፣የክፍለ-ከተማ ገቢ ፅ/ቤት ኃላፊዎች እና ማኔጅመንት አባላት የጋር ውይይት አካሄዷል።
መምሪያው በበጀት ዓመቱ ከመደበኛ እና ከከተማ አገልግሎት ገቢ በድምሩ 2.9ቢሊየን ብር ገቢ ለመሰብሰብ አቅዶ እስከ 14/07/2018 ከመደበኛ ገቢ 1.22 ቢሊየን ብር ወይም 69% እና ከከተማ አገልግሎት 476.8ሚሊየን ብር ወይም 41.8% በድምሩ 1,7ቢሊየንብር ወይም ከዓመቱ 58.2% መሰብሰቡን አቶ አበባየሁ ሞገስ የመምሪያው ሀላፊ ሪፖርቱ ን በጥንካሬ እና ድክመት በመለየት በዝርዝር እቅርበዋል።
ከክፍለ ከተምች በአንፃራዋ ሲታዬ አፄ ዘረያቆብ እና እምዬ ምኒሊክ የተሻለ ገቢ የሰብስቡ መሆኑን አቶ አበባየሁ ሞገስ ጠቁመዋል።
አቶ ሰለሞን ጌታቸው የደ/ብርሀን የከተማው የብልፅግናፓርቲ ቅርንጫፍ ፀ/ቤት ሀላፊግብር መሰብሰብ ያለው ፋይዳ ለህብረተሰብ ጥቅም እንደሆነ ገልፀው ዝቅተኛ አፈፃፀም ያላቸውን የገቢ አርዕስት በመለየት ምክንያት ከመደርደር በመውጣት የጠራ መርጃ ላይ በመመስረት ወደተግባር መገባት ያለበበት መሆኑን ገልፀዎል ።

የተከበሩ አቶ በድሉ ዉብሸት የደ/ብርሀን ከተማ ከንቲባ የተጀመሩ የልማት ስራዎቾን ለማጠናቀቅ ገቢ መሰብሰብ ወሳኝ መሆኑን ገልፀው ።መደበኛ ገቢ የተሻለ የተሰበሰበ እንደሆነ እና ውጤቱም የመጣው በባለሞያው ጥርት መሆኑን ገልፀው ዝቅተኛ አፈፃፀም ላይ ያለው የከተማ አገልግሎት ገቢ አፈፃፀሙን ከፍ ለማድርግ ከአጋርና ባለድርሻ አካላት ጋር ቅንጅታዊ አሰሪሩን በማጠናከር በቀጣይ ወራት 2.9 ቢሊየን ብር መቶ ፐርሰንት ለማሳካት፤ ዝቅተኛ ገቢ ያስመዘገባችሁ ክፍለ ከተሞች የሰራር ስልቶችን በመቀየር ዕቅዳችሁን በመከለስ በተነሳሽነት ስሜት ለስራ መነሳሳት እንዳለባቸው አሳስበዋል።

የክልሉ ገቢዎች  ቢሮ  የድጋፍ ቡድን የደ/ብርሀን ከተማ ገቢ አሰባሰቡን ገመገመ።በቀን 30/06/2018 ከክልል በወረደው ቸክሊስት መሰረት የ5ቱም ከፍለ ከተማ የማኔጅመንት አባላት እና የመም...
09/03/2026

የክልሉ ገቢዎች ቢሮ የድጋፍ ቡድን የደ/ብርሀን ከተማ ገቢ አሰባሰቡን ገመገመ።
በቀን 30/06/2018 ከክልል በወረደው ቸክሊስት መሰረት የ5ቱም ከፍለ ከተማ የማኔጅመንት አባላት እና የመምሪያው የማኔጅመንት አባላት በተገኙበት ገቢ አሰባሰቡ ተገምግምአል።
የክልሉ የድጋፍ ቡድን ከመምሪያ እስከ ክፍለ ከተማ የከትትልና ድጋፍ በማድረግ የታዪትን እጥርት እና ጥንካሬ በመለየት የማሳየት ሰራ የተሰራ ሲሆን በተለይ የታዩ እጥርቶች በቀጣይ የቸክሊሰት አካል በማድረግ ሊሰራ እንደሚገባ አስተያየት ተሰጥቶል።
በመጨረሻም የመምሪያው ሀላፌ አቶ አበባየሁ ሞገስ ሲያጠቃልሉ የክልሉ ድጋፍ አቅም አንደሆነ እና በቀጣይም መቀጠል እንዳለበት ገልፀው በድጋፍ ወቅት የታዩ ጥንካሬዎች በማሰቀጠል አጥረቶችን የአለት እቅዳችን አካል በማድረግ የታቀደውን እቅድ 100% መፈፀም እንደማጠበቅ አሳስበዎል።

ለጥቃቅና አነስተኛ ኢተርፕራይዝ ግንዛቤ ተሰጠ።በ25/06/2018 ከስራና ክህሎት መምሪያ ጋር በጋራበመሆን ቫት ተሠዝጋቢ ለሆኑ የማህበሩ አባላት በዋናዋና የክልሉ ገቢ ግብር አዎጀ 301/201...
04/03/2026

ለጥቃቅና አነስተኛ ኢተርፕራይዝ ግንዛቤ ተሰጠ።
በ25/06/2018 ከስራና ክህሎት መምሪያ ጋር በጋራበመሆን ቫት ተሠዝጋቢ ለሆኑ የማህበሩ አባላት በዋናዋና የክልሉ ገቢ ግብር አዎጀ 301/2017 ላይ ግንዛቤ ስራ ተሰቶአል።
ግንዛቤ የተሰጠባቸው ሰለተጨማሪ እሴት ታክስ ፣ሰለአማረጭ አነሰተኛ ግብር አከፍፈል |፣2.5%|፣ሰለስራ ግብር እና አመታዊ ግብር በየሩበአመቱ እንደሚከፈል ለማህበሩ አባላት ግንዛቤ የተሰጠ ሲሆን በተሰጠው የግንዛቤ ላይ ግልፅ የለሆነላቸውን ጥያቄ አንሰተው ለጥያቄው ማብራሪያ በመሰጠት የአለቱ የግንዛቤ ማስጨበጥ ስራው ተጠናቋል።

ቢሮው የተገልጋዮችን እርካታ ለማሳደግ በቴክኖሎጂ የተደገፈ ቀልጣፋ አገልግሎት ለመስጠት እየሰራ መሆኑን አስታወቀ።ደብረ ብርሃን፤የካቲት /2018 ዓ.ም የአማራ ክልል ገቢዎች ቢሮ"የግብር አሰባ...
03/03/2026

ቢሮው የተገልጋዮችን እርካታ ለማሳደግ በቴክኖሎጂ የተደገፈ ቀልጣፋ አገልግሎት ለመስጠት እየሰራ መሆኑን አስታወቀ።

ደብረ ብርሃን፤የካቲት /2018 ዓ.ም የአማራ ክልል ገቢዎች ቢሮ"የግብር አሰባሰባችንን በማዘም ዲጂታል ኢትዮጵያን እውን እናደርጋለን በሚል መሪ መልዕክት ለገቢ የሥራ ኃላፊዎች እና ባለሙያዎች ሲሰጥ የሰነበተው ሥልጠና ተጠናቀቀ።

የአማራ ክልል ገቢዎች ቢሮ ኃላፊ መንገሻ ፈንታው (ዶ.ር) እንደገለጹት፣የግብር ከፋዮችን እርካታ ለማሳደግ በቴክኖሎጂ የተደገፈ ፈጣንና ቀልጣፋ አገልግሎት ለመስጠት ቢሮው እየሰራ መሆኑን አስታውቀዋል።

ለዚህም ሳይሻሻል ላለፉት 10 ዓመታት ሲያገለግል የቆየው አዋጅ ቁጥር 240/2008 በአዋጅ ቁጥር 301/2017 እንዲተካ መደረጉን አብራርተዋል።አዲሱ አዋጅ በቴክኖሎጂ የተደገፈ አዳዲስ አሰራሮችን ይዞ የመጣ ስለሆነ ትክክለኛ የግብር ውሳኔ ለመወሰን የሚያስችል፣ቅሬታና አቤቱታን የሚያስቀር ከመሆኑም ባሻገር ፈጣን አገልግሎት ለመስጠት ምቹ ሁኔታ የሚፈጥር ነው ብለዋል።

በዚህ መሠረት ለተቋሙ የሥራ ኃላፊዎች እና ባለሙያዎች በተሻሻለው አዋጅ ዙሪ ሥልጠና መሰጠቱ ጠንካራ ባለሙያዎች የበለጠ የሚያጠነክር፣አዳዲሶቹን ደግሞ ከነባር ሠራተኞች በቀጥታ ልምድና ተሞክሮ እንዲቀስሙ የሚያደርግና በቀጣይ ሥራቸው ውጤታማ እንዲሆኑ ትልቅ አቅም የሚፈጥር መሆኑንም አመልክተዋል።

የክልሉ መንግሥት በገቢ ግብር አዋጁ እና በአዳዲስ መመሪያዎች ዙሪያ ለገቢ ሠራተኞች ሥልጠና ማስፈጸሚያ ካለው በጀት ቀንሶ በጀት በመመደብ ሥልጠናው እንዲሳካ ለደረገው ቁርጠኛ ውሳኔ ዶክተር መንገሻ አመስግነዋል።

በተመሳሳይ ደብረ ብርሃን ዩኒቨርሲቲ ከ500 ለሚበልጡ አሰልጣኞች የመኝታ፣የምግብና እና መሰል አገልግሎት በመስጠቱ በቢሮው ስም አመስግነዋል።

በሌላ በኩል ቢሮው በችግር ውስጥ ለሚገኙ 2 የቀድሞው የተቋሙ ሠራተኞች እና ለ1 አቅም ደካማ የጠባሴ ክፍለ ከተማ ነዋሪ ከ4 መቶ ሺህ ብር በላይ ሃብት አሰባስቦ ድጋፍ ማድረጉን በመርሐ ግብሩ ላይ ተገልጿል።

በመጨረሻም የክልሉ ገቢዎች ቢሮ ስልጠናው እንዲሳካ ደብረ ብርሃን ዩኒቨርስቲ ከ500 ለሚበልጡ ሰልጣኞች የምግብ፣የመኝታ፣የሻይ ቡና ወጪ በአነስተኛ ዋጋ በማቅረቡ ምስጋና በማቅረብ የዕውቅና የምስክር ወረቀት አበርክቶለታል።

Address

ዘርያዕቆብ ክፍለከተማ አልማ ህንፃ 3ኛ ፎቅ
Debre Birhan

Telephone

116376039

Website

Alerts

Be the first to know and let us send you an email when የደ/ብርሃን ሪጂዮ ፖሊታንት ከተማ አስተዳደር ገቢዎች መምሪያ posts news and promotions. Your email address will not be used for any other purpose, and you can unsubscribe at any time.

Contact The Organization

Send a message to የደ/ብርሃን ሪጂዮ ፖሊታንት ከተማ አስተዳደር ገቢዎች መምሪያ:

Share