East Gojjam Zone Agriculture Department/የምስራቅ ጎጃም ዞን ግብርና መምሪያ

  • Home
  • Ethiopia
  • Debra Markos
  • East Gojjam Zone Agriculture Department/የምስራቅ ጎጃም ዞን ግብርና መምሪያ

East Gojjam Zone Agriculture  Department/የምስራቅ ጎጃም ዞን ግብርና መምሪያ ግብርና ከማምረት በላይ ነው!! Agriculture Is Beyond Production

የአረንጓዴ አሻራ መርሐ-ግብር ውጤት የሆነው የአትክልትና ፍራፍሬ ልማት የአርሶ አደሮችን ህይወት እየቀየረ ነው።‎‎ሰኔ 16/2018 ዓ.ም (ደብረ ኤልያስ ኮሙኒኬሽን) በምስራቅ ጎጃም ዞን በደ...
23/06/2026

የአረንጓዴ አሻራ መርሐ-ግብር ውጤት የሆነው የአትክልትና ፍራፍሬ ልማት የአርሶ አደሮችን ህይወት እየቀየረ ነው።

‎ሰኔ 16/2018 ዓ.ም (ደብረ ኤልያስ ኮሙኒኬሽን) በምስራቅ ጎጃም ዞን በደብረ ኤልያስ ወረዳ የአረንጓዴ አሻራ መርሐ-ግብር ውጤት የሆነው የአትክልትና ፍራፍሬ ልማት የላቀ ተጠቃሚ እያደረጋቸው መሆኑን አርሶ አደሮች ተናገሩ።

‎በወረዳው፥ በግብርናው ዘርፍ የአርሶ አደሩን ሁለንተናዊ ተሳትፎና ተጠቃሚነት ለማረጋገጥ ልዩ ትኩረት ተሰጥቶ እየተሰራ ይገኛል።

‎ባለፋት አመታት በሀገራችን ብሎም በወረዳችን ለአረንጓዴ አሻራ ችግኝ ተከላ መርሃ ግብር በተሰጠው ልዩ ትኩረት አርሶ አደሩ በአትክልትና ፍራፍሬ ልማት ዘርፍ በመሰማራት የላቀ ተጠቃሚ እየሆነ መጥቷል።

‎በወረዳው በአበሸብ ቀበሌ ነዋሪ የሆኑት አርሶ አደር መኮንን ቀሬ፣ በየዓመቱ የዝናብ ወቅትን ጠብቀው ማሳቸውን በተለያዩ ሰብሎች ከመሸፈን ይልቅ ፊታቸውን ወደ አረንጓዴ አሻራ አትክልትና ፍራፍሬ ልማት በማዞር አቅደው መስራት ከጀመሩ ሰነባብተዋል።

‎የጉድጓድ ውሃን በመጠቀም እንደ አቮካዶ ያሉ ቋሚ የአትክልትና ፍራፍሬ ተክሎችን ማልማት ከጀመሩ ወዲህ የእርሳቸውም ሆነ የቤተሰባቸው ኑሮ እየተሻሻለ መምጣቱን አብራርተዋል።

‎ቋሚ የአትክልትና ፍራፍሬ ልማት ጠቃሚና አዋጭ መሆኑን የተረዱት አርሶ አደር መኮንን፣ በቀጣይም በዘርፉ በስፋት ለመስራት ከመንግስት የቴክኖሎጂ አቅርቦት ድጋፍ ቢደረግላቸው የኢኮኖሚ አቅማቸው ይበልጥ እንደሚያድግ ያስረዳሉ።

‎በዘርፉ የተሰማሩት ሌላኛው አርሶ አደር ሻምበል ታደለ ቀሬ በበኩላቸው፣ መንግስት ያመጣውን የአረንጓዴ አሻራ መርሃ ግብር ጥቅም በመረዳት ወደ ፍራፍሬ ልማት መግባታቸውን ይናገራሉ። በግብርና ባለሙያዎች ያልተቋረጠ ድጋፍና ክትትል በመታገዝም ዘርፈ ብዙ ተጠቃሚ መሆን መቻላቸውን ገልጸዋል።

‎ባለፉት ዓመታት በቀበሌው በአረንጓዴ አሻራ መርሐ-ግብር ከ33 ሄክታር በላይ መሬት በአቮካዶ ልማት መሸፈኑን ያስታወሱት የአበሸብ ቀበሌ ግብርና ጽ/ቤት አስተባባሪ አቶ ስሜነህ ላቀ፣ አርሶ አደሩ በቋሚ አትክልትና ፍራፍሬ ተክሎች ላይ ትኩረቱን እንዲያደርግ እየተሰራ እንደሚገኝ ገልጸዋል። ውጤታማ የሆኑ አርሶ አደሮችን ተሞክሮ ሌሎችም እንዲከተሉ በማድረግ ዘርፉን ለማሳደግ በትኩረት እየተሰራ እንደሚገኝም ተናግረዋል።

‎የአትክልትና ፍራፍሬ ምርቶች ለህብረተሰቡ የተመጣጠነ ምግብ ከማስገኘታቸውም በላይ ወደ ውጭ በመላክ የውጭ ምንዛሬ ማግኘት የሚቻልበት ዘርፍ መሆኑን ያነሱት ደግሞ የወረዳው ግብርና ጽ/ቤት ኃላፊ አቶ ጌትነት ሰዋለም ናቸው።

‎በወረዳው ባለፉት አመታት በተሰራው የአረንጓዴ አሻራ ችግኝ ተከላ መርሐ-ግብር 495 ሄክታር መሬት በአትክልትና ፍራፍሬ ተክል የተሸፈነ መሆኑን ገልፀው፣ በዘንድሮው ዓመትም የተሻለ ኢኮኖሚያዊ ተጠቃሚነትን ሊያረጋግጡ የሚችሉ ከ120 ሺህ በላይ የአቮካዶና የቡና ችግኞችን በ117 ሄክታር መሬት ላይ ለመትከል ታቅዶ እየተሰራ መሆኑን ገልጸዋል።

‎የወረዳው አስተዳዳሪ አቶ ሀብታሙ እሱባለው በበኩላቸው፤ በወረዳው እየተከናወነ የሚገኘው የአረንጓዴ አሻራ መርሃ ግብር የማህበረሰቡን ኢኮኖሚያዊ ተጠቃሚነት ሊያረጋግጡ የሚችሉ እና ለምግብነት የሚያገለግሉ የአትክልትና ፍራፍሬ ችግኞችን በመትከል የአርሶ አደሩን ሁለንተናዊ ተጠቃሚነት ለማረጋገጥ ትኩረት ተሰጥቶ እየተሰራ መሆኑን አብራርተዋል። ለዚህም የተሻሻሉ የፍራፍሬ ዝርያዎችን ለማልማት በስፋት ትኩረት ተሰጥቷል ብለዋል።

‎በዘርፉ አርሶ አደሩን በማደራጀት ተጠቃሚ እንዲሆን የባለሙያ ድጋፍና ክትትል እየተደረገ መሆኑን ያነሱት አስተዳዳሪው፣ ወረዳው

‎በምስራቅ ጎጃም ዞን ደብረ ኤልያስ ወረዳ በአበሸብ ቀበሌ የአፈር ለምነትን ለማሻሻል በክላስተር እየተሰራ የሚገኝ በግብጦ(በአረንጓዴ ማዳበሪያ) እና በኖራ ቴክኖሎጅ መሬትን የማከም ሳይንሳዊ ...
22/06/2026

‎በምስራቅ ጎጃም ዞን ደብረ ኤልያስ ወረዳ በአበሸብ ቀበሌ የአፈር ለምነትን ለማሻሻል በክላስተር እየተሰራ የሚገኝ በግብጦ(በአረንጓዴ ማዳበሪያ) እና በኖራ ቴክኖሎጅ መሬትን የማከም ሳይንሳዊ አሰራር

በእነብሴ ሳር ምድር ወረዳ ግብርና ጽ/ቤት በሰቆጣ ቃልኪዳን ፕሮጀክት የበጀት ድጋፍ አማካኝነት በስርዓተምግብ የበለጸገ የሽምብራና የቦለቄ ምርጥ ዘር ለአጥቢና ነፍሰጡር እናቶች ስርጭት ማካሄዱ...
20/06/2026

በእነብሴ ሳር ምድር ወረዳ ግብርና ጽ/ቤት በሰቆጣ ቃልኪዳን ፕሮጀክት የበጀት ድጋፍ አማካኝነት በስርዓተምግብ የበለጸገ የሽምብራና የቦለቄ ምርጥ ዘር ለአጥቢና ነፍሰጡር እናቶች ስርጭት ማካሄዱን አስታወቀ።

በወረዳው ግብርና ጽ/ቤት የግብርና ኤክስቴንሽን ኮሙዩኒኬሽን የስራ ቡድን መሪ የሆኑት አቶ ዳምጠው ይበልጣል እንደገለጹት የህጻናትን መቀጨጭና መቀንጨር ለመከላከል በሰቆጣ ቃልኪዳን ፕሮጀክት የበጀት ድጋፍ አማካኝነት በስርዓተምግብ የበለጸገ የሽምብራና የቦለቄ ምርጥ ዘር ለአጥቢና ነፍሰጡር እናቶች ስርጭት ማካሄዱን አስታውቀዋል።

የምርጥ ዘር ስርጭት የተደረገላቸው እናቶችም ምስጋናቸውን አቅርበው ለልጆቻቸው ተገቢውን ድጋፍና እንክብካቤ በማድረግ እንደሚሰሩ ገልጸዋል።
@ enbse communication

በጎንቻ ሲሶ እነሴ ወረዳ የቡናና የፍራፍሬ ልማት ስራ የቅድመ ዝግጅት ስራዎች መጠናቀቃቸው  ተገለፀ።በምስራቅ ጎጃም ዞን በጎንቻ ሲሶ እነሴ ወረዳ የቡናና የፍራፍሬ ልማት ስራ የቅድመ ዝግጅት ...
20/06/2026

በጎንቻ ሲሶ እነሴ ወረዳ የቡናና የፍራፍሬ ልማት ስራ የቅድመ ዝግጅት ስራዎች መጠናቀቃቸው ተገለፀ።

በምስራቅ ጎጃም ዞን በጎንቻ ሲሶ እነሴ ወረዳ የቡናና የፍራፍሬ ልማት ስራ የቅድመ ዝግጅት ስራዎች መጠናቀቃቸውን የወረዳው ግብርና ጽ/ቤት ምክትል ሃላፊ አቶ አበበ አብሬ ገለጹ ።

እንደ ሃላፊው ገለጻ የ2018 ዓ,ም የፍራፍሬ ችግኞች እና የጉድጓድ ዝግጅት ስራዎች በመደበኛ እና በፕሮጀክት በጀት ድጋፉ እንዲሁም በማህበረሰብ ተሳትፎ ሲሰራ ቆይቶ ዛሬ ላይ ለተከላ ዝግጁ መሆኑን ተናግረው የገበያ መረጋጋትን ለመፍጠርና የምግብ ዋስትናን ለማረጋገጥ የአትክልትና ፍራፍሬ ልማትን በተቀናጀ አግባብ መስራት ወሳኝ መሆኑን ጨምረው ገልጸዋል።
@ የጎንቻ ሲሶ እነሴ ወረዳ ኮሚኒኬሽን

በተያዘው የክረምት የአረንጓዴ አሻራ መርሃ ግብር ከ5 ሚሊዮን በላይ ችግኝ ለመትክል ቅድመ ዝግጅት ተደርጓል፡፡***** በዘንድሮው የክረምት አረንጓዴ አሻራ 5 መቶ 23 ሄክታር መሬት በመለየት...
19/06/2026

በተያዘው የክረምት የአረንጓዴ አሻራ መርሃ ግብር ከ5 ሚሊዮን በላይ ችግኝ ለመትክል ቅድመ ዝግጅት ተደርጓል፡፡
*****
በዘንድሮው የክረምት አረንጓዴ አሻራ 5 መቶ 23 ሄክታር መሬት በመለየት የችግኝ መትከያ ጉድጓድ ዝግጅት እያደረገ መሆኑን የማቻከል ወረዳ ግብርና ፅ/ቤት አስታውቋል፡፡

በወረዳው አማኑኤል ከተማ የነጭ ዙሪያ ቀበሌ ለችግኝ ተከላ የጉድጓድ ቁፋሮ ሲያደርጉ ያገኘናቸው አርሶ አደሮች ከዚህ በፊት የተሰሩ የችግኝ ተከላዎች የአካባቢውን ስነ ምህዳር እንዲጠበቅ ከማድረጋቸው ባሻገር ለምርትና ምርታማነት መጨመር ትልቅ አስተዋጾኦ እያበረከቱ መሆናቸውን ተናግረዋል፡፡

ከዚህ በፊት የለሙ ተፋሰሶች እየሰጡ ያለውን ጥቅም በመረዳት በዚህ አመት ለተከላ የተለዩ ቦታዎችን በባለቤትነት በማልማትና በመጠበቅ የሚጠበቅባቸውን አገልግሎት እንዲሰጡ ለማድረግ ስለመዘጋጀታቸው አርሶ አደሮቹ ተናግረዋል፡፡

የማቻክል ወረዳ ግብርና ጽህፈት ቤት ኀላፊ አቶ መላኩ ተበጀ በ2018 ዓ.ም የአረንጓዴ አሻራ መርሃ ግብር 5 መቶ 23 ሄክታር መሬት በመለየት የችግኝ መትከያ ጉድጓድ በንቅናቄ እየተዘጋጀ መሆኑን ገልፀዋል፡፡

በዘንድሮው የአረንጓዴ አሻራ መርሃ ግብር ከ5 ሚሊዮን 2 መቶ ሺህ በላይ የተለያዩ ዝርያ ያላቸውና የተለያዩ ጥቅም የሚሰጡ ችግኞች ስለመዘጋጀቱም ተናግረዋል፡፡

የማቻክል ወረዳ ዋና አስተዳዳሪ አቶ አንዷለም እናውጋው በበኩላቸው በአረንጓዴ አሻራ የችግኝ ተከላ መርሃ ግብር በየአመቱ ኢኮኖሚያዊ ጠቀሜታ ያላቸውንና በክላስተር የሚለሙ ችግኞችን በማዘጋጀትና በመትከል አርሶ አደሩን ተጠቃሚ ማድረግ ተችሏል ብለዋል፡፡

በተለይ የወረዳውን የአየር ንብረት በመጠቀም ውጤታማ ለመሆን በቡና ልማት ላይ ሰፊ እንቀስቃሴ እየተደረገ ነው ብለዋል፡፡ ዘላቂ የተፈጥሮ ሃብት አጠቃቀም ስርዓት በመዘርጋት የአየር ንብረት ለውጥ የሚያስከትለውን ተፅዕኖ ለመቋቋም አርሶ አደሩ በሰፊው እንዲተክልና ኢኮኖሚውን እዲያሳድግ በትኩረት እየተሰራ ስለመሆኑም ገልጸዋል፡፡




 #በምስራቅ ጎጃም ዞን #በጎዛምን ወረዳ #በየቦቅላ ቀበሌ #ለ2018/19 ምርት ዘመን የአፈር ማዳበሪያ ስርጭት ከፊል ገፅታ በምስል
17/06/2026

#በምስራቅ ጎጃም ዞን
#በጎዛምን ወረዳ
#በየቦቅላ ቀበሌ
#ለ2018/19 ምርት ዘመን የአፈር ማዳበሪያ ስርጭት ከፊል ገፅታ በምስል

13/06/2026
 #በምስራቅ ጎጃም ዞን  #በማቻከል ወረዳ #በየውላ ችግኝ ጣቢያ #ለ2018 በጀት ዓመት የአረንጓዴ አሻራ መርሀ ግብር  #ለሰፋፊ ክላስተር ዓላማ የሚሆን በጥራትና በመጠን የተዘጋጀ  #የቡና ...
13/06/2026

#በምስራቅ ጎጃም ዞን
#በማቻከል ወረዳ
#በየውላ ችግኝ ጣቢያ
#ለ2018 በጀት ዓመት የአረንጓዴ አሻራ መርሀ ግብር
#ለሰፋፊ ክላስተር ዓላማ የሚሆን በጥራትና በመጠን የተዘጋጀ
#የቡና ችግኝ ዝግጅት ስራ ከፊል ገፅታ በምስል

 #በምስራቅ ጎጃም ዞን #በደብረ ኤልያስ ወረዳ #የ2018 ዓ/ም የአረንጓዴ አሻራ መርሀ ግብር #የችግኝና የጉድጓድ ቁፋሮ ዝግጅት ስራ ከፊል ገፅታ በምስል
13/06/2026

#በምስራቅ ጎጃም ዞን
#በደብረ ኤልያስ ወረዳ
#የ2018 ዓ/ም የአረንጓዴ አሻራ መርሀ ግብር
#የችግኝና የጉድጓድ ቁፋሮ ዝግጅት ስራ ከፊል ገፅታ በምስል

የምስራቅ ጎጃም ዞን አስተዳደርን አቋም የሚተነትን አቋም መግለጫ!በረሃማነት እንዳይስፋፋና የተፈጥሮ ሀብታችን እንዳይመናመን የጀመርነውን የመከላከል ስራ በማጠናከር የተራቆቱ ቦታዎችን በችግኝ ...
12/06/2026

የምስራቅ ጎጃም ዞን አስተዳደርን አቋም የሚተነትን አቋም መግለጫ!

በረሃማነት እንዳይስፋፋና የተፈጥሮ ሀብታችን እንዳይመናመን የጀመርነውን የመከላከል ስራ በማጠናከር የተራቆቱ ቦታዎችን በችግኝ ተከላ በማልማት የአረንጓዴ ልማት ስትራቴጅን እውን ማድረግ የሁሉም ዜጋ ሃላፊነት ሊሆን ይገባል፡፡

ደን ህይወት ነው፡፡ ያለ ደን ንፁህ አየርና ውሃ ማግኘት አይቻልም፡፡ ይህንን ማግኘት የሚቻለው አካባቢ በደን ሲሸፈን ብቻ ነው፡፡ መንግስት ይህንን በመገንዘብ በረሃማነት እንዳይስፋፋና የተፈጥሮ ሀብታችን እንዳይመናመን የጀመርነውን የመከላከል ስራ በማጠናከር የተራቆቱ ቦታዎችን በችግኝ ተከላ በማልማት የአረንጓዴ ልማት ስትራቴጅን እውን እያደረገ ነው፡፡

የምስራቅ ጎጃም ዞን አስተዳዳር በ2018/19 ዓም ለ8ኛ ጊዜ የአረንጓዴ አሻራ ፕሮግራም ለማካሄድ መጠነ ሰፊ የቅድመ ዝግጅት ስራዎችን እያካሄደ ነው፡፡ በዞኑ ለአረንጓዴ አሻራ ፕሮግራም 263 ሚሊዬን ችግኝ ለማዘጋጀት ታቅዶ 264 ሚሊዬን ችግኝ ለተከላ ተዘጋጅቷል፡፡

በዚህ አመት ለሚካሄደው የአረንጓዴ አሻራ ፕሮግራም የአንደኛው ዙር ችግኝ ተከላ 236 ሚሊዬን ጉድጓዶች ለመቆፈር ታቅዶ እስካሁን ድረስ 231 ሚሊን ጉድጓድ ለአንደኛው ዙር ተከላ እንዲዘጋጅ ተደርጓል፡፡ 8ሽ1መቶ 79 ሄክታር የተከላ ካርታ ለማዘጋጀት ታቅዶ 8 ሽ 53 ሄክታር የተከላ ካርታ ተዘጋጅቷል፡፡

ለአንድ ጀምበር የችግኝ ተከላ 5ሽ 3 መቶ 67 ሄክታር ለመትከል የቅድመ ዝግጅት ስራው ተጠናቋል፡፡

ዞናችን ለደን ልማት ምቹ የአየር ንብረትና ሰፊ ተፈጥሯዊ ፀጋ ያለው ቢሆንም የአረንጓዴ አሻራ ፕሮግራም ከመጀመሩ በፊት በሚፈለገው ደረጃ በቁርጠኝነት ተይዞ ያልተሰራ በመሆኑ ችግኝ ከተተከለ በኋላ የሚደረገው እንክብካቤም መሠረታዊ ጉድለት ነበረበት፡፡

በዞናችን በተለይም ክልላችን በ2011/2012 ዓ.ም የችግኝ ተከላ ወቅት ከዓመቱ መጀመሪያ ጀምሮ ሲደረግ ከነበረው ዝግጅት ባሻገር በሀገር አቀፍ ደረጃ “የአረንጓዴ አሻራ ቀን” በሚል መርህ የተሰጠውን ልዩ ትኩረት እንደ ዕድል በመጠቀም ለቀጣዮቹ ዓመታት ጭምር መሠረት የምንጥልበት አፈፃፀም እንዲኖር ተደርጎ እየተሰራ ነው፡፡

የምስራቅ ጎጃም ዞን አስተዳደር የማይፀድቅ እና ባለቤት የሌለው ችግኝ መትከል እንደማይገባ የጸና አቋም አለው፡፡ በ2017/18 የአረንጓዴ አሻራ ፕሮግራም ከተተከሉ ችግኞች 79 ነጥብ 8 በመቶ የሚሆኑትን የተተከሉ ችግኞች ማጽደቅ ተችሏል፡፡

በዚህ ዓመት የሚከናወነው የችግኝ ተከላ ሥራ ካለፉት አመታት ያገኘነውን ልምድ በመቀመር የተዘጋጁትን ችግኞች በመትከልና በመንከባከብ አረንጓዴ የለበሰች ምድር ለልጆቻችን ልናስተላልፍ ይገባል፡፡

የዞኑ ሕዝብ ከሰብል ልማት ሥራ እና ሠላሙን ከማስጠበቅ ጎን ለጎን ችግኝ በመትከል አረንጓዴ፣ ለሥራና ለመኖሪያ ምቹ አካባቢ በመፍጠርና ለኢኮኖሚያዊ ተጠቃሚነት መረጋገጥ የድርሻውን ሊወጣ ይገባል፡፡

ሰኔ 2018 ዓ.ም
@ምስራቅ ጎጃም ዞን ኮሚኒኬሽን

Address

0587717275
Debra Markos
01

Website

Alerts

Be the first to know and let us send you an email when East Gojjam Zone Agriculture Department/የምስራቅ ጎጃም ዞን ግብርና መምሪያ posts news and promotions. Your email address will not be used for any other purpose, and you can unsubscribe at any time.

Contact The Organization

Send a message to East Gojjam Zone Agriculture Department/የምስራቅ ጎጃም ዞን ግብርና መምሪያ:

Share