11/09/2026
እንኳን ለ2019 ዓ.ም አዲሱ አመት አደረሣችሁ አደረሠን!!
የሰ/ሸዋ ዞን መንገድ ትራንስፖርትና ሎጀሥቲክሥ መምሪያ ኃላፊ አቶ ደጀኔ በቀለ አዲሱን አመት አስመልክተዉ የእንኳን አደረሳችሁ መልዕክታቸዉን አስተላልፈዋል።
በዓሉ የደሥታ፣የመጠየቅና የአብሮነት ጊዜ እንደመሆኑ መጠን ከፍተኛ የህዝብና የትራፊክ እንቅሥቃሴዎች የሚበዙበት በመሆኑ መላ የዞናችን የትራንስፖርት አገልግሎት ሰጪ አሽከርካሪዎች በበዓል ወቅት የትራፊክ አደጋ እንዳይከሰት የትራፊክ ህጎችን በማክበር እና አልኮል ጠጥቶ ከማሽከርከር በመቆጠብ ፣ ለእግረኞች ቅድሚያ በመስጠትና ፍጥነትን በመቀነስ እንዲያሽከረክሩና ሁላችንም ከፍተኛ ጥንቃቄ ማድረግ ይኖርብናል።
የትራንስፖርት ተቆጣጣሪ ትራፊክ ፖሊሶች እና የትራንስፖርት ባለሙያዎች ከወትሮው በላቀ የትራንስፖርት ተጠቃሚዎች ደህንነት እንዲጠበቅ እና መጉላላት ሳይኖር ትክክለኛ አገልግሎት እንዲሰጥ ሙያዊና የዜግነት ህዝባዊ አደራ መወጣት ይገባናል።
በመጨረሻም ለመላዉ የዞናችን ህዝብ፣ የተቋማችን አመራሮችና ሠራተኞች፣ትራፊክ ፓሊሶች፣አሽከርካሪዎች፣አጋርና ባለድርሻ አካላት አዲሱ ዓመት የሰላም ፣የጤና ፣ የፍቅርና ያቀድነው ሁሉ የሚሳካበት አመት እንዲሆን ከልብ እመኛለሁ! መልካም ምኞታቸዉን ተመኝተዋል።
መልካም አዲሥ ዓመት!!
ደጀኔ በቀለ
የሰ/ሸዋ ዞን መንገድ፣ትራንሥፖርትና ሎጀሥቲክሥ መምሪያ ኃላፊ