የደብረብርሃን ከተማ ብልጽግና ፓርቲ ጽ/ቤት

የደብረብርሃን ከተማ ብልጽግና ፓርቲ ጽ/ቤት የደብረብርሃን ከተማ ብልጽግና ፓርቲ ጽ/ቤት የእናንተው ቀዳሚ የመረጃ ምንጭ ነው Like Share Invite ያድርጉ እናመሰግናለን
ኢትዮጵያን እና ህዝቦቿን ፈጣሪ ይባርክ

"ምርጫው በሰላም እንዲጠናቀቅ በቂ እና አስተማማኝ የጸጥታ ዝግጅት ተደርጓል" እሸቱ የሱፍ (ዶ.ር) 7ኛው ጠቅላላ ምርጫ በሰላም እንዲከናወን የቅድመ ዝግጅት ሥራዎች ሲከናወኑ መቆየታቸውን  የ...
27/05/2026

"ምርጫው በሰላም እንዲጠናቀቅ በቂ እና አስተማማኝ የጸጥታ ዝግጅት ተደርጓል" እሸቱ የሱፍ (ዶ.ር)

7ኛው ጠቅላላ ምርጫ በሰላም እንዲከናወን የቅድመ ዝግጅት ሥራዎች ሲከናወኑ መቆየታቸውን የአማራ ክልል ሰላም እና ጸጥታ ቢሮ ኀላፊ እሸቱ የሱፍ (ዶ.ር) ገልጸዋል።

ምርጫው በሰላማዊ መንገድ እንዲካሄድ ለማስቻል በምርጫ ክልል እና በምርጫ ጣቢያዎች የሰው ኀይል ሥምሪት መደረጉንም ጠቁመዋል።

በተለይም በምርጫው ዕለት የሰላም እና የጸጥታ ችግሮች እንዳይፈጠሩ የክልሉ የጸጥታ ኀይል ከፌዴራል የጸጥታ መዋቅር ጋር በመቀናጀት ወደ ሥራ መገባቱን ዶክተር እሸቱ የሱፍ አረጋግጠዋል።

አሁን ላይ በክልሉ ባሉ ሁሉም የምርጫ ክልሎች እና ጣቢያዎች መራጩ ድምጹን መስጠት የሚችልበት አስተማማኝ ሰላም መኖሩን እና በቂ የጸጥታ ዝግጅት መደረጉንም ኀላፊው አብራርተዋል።

የጸጥታ ኀይሉ በተጠንቀቅ የቆመው ለሀገር ሉዓላዊነት እና ሕዝቡ ይመራኛል ብሎ ያመነበትን መንግሥት በሰላም እና በነጻነት እንዲመርጥ ነው ብለዋል።

የክልሉ መንግሥት ምርጫን ለማደናቀፍ የሚንቀሳቀስን ኀይል እንደማይታገስ ያነሱት ኀላፊው እንዲህ ዓይነት ክስተቶችን የጸጥታ ኀይሉ በአግባቡ የመምራት እና እርምጃ የመውሰድ ኀላፊነቱን እንደሚወጣም አረጋግጠዋል።

በደብረ ብርሃን ከተማ የጫጫ ክፍለ ከተማ የነጋዴ ሴቶች ማህበር የገበያ ማዕከል ግንባታ የመሠረት ድንጋይ ተቀመጠ​በደብረ ብርሃን ከተማ አስተዳደር የጫጫ ክፍለ ከተማ የነጋዴ ሴቶች ማህበር በባ...
27/05/2026

በደብረ ብርሃን ከተማ የጫጫ ክፍለ ከተማ የነጋዴ ሴቶች ማህበር የገበያ ማዕከል ግንባታ የመሠረት ድንጋይ ተቀመጠ

​በደብረ ብርሃን ከተማ አስተዳደር የጫጫ ክፍለ ከተማ የነጋዴ ሴቶች ማህበር በባለቤትነት የሚያስተዳድረው ባለ 5 ወለል (G+5) ዘመናዊ የገበያ ማዕከል ግንባታ የመሠረት ድንጋይ በይፋ ተቀመጠ።

​በ6,400 ካሬ ሜትር ቦታ ላይ የሚያርፈው ይህ ታላቅ የገበያ ማዕከል፣ 200 የሴት ነጋዴዎችን በጋራ በማስተባበር የሚገነባ ሲሆን፣ የከተማዋን የንግድ እንቅስቃሴ በማዘመን ረገድ የላቀ ፋይዳ ይኖረዋል ተብሎ ይጠበቃል።

​በመሠረት ድንጋይ ማስቀመጫ ሥነ-ሥርዓቱ ላይ ተገኝተው ንግግር ያደረጉት የደብረ ብርሃን ከተማ አስተዳደር ከንቲባ ጽሕፈት ቤት ኃላፊ አቶ በኃይሉ ገብረህይወት፣ ማህበሩ የጀመረው ይህ የተቀናጀ የልማት ስራ ለሌሎችም ሴት ነጋዴዎች አርአያ የሚሆን መሆኑን ገልጸዋል። አያይዘውም፣ "የሴቶችን ኢኮኖሚያዊ ተጠቃሚነት ለማረጋገጥ የሚደረጉ ጥረቶች የከተማችን የብልጽግና ጉዞ አካል ናቸው" ብለዋል።

​የደብረ ብርሃን ከተማ አስተዳደር ንግድ መምሪያ ኃላፊ አቶ ወ/ሮ ይርጋለም ምስጋናው በበኩላቸው፣ የገበያ ማዕከሉ ግንባታ ከተማዋን ለኢንቨስትመንት ምቹ ከማድረጉም ባሻገር፣ የንግድ ሥርዓቱን በዘመናዊ መንገድ ለመምራት ከፍተኛ ሚና እንደሚኖረው ጠቁመዋል።

መምሪያው ግንባታው በተያዘለት ጊዜ እንዲጠናቀቅ አስፈላጊውን የቴክኒክ ድጋፍ እና ክትትል እንደሚያደርግም ተናግረዋል።

​የጫጫ ክፍለ ከተማ ዋና ሥራ አስፈጻሚ አቶ አይደፈር የሺጥላ በንግግራቸው፣ ማህበሩ ይህንን ግዙፍ ፕሮጀክት ለመጀመር ላሳየው ጥንካሬ ምስጋና አቅርበዋል።

የክፍለ ከተማው አስተዳደርም የፕሮጀክቱን ስኬታማነት ለማረጋገጥ ከማህበሩ ጎን እንደሚቆም ገልጸዋል።

በዚሁ መድረክ የደብረብርሃን ኢንቨስትመንት መምሪያ ኃላፊ እና የመሬት መምሪያ ምክትል ኃላፊ ተገኝተው ፕሮጀጅቱ ውጤታማ እንዲሆን አስፈላጊውን ድጋፍ እና ክትትል እንደሚያደርጉ ገልጸዋል።

​የማህበሩ አባላት በበኩላቸው፣ የገበያ ማዕከሉ መጠናቀቅ የንግድ አቅማቸውን እንደሚያሳድግ እና በከተማዋ የንግድ ዘርፍ ያላቸውን ተሳትፎ ወደ ላቀ ደረጃ እንደሚያሸጋግረው በመግለጽ፣ ግንባታው እንዲፋጠን ያላቸውን ቁርጠኝነት አሳይተዋል።

​ይህ የገበያ ማዕከል ግንባታ ሲጠናቀቅ ለበርካታ የከተማዋ ነዋሪዎች ምቹ የመገበያያ አማራጭ ከመፍጠሩም በላይ፣ የሴቶችን የኢኮኖሚ አቅም በመገንባት በኩል ትልቅ ምዕራፍ እንደሚሆን ይጠበቃል።

ትናንት፣ ዛሬና ነገ....በሀገራችን ውስጥ በሚዛን ሊያዝ የሚገባው ነገር በትናንት፣  በዛሬና በነገ መካከል ያለው ምልከታ ነው፡፡ ትናንትን ፈፅሞ የመቀደስም ሆነ ትናንትን ፈፅሞ የማርከስ ጉዞ...
27/05/2026

ትናንት፣ ዛሬና ነገ....

በሀገራችን ውስጥ በሚዛን ሊያዝ የሚገባው ነገር በትናንት፣ በዛሬና በነገ መካከል ያለው ምልከታ ነው፡፡ ትናንትን ፈፅሞ የመቀደስም ሆነ ትናንትን ፈፅሞ የማርከስ ጉዞ ሀገርን ያለ ወረት ያስቀራል።

ዛሬንና ነገን ማቃለልም ሆነ ዛሬና ነገን የሁሉም ነገር መጀመሪያ ማድረግ ሀገርን ያለ መነሻ ያስቀራል፡፡ ብልፅግና ትናንት ከዛሬና ከነገ ጋር በሚዛን የሚታይበትን መርሕ ይከተላል፡፡

• ከትናንቱ መልካሙን መውሰድ፤ እንከኑን ማረም
• ዛሬን፣ በትናንት መሠረት ላይ ገንብቶ በሚገባ መጠቀም
• ለነገ ተግባብቶ ወረት ማቆየት

ትናንትን ከዛሬና ነገ ጋር በሚዛን ለማየት እንዲቻል፣ የትናንት ቁርሾዎችን የምናክምባቸው፣በትናንትጉዞ ላይ የምንግባባባቸው ፤ ነገን በጋራ የምንተልምባቸው መንገዶችን መከተል አለብን ብሎ ያምናል፡፡

እነዚህም፡-
👉በሰከነ ምክክር አዲስ ቃል ኪዳን ማሠር ፤

ጠንካራና ቅቡልነት ያለው ሀገረ መንግሥት በፅኑ መሠረት ላይ ለመገንባት፣ ሀገራዊ መግባባትን መፍጠር እንደሚያስፈልግ ፓርቲያችን በቀዳሚነት አስቀምጧል፡፡ለዘመናት በመሠረታዊ ሀገራዊ ጉዳይ እንኳን ያላግባቡን ጉዳዮች በሀገራዊ ምክክር ምላሽ እንዲያገኙ ቁርጠኛ አቋምም አለው። ፓርቲያችን ብሔራዊ መግባባት ለሀገረ መንግሥቱ ግንባታ የማዕዘን ድንጋይ እንደሆነ ያምናል።

የፖለቲካ ማኅበረሰቡ የትናንት ቅራኔዎችን በመግባባትና በዕውቅና፣ በዕርቅና በሽግግር ፍትሕ መፍታት እንዳለበት እናምናለን፡፡ ስለዚህም በስክነትና በዕውቀት፣ ሀገራዊ ምክክሩ እንዲሠምር ሕዝባችንና የፖለቲካ ልሂቃን አዎንታዊ ሀገራዊ ድርሻቸውን እንዲወጡ ጥሪ አናቀርባለን።

በዚህ የጸና እምነታችንና መሻታችን የተነሣ የኢትዮጵያ ሀገራዊ የምክክር ኮሚሽንን በማቋቋም ሂደት እንደ ፓርቲና እንደ መንግሥት የሚጠበቅብንን አድርገናል፡፡

የሕዝብ ተሳትፎን በማረጋገጥ፣ ለኮሚሽኑ ሥራ አስፈላጊ የሆኑትን የፋይናንስ፣ የሎጀስቲክስና የመረጃ አቅርቦቶችን ያለተዐቅቦ በማሟላት፣ እንዲሁም ነጻነቱን በማክበር ባለፈው ምርጫ ዘመን ቃል የገባንውን በተግባር ፈፅመናል።

በቀጣይ አምስት ዓመታትም፡-

በኢትዮጵያ ሀገራዊ የምክክር ኮሚሽን መሪነት በሂደት የሚደረስባቸው ውሳኔዎችና ምክረ ሐሳቦች ይኖራሉ ብለን ተስፋ እናደርጋለን፡፡

እነዚህን ውሳኔዎችና ምክረ ሐሳቦች ወስደን ለሕገ መንግሥት ማሻሻያዎች፣ ለፖለቲካ ሥርዓት ማሻሻያዎች፣ ለሰብአዊ መብቶች ማሻሻያዎች እና ለቀደሙ በደሎች የመፍትሔ መንገዶች አድርገን እንደ ፓርቲና መንግሥት ለመፈጸምና ለማስፈጸም እንሠራለን።

👉በሽግግር ፍትሕ መሥመር፤ ቁርሾን መሻር ፤

በኢትዮጵያ ለዘመናት የኖሩ በደሎች፣ ቁርሾዎችና የሰብአዊ መብት ጥሰቶች አሉ፡፡ እነዚህን በተመለከተ ፈውስ የሚሰጥ ፍትሕን እና ይቅርታን ለማረጋገጥ የሽግግር ፍትሕ እንደሚያስፈልገን ፓርቲያችን ያምናል። ይህንን መሠረት በማድረግም ባለፉት ዓመታት ሕጋዊና ተቋማዊ ሥራዎች ተጀምረዋል፡፡

በቀጣይ ዓመታትም፡-

ለተፈጸሙ በደሎች እና የሰብአዊ መብት ጥሰቶች በሽግግር ፍትሕ ማዕቀፍ የወንጀል ምርመራና ክስ፣ እውነትን የማፈላለግ እና ይፋ የማውጣት ተግባር፣ በቅድመ ሁኔታ ላይ የተመሠረተ ምሕረት፣ ግለሰባዊ እና ማኅበረሰባዊ ዕርቅ ለማስፈን እንሠራለን፡፡

ይህንንም ተግባራዊ ለማድረግ ሕጋዊና ባህላዊ መንገዶችን እንጠቀማለን፤ ማካካሻና ተቋማዊ ማሻሻያን ይተገበራል።በዚህም ተጎጂዎችን ማዕከል ያደረገ የሽግግር ፍትሕ እንደ ሀገር እንዲተገበር እንሠራለን።

የብሔራዊ መግባባት፣ የዕርቅና የፍትሕ ሂደት እንዲሠምር የሀገራትን ተሞክሮ ከሀገራዊ ነባራዊ ሁኔታ ጋር አስማምተን እንጠቀማለን። እንዲሁም ባሕላዊ የግጭት አፈታትና የዕርቀ ሰላም ሥርዓቶችን እንደየአካባቢው እንተገብራለን፡፡ ይህንንም በማድረግ ሀገራዊ አንድነታችንን እና ብሔራዊ መግባባታችንን እናጠናክራለን፡፡

የሽግግር ፍትሕ ሂደት ከተፅዕኖ እና ከፖለቲካዊ ጣልቃ ገብነት ነጻ እና ገለልተኛ ሆኖ እንዲከናወን እናደርጋለን፡፡ ተአማኒነቱን እና ቅቡልነቱን ለማረጋገጥ፣ ሐቅ አፈላላጊ ኮሚሽን፣ ልዩ ዐቃቤ ሕግና ልዩ ችሎት ይቋቋምለታል፡፡

በእነዚህ ተቋማት በሚመራ ምርመራና ዳኝነት አማካኝነት እንዲከናወን በማድረግ፣ የሽግግር ፍትሕ ያስቀመጣቸውን ብሔራዊ ግቦች እንዲመታ እናደርጋለን።

👉የተሐድሶ ፕሮግራም ፤

በተለያዩ አካባቢዎች ነፍጥ አንግተው ጫካ የገቡ አካላት ወደ ሰላም መንገድ እንዲመጡ ፓርቲያችን ሲሠራ ቆይቷል፡፡ በዚህ መንገድም በሺዎች የሚቆጠሩ ታጣቂዎች የሰላም አማራጭን ተቀብለው ገብተዋል።

እነዚህ ታጣቂዎች በተሐድሶ ፕሮግራም ውስጥ እንዲያልፉ ማድረግ ይገባናል፡፡ ታጣቂ ቡድኖች እንዲበተኑ፤ ታጣቂዎች ትጥቅ እንዲያወርዱ እና ወደ ሰላማዊው መንገድ እንዲቀላቀሉ ለማድረግ የቦታ፣ የገንዘብ፣ የቴክኒክ እና የሥነ ልቦና ዝግጅት ይፈልጋል፡፡

ለዚህ ታላቅ ተግባር የሚያስፈልገውን የሰው ኃይል፣ የበጀትና የቁሳቁስ ዝግጅት በማከናወን የተሐድሶን ፕሮግራም በተሟላ መልኩ ለማከናወንና የጸና ሰላምን ለመመሥረት ፓርቲያችን ይሠራል፡፡



#ኢትዮጵያንወደተምሳሌትሀገር
#ብልፅግናፓርቲንይምረጡ

የብልጽግና ፓርቲ የምርጫ ዕጩዎች ይፋ ተደረጉ! 🗳️🇪🇹​የብልጽግና ፓርቲ ለ7ኛው ሀገራዊ ምርጫ የደብረ ብርሃን ከተማ አስተዳደርን ወክለው የሚወዳደሩ ዕጩዎቹን አስተዋውቋል። በዚሁ መሰረት ለሕ...
27/05/2026

የብልጽግና ፓርቲ የምርጫ ዕጩዎች ይፋ ተደረጉ! 🗳️🇪🇹

​የብልጽግና ፓርቲ ለ7ኛው ሀገራዊ ምርጫ የደብረ ብርሃን ከተማ አስተዳደርን ወክለው የሚወዳደሩ ዕጩዎቹን አስተዋውቋል። በዚሁ መሰረት ለሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት እና ለክልል ምክር ቤት የሚወዳደሩት ዕጩዎች ዝርዝር እንደሚከተለው ቀርቧል፦

​📌 ለሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት (የፓርላማ) ዕጩዎች፡
​የተከበሩ ወ/ሮ ገነት ቤተ - የደብረ ብርሃን ከተማ ምርጫ ክልል ዕጩ
​📌 ለክልል ምክር ቤት ዕጩዎች፡
✨​የተከበሩ አቶ በድሉ ውብሸት - የደብረ ብርሃን ከተማ ምርጫ ክልል ዕጩ
✨​የተከበሩ ወ/ሮ ይርጋለም ምስጋናው - የደብረ ብርሃን ከተማ ምርጫ ክልል ዕጩ

​🌾 የብልጽግና ፓርቲ የምርጫ ምልክት "ስንዴ" ነው!

​ኢትዮጵያን ወደ ተምሳሌት ሀገር 🇪🇹✨
​ #ብልጽግና #ምርጫ2018 #ደብረብርሃን #ኢትዮጵያ

27/05/2026

ኢትዮጵያን ወደ ተምሳሌት ሀገር!
ብልፅግናን ይምረጡ!


‎‎
‎‎

ዜና እረፍትጥልቅ የሀዘን መግለጫየእቴጌ ጣይቱ ክፍለ ከተማ የሚሊሻ ጽ/ቤት ኃላፊ 10 አለቃ ተ/አረጋይ ጌታቸው በደረሰባቸው ድንገተኛ አደጋ ህይወታቸው አልፏል ።10 አለቀ ተ/አረጋይ ጌታቸው ...
27/05/2026

ዜና እረፍት
ጥልቅ የሀዘን መግለጫ

የእቴጌ ጣይቱ ክፍለ ከተማ የሚሊሻ ጽ/ቤት ኃላፊ 10 አለቃ ተ/አረጋይ ጌታቸው በደረሰባቸው ድንገተኛ አደጋ ህይወታቸው አልፏል ።

10 አለቀ ተ/አረጋይ ጌታቸው ባለትዳር እና የአንድ ሴትና የአራት ወንድ አባት ነበሩ ።

10 አለቃ ተ/አረጋይ በ1990--1993 በኢትዮ-ኤርትራ ዘምተው ለሀገር ውለታ የከፈሉና በቦርድ የተሰናበቱ፣ ከ2005 ዓ/ም ጀምሮ እስከ 2016 ዓ/ም በደብረብርሃን ከተማ ህዝባዊ ሚሊሻነት ህዝብን ያገለገሉ ነበሩ።

በ2013-2014 ዓ/ም ሀገር ችግር ውስጥ በገጠማት ወቅት በሰሜኑ ጦርነት ከ4 ጊዜ በላይ የሰላም አስከባሪና ሚሊሻን ይዘው በጀግንነት ተዋግተዋል።

ከ25/01/2016 ዓ/ም የእቴጌ ጣይቱ ክፍለ ከተማ ሰላም አስከባሪ ባለሙያ ሆኖ ያገለገለ።

ከ05/10/2016ዓ/ም የእቴጌ ጣይቱ ክፍለ ከተማ የሚሊሻ ጽ/ቤት ፀጥታ ስምሪት ቡድን መሪ ሆኖ የሰሩ።

ከ16/11/2017ዓ/ም አስከ ህይወታቸው እስከ አለፈበት ሰዓት ድረስ የህዝብን አደራ ተወጥተዋል ።

እንደ አንድ የህዝብ አደራ እንደተቀበለ አመራር እና እንደ ተወላጅ ከተማዋ የሚገባትን እድገትና ማዕረግ እንድታገኝ እንዲሁም ነዋሪዎቿ ሁሉን አቀፍ ተጠቃሚነታቸው እንዲረጋገጥ በከፍተኛ ቁጭት እየሰሩ የሚገኙ ብርቱ አመራር ነበሩ ።

10 አለቃ ተ/አረጋይ ጌታቸው ነፍሳቸውን በአጸደ ገነት እንዲያኖርልን ፤ ለወዳጅ ዘመዶቹ እንዲሁም ለቤተሰቦቹ ደግሞ መጽናናትን ከልብ እንመኛለን።

ቀብሩም በእቴጌ ጣይቱ ክፍለ ከተማ በቅዱስ ጊዮርጊስ ቤተክርስቲያን ከቀኑ 6 ስዓት ወዳጅ ዘመዶቻቸው በተገኙበት የስርዓት ቀብራቸው ተፈፅሟል።

1 ሺህ 447ኛው ኢድ አል አድሃ(አረፋ) በዓል  ደብረ ብርሃን ከተማ በድምቀት ተከበረ፤በበዓሉ ላይ የደብረ ብርሃን ከተማ  አስተዳደር  ለመስጂድ  መስሪያ እና  ለመቃብር ቦታ ከ5 ሺህ ካሬ ...
27/05/2026

1 ሺህ 447ኛው ኢድ አል አድሃ(አረፋ) በዓል ደብረ ብርሃን ከተማ በድምቀት ተከበረ፤

በበዓሉ ላይ የደብረ ብርሃን ከተማ አስተዳደር ለመስጂድ መስሪያ እና ለመቃብር ቦታ ከ5 ሺህ ካሬ ሜትር በላይ የይዞታ ማረጋገጫ አስረከበ፤

የደብረ ብርሃን ከተማ ተቀዳሚ ከንቲባ አቶ በድሉ ውብሸት በበዓሉ ላይ ተገኝተው እንደተናገሩት፣ ደብረ ብርሃን የቆየው የአብሮነት፣የመከባበር፣የአንድነት እሴታችን መገለጫ ከተማ መሆኑን አንስተዋል።

ከተማ አስተዳደሩ የሙስሊሙን ማኅበረሰብ ጥያቄ በመመለስ ፍትሃዊ ተጠቃሚነት እንዲረጋገጥ እየሰራ መሆኑን አስታውቀዋል።

ዛሬም በዚህ ታላቅ በዓል ላይ የምስራች ይዘው መምጣታቸውን ጠቁመው፣ ቀደም ሲል ለቀረበላቸው ጥያቄ ምላሽ የሚሆን ለመስጂድ መስሪያ እና ለመቃብር ቦታ 5 ሺህ 300 ካሬ ሜትር ለከተማው እስልምና ጉዳዮች ምክር ቤት ማስረከባቸውን አስታውቀዋል።

የከተማው ሙስሊም ሰላም ወዳድ በመሆኑ ለከተማው የኢንዱስትሪ ዕድገት እና ሁሉን አቀፍ ልማት አስተዋጽኦ ከፍተኛ መሆኑን በመግለጽ ወደፊትም ተሳትፏቸው ተጠናክሮ እንዲቀጥል ጥሪ አቅርበዋል።

በዓሉን ስናከብር የተቸገሩትን በማሰባሰብ፣ በመደገጋፍና የተገኘውን በጋራ በመካፈል ሊሆን ይገባል ብለዋል።እጅ ለእጅ ተያይዘን የከተማችንን ሰላም በማስከበር ልማቷንና ዕድገቷን እናስቀጥል ሲሉም አክለዋል።

በመጨረሻም በዓሉ የደስታ፣የፍቅርና የአንድነት እንዲሆን መልካም ምኞታቸውን ገልጸዋል።

የደብረ ብርሃን ከተማ እስልምና ጉዳይ ምክር ቤት ተሰብሳቢ ኡስታዝ አህመድ መሐመድ አማን እንደተናገሩት፣ከለውጡ መንግሥት በፊት ሙስሊሙ ማኅበረሰብ ለሚያነሻቸው ጥያቄዎች ፍትሃዊ ምላሽ ከመስጠት ይልቅ የተለያዩ ስም እየተለጠፈበት ይሸማቀቅ እንደነበር አስታውሰዋል።

ዛሬ ግን ያ የጨለማ ታሪክ ተቀይሯል። መጅሊሳችን አዲስ አደረጃጀት ይዞ ወደ ሥራ ከገባ ጀምሮ፣ የእናንተን የዘመናት ጥያቄዎችና ብሶቶች ይዞ ወደ ከተማው አስተዳደር ሲመላለስ መቆየቱን አስታውሰው፣ከተማ አስተዳደሩ ለመስጂድ መስሪያ 3 ሺህ ካሬ ሜትር እና ለመቃብር ቦታ 2 ሺህ 300 ካሬ ሜትር ስላስረከባቸው አመስግነዋል።

በሂደቱ ክቡር ከንቲባ በድሉ በቢሮ ብቻ ሳይሆን መስክ ድረስ እየሄዱና ክትትል እያደረጉ በዚህ በተቀደሰ ቀን ይህን ታላቅ የምስራች ስላሰሙን በሙስሊሙ ማኅበረሰብ ስም አመሰግነዋለሁ ብለዋል።

በዓሉ የአብሮነት፣የመተሳሰብና የፍቅር መሆኑን የበዓሉ ተሳታፊዎች በሰጡት አስተያየት አመልክተዋል።

27/05/2026

ግንቦት 24 በሚካሄደው ጠቅላላ ምርጫ የስንዴ ነዶ ላይ ምልክት በማድረግ ብልፅግና ፓርቲን ይምረጡ!

ኢትዮጵያን ወደ ተምሳሌት ሀገር!

#ብልፅግናፓርቲንይምረጡ


የደብረብርሃን ከተማ ብልጽግና ፓርቲ ጽ/ቤት

 #ምርጫችን= ብልጽግና #ምልክታችን= የስንዴ ነዶ #መልዕክታችን= ኢትዮጵያን ወደ ተምሣሌት ሀገር!!
27/05/2026

#ምርጫችን= ብልጽግና
#ምልክታችን= የስንዴ ነዶ
#መልዕክታችን= ኢትዮጵያን ወደ ተምሣሌት ሀገር!!

"ከመከፋፈል ይልቅ አብሮነትን፤ ከልዩነትን ይልቅ አንድነትን አስቀድመን በጋራ ለሀገራችን ሰላም እና ልማት መሥራት ይኖርብናል" ርእሰ መሥተዳደር አረጋ ከበደርእሰ መሥተዳደር አረጋ ከበደ ለኢድ...
27/05/2026

"ከመከፋፈል ይልቅ አብሮነትን፤ ከልዩነትን ይልቅ አንድነትን አስቀድመን በጋራ ለሀገራችን ሰላም እና ልማት መሥራት ይኖርብናል" ርእሰ መሥተዳደር አረጋ ከበደ

ርእሰ መሥተዳደር አረጋ ከበደ ለኢድ አል አድሃ በዓል ያስተላለፉት መልእክት ቀጥሎ ቀርቧል።

እንኳን ለኢድ አል አድሃ በዓል አደረሳችሁ!

የኢድ አል አድሃ (አረፋ) በዓለ ስለእውነት መስዕዋት መሆንን ያስረዳናል። ፍጹም መታመን የተረጋገጠበት ዕለት ነው።

የኢድ አል አድሃ የእርስ በርስ ግንኙነትን ለማጠናከር እና ማሕበራዊ እሴቶቻችን ለማጎልበት ላቅ ያለ ፋይዳ አለው። በዓሉ የመቻቻል፣ የመከባበርና የመረዳዳት እሴቶቻችን ጎልቶ የሚታይበት እለት ነው።

በጽናትና በትግሥት ጥላቻና ጥፋት ወደ ፍቅርና ሰላም የተቀየረበት፣ ሞት ወደ ሕይወት የተለወጠበት እለት ነው። ይህም ለራዕይ እና ለዓላማ መቆምን ያስተምረናል።

በዚህ አስተምህሮ ምሳሌነት ዛሬም ስለእውነት በጋራ በመቆም አንድነታችን ማጽናት፣ ሰላማችን ማረጋገጥና ልማታችን ማፋጠን አንዳለብን ይነግረናል።

ከመከፋፈል ይልቅ አብሮነትን፤ ከልዩነትን ይልቅ አንድነትን አስቀድመን በጋራ ለሀገራችን ሰላም እና ልማት መሥራት ይኖርብናል።

በመሆኑም በዓሉን ስናከብር መልካም ነገር በመፈጸም፣ አቅመ ደካሞችንና ጠያቂ ያጡ ወገኖችን በመደገፍ ሊሆን ይገባል እያልኩ፦ በዓሉ የሰላም፣ የደስታ፣ የመተሳሰብና የአንድነት እንዲሆን እመኛለሁ። ኢድ-ሙባረክ!

Address

Debre Birhan

Telephone

+251116812872

Website

Alerts

Be the first to know and let us send you an email when የደብረብርሃን ከተማ ብልጽግና ፓርቲ ጽ/ቤት posts news and promotions. Your email address will not be used for any other purpose, and you can unsubscribe at any time.

Share