የደብረ ብርሃን ከተማ አስተዳደር ሲቪል እና ቤተሰብ ምዝገባ አገልግሎት ቡድን

  • Home
  • Ethiopia
  • Debre Birhan
  • የደብረ ብርሃን ከተማ አስተዳደር ሲቪል እና ቤተሰብ ምዝገባ አገልግሎት ቡድን

የደብረ ብርሃን ከተማ አስተዳደር ሲቪል እና ቤተሰብ ምዝገባ አገልግሎት ቡድን ይህ ገፅ የደብረ ብርሃን ከተማ አስተዳደር ከንቲባ ጽ/ቤት ወሳኝ ኩነት ምዝገባ ቡድን ሲሆን ስለ ወሳኝ ኩነቶች ምዝገባ የሚተነተንበት፣ ገለፃ የምናደርግበት፣ እርስዎም የሚወያዩበትና የሚሳተፉበት ገፅ ነው፡፡

ይህ ገፅ የደብረ ብርሃን ከተማ አስተዳደር የሲቪል እና ቤተሰብ ምዝገባ አገልግሎት ቡድን ሲሆን ስለ ሲቪል እና ቤተሰብ ምዝገባ የምንተነትንበት፣ ገለፃ የምናደርግበት፣ እርስዎም ሐሳብና አስተያየት በመስጠት የሚሳተፉበት ገፅ ነው፡፡

011 637 51 22

.                                                       ያንብቡ!                                            መልዕክቱንም ለሌሎች ያጋ...
26/03/2026

. ያንብቡ!
መልዕክቱንም ለሌሎች ያጋሩ!
ኩነትን በወቅቱ በማስመዝገብ ኃላፊነትዎን ይወጡ!
የደብረ ብርሃን ከተማ አስተዳደር ሲቪልና ቤተሰብ ምዝገባ አገልግሎት ቡድን

.                                                     ያንብቡ!                                            መልዕክቱንም ለሌሎች ያጋሩ!...
19/03/2026

. ያንብቡ!
መልዕክቱንም ለሌሎች ያጋሩ!
ኩነትን በወቅቱ በማስመዝገብ ኃላፊነትዎን ይወጡ!
የደብረ ብርሃን ከተማ አስተዳደር ሲቪልና ቤተሰብ ምዝገባ አገልግሎት ቡድን

የልደትና ሞት ምዝገባ አፈፃፀምን ለማሻሻል የጤናና ሲቪልና ቤተሰብ ምዝገባ አገልግሎት ቡድን ተቋማት ቅንጅታዊ ድጋፍ ሊጠናከር እንደሚገባ ተገለጸ ። መጋቢት 4/2018 ዓ.ምየደብረ ብርሃን ከተ...
13/03/2026

የልደትና ሞት ምዝገባ አፈፃፀምን ለማሻሻል የጤናና ሲቪልና ቤተሰብ ምዝገባ አገልግሎት ቡድን ተቋማት ቅንጅታዊ ድጋፍ ሊጠናከር እንደሚገባ ተገለጸ ።
መጋቢት 4/2018 ዓ.ም
የደብረ ብርሃን ከተማ አስተዳደር ሲቪልና ቤተሰብ ምዝገባ አገልግሎት ቡድን ከከተማ አስተዳደሩ ጤና መምሪያ ጋር በመቀናጀት ባለፉት ሶስት ቀናት በአንድ ሆስፒታልና በስምንት ጤና ጣቢያ በልደትና ሞት ምዝገባ አተገባበር ዙሪያ ውጤታማ ድጋፋዊ ክትትል አድርጓል ።
በተደረገው ድጋፋዊ ክትትል ከምዝገባ ጣቢያ ጀምሮ የተስተዋሉ በርካታ የአሰራር ክፍተቶችን መሙላት መቻሉን የከተማ አስተዳደሩ ሲቪልና ቤተሰብ ምዝገባ አገልግሎት ቡድን አቶ ሰለሞን ጌታቸው ገልፀዋል ።
በቀጣይ የወቅታዊ ልደት እና ሞት ምዝገባ አፈፃፀምን ለማሻሻል የጤናና ሲቨልና ቤተሰብ ተቋሟት ከሚመለከታቸው የጋራ ቼክሊስት በማዘጋጀት በሆስፒታሎችና ጤና ጣቢያዎች በመገኘት በቀጣዩ ሩብ ዓመት ድጋፍና ክትትል ማድረግ እንደሚገባቸው በማመላከት የጋራ መግባባት መፈጠሩን በድጋፋዊ ክትትሉ ከተሰማሩ ባለሙያዎች ተገልጧል፡፡
በተደረገው ድጋፋዊ ክትትል በርካታ ጥንካሬዎችና ጉድለቶችን በየደረጃው በሚገኙ ጤና ተቋማቱ የሚከሰቱ ኩነቶች በሙሉ አቅም ከማሳወቂያ ወረቀት ጋር በማስተሳሰር እንዲመዘገብ ቡድኑ ተገቢውን ድጋፍና ክትትል ያደርጋል ሲሉ አቶ ሰለሞን ጌታቸው ገልፀዋል ።
በተያያዘም ድጋፋዊ ክትትሉ ክፍተቶችን ከማሳየት ባሻገር በባለሙያ ላይ የታዩ የክህሎት ውስንነቶችን የሞላ መሆኑን ገልፀው ለሆስፒታልና ለክፍለ ከተማ በተሰጠው ግብረ - መልስ መሰረት አስፈላጊውን ማስተካከያ እንደሚያደርጉ አስታውቀዋል ።
በተጨማሪም ወ/ሮ ሰላማዊት አብደላ ከጠየና መምሪያ ለምዝገባ አግልግሎት የሚውል የልደት ሰርተፍኬት በተለመደው አግባብ ዞኑ ለክፍለ ከተሞች እንዲያቀርብና ክፍለ ከተሞችም ለመዝጋቢ ባለሙያዎች በወቅቱ እንዲያስተላልፉና የምዝገባ ስራው ተጠናክሮ እንዲቀጥል አሳስበዋል ።
በአስራ አምስት ሆስፒታሎች ተደረገው ድጋፋዊ ክትትል በተገኙ ጭብጦች ለሚመለከታቸው በያሉበት የቃል ግብረ-መልስ ተሰጥቷቸዋል ።በድጋፍና ክትትሉ አንዳንድ ባለሙያዎች እንዳነሱት የድጋፍና ክትትሉ መደረጉ በክብር መዝገብ ሹሞችና በጤና ኤክስቴንሽን ባለሙዎች መካከል ያለውን ቅንጅታዊ አሰራር እንደሚያጠናክር አስታውቀዋል ።
ከዚህ ቀደም በምዝገባ ስራ ላይ አጋጥሟቸው የነበሩ የአሰራር ክፍተቶችን መፍታት የሚያስችል ዕውቀት ማግኘታቸው ገልፀው ከሚመለከታቸው የሚደረግላቸው ድጋፍ ተጠናክሮ እንዲቀጥል ጠይቀዋል ። ያንብቡ!
መልዕክቱንም ለሌሎች ያጋሩ!
ኩነትን በወቅቱ በማስመዝገብ ኃላፊነትዎን ይወጡ!
የደብረ ብርሃን ከተማ አስተዳደር ሲቪልና ቤተሰብ ምዝገባ አገልግሎት ቡድን

የልደትና ሞት ምዝገባ በሚካሄድባቸው ጤና ጣቢያዎችና ሆስፒታሎች ከከተማ አስተዳደሩ ጤና መምሪያ ጋር በመቀናጀት ድጋፍና ክትትል በማድረግ ላይ ይገኛል።መጋቢት 02/2018 ዓ.ም  የደብረ ብርሃ...
11/03/2026

የልደትና ሞት ምዝገባ በሚካሄድባቸው ጤና ጣቢያዎችና ሆስፒታሎች ከከተማ አስተዳደሩ ጤና መምሪያ ጋር በመቀናጀት ድጋፍና ክትትል በማድረግ ላይ ይገኛል።
መጋቢት 02/2018 ዓ.ም
የደብረ ብርሃን ከተማ አስተዳደር ሲቪልና ቤተሰብ ምዝገባ ቡድን ከከተማ አስተዳደሩ ጤና መምሪያ ጋር በመቀናጀት የወቅታዊ ልደት እና ሞት ምዝገባ በሚካሄድባቸው የተለያዩ ጤና ጣቢያዎችና ሆስፒታሎች የ8 ወር እቅድ አፈጻጸም አስመልክቶ ከመጋቢት 02/2018 ዓ.ም ጀምሮ ድጋፍና ክትትል በማድረግ ላይ ይገኛል። ድጋፍና ክትትሉ በዋነኛነት በዕቅድ አፈፃፀም ፣ በግብአትና ቴክኖሎጂ አጠቃቀም ፣ በግንዛቤ ፈጠራና በቅንጅታዊ ስራዎች ላይ ያተኮረ መሆኑ ተገልፁአል ።

በድጋፍና ክትትሉ ለሚሰማሩ ከከተማ አስተዳደሩ ጤና መምሪያ እና ከሲቪልና ቤተሰብ ምዝገባ ቡድን የተወጣጡ ባለሙያዎች በተዘጋጀው የቸክሊስት ሰነድ ዙሪያ ግልፀኝነት መፈጠሩን አቶ ሰለሞን ጌታቸው አስታውቀዋል።
ድጋፍና ክትትሉ ቀደም ሲል ከነበሩ ጊዜያት የሚለየው በቅርቡ የተጀመረው የታብሌት ኦን-ላይን ቴክኖሎጂ አመዘጋገብ ላይ የገጠሙ ችግሮችን መፍታት የሚያስችል እንደሆነም ተገልፁዋል ።
በምዝገባ ስራው ላይ ጎልተው የወጡ ተሞክሮዎች እና ክፍተቶች በቼክ ሊስቱ መሰረት በየጤና ተቁዋማቱ ይለያሉ ብለዋል ።
በድጋፍና ክትትሉ በተገኙ ጭብጦች ላይ ለሚመከታቸው ባለሙያዎችና አመራሮች የቃል ግብረ-መልስ ተሰጥቷቸዋል ።
በድጋፍና ክትትሉ በታዩ ጥንካሬዎች ፣ጉድለቶችና በቀጣይ የትኩረት አቅጣጫዎች ዙሪያ ለሚመለከታቸው ባለሙያዎችና አመራሮች የጽሁፍ ግብረ-መልስ የሚሰጥ መሆኑን አቶ ሰለሞን ገልፀዋል ።
ያንብቡ!
መልዕክቱንም ለሌሎች ያጋሩ!
ኩነትን በወቅቱ በማስመዝገብ ኃላፊነትዎን ይወጡ!
የደብረ ብርሃን ከተማ አስተዳደር ሲቪልና ቤተሰብ ምዝገባ ቡድን

05/03/2026

የሲቪልና ቤተሰብ ኩነቶችን ማስመዝገብ ግዴታ መሆኑን ያውቃሉ?
= = = = = = = = =
ልደት ከተከሰተ እስከ 90 ቀናት/ ሞት ከተከሰተ እስከ 50 ቀናት/ ጋብቻ፣ ፍቺና ጉድፈቻ በተከሰቱ እስከ 30 ቀናት ውስጥ፤ በቀበሌ ጽ/ቤት ያስመዝግቡ!!
#በልደት ምዝገባ ወቅት መሟላት የሚገባቸው #ቅድመ ሁኔታዎችና #ደጋፊ ማስረጃዎች
 ቅድመ ሁኔታዎች፡-
1. የህፃኑ ወላጆች በህይወት ካሉ አባት እና እናት ሁለቱም ወይም ልደትን ለማስመዝገብ ከአቅም በላይ በሆነ ምክንያት ተገኝቶ ልደቱን ማስመዝገብ ያልቻለው ወላጅ አባት ከሆነ ለህፃኑ ወላጅ እናት ልዩ የልደት ውክልና በመስጠት እንዲሁም ተገኝታ ማስመዝገብ ያልቻለችው ወላጅ እናት ከሆነች ለህፃኑ ወላጅ አባት ልዩ የልደት ውክልና በመሰጠት ልደትን ማስመዝገብ ይችላሉ፡፡
2. ከወላጆቹ አንዱ በህይወት የሌለ እንደሆነ በህይወት ያለው ወላጅ የሟች ወላጅን ህጋዊ የሞት ማስረጃ ሲያቀርብ ልደቱ ይመዘገባል፡፡
3. ችሎታ የሌላቸው ሰዎች በተንከባካቢዎቻቸው ወይም በአሳዳሪዎቻቸው አማካይነት መመዝገብ ይችላሉ፡፡
4. ልደት የሚመዘገበው በህይወት ለተወለደ ወይም በሕይወት ተወልዶ ወዲያውኑ ለሞተ ሲሆን ሞቶ የተወለደ ከሆነ ግን አይመዘገብም፡፡
5. ዕድሜው 18 ዓመትና በላይ የሆነ ልደት ምዝገባ አገልግሎት ፈላጊ ልደቱን ራሱ ማስመዝገብ አለበት፡፡
6. 18 ዓመት ሳይሞላቸው ልጅ የወለዱ ወላጆች የልጃቸውን ልደት ለማስመዝገብ ሲቀርቡ ከሚኖሩበት መደበኛ መኖሪያ ቦታ ካለው ዝቅተኛ አስተዳደር ጽህፈት ቤት ማንነታቸውን የሚገልጽ የድጋፍ ደብዳቤ በማቅረብ ልደቱን ማስመዝገብ ይችላሉ፡፡
7. ዕድሜው 18 ዓመትና በላይ የሆነ ልደት ተመዝጋቢ ወላጆቹን በሚመለከት ቦታ ላይ መረጃውን ካስሞላ በኋላ የወላጅ ፊርማ ቦታ ላይ ሰረዝ (-) ምልክት በማድረግ ይታለፋል፡፡
 ደጋፊ ማስረጃዎች፤-
1. ልደቱ የተከሰተው በጤና ተቋም ከሆነ አስመዝጋቢው ከጤና ተቋም የተሰጠውን የልደት ማሳወቂያ ቅጽ ማቅረብ አለበት፡፡
2. የህጻኑ አሳዳሪ ወይም ተንከባካቢ ልደቱን ለማስመዝገብ ሲቀርብ ከፍርድ ቤት የተሰጠ የአሳዳሪነት ወይም የተንከባካቢነት ሕጋዊ ማስረጃ ማቅረብ አለባቸው፡፡
3. ተጥሎ የተገኘ ህፃንን ለማስመዝገብ የሚመጣ ፖሊስ ወይም አግባብ ያለው የመንግስት አካል ማንነቱን የሚገልጽ ሕጋዊ መታወቂያ ወይም ማስረጃ ማቅረብ አለበት፡፡
4. ከውጭ አገር ወደ ኢትዮጵያ የገቡ ኩነት ምዝገባ ደጋፊ ማስረጃዎች በኢትዮጵያ ኤምባሲና ቆንስላ ጽ/ቤት እና በሰነዶች ምዝገባና ማረጋገጫ ካልተረጋገጡ ተቀባይነት አይኖራቸውም፡፡
ያንብቡ!
መልዕክቱንም ለሌሎች ያጋሩ!
ኩነትን በወቅቱ በማስመዝገብ ኃላፊነትዎን ይወጡ!
የደብረ ብርሃን ከተማ አስተዳደር ሲቪልና ቤተሰብ ምዝገባ ቡድን

ወሳኝ ኩነቶች ሲባል-----------------ወሳኝ ኩነቶች ሲባል አንድ ሰው ወደ ህይወት የሚገባበትና በህይወት ዘመኑ ውስጥ የሚያልፍባቸው ወሳኝ ተፈጥሮአዊና ማህበረሰባዊ ክስተቶች ናቸው፡፡ü...
05/03/2026

ወሳኝ ኩነቶች ሲባል-----------------
ወሳኝ ኩነቶች ሲባል አንድ ሰው ወደ ህይወት የሚገባበትና በህይወት ዘመኑ ውስጥ የሚያልፍባቸው ወሳኝ ተፈጥሮአዊና ማህበረሰባዊ ክስተቶች ናቸው፡፡
ü ተፈጥሯዊ ኩነቶች የሚባሉት፡- ልደት፣ ሞትና የሽል ሞት ሲሆኑ፣
ü ማህበረሰባዊ ኩነቶች የሚባሉት፡- ቀሪዎቹ 7 ኩነቶች ናቸው ፡፡
Ø ከሚሰጣቸው ትኩረት አንፃር ኩነቶች በሦስት ይከፈላሉ። እነዚህም፡-
ከፍተኛ ትኩረት የሚሰጣቸው /first priority/ ኩነቶች፡- ልደትና ሞት፣
መካከለኛ ትኩረት የሚሰጣቸው /second priority/ ኩነቶች፡- ጋብቻ፣ ፍቺና የሽል ሞት፣
ዝቅተኛ ትኩረት የሚሰጣቸው/low priority/ ኩነቶች ቀሪዎቹ 5ቱ ናቸው ፡፡
የተባበሩት መንግስታት ድርጅት የወሳኝ ኩነት ምዝገባ ስርዓትን በአንድ ሀገር ለማደራጀት ቅድሚያ ሊሰጣቸው የሚገቡ ኩነቶች ልደት፣ ሞት፣ ጋብቻና ፍቺ እንደሆኑ ይገልጻል፡፡
ልደትና ሞት በሰው ልጅ ላይ አንድ ጊዜ የሚከሰቱ ተፈጥሮአዊ ክስተቶች ናቸው፡፡ ሰዎች በልደት አማካይነት ወደ ዓለም ህብረተሰብ ይቀላቀላሉ፤ በአንጻሩ በሞት አማካይነት ከዓለም ይለያሉ፡፡ ልደትና ሞት በሰው ልጅ አፈጣጠርና አኗኗር የህይወት መነሻና መድረሻ እርከኖች መለያ ናቸው፡፡ የልደት ኩነት በዚህ ምድር የሰዎች የመኖር ህጋዊ መብት ምንጭ በመሆኑ ማንኛውም ሰው በአንድ በታወቀ የአስተዳደር ክልል ለመኖር ህጋዊ የዜግነትና ማንነት መብት የሚያገኝበትና ለዚህም ማረጋገጫ የሚሆነውን ህጋዊ ሰነድ በመንግስት የሚዘጋጅበት የህይወቱ የመብት መነሻ እርከን ነው፡፡ በአንጻሩ ሞት የዚህ መብት መጨረሻ ወይም መቆሚያ እርከን ነው፡፡
ጋብቻና ፍቺ ሰው “ህጋዊ ሰው” የመሆን መብት በሚያገኝበትና በሚያጣበት የማህበረሰባዊ አኗኗር ስርዓት ውስጥ የሚከሰቱ ዋነኛ የሰዎች ማህበረሰባዊና ህጋዊ አቋም ለውጥ ጠቋሚ ኩነቶች ናቸው፡፡ እነዚህ በግለሰቦች ላይ የሚከሰቱ ተፈጥሮአዊና ማህበረሰባዊ ለውጦች የአንድን ሀገር የህዝብ አስተዳደር በስርዓት ለመምራት መነሻ መሰረቶች ናቸው፡፡
ያንብቡ!
መልዕክቱንም ለሌሎች ያጋሩ!
ኩነትን በወቅቱ በማስመዝገብ ኃላፊነትዎን ይወጡ!
የደብረ ብርሃን ከተማ አስተዳደር ሲቪልና ቤተሰብ ምዝገባ ቡድን

05/03/2026

የሲቪል እና ቤተሰብ የምዝገባ ቦታ
1. ኩነቶችን በተከሰቱበት ቦታ መመዝገብ (Registration by Place of Occurrence)
የሰዉ ልጆች በተለያዩ ምክንያቶች በጊዜያዊነትም ይሁን ለዘለቂታዉ ለመኖር በመደበኛነት ይኖሩበት ከነበረዉ ቦታቸዉ ለቀዉ ሊንቀሳቀሱ ይችላሉ፡፡ ኩነቶች ደግሞ አንድ ሰው ወደ ህይወት የሚገባበትና በህይወት ዘመኑ ውስጥ የሚያልፍባቸው ተፈጥሮአዊና ማህበረሰባዊ ክስተቶች በመሆናቸዉ ሰዎች በእያሉበት ቦታ ሁሉ ይከሰታሉ፡፡ እነዚህን በእንቅስቃሴ ላይ ባሉ ሰዎች የተፈጠሩ ኩነቶችን ለመመዝገብ ሰዎቹ ወደ መደበኛ መኖሪያ ቦታቸዉ መመለስ ሳይኖርባቸዉ ኩነቱ በተፈጠረበት አካባቢ በሚገኝ የምዝገባ ጽ/ቤት የመመዝገብ ሂደት ኩነቶች በተፈጠሩበት ቦታ ምዝገባ (Registration by place of occurrence) ይባላል፡፡ ኩነቶችን በተከሰቱበት ቦታ ከሚመዘግቡ አገሮች ዉስጥ ህንድን በምሳሌነት መጥቀስ ይቻላል፡፡
2. በመደበኛ መኖሪያ ቦታ መመዝገብ (Registration by Place of Residence)
ይህ አመዘጋገብ ኩነቶች የትም ቦታ ይከሰቱ ወይም ይፈጠሩ ምዝገባዉ የሚካሄደዉ የኩነቱ ባለቤቶች (ኩነቱ የተከሰተላቸዉ ግለሰቦች) በመደበኛነት በሚኖሩበት አካባቢ በሚገኝ የምዝገባ ጽ/ቤት ይሆናል፡፡ በአገራችን ኢትዮጵያ የወሳኝ ኩነቶችን ምዝገባ ስርዓት ለመዘርጋት በወጣዉ ህግ ማለትም በወሳኝ ኩነቶች ምዝገባ እና የብሔራዊ መታወቂያ አዋጅ ቁጥር 760/2004 መሰረት የኩነቶች ምዝገባ ሚካሄደዉ የኩነቱ ባለቤቶች በመደበኛነት በሚኖሩበት ቦታ እና በተለየ ሁኔታ አንዳንድ ኩነቶች ከመደበኛ መኖሪያ ቦታ ዉጭ እንደሆነ በግልጽ ተቀምጧል፡፡ ይህ ማለት አንድ የትዉልድ ቦታዉ ጎንደር ከተማ የሆነ እና በመደበኛነት እየሰራ የሚኖርበት ቦታ ደግሞ ባህርዳር ከተማ የሆነ ሰው ልደቱን አስመዝገቦ የልደት የምስክር ወረቀት ማዉጣት ቢፈልግ ወደ ትዉልድ ቦታዉ ጎንደር መሄድ ሳይጠበቅበት ባህር ዳር በሚኖርበት ቀበሌ በሚገኝ የወሳኝ ኩነቶች ምዝገባ ጽ/ቤት የኗሪነት መታወቂያ ይዞ በመሄድ የልደት ምስክር ወረቀት ማዉጣት ይችላል፡፡
ያንብቡ!
መልዕክቱንም ለሌሎች ያጋሩ!
ኩነትን በወቅቱ በማስመዝገብ ኃላፊነትዎን ይወጡ!
የደብረ ብርሃን ከተማ አስተዳደር ሲቪልና ቤተሰብ ምዝገባ ቡድን

05/03/2026

ወሳኝ ኩነት እና ወንጀል መከላከል
የወሳኝ ኩነት ምዝገባ ማስረጃዎች በዋናነት እና ያለምንም ተጨማሪ መረጃ አገልግሎት ከሚሰጡባቸው ዘርፎች መካከል የህግ ዘርፍ ተጠቃሽ ነው፡፡ በህግ ፊት የወሳኝ ኩነት ምዝገባ ማስረጃዎች እራሳቸውን ችለው ያለምንም ተጨማሪ የሰው ምስክር ፍትህ ለመስጠት እንደሚያገለግሉ በተለያዩ ህጎች ላይ በግልፅ ተቀምጧል፡፡
በሌላ በኩል በግለሰቦች ላይ የሚከሰቱ የተለያዩ ኩነቶች በወሳኝ ኩነት ምዝገባ ፅ/ቤቶች በኩል ሲመዘገቡ ህጋዊነትን ያገኛሉ፡፡
ለምሳሌ ሁለት ተጋቢዎች ጋብቻ ቢፈፅሙ ወደ ወሳኝ ኩነት ምዝገባ ፅ/ቤት ቀርበው ሲያስመዘግቡ ጋብቻዉ ህጋዊ ከመሆንም አልፎ ኩነቱን አስመዝግበው የሚያገኙት የጋብቻ ምስክር ወረቀት ጋብቻቸውን በተመለከተ ያለምንም ተጨማሪ ምስክር ዋና ህጋዊ ማስረጃ ሆኖ ያገለግላል፡፡
የወሳኝ ኩነት ምዝገባ ማስረጃዎች ወንጀልን ከመከላከል ረገድ ምን አስተዋፅኦ አላቸው የሚለውን ስንመለከት ከላይ በጠቀስነው ምሳሌ መሰረት አንድ ጋብቻ ተመዝግቦ የምስክር ወረቀት በሚያገኝበት ጊዜ በጋብቻ ላይ ጋብቻ እንዳይፈፀም አብይ ማስረጃ ሆኖ ያገለግላል፤ የተጋቢዎችን ዝምድናና ግንኙነት ህጋዊነት ለማረጋገጥ ያገለግላል፣
ከተጋቢዎቹ አንዱ ህይወት በሚያልፍበት ጊዜ ህጋዊ ወራሽትን ለማረጋገጥ እና ንብረቱ ለሌላ ውርስ ለማይገባው ሰው እንዳይተላለፍ ለመከላከል ይረዳል ።
ከዚህ በተጨማሪም ልጆች በጋብቻ ውስጥ መወለዳቸውን እና ህጋዊ ልጅ መሆናቸውን ለማረጋገጥ ይረዳል፡፡
የፍቺ ማስረጃን በምንመለከትበት ጊዜ ፍቺ ለመፈፀሙ ህጋዊ ማስረጃ በመሆን እንደገና የማግባት ጥያቄን በህግ ለማቅረብ፣ከፍቺ በኋላ ስለተወለዱ ልጆች ህጋዊ መረጃ ለመሆን ፤ከፍቺ በኋላ በአንዳቸው የቀድሞ የትዳር ጓደኛ ምክንያት ከሚመጡ የገንዘብም ሆነ የንብረት ጥያቄዎች እዳ ከመጠየቅ ነፃ ለመሆን ከዚህም በተጨማሪ ፍቺው ለተፈፀመበት ቀን እና ቦታ ህጋዊ ማስረጃ በመሆን ከዛ ውጪ የሚመጡ የተጭበረበሩ መረጃዎችን በህግ ፊት ውድቅ ለማድረግ ከፍተኛ አስተዋፅኦ አለው፡፡
የሞት እና የልደት ማስረጃዎችም በተመሳሳይ ለህግ እና ወንጀልን ለመከላከል አገልግሎት በሰፊው የሚውሉ ሲሆን የልደት ማስረጃን በሚመለከት የማንነት ህጋዊ መሰረት በመጣል የህፃን/ኗን ህጋዊ ማንነት ማረጋገጥ፣ የወላጆችን ማንነት በማረጋገጥ ከወላጅ ማንነት ጋር በተያየዘ የሚፈፀሙ ወንጀሎችን አስቀድሞ ለማወቅ እና ለመከላከል ይረዳል፡፡ የሞት ማስረጃም እንዲሁ የሞት ምክንያት፣ሞቱ የተከሰተበትን ጊዜ እና ቦታ በማሳወቅ ከአንድ ሰው ሞት ጀርባ ያለውን ሁኔታ ለማወቅ ዋነኛ የመረጃ ምንጭ ሆኖ ያገለግላል፡፡
ከላይ እንደተገለፀው የወሳኝ ኩነት መረጃዎች ወንጀል እንዳይፈፀም ለመከላከል የሚያገለግሉ አብይ መረጃዎች ሲሆኑ ወንጀል ተፈፅሞ ሲገኝም አስፈላጊውን ውሳኔ ለማስተላለፍ ለፍትህ አካላት ዋና ማስረጃ ሆነው ያገለግላሉ፡፡
ያንብቡ!
መልዕክቱንም ለሌሎች ያጋሩ!
ኩነትን በወቅቱ በማስመዝገብ ኃላፊነትዎን ይወጡ!
የደብረ ብርሃን ከተማ አስተዳደር ሲቪልና ቤተሰብ ምዝገባ ቡድን

Address

Debre Birhan

Website

Alerts

Be the first to know and let us send you an email when የደብረ ብርሃን ከተማ አስተዳደር ሲቪል እና ቤተሰብ ምዝገባ አገልግሎት ቡድን posts news and promotions. Your email address will not be used for any other purpose, and you can unsubscribe at any time.

Share