04/08/2026
በደብረ ማርቆስ ከተማ አስተዳደር በንጉስ ተክለ ሃይማኖት ክፍለ ከተማ“ከተረጅነት ወደ ምርታማነት ለተሟላ ሉዓላዊነት”በሚል መሪ ሀሳብ ከ4 ሄክታር በላይ መሬት በማህበረሰብ ንቅናቄ ማሳን በሰብል የመሸፈን ስራ ተጀመረ።
በንጉስ ተክለሃይማኖት ክፍለ ከተማ ሀምሌ 28/2018ዓ.ም “ከተረጅነት ወደ ምርታማነት ለተሟላ ሀገራዊ ሉዓላዊነት” በሚል መሪ ሀሳብ ከ4 ሄክታር በላይ መሬት በሕዝብ ንቅናቄ ማሳን በሰብል የመሸፈን ስራ የደብረ ማርቆስ ከተማ አስተዳደር ተቀዳሚ ምክትል ከንቲባ አቶ ተሾመ ዋለ፣ የክልል ደጋፊ አመራሮችና ባለሙያዎች ፤ አቶ አበባው ግዛቸው የደብረ ማርቆስ ከተማ አስተዳደር ብልፅግና ፓርቲ የአቅም ግንባታና የፖለቲ ዘርፍ ሃላፊ፣ አቶ መለሠ ሙላት የደብረ ማርቆስ ከተማ አስተዳደር ግብርና መምሪያ ሃላፊ፣ የንጉስ ተክለሃይማኖት ክፍለ ከተማ ዋና ስራ አስፈፃሚ አቶ አንማው መላክ ፣ የክፍለ ከተማው ብልፅግና ፓርቲ ጽህፈት ቤት ሃላፊ አቶ መሃሪው ነገሰ ፣የክፍለ ከተማና የቀበሌ አመራሮች ፣የግብርና ባለሙያዎች፣የአካባቢው አርሶ አደሮች እና በጎ ፈቃደኛ ወጣቶች በተገኙበት በስኬት እየተከናወነ ይገኛል።
ሀገር አቀፍ አቅጣጫን መሰረት ያደረገ አዲስ ጅምር የአካባቢውን አጠቃላይ ምርትና ምርታማነት በማሳደግ የሕዝብን የምግብ ዋስትና በራስ አቅም አስተማማኝ በሆነ መንገድ ለማረጋገጥ እና የጥገኝነት አስተሳሰብንና ተረጅነትን ማስቀረት ቁልፍ ዓላማው ያደረገ መሆኑን የክፍለ ከተማው ዋና ስራ አስፈፃሚ አቶ አንማው መላክ ገልፀዋል።
የፕሮግራሙ ዋና አላማም ፦ከጠባቂነትና ከጥገኝነት በመላቀቅ ሰባዊ ድጋፎችን በራስ አቅም ለመሸፈን ከሀገራዊ ኢኒሸቲቮች ውስጥ አንዱ በመሆኑ ሰርቶ የሚለወጥና የጥገኝነት አስተሳሰብን የሚፀየፍ ማህበረሰብ ለመፍጠር፣ምርትና ምርታማነትን በማሳደግ የልማት አርበኛ ለመሆን፣በእራስ አቅም በምግብ እራስን ለመቻል እና ከውጭ እርዳታና ከተረጅነት ስነ-ልቦና ለመላቀቅ መሆኑን የክፍለ ከተማው ዋና ስራ አስፈፃሚ አቶ አንማው መላክ ገልፀዋል።
በስተመጨረሻም አርሶ አደሮች የዘመናዊ የግብርና ቴክኖሎጂዎችን በመጠቀም ምርታማነታቸውን እንዲያሳድጉ ጥሪ ተደርጓል።
🕊ሰላም ለሁሉም፤ ሁሉም ለሰላም🕊