ደብረ ብርሃን ሪጅዮፖሊታን ከተማ ወጣትና ስፖርት መምሪያ

  • Home
  • Ethiopia
  • Debre Birhan
  • ደብረ ብርሃን ሪጅዮፖሊታን ከተማ ወጣትና ስፖርት መምሪያ

ደብረ ብርሃን ሪጅዮፖሊታን ከተማ ወጣትና ስፖርት መምሪያ Contact information, map and directions, contact form, opening hours, services, ratings, photos, videos and announcements from ደብረ ብርሃን ሪጅዮፖሊታን ከተማ ወጣትና ስፖርት መምሪያ, Debre Birhan.

20/08/2025
10/09/2023
08/09/2023
መፅሀፍ ማንበብ  #5 ጥቅሞች 1,ስላለፈው ዘመን ለማወቅ አሁን እየሆነ ስላለው ለማስተዋል ወደ ፊት ስለሚሆነው ለመተንበይና ቅድመ ዝግጅት ለማድረግ ይጠቅማል።2,መፅሀፍ ስናነብ በህይወት ያሉት...
07/09/2023

መፅሀፍ ማንበብ #5 ጥቅሞች
1,ስላለፈው ዘመን ለማወቅ አሁን እየሆነ ስላለው ለማስተዋል ወደ ፊት ስለሚሆነው ለመተንበይና ቅድመ ዝግጅት ለማድረግ ይጠቅማል።
2,መፅሀፍ ስናነብ በህይወት ያሉትም ያለፉትም ደራሲዎች ያላቸውን ያስተሳሰብ ልህቀት እዲሁም በህይወታቸው ያጋጠማቸውን ጥሩናመጥፎ ገጠመኞችን ጠቃሚ ምክሮችን ከጎናቸው ቁጭ ብለን ባይሆንም ከመፅሀፋቸው ውስጥ እናገኛለን ያ ደ'ሞ የህይወት ስንቅና ትትቅ ይሆነናል በምናልፍበት በእያንዳንዱ ሁኔታ ህይወት ልታስተምረን ያዘጋጀችውን ልንማር የተማርነውን ደ'ሞ ለሚመጣው ትውልድ ልናስተምር ልክ እንደ ደራሲዎቹ በመፅሀፋችን የኛን የአስተሳሰብ ልዕልና ለሚመጣው ትውልድ ልናስተላልፍ፣ልንጠቅም፣ልናስተካክል፣ልናስተምር፣በበጎ አስተሳሰብ ተፅዕኖ ለመፍጠር ያስችለናል።
3,ማንበብ በዲፕሎማ፣በዲግሪ፣በማስተርስ፣በፕሮፌሰርነት አይገደብም፣ማዕረግ አያሰጥም ነገር ግን ህይወታችንን በጥበብና በማስተዋል እድንመራ ሌላው ደ'ሞ እኛ ማንበብ እስከቻልን ድረስ ብዙ እያወቅን፣ብዙ እየተማርን፣በራሳችን ላይ ለውጥ አምጥተን ለብዙዎች የማንበብ ልምድ ምሳሌ ሆነን ከራሳችን አልፈን ቤተሰባችንን፣ጓደኞቻችንን፣ማህበረሰባችንን እንለውጣለን።
4,የአስተሳሰብ ለውጥ እንዲኖረንና እስከ ዛሬ ከለመድነው የህይወት ሂደት ወተን በተሻለው ሀሳብ እድንመራ በሚጠቅመን ነገር ላይ ጊዜያችንን እንድናውል ይረዳናል።
5,ዛሬ ከዚህ መፅሐፍ ምን እማር ይሆን? ጊዜያችንን በተራ ነገር አሳልፈን ከምንቆጭ በንባብ ላይ አውለን ለሌላው መካሪ፣አራሚ፣አስታራቂ እንዲሁም በሳል ሆነን በህይወታችን ለሚገጥሙን ፈተናዎች አላስፈላጊ መንገድ ከመሄድ ፊት ለፊት የምንጋፈጥበትን ጥበብ ያዳብርልናል መፅሐፍ ማንበብ።

የደብረብርሃን ከተማ የሰዓት እላፊ ገደብ መሻሻሉን  የማዕከላዊ ሸዋ ኮማንድ ፖስት አስታወቀ ። የማዕከላዊ ሸዋ ኮማንድ ፖስት  አባልና የደብረብርሃን ከተማ ተቀዳሚ ምክትል ከንቲባ አቶ በድሉ ...
06/09/2023

የደብረብርሃን ከተማ የሰዓት እላፊ ገደብ መሻሻሉን የማዕከላዊ ሸዋ ኮማንድ ፖስት አስታወቀ ።

የማዕከላዊ ሸዋ ኮማንድ ፖስት አባልና የደብረብርሃን ከተማ ተቀዳሚ ምክትል ከንቲባ አቶ በድሉ ውብሸት እንደገለጹት የከተማውን ማህበራዊና ኢኮኖሚያዊ እንቅስቃሴዎች ለማነቃቃት ከዚህ በፊት ኮማንድ ፖስቱ ጥሎት የነበረውን የሰዓት እላፊ ገደብ እንዲሻሻል መደረጉን አስታውቀዋል፡፡

በዚህም መሠረት ከዛሬ ጳቁሜ 1/2015 ዓ.ም ጀምሮ ከዚህ በፊት ለሰው እና ተሸከርካሪዎች ከጠዋቱ 12 ሰዓት እስከ ምሽቱ 1 ሰዓት የነበረው የሰዓት እላፊ ገደብ አሁን ከጠዋቱ 12 ሰዓት እስከ ምሽቱ 2 ሰዓት ተሻሽሎ ተግባራዊ እንዲሆን መወሰኑን አመልክተዋል፡፡

በተመሳሳይ የከተማ ባጃጅ እና ሞተር ሳይክል ከጠዋቱ 12 ሰዓት እስከ ምሽቱ 1 ሰዓት መደረጉን ጠቅሰው አገልግሎት ሰጪዎችና ተገልጋዮች የሰዓት ገደቡን አክብረው እንዲንቀሳቀሱ ከንቲባው አሳስበዋል፡፡

ምንጭ፦ደከአኮ

04/09/2023

ጥበበኛዉ
ነሐሴ 29 ቀን 2015 ዓ.ም

ዐፄ ምኒልክ በሳል እና ሁሉን አካታች፣ ችግሮችን ደግሞ በስልት እና በጥበብ የሚፈቱ ነበሩ:: ከስሜታዊነት ይልቅ እርጋታ፣ በመጀመሪያ ኃይል ከመጠቀም ይልቅ ንግግር እና ስምምነትን የሚያስቀድሙ ነበሩ::

በምኒልክ ቤተ መንግሥት ወሳኝ የነበሩ ሰዎች ከተለያየ ብሔረሰብ የተገኙ እንደሆኑ ሁሉ በሀገር አንድነት ዘመቻውም የተሳተፈው ሰራዊትም ኅብረ ብሄራዊ እንደነበር በዕውቀቱ ስዩም ከአሜን ባሻገር በተሰኘው መጽሐፉ አስፍሯል:: ይቀጥልናም በተለይ ኦሮሞ ያልተሳተፈበት የምኒልክ ዘመቻ በጣም ውስን መሆኑን ያነሳል:: ለአብነት ወላይታን እና ከፋን ለማስከበር በተደረጉ ዘመቻዎች አባ ጅፋር የኦሮሞ ፈረሰኛ ጦር ይዘው ተዋግተዋል:: የጂማው ሞቲ የየምን ግዛት ለማስገበር መሳተፉንም አንስቷል::

በወላይታ ዘመቻ ንጉሥ ጦናን አቁስለው የማረኩት የራስ ሚካኤል ኦሮሞ ነፍጠኞች ናቸው:: ከዚህ ጋር ተያይዞ የሚነሳ የምኒልክን መሐሪነት እና ደግነት የሚያወሳ ሁነት እናንሳ:: የወላይታው ንጉሥ ጦና ለኢትዮጵያ ግዛት አንድነት ሲባል ለማዕከላዊ መንግሥት በሰላም እንዲገብሩ በምኒልክ ቢጠየቁ አልስማማም አሉ:: በዚህም የግዛት ማስከበር እርምጃ ተወሰደባቸው:: ከእልህ አስጨራሹ ጦርነት በኋላ ቆስለው የተማረኩትን ንጉሥ ጦናን የምኒልክ ወታደሮች በማይረባ ወሳንሳ ተሸክመው ለምኒልክ ሲያቀርቡ፣ ምኒልክም “ወንድሜን በማይረባ ወሳንሳ ታመጡታላችሁ!” ብለው መቆጣታቸው እና ከዙፋናቸው ወርደው መቀበላቸው በታሪክ ሰፍሯል:: ንጉሥ ጦናንም ራሳቸው አስታመው ካዳኗቸው በኋላ መልሰው የወላይታ ግዛት ገዥ እንዳደረጓቸው ይነገራል:: በታሪክ በደል ደርሶብናል ተብሎ በአንዳንድ ወገኖች የሚነሳው የአርሲ ጉዳይም ተመሳሳይ መሆኑን በዕውቀቱ ስዩም የተለያዩ መጽሐፍትን ዋቢ አድርጎ ይገልጻል::

ቸሩሊ የተባለ ጸሐፊ የኦሮሞ ሕዝብ ስነ ቃል በተሰኘው ሥራው በአርሲ ዘመቻ ከምኒልክ ወገን ዘማቾች አንዱ በፊታውራሪ ዱፌራ የሚመራ የኦሮሞ ጦር እንደነበር መዝግቧል:: በወቅቱ በአስገባሪ እና በገባሪ ጦር ውስጥ በኦሮምኛ ፉከራዎች ይሰሙ እንደነበር ጽፏል:: የሐሰት ትርክት ተፈብርኮ ለጥፋት ዓላማ ከዋለባቸው የታሪክ አጋጣሚዎች መካከል ዐፄ ምኒልክ የሀገራቸውን አንድነት ለማስጠበቅ ካደረጉት እንቅስቃሴ ጋር ተያይዞ በተለይም የአርሲ ዘመቻቸው አንዱ ነው:: በትርክቱ የተፈበረኩ የውሸት ክስተቶች እና ከንጉሡ ግብር እና ተግባር ለየቅል የሆኑ ጉዳዮች ተካተዋል:: ‹‹በአርሲ ዘመቻ የሴቶች ጡት ተቆርጧል›› የሚሉ የፈጠራ ታሪኮች መሰል ትርክት ዋነኛ አራጋቢዎች ፕሮፌሰር አባስ ገነሞ፣ ተስፋየ ገብረ አብ እና ሌሎች አክራሪ ብሔርተኞች ናቸው::

ተስፋየ ገብረ አብ “የቡርቃ ዝምታ” በተሰኘው የፈጠራ ስራው መሰል ትርክቶችን እና አደገኛ ሀሳቦችን በገጸ ባህሪያት አማካኝነት አንጸባርቋል:: ይሁንና ፕሮፌሰር አባስን እና ተስፋየ ገብረ አብን ጨምሮ ሌሎች አክራሪዎች በጻፏቸው መጻሕፍት ውስጥ ጡት ቆረጣ መፈጸሙን የሚያሳይ አንድም የታሪክ ሰነድ ማቅረብ አልቻሉም:: ይህን ትርክት አብዛኞቹ የታሪክ ምሁራንም አይቀበሉትም:: በአዲስ አበባ ዩኒቨርስቲ የታሪክ መምህር አቶ አበባው አያሌው በአንድ ወቅት ለአዲስ አድማስ ጋዜጣ በሰጡት ቃለ ምልልስ በኢትዮጵያ ታሪክ ውስጥ ሴት ልጅ በጦርነት ጊዜ የተለየ ጥበቃ እንደሚደረግላት ጠቅሰው በአኖሌ ጡት ተቆርጧል ለሚለው ማረጋገጫ የሚሆን የታሪክ ሰነድ የለም ብለዋል:: አፈ ታሪኩ ከብሔርተኝነት ጋር ተያይዞ የተፈጠረ ነው ያሉት አቶ አበባው፤ አፈ ታሪክን መነሻ አድርጐ ሃውልት መገንባት አይገባም፤ ከዚህ በተጨማሪ ሃውልቱ ጥላቻን እና ቂም በቀልን በማንፀባረቅ ከመጉዳት በስተቀር አንዳች ፋይዳ የለውም ብለዋል::

የታሪክ ምሁር እና ፖለቲከኛ የነበሩት ነጋሶ ጊዳዳ (ዶ/ር) በበኩላቸው ከአፈ ታሪክ የዘለለ ማረጋገጫ ሰነድ እንዳላገኙ በአንድ ወቅት ገልጸው ነበር:: በተመሳሳይ ረዳት ፕሮፌሰር መረራ ጉዲናም የፖለቲካ ጨዋታቸው አንደዛሬው ሳይቀየር “እኔ ስለ አኖሌ ታሪክ ወያኔ ሃውልት ሰርቶ ሲያስመርቅ እንጂ በኦሮሞ ታሪክ ሰምቸው አላውቅም” ሲሉ ተናግረዋል::

ባለንበት ወቅት በስሜት በሚነዳ የብሔር ፖለቲካችን ውስጥ ታሪክ ትልቅ ማገዶ ሆኖ ቀርቧል:: በሀገር ውስጥም ሆነ በውጭ ጸሐፍት ኢትዮጵያን በተመለከተ የተጻፉ የታሪክ ድርሳናት በጥንቃቄ የሚመረምሩበት ሁኔታ እስካልተፈጠረ ድረስ የታሪክ ኩነቶችን ታከው የሚፈበረኩ ውልድ ታሪኮች መቆሚያ አይኖራቸውም::

ዐፄ ምኒልክ ዘመናዊነትን ለሀገራቸው ለማስተዋወቅ ከፍተኛ ፍላጎት የነበራቸው፤ እንዲሁም በባቡር፣ ስልክ፣ ፖስታ፣ ኤሌክትሪክ፣ አውቶሞቢል፣ የውሃ ቧንቧ፣ ህክምና፣ ሆሰፒታል/ መድኃኒት ቤት፣ ባንክ፣ ገንዘብ ማተሚያ ቤት፣ ጋዜጣ፣ ሆቴል እና ፖሊስ አገልግሎት መኪና፣ ወፍጮ፣ ቀይ መስቀል፣ የሚኒስተሮች ሹመት፣ የሙዚቃ ሸክላ የመሳሰሉትን ሥራዎች ያስገቡ ነበሩ:: ዐፄ ምኒልክ ቴክኖሎጂን በማስተዋወቅ ብቻ ሳይሆን በአስተዳደር፣ በበጎ ተግባር፣ በውጭ ግንኙነት እና በሌሎች መስኮች የተዋጣላቸው መሪ እንደነበሩ የተለያዩ ጸሐፊያን፣ የታሪክ ምሁራን እና የውጭ ሀገር ዜጎች ሳይቀር መስክረዋል:: ይህም በእሳቸው ላይ የተነዙት ትርክቶች ከእውነት የራቁ ስለመሆናቸው ማስረጃ ነው::

አንጋፋው ጋዜጠኛ ጳውሎስ ኞኞ ዐፄ ምኒልክ በሀገር ውስጥ የተጻጻፏቸውን ደብዳቤዎች በመመርመር ማጠቃለያ ሀሳቡን ሲያስቀምጥ “ሁሉም ደብዳቤዎች የንጉሠ ነገሥቱን ትሁት ግለ- ባህርያት ያንጸባርቃሉ” ብሏል:: ሌላው ቀርቶ ይላል ጳውሎስ ኞኞ ምኒልክ የማይስማሙበት ነገር እንኳን ቢገጥማቸው አሉታዊ መልሳቸው ተቀባዩን ቅር እንዳያሰኝባቸው ተጨንቀውና ተጠበው ነበር ደብዳቤውን የሚጽፉት:: ዐፄ ምኒልክን እምዬ በሚል ሙገሳ ሕዝቡ የሚጠራቸው ያለ ምክንያት አልነበረም:: ጸሐፌ ትእዛዝ ገብረ ሥላሤም የጳውሎስ ኞኞን ሀሳብ ይጋሩታል፤ ጸሐፌ ትእዛዙ ዐፄ ምኒልክ አስተዋይ እና ሩህሩህ እንደነበሩ ጽፈዋል::

አንጋፋው ተመራማሪ ፕሮፌሰር ፍቅሬ ቶሎሳ ስለ ዐፄ ምኒልክ እንደጻፉት፣ ምኒልክ የቆሰለውን ምርኮኛ ገድሎ በመጨረስ ፋንታ ቁስላቸውን ራሳቸው አክመው አጠገባቸው አስቀምጠው አብረዋቸው እንዲመገቡ በማድረግ ፍቅር ያሳዩአቸው ነበር:: ሀገራቸውን ለመውረር የመጡ ምርኮኞች ጣሊያኖችን እንኳን በርህራሄ እና በደግነት ነበር የያዟቸው:: ዐፄ ምኒልክ ከአባታቸው ከንጉሥ ኃይለ መለኮት ጋር ከኖሩበት 10 ዓመታት ይልቅ፣ ከዐፄ ቴዎድሮስ ጋር በኖሩበት 11 ዓመታት ውስጥ አያሌ ነገሮችን መማራቸውን ተክለ ጻድቅ መኩሪያ ያስረዳሉ:: የውጭ ግንኙነት እና ሕዝብን የማሰልጠን የመሳሰሉ ጽንሰ ሃሳቦችን ከቴዎድሮስ ገና በልጅነታቸው የቀሰሟቸው ናቸው:: ይህም በኋላ ላይ በዓድዋ ጦርነት እንደጠቀማቸው ማየት ይቻላል::

ለዐፄ ቴዎድሮስ በእንግሊዞች መረታት፣ ለተክለ ጊዮርጊስ በዮሐንስ መሸነፍ እንዲሁም ራሳቸው ምኒልክ ለዮሐንስ መገበር ዋናው ምክንያት የጦር መሳሪያ ጉዳይ መሆኑን ተረድተዋል:: ጎራዴ እና ጦር ብቻቸውን ዘመኑን እንደማይዋጁ እና እንዳለፈባቸው ምኒልክ ገና የሸዋ ንጉሥ ሳሉ ገብቷቸዋል:: በዚህም ዘመናዊ ጠመንጃ እና ጥይት ማምረት ከሚችሉ ሀገራት ጋር መወዳጀት መሣሪያዎቹ በብዛት እጃቸው እንዲገቡ አማራጭ የሌለው ጉዳይ ነው:: ለዚህም ደግሞ የእነዚህን ሀገራት ዜጎች በቅርባቸው አድርገው መንከባከብ ከዚያም ለመንግሥቶቻቸው ስጦታ እየላኩ መወዳጀት አንዱ የዲፕሎማሲ አካሄዳቸው ነበር:: ከጠቡ በፊት ከጣሊያን፣ በኋላ ግን ከፈረንሳይ እና ሞስኮቭ (ሩሲያ) ጋር ወዳጅነት መስርተዋል:: በዚህም ወደ ንጉሠ ነገሥትነት ማዕረግ ለመምጣትም ሆነ ወራሪውን ጣሊያንን ድል አድርጎ ለመመለስ የረዳቸውን የጦር መሣሪያ ከእነዚህ ሀገራት ማግኘት ችለዋል::

በተለይ የሩሲያ መንግሥት በአፍሪካ ምንም ዓይነት የቅኝ ግዛት ዓላማ እንዳልነበረው ምኒልክ በመረዳታቸው ወዳጅነታቸውን አጠናክረዋል:: የሁለቱን ሀገራት ግንኙነት በማስጀመር የሚነሳውም በምኒልክ የደጃዝማችነት ማዕረግ የተሰጠው ሩሲያዊው ኮንት ኒኮላይ ሊዎንቴቭ ነበር::

ዐፄ ምኒልክ ኢትዮጵያዊ ማንነትን ለመፍጠር የሄዱበትን ርቀት እና ብስለት በመመልከት አንዳንዶች ከጀርመኑ ኦቶማን ቢስማርክ ጋር ያመሳስሏቸዋል:: ቢስማርክ የተበታተነች ጀርመንን ሰብስቦ አንድ ሀገር በማድረግ እንዳቆማት ሁሉ ዐፄ ምኒልክም አንድነቷ የጠነከረና ለቅኝ ግዛት ያልተበገረች ኢትዮጵያን በመፍጠር ቁልፍ ሰው ነበሩ::

የታሪክ ምሁሩ ፕሮፌሰር ሹመት ከአሚኮ ጋር በነበራቸው ቆይታ አንደተናገሩት ዐፄ ሚኒልክ ድንበሩ የታወቀ አንድ ሉአላዊ ሕዝብ እና ሀገር በመስራታቸው የተሻለ የሕዝብ ለሕዝብ ግንኙነት ተፈጥሯል:: ይህም ከእርሳቸው በፊት በጣም ቀጭጮ የነበረውን የሕዝብ እንቅስቃሴ እና ግብይት በአንድ የፖለቲካ ምህዳር ውስጥ በማምጣት እንዲነቃቃ አድርገውታል ይላሉ:: ንጉሡ ቀደም ብለው ሕዝቡን በኢኮኖሚና በማህበራዊ ግንኙነት ባያስተሳሰሩት ኖሮ ያ ሕዝብ በዚያ አይነት ህብረት የተጋረጠበትን የህልውና አደጋ (የጣሊያን ወረራ) ሊቋቋም ባልቻለ ነበር” ብለዋል:: ይህ ስኬት ታዲያ ከራሳቸው ከንጉሡ የግል ስብእና እና ባህሪ የሚመነጭ ነበር የሚሉት ኘሮፌሰር ሹመት ዐፄ ምኒልክ በዐፄ ቴዎድሮስ አደባባይ ከማደጋቸው ጋር ተያይዞ የተሻለ ልምድ እንዲያካብቱ አድርጓቸዋል:: በሌላ በኩል ደግሞ ሩህሩህ፣ አቅራቢ፣ እና ቂም የማይዝ ባህሪያቸው የሀገር ግንባታ ኘሮጀክታቸውን ወደ ስኬት እንዲያመራ ማድረጉን ፕሮፌሰር ሹመት አስረድተዋል::

(ቢኒያም መስፍን)
በኲር ነሐሴ 29 ቀን 2015 ዓ.ም ዕትም
በአማራ ሚዲያ ኮርፖሬሽን ዘወትር ሰኞ የምትታተመውን የበኲር ጋዜጣን ሙሉ ፒዲኤፍ
http://www.amharaweb.com/Bekur ላይ ማግኘት ይችላሉ።

ለተሰንበት ግደይ በአለም ፈጣኑን 4ተኛውን ሰአት በማስመዝገብ በበርሊን የተካሄደውን የ5000 ሜትር ውድድር አሸንፋለች፤ ከአምስቱ ፈጣን ሰአት ሶስቱ የሷ ነው🔥
04/09/2023

ለተሰንበት ግደይ በአለም ፈጣኑን 4ተኛውን ሰአት በማስመዝገብ በበርሊን የተካሄደውን የ5000 ሜትር ውድድር አሸንፋለች፤ ከአምስቱ ፈጣን ሰአት ሶስቱ የሷ ነው🔥

03/09/2023
03/09/2023
02/09/2023
02/09/2023

Address

Debre Birhan

Telephone

+251116810002

Website

Alerts

Be the first to know and let us send you an email when ደብረ ብርሃን ሪጅዮፖሊታን ከተማ ወጣትና ስፖርት መምሪያ posts news and promotions. Your email address will not be used for any other purpose, and you can unsubscribe at any time.

Contact The Organization

Send a message to ደብረ ብርሃን ሪጅዮፖሊታን ከተማ ወጣትና ስፖርት መምሪያ:

Share