04/06/2026
የክረምቱን መግባት ተከትሎ ከሚከሰት የወባ በሽታ ጥንቃቄ ማድረግ ይገባል።
ወቅቱን መገንዘብ እና ተገቢውን ቅድመ ጥንቃቄ ማድረግ እጅግ መሠረታዊ ነገር ነው። ሞቃታማው ወራት አልፎ ቅዝቃዜ ከሚተካበት ወራት ልንደርስ ጫፍ ላይ እንገኛለን። ይህ ወቅት ታዲያ ጥንቃቄ የሚፈልግ ጊዜ ነው።
በተለይም ለሰው ልጅ የጤና ጠንቅ የኾነችው ወባ አምራቹን በስፋት ልታጠቃ የምትችልበት ምቹ አጋጣሚ የሚፈጠርበትም ጊዜ ነው።
ወረዳችን ላይ በርካታ የማህበረሰብ ክፍሎች የወባ በሽታ ተጠቂ የሚሆኑበት ወቅት እየደረሰ በመሆኑ ጥንቃቄ ማድረግ ይኖርብናል ።